#Mekelle
ዛሬ በመቐለ ከተማ በሚገኝ በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት በራፍ በጠራራ ፀሐይ ነዋሪዎችን ያስደነገጠ ድርጊት ተፈጽሟል።
አንድ መምህር በተማሪው በስለት ብዙ ቦታ ተውግቶ በህክምና እርዳታ ህይወቱ ተርፏል።
ተማሪው በምሳ ሰአት መውጪያ ላይ የደበቀውን ስል ቢላዋ በማውጣት መምህሩን 2 ጊዜ ደረቱ ላይ፣ 1 ጊዜ በሆዱ ላይ ፣ 1 ጊዜ በጀርባው ላይ ፣ 1 ጊዜ ጉኑ ላይ በአጠቃላይ 5 ቦታ ላይ ወግቶታል።
መምህሩን ወድያውኑ ወደ ዓይደር ሆስፒታል ማድረስ በመቻሉ በከባድ የቆዶ ህክምና ህይወቱ መታደግ ተችሏል።
ይህንን መረጃ ያጋሩት የዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ፋሲካ ዓምደስላሴ " ብዙ ተማሪዎች ስለት ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ እየሰማን ነው እንደ ማህበረሰብ አንድ ነገር ማድረግ አለብን " ብለዋል።
ድርጊቱን በተመለከተ ከፖሊስ በኩል የተባለ ነገር የለም።
ሆኖም ወላጆች እባካችሁ የልጆቻችሁን ውሎ ተከታተሉ። ካልተገባ ተግባርም እንዲርቁ ምከሩ ፤ ቸል አትበሏቸዋል እንላለን።
በሌላ በኩል ፤ በዛው መቐለ 6 ቀናት ያስቆጠረ ህፃን እናቱ ከቤት ትታው ወደ መፀዳጃ ቤት ታመራለች ፤ ዳናዋን ተከትሎ ህፃኑ ወደ ተኛበት ክፍል የገባ የቤታቸው ውሻ የህፃኑ መራብያ አካል ላይ ጉዳት አድርሷል።
እናቲቱ ወድያውኑ ደርሳ ልጇን ወደ ዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል ይዛው እንደመጣች ዶ/ር ፋሲካ ዓምደስላሴ አጋርተዋል።
በእነዲህም አለና ወላጆች ልጨቅላ ልጆቻቹ የምታደረጉት ጥንቃቄ አይለያችሁ።
የተከሰቱት ድርጊቶች ምንም እንኳን ለመስማት የሚከብዱ ቢሆኑም ለወላጆች ጥንቃቄ ሲባል ያጋራናቸው ናቸው።
#Mekelle #AyderHospital
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት። አንደኛውን ከንቲባ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሾም አንዱን በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ነው የሾመው። ከትላንት በስቲያ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምስራቃዊ ዞን ፅ/ቤት በፃፈው የሹመት ደብዳቤ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህሩን ዓለም አረጋዊን የከተማይቱ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አቶ ዓለም የሹመት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል። …
#Mekelle
በመቐለም ሁለት ከንቲባ መሾሙ ተሰማ።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመቐለ ከተማ አዲስ ከንቲባ ሾመ።
ከተማዋ በቅርቡ በም/ቤት ከንቲባ ተሹሞላት እንደነበር አይዘነጋም።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ አዲስ የተሾሙት ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ህወሓት ለሁለት ሳይሰነጠቅ የፓለቲካ ፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ናቸው።
በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ከጦርነቱ በፊት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ በመሆን ያገለገሉ ናቸው።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ባገኘው መረጃ አዲሱ ከንቲባ ከዛሬ ጀምሮ የከንቲባ ስልጣናቸው የሚፀና ይሆናል።
ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እሁድ 22/2017 ዓ.ም ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ወጣቶች ባደረጉት ውይይት ፤ " ሁለት ከንቲባ የሚባል አይሰራም ፤ አንድ ከንቲባ ነው ያለው ያውም መንግስት የመደበው ብቻ ነው። በምክር ቤት ስም የሚካሄድ ከንቲባ የመቀየር ሂደት ተቀባይነት የለውም ፤ ህገ-ወጥ አካሄዱ መልክ እንዲይዝ ይሰራል " ብለዋል።
ባለፈው ጥቅምት 2017 ዓ.ም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) የከተማዋ ከንቲባ በማድረግ የሾመ ሲሆን የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሹመቱ ውድቅ ማድረጉ መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።
ከቀናት በፊት ዒግራይ ላይ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ዐለም አረጋዊን ከንቲባ አድርጎ ሲሾም በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ደግሞ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔርን ከንቲባ አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaMekelle

Photo
#Mekelle
" ህዝቡ ከገባበት የጦርነት ጦስ እንዲያንሰራራ ከመምራት ይልቅ ለስልጣናቸው ብቻ ሲሯሯጡ የህዝቡን ስቃይ እጅግ መራራ አድርገውታል " - ተገልጋይ
በትግራይ ክልል ፣ መቐለ ከተማ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የተመደቡ ከንቲባዎች በስራ ገበታ የሉም ፤ የከንቲባ ፅህፈት ቤት ታሽጎ በፀጥታ ሃይሎች ጥበቃ ስር ይገኛል።
ተገልጋዮች ከከንቲባ ማግኘት ያለባቸው አገልግሎት ለማግኘት ቢመላለሱም የሚያስተናግዳቸው የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም ጠዋት መቐለ አስተዳደር ፅህፈት ቅጥር ግቢ ድረስ ተጉዞ አጭር ምልከታ አደርጓል።
በአስተዳደሩ ዋና በር በቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተገለግጋሎች ሲገቡ ሲወጡ ይታዩሉ ፤ ፍትሻ በሚካሄድበት ቦታ ከተለመደው በተለየ ብዛት ያላቸው የፀጥታ አካላት ይስተዋላሉ።
5ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው የዋና ከንቲባ ፅህፈት ቢሮ (ከህዳር 22/2017 ዓ.ም ) እንደታሸገ ሆኖ ግራና ቀኝ የፓሊስ ደንብ ልብስ በለበሱ የፀጥታ አካላት ይጠበቃል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከከንቲባ የሚሰጥ አገልግሎት ለማግኘት ከአንድ ወር በላይ የተመላለሰ ተገልጋይ አግኝቶ አስተያየቱ ተቀብሏል።
ተልጋዩ ፀጋዛኣብ ርእሰደብሪ ይባላል የመቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ነው።
ያለውን የመሬት ጉዳይ አስመልክቶ ከንቲባ አግኝቶ ለማነጋገር ቢመላለስም እስካሁን እንዳልተሳከለት ገልጿል።
" በሁለቱም በኩል ያሉ የህወሓት አመራሮች ማሰብ ተሰኗቸዋል ? ፤ ህዝቡ ከገባበት የጦርነት ጦስ እንዲያንሰራራ ከመምራት ይልቅ ለስልጣናቸው ብቻ ሲሯሯጡ የህዝቡን ስቃይ እጅግ መራራ አድርገውታል " ሲል በምሬት ተናግሯል።
ካለፈው ወርሀ ነሃሴ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ወደ ሁለት ቡድን መሰንጠቃቸው ያወጁት የደረብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እና የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን በየፊናቸው በየቦታው አመራር በመመደብና በመገለጫዎች መወራረፍ ቀጥለውበታል።
ባለፈው ወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም የቀድሞ ከንቲባ ይትባረክ ኣምሃ ተክቶ በደረብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት እጩ አቅራቢነት በከተማው ምክር ቤት ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ረዳአ በርሀ (ዶ/ር) በጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ወድያውኑ ተቀባይነት ማጣታቸው ተከትሎ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ብርሃነ ገ/የሱስ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ተሹመዋል።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሸሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም በፅህፈት ቤቱና በክፍለ ከተሞች አመራሮች በቅጥር ግቢው በሚገኘው የመሰብሰብያ አዳራሽ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጨምሮ ሚድያዎች በተገኙበት አቀባበል ቢደረግላቸውም ከነጋታው ጀምሮ ይህ ዜና አስከተጠናቀረበት ሰዓት ተመልሰው ቢሮ አልገቡም።
በወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም የተሾሙት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) እንዲሁም ቢሮ ላይ የሉም።
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ምክር ቤቶች በመጠቀም ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ " በተሰጠኝ ስልጣን መሰረት " በማለት መቐለ ጨምሮ በትግራይ ስድስት ዞኖች የየራሳቸው አስተዳዳሪዎች በመሾም ህዝቡን ግራ አጋብተውታል።
ይህንን መሰል ግራ የገባው የሁለቱ የህወሓት ቡድኖች አካሄድ ማብቅያው መቼ ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው።
#TikvahEthiopiaMekelleFamily

መቐለ ያለ ከንቲባ አንድ ወር ሆናዋታል።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከተማዋ እንዲስተዳድሩ ህዳር 22/2017 ዓ.ም የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ህዳር 23/2017 ዓ.ም በአስተዳደሩ ቅጥር ግቢ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ፅህፈት ቤታቸው አልገቡም።
የከንቲባ ፅህፈት ቤት ታሽጎ በፓሊስ ጥበቃ ስር እንደሚገኝ የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል መግለጹ ይታወሳል።
ከህዳር 23 አስከ ዛሬ እሮብ ታህሳስ 23/ 2017 ዓ.ም አንድ ወር ሙሉ የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነቸው መቐለ የሚያስተዳድራት ከንቲባ የለም ፤ ተገልጋዮች ከፍተኛ መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሆን በምሬት ይገልፃሉ።
ዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ከመቐለ እና አከባቢዋ የተወጣጡ ወጣቶች በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ ከንቲባ ስራ እንዲጀምሩ ያለመ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
ወጣት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ህጋዊው ከንቲባ ወደ ፅህፈት ቤታቸው ሳይገቡ ከቦታው ንቅንቅ እንደማይሉ ፤ ከተማዋ የግርግር እና ረብሻ ምንጭ እንድትሆን እንደማይፈቅዱ ድምፃቸው በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።