TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የትግራይን ህዝብ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ እንዲፈታ ይደረጋል" - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ " ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች መልእክት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለዋል። ሰልፉን የጠራው የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያዘጋጀው መልእክት የተቀበሉት ፕሬዜዳንቱ አቶ ጌታቸው…
" ከውጭ የሚመጣ ተሟጋች አያስፈልገንም !! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሂጃብ ጉዳይ ምን አሉ ?

" ከውጭ የሚመጣ ተሟጋች አያስፈልገንም። ጉዳዩ በራሳችን ነው የምንጨርሰው። ያለን አንድነት እና መፈቃቀር ሊነካ አይገባም።

የአክሱም ህዝብም በዚህች ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዳለው ነው የማውቀው። አንዳንድ በክፋት የተሰማራ ካልሆነ፥ እያያችሁት እንዳለ ይህ ጉዳይ ያላሳዘነው፣ መፍትሔ መበጀት አለበት ያላለ የለም።

ችግሩ እንደሚፈታ ነው ማምነው፣ ያለን ግንኙነትም የሚያሳየው ይህ ነው። በመዘግየቱ ግን ለሙስሊሙ ማሕበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ልጆቹ ወደትምህርት ቤት መላክ የሚፈልግ የትግራይ ህዝብ ሁሉ ይቅርታ መጠየቅ አለብን ብዬ ነው የማምነው። "


Quote - #DW

@tikvahethiopia