TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ህጋዊ ያልሆነው ቡድን የሚመድባቸው አስተዳዳሪዎች እና የስራ ሃላፊዎች የሚያስተዳድሩት ሃብት የለም " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው በፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በኩል ባወጣው መግለጫ ነው። " ህጋዊ ያልሆነው ቡድን "  ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ግልፅ የመንግስት ግልበጣ አካሂደዋል…
#ትግራይ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደተር በ4 ከተሞች የጠራቸው የህዝብ ስብሰባዎች በአንዱ ሲካሄድ በሦስቱ  ተስተጓጉሏል።

ለስብሰባዎች መሰተጓጎል የፀጥታ ስጋት እንደ ምክንያት መቀመጡ አንዳንድ የከተሞቹ ነዋሪዎች ይገልፃሉ።

ባለፈው እሮብ ህዳር 4/2017 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ  ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተሾሙት ሰለሙን ትኩእ በዓዲግራት ከተማ ከዛላኣንበሳ ከተማ ተፈናቃዮች ለመወያየት እና በህዝብ የተመረጠ አዲስ አስተዳዳሪ ለመሾም የጠሩት ስብሰባ ፈተና የበዛበት ነበር።

ስብሰባ ከተከናወነበት አዳራሽ የወጡ የቪድዮ እና ድምፅ ፋይሎች እንደሚያሳዩት የማይናቅ ቁጥር ያላቸው እናቶች በስድብ ፣ ጩኸት እና ዋይታ ሰብሰባው እንዳይካይሄድ ሲከላከሉ ታይተዋል።

ቢሆንም የእናቶቹ ረብሻ በፀጥታ አካላት እንዲረገብ ሆኖ ወይይቱ ተካሂዶ የዛላምበሳ ከተማ አስተዳዳሪ በህዝብ ድምፅ እንዲመረጥ ሆኗል።

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የጉሎመኸዳ ወረዳ ሦስተኛ ከተማ የሆነችው የዛላኣንበሳ ከተማ እስካሁን በኤርትራ ስራዊት ቁጥጥር ስር እንደምትገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የወረዳው አስተዳዳሪዎችን ዋቢ በማድረግ በተደጋጋሚ  መዘገቡ ይታወሳል።

እሁድ ህዳር 8 /2017 ዓ/ም በትግራይ ምስራቃዊ  እና ማእከላዊ ዞኖች በሚገኙ ውቕሮ ፣ ዓብዩ ዓዲ እና አክሱም ከተሞች በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተጠሩ ህዝባዊ ስብሰባዎች መሰረዛቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቁመዋል።

ስብሰዎቹ ከፀጥታ ስጋት ጋር በተገናኘ የተሰረዙ እንደሆነ የገለጹ አሉ።

ከዚህ ተቃራኒ አስተያያት የሰጡ ደግሞ " በተለይ በዓብዩ ዓዲ እና አክሱም ከተሞች ሊካሄዱ ታቅተደው የተሰተጓጎሉት ህዝባዊ ስብሰባዎች በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በዞኑ ያካሄደው የአስተዳደር  የስልጣን ግልበጣ አካል ናቸው " ብለዋል።

ዛሬ ሊካሄድ የታሰበው ስብሰባ የተሰተጓጎለባቸው የውቕሮ ፣ የተምቤን ዓብዩ ዓዲ እና የአክሱም ከተሞች በአሁኑ ሰዓት ከወትሮ የተለየ የፀጥታ ስጋትና መደፍረስ እንደሌለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ወደ ከተሞቹ ስልክ በመደወል አረጋግጧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

" ' ተቀምተናል ' የሚሉትን ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው "  - ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ 

ዛሬ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የፀጥታ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት አቶ ጌታቸው ፥ " የህዝብ ጥቅም ማእከል አድርጎ በሚንቀሳቀስ የፓለቲካ ፓርቲ ውስጥ ለግሉ ጥቅም ብቻ የሚያስብ አመራር ከተፈጠረ ረጅም ጊዜ ሆኗል " ብለዋል።

" ' ስልጣን ለኛ ነው የሚገባው ' የሚሉ የህዝብ አጀንዳ በማፈን ፍላጎታቸው ለማሳካት የግጭትና የግርግር መልእክቶች በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ " ሲሉም ገልጸዋል።

እነዚህን አካላት በስም አልጠቀሷቸውም።

ፕሬዜዳንቱ በስም ያልገለፁዋቸው አካላት " ተቀምተናል " የሚሉት ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እያካሄዱ እንደሆነ አመላክተዋል። 

" ትኩረታችን የትግራይ ህዝብ መሆን ይገባ ነበር " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ለወንበር ሲባል የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች የማደናቅፍ ስራዎች ተባብሰው ቀጥለዋል " ሲሉ ገልፀዋል። 

" ' ሰራዊት ከኛ ጎን ነው ' በማለት የግለሰቦችን ስልጣን ለማርካት ታስቦ የፀጥታ ሃይል ለመከፋፈል አልሞ እየተሰራ ነው " ሲሉም አክለዋል። 

አቶ ጌታቸው ፥ " በትግራይ ሁሉንም ነገር በብቸኝነት ተቆጣጥሮ የቆየ ሃይል አሁንም የፀጥታ ሃይል ፤ ሚድያ ተቆጣጥሮ በለመደው መንገድ በመሄድ የግል ጥቅሙን ለማረጋገጥ ጠላት ከሚለው እየተደራደረ ይገኛል " ብለዋብ።

" ጠላት " ያሉትን ሃይል በስም አልገለፁም። 

የም/ ቤት አባላት በማንሳት የአስተዳዳሪዎች ስልጣን እንዲለወጥ መስራት መፈንቅለ መንግስት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው " መንግስትን ለማፍረስ የሚደረጉ መድረኮች በመንግስት በጀት ነው የሚካሄዱት " ሲሉ ተግባሩን ኮንነዋል።

" ' የፀጥታ ሃይል ከኛ ነው ' የሚለው አነጋገር የፀጥታ ሃይሉን በመጠቀም ' ከስልጣን እናስወግዳችኋለን ' የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ የሚሰራ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

ፎቶ፦ DW

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

" የፌደራል መንግስት ውስጣዊ ችግራችን በውይይት መፍታት ካልቻልን ትግራይን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው በግልፅ ነግሮናል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ  ወደ ሁለት በተከፈሉ የህወሓት አመራሮች እየታመሰ የሚገኘው የክልሉ የፓለቲካ ሁኔታ ከመሻሻል ይልቅ ተባብሶ መቀጠሉ ተናግረዋል።

" በምንገኝበት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ የፓለቲካ የአሰላለፍ ለውጥ እየተፈጠረ ነው ፤ የትግራይ ሁኔታም ከሚታየው ለውጥ ተያይዞ ያሉት ዕድሎች እና ፈተናዎች መተንተን ያስፈልጋል "  ብለዋል።

" የትግራይ ፓለቲካ ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ መገንዘብ ትቶ በአመራሮቹ እየታመሰ ነው " ሲሉም ገልጸዋል።

" የፌደራል መንግስት ውስጣዊ ችግራችንን እንድንፈታ እየገለፀ ነው ካልተቻለ ግን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው ግልፅ አድርጓል " ሲሉም አክለዋል።

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ተባብሶ መቀጠሉን የገለጹት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ በቅርቡ በአፍሪካ ህብረት ለሚካሄደው በፕሪቶሪያ የሰላም አፈፃፀም የሚመለከት የግምገማ መድረክ ከወዲሁ " እኔ ነው መሳተፍ ያለብኝ " ወደ ሚል መሳሳብ ተገብቷል ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

" የህወሓት አመራር ሉአላዊ የትግራይ ግዛት ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ታጣቂዎች ነጻ ሆኖ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ዋና አጀንዳ ዘንግቶ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የእለት ተእለት ስራዎች በማድናቀፍ ተጠምዷል " ሲሉም ከሰዋል።

" ከፕሬዜዳንት ስልጣን ወርደዋል ፤ ወደ ውጭ አገር ሊወጡ እያመቻቹ ነው ፤ ውጭ ሀገር ወጥተው እንዲቀሩ መንግሥት እያመቻቸላቸው ነው "  ተብሎ ሲወራባቸው ስለ መሰንበቱ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ " ለስራ በምወጣበት ጊዜ ከሁለቱ ምክትሎች አንዱ መወከል የተለመደ አሰራር ነው መወከሌም እቀጥላሎህ ፤ ' ከሀገር ሊወጣ ነው ' ተብሎ የተነዛው ወሬም ከሃቅ የራቀ መሰረተ ቢስ የውሸት ወሬ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

' ለስልጣን መቆራቆስ ትተን በጦርነት እና ጦርነት ወለድ ችግሮች የተጎሳቆለው ህዝባችን መካስ ማስቀደም አለብን " ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ በእሳቸው የሚመሩ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከሚመራው የህወሓት ከፍተኛ አመራር ጋር የሃይማኖት አባቶች በጀመሩት የእርቅ ጥረት ችግሮቻቸው ለመፍታት ቁርጠኛ እንደሆኑ አረጋግጠዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia