TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥቆማ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ አውጥቷል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ የካቲት ወር በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚሳተፉ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገች ነው።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው የመስተንግዶ መርሃግብር በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል ካዴቶችን በመቀበል አሰልጥኖ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ማሰማራት እንደሚፈልግ ገልጿል።

በመሆኑም ፦

- የእንግሊዘኛ፣
- የፈረንሳይኛ
- የዓረብኛ ቋንቋዎችን መናገርና መጻፍ የሚችሉ እና ዕድሚያቸው ከ18-30 የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ምዝገባው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት ነው የሚከናወነው።

ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ሲመጡ የትምህርት ማስረጃቸውን እና ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው እንዲቀርቡ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ " የአገራት መሪዎች፣ የዓለምአቀፍና ቀጠናዊ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በሚሳተፉበት የአህጉራችን ትልቁ ጉባዔ ላይ በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል በመሆን የዚህ ታሪክ አካል ሆናችሁ አገራችሁን ያለ ክፍያ በኩራት እንድታገለግሉ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

አንድ የስራ ማስታወቂያ እንጠቁማችሁ። ዕድላችሁንም ሞክሩ።

ማስታወቂያውን ያወጣው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ነው።

የስራ መደቦቹ ምን ምን ናቸው ?

1. ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ባለሙያ

° ደረጃ ፡- 14
° ደመወዝ ፡- 38,557
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ቢዝነስ አስተዳደር፣ኢኮኖሚክስ እና በተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ / ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡-3/2 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት


2. ከፍተኛ የማርኬቲንግ ባለሙያ

° ደረጃ ፡- 14
° ደመወዝ ፡- 38,557
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት ፡- በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ ቢዝነስ አስተዳደር፣ ኢኮኖሚክስ እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ/ ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡- 3/2 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

3. ከፍተኛ የብራንዲንግ ባለሙያ

° ደረጃ፡- 14
° ደመወዝ፡- 38,557
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በማርኬቲንግ ፣ ቢዝነስ አስተዳደር እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ/ ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡-3/2 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-በግራፊክስ ፣ በዲዛይን እና ተዛማች ሰርተፊኬሽን ያለው/ያላት
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

4. ሁለገብ የጥገና ሠራተኛ

° ደረጃ፡-9
° ደመወዝ፡- 24,435
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በእንጨት ወይም በብረት ሥራ
° የትምህርት ደረጃ፡- 10+2
° የስራ ልምድ ፡- 3 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

5. የመረጃ ዴስክ ባለሙያ

° ደረጃ፡-11
° ደመወዝ፡- 29,029
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በጆርናሊዝም፣ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ፣ ፖለቲካል ሣይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ/ ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡-1/0 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

ምዝገባ በኦን ላይን https://tinyurl.com/ipdchoexternalvacancy ላይ ነው የሚከናወነው።

ለሥራ መደቡ የሚያስፈልጉ የትምህርት ፤ሥራ ልምድ እና ሌሎች ማስረጃዎች ወደ ፒዲኤፍ/pdf/ በመቀየር በአንድ ፋይል መያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ማስታወቂያ ትላንት ነው የወጣው ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ ነው የሚቆየው።

አመልካቾች ከስራ መደቡ ጋር #ቀጥተኛ_የሆነ የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል የተባለ ሲሆን ከግል ድርጅቶች የሚቀርብ ስራ ልምድ ግብር መከፈሉ ማረጋገጫ መቅረብ አለበት።

ተጨማሪ መረጃ ደግሞ በስልክ ቁጥር 0118 72 24 20 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

መልካም ዕድል !

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

እስከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት የሚያስገኘውን የ " The Earthshot Prize 2025 " ኢትዮጵያውያን እንዲወዳደሩ ጥሪ ቀረበ።

በእንግሊዝ ልዑል ዊሊያምና ሮያል ፋውንዴሽን በፈረንጆቹ 2020 የተቋቋመውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአካባቢና አየር ብክለት የፀዳ፣ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የሚያበረክትና ለተፈጥሮ ተስማሚ የሆነ ስራ እየሰሩ ያሉ ተቋማትን ፣ የቢዝነስ ፈጠራ ባለሙያዎችን (ኢንተርፕረነሮችን) ወይም ግለሰቦችን የሚሸልመው " The Earthshot Prize 2025 " የዘንድሮ እጩ ተወዳዳሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

በአፍሪካ የውድድሩ ዋና አጋር መልቲቾይስ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች እንዲወዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

በ5 የተለያዩ ምድቦች የሚካሄደው ይህ ዓመታዊ ሽልማት ላይ በተለይ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑና ተፈጥሮን የማይበክሉ ቢዝነሶችን የሚያንቀሳቅሱ ኢትዮጵያውያን  መሳተፍ ይችላኩ።

ውድድሩ እስከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት የሚያስገኝ ነው ተብሏል።

ፕሮጀክቶቻቸውን ለማስፋፋትና እየተባባሰ ለመጣው የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ እንዲያበረክቱም ያግዛል።

መልቲቾይስ አፍሪካ ፤ በደቡብ አፍሪካ በተከናወነው የ2024 ውድድር ከጋና " ግሪን አፍሪካ ዩዝ ኦርጋናዜሽን " እንዲሁም ከኬንያ " ኪፕ ኢት ኩል" የተሰኙ የአረንጓዴ ጉዳይ አቀንቃኞችና የሥራ ፈጣሪዎች አሸናፊ እንደሆኑ አስታውሷል።

ለዚህ ዓመቱ ሽልማት ማመልከት የሚቻለው እስከ ፈረንጆቹ ዲሴምበር 04 / 2024  ሲሆን ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች እና ተቋማት  በ https://www.multichoice.com/earthshot-nomination.php#prId=324466  እንዲያመለክቱ ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopia

Via @TikvahethMagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች። ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል። ምን መማር ይቻላል ? - Android Kotlin Development Fundamentals - Data Science Fundamentals - Programming Fundamentals ትምህርቱን እንዴት…
#ጥቆማ

በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖሩና የ " 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ " ስልጠናዎችን ለመሰልጠን ላሰቡ ጥሩ እድል መመቻቸቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አሳውቋል።

ስልጠናዎቹን ለመውሰድ ለሚመጡ ሰልጣኞች የኮምፒውተር እና ኢንተርኔት አቅርቦት ዝግጁ መደረጉ ተጠቁሟል።

የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ እንዲመዘገቡም ጥሪ ቀርቧል።

የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ የመንግስትና የግል ሰራተኞች፣ በአጠቃላይ ሁሉም ዜጎች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ ስልጠናዎችን መሰልጠን ይችላሉ ተብሏል።

ስልጠናው ከጥር 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሁልጊዜ በሳምንቱ የእረፍት ቀናት (ቅዳሜና እሁድ) እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የስልጠና ቀናት
#ቅዳሜ እና #እሁድ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ አመሻሽ 11:30 እንደሆነ ተመላክቷል።

የስልጠና ቦታው አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ቢሮ ሲሆን ለመመዝገብ ይህን ሊንክ 
https://awareness.insa.gov.et/index.php/143154?lang=am መጠቀም ይቻላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ብሩህ እናት !

ሴቶችን እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚያሸልም “ ብሩህ እናት ” የተሰኘ የፈጠራ ውድድር መዘጋጀቱ ተገለጸ።

የሴቶችን ድካም የሚያቀሉ ቴክኖሎጂ ተኮር የፈጠራ ሀሳቦችን በማቅረብ ለሚያሸንፉ ሴቶች ቋሚ ችግር ፈቺ ተቋም የሚሆኑበትና ከ100 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ብር የሚያሸልም ውድድር ለሴቶች ብቻ ማዘጋጀቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል።

የፈጠራ ውድድሩ የተዘጋጀው ከኢንተርፕርነሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት፣ ከእናት ባንክ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ጉዳይ ጋር በጋራ በመሆን መሆኑን መስሪያ ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በዚህም “ ማሰልጠን፣ መሸለም፣ ማብቃት ” በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢ ላሉ ሴቶች እድሉ እንጀተመቻቸ፣ ከተመዘገቡት 5ዐ የተሻለ ሀሳብ ላቀረቡ ተወዳዳሪዎች ስልጠና እንደሚሰጥ አመልክቷል።

“ ፕሮግራሙ ላይ የላቀ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ሴቶች ተወዳዳሪዎች መከካልም 10 ለሚሆኑት አሸናፊ የቢዝነስ ሀሳብ ፈጣሪዎች እውቅናና የገንዘብ ሽልማት እንዲያገኙ ይደረጋል ” ሲል መስሪያ ቤቱ ጠቁሟል።

ለውድድሩ አሸናፊዎች ሽልማቱ ምንድን ነው ?

ከተመዝጋቢዎቹ የተሻለ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሀሳብ ያቀረቡ 1ዐ ተወዳዳሪዎች እንደየደረጃቸው ከ100 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ሽልማት መዘጋጀቱ ተገልጿል።

በገለጻው መሠረት፣ ለ1ኛ አሸናፊ 500 ሺሕ፣ ለ2ኛ አሸናፊ 400 ሺሕ፣ ለ3ኛ አሸናፊ 300 ሺሕ፣ ለ4ኛ አሸናፊ 200 ሺሕ፣ ለ5ኛ አሸናፊ 150 ሺሕ እንዲሁም ከ6 እስከ 10ኛ ላሉ አሸናፊዎች 100 ሺሕ ብር ይሸለማሉ።

በመግጫው የተገኘው እናት ባንክ በበኩሉ፣ ለአሸነፉበት ሴቶች ቴክኖሎጂ ተግባራዊነት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ብድር እንደሚያመቻች ገልጿል።

ምዝገባው መቼ ተጀምሮ ? መቼ ይጠናቀቃል ?

ምዝገባው ከዛሬ (ሰኞ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጅምሮ እስከ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ/ም ደረስ እንደሚከናወን ተነግሯል።

ለተወዳዳሪዎች የቡት ካምፕ ስልጠና ከመጋቢት 8 እስከ መጋቢት 19/2017 ዓ/ም እንደሚሰጥ እና የውድድሩ ማጠቃለያና ሽልማት መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሚሆን ተመላክቷል።

ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://shorturl.at/8g9mv

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia