TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Lecturers Claims and questions -.pdf
🔈#የመምህራንድምጽ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር (ኢመማ) 37ኛ መደበኛ የም/ቤቱን ስብሰባ በአዳማ ባካሔደበት ወቅት ከም/ቤት አባላት ለተለያዩ አካላት ተደራሽ መደረግ ያለባቸው ፦
- የመምህራን የመብት፣
- የጥቅማ ጥቅም
- አጠቃላይ በትምህርት ሥራው ላይ ያሉና መፈታት ያለባቸው ጉዳዮችን አስመልክቶ በስፋት ውይይት ተደርጎ ነበር።

ከም/ቤቱ አባላት ከዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ የተነሱ በርካታ በአሰራር ሊመለሱ የሚገቡ የመልካም አስተዳደርና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ተነስተው ነበር።

በአጭር ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ ምላሽ የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፥ ለአቶ ኮራ ጡሹኔ (በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ) ደብዳቤ ልኳል።

በአጭር ጊዜ ምላሽ የሚሹ የተባሉት ጉዳዮች ምንድናቸው ?

1. የመምህራን የመኖሪያ ቤት ጉዳይ አንዱ ነው።

በ2008 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴርና ኢመማ በጋራ ባዘጋጁት የመምህራን የመኖሪያ ቤት ፓኬጅ በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ፓኬጁ ሥራ ላይ ውሎ በርካታ መምህራን የዚህ ፓኬጅ ተጠቃሚ ተደርገዋል።

ነገር ግን የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከክልሎች ዋና ከተማ አልፈው በዞኖች ጭምር የሚገኙና ከተልዕኮአቸው አንዱ በሆነው በማህበረሰብ አገልግሎት የአካባቢውን ማህበረሰብ እያገለገሉ ያሉ ሆኖ ሳለ ' የፌዴራል ተቋማት ናችሁ ' በሚል የዩኒቨርስቲ መምህራን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ተጠቃሚ ሳይሆኑ እስከ አሁን ቆይተዋል፡፡

ስለሆነም መምህራኑ ጥያቄያቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ስለሆነና በም/ቤቱም በሰፊው የተነሳ ሀሳብ በመሆኑ ከክልልና ከአካባቢ የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ለዩኒቨርስቲ መምህራን ምላሽ እንዲሰጥ ማህበሩ ጠይቋል።

2. በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ በርካታ ዩኒቨርሰቲዎች የማስተማሪያ ሆስፒታል (Teaching Hospitals) አላቸው።

ይሁንና የዩኒቨርስቲ መምህራን በሚያስተምሩበት ተቋም ውስጥ መምህራንም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው የሚታከሙበት በክፍያ ስለሆነ ይህ አሰራር መምህራን በተቋሙ ላይ የባለቤትነት ስሜት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ብቻም ሳይሆን ፍትሃዊነት የጎደለውና የመምህራንንም የሥራ ተነሳሽነት ይቀንሳል፡፡

ስለሆነም የዩኒቨርስቲ መምህራንና ቤተሰቦቻቸው በማስተማሪያ ሆስፒታሎች ውስጥ ነፃ ህክምና የሚያገኙበት መንገድ እንዲመቻች ጠይቋል።

3. ዩኒቨርሰቲዎች በሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ ላይ የሚገኙና አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች የበረሀና የውርጭ አበል ጭምር በሌሎች ሴክተሮች ሠራተኞች የሚከፈልባቸው ሆነው ሳለ ዩኒቨርስቲ መምህራን ግን የበረሀም ይሁን የውርጭ አበል አለመከፈለ ቅሬታ እየፈጠረ ስለሚገኝ መፍትሄ እንዲሰጠው ጠይቋል።

እነዚህ ጥያቄዎች የዩኒቨርስቲ መምህራን በም/ቤቱ ላይ ካነሷቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ የሚሹና ሚኒስትር ዴኤታው በም/ቤቱ ተገኝተው በነበረበት ወቅትም ጥያቄዎቹ የተነሱ ናቸው።

እሳቸውም ጥያቄዎቹ የተነሱበትን አውድ መገንዘባቸውን ማህበሩ በደብዳቤው አመልክቷል።

ስለሆነም አፋጣኝ የሆነ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቋል።

ቀደም ሲልም የቀረቡት የዩኒቨርስቲ መምህራን ጥያቄዎች በተለይ የኑሮ ውድነት እና የጥቅማ ጥቅም እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከማህበሩ ጋር መድረክ ተፈጥሮ መፍትሄ እንዲበጅላቸውም ጥሪውም አቅርቧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የመምህራንድምጽ

🔵 "የሁለት ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ቤተሰብ እንዴት እናስተዳድር?" - የደቡብ ወሎ ዞን መምህራን

🟢 " የሚመለከተው ኮማንድ ፓስቱን ስለሆነ በወረዳ በኩል እንዲፈቱ አነጋግረናል " - የዞኑ መምህራን ማኀበር

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የሚገኙ መምህራን የሁለት ወራት የደመወዝ ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው የከፋ ችግር ላይ በመሆናቸው አማረዋል።

ክፍያው ያልተፈጸመላቸው በክልሉ ባለው የሰላም መደፍረስ ሳቢያ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ ባለመገኘታቸው ' ሳታስተምሩ ደመወዝ አይከፈላችሁም ' በሚል መሆኑን አስረድተዋል።

" የሁለት ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ቤተሰብ እንዴት እናስተዳድር ? " ሲሉ ጠይቀው፣ ከዚሁ ትንሽ ደመወዝ ብሶ ባለመከፈሉ ችግር ላይ በመውደቃቸው የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጧቸው በአጽንኦት ጠይቀዋል።

የቀረበው ቅሬታ እንዲቀረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት የዞኑ መምህራን ማኀበር፣ " የሚመለከተው ኮማንድ ፓስቱን ስለሆነ በወረዳ በኩል እንዲፈቱ አነጋግረናል " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

" መምሪያ ኃላፊው ጋ ተነጋግረናል። በዚያ በኩል እየገመገሙ መስራት የሚችሉና መምህራን ያልገቡባቸው ትምህርት ቤቶቸ ከሆነ የግድ የማይከፈል መሆኑን፤ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሆነ ግን እንዲከፈል እየተደረገ እንደሆነ ነው " ብሏል።

በትምህርት ቤት ቢገኙም ተማሪ ባለመገኘቱ ብቻ ስላላስተማሩ ደመወዝ እየተከፈላቸው  ቅሬታ ለሚያቀርቡት መምህራን ምላሽ እንዲሰጥ ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠን ምላሽ ደግሞ፣ " ትምህርት መምሪያን አነጋግሩ " ብሏል።

የቀረበውን ቅሬታ በመግለጽ ምላሽ እንዲሰጡ ለሳምንት የጠበቅናቸው የዞኑ ትምህርት መምሪያና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጉዳዩን በጽሞና ከሰሙ በኋላ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በተጨማሪ፣ መምህራን እያቀረቡት ያለውን የደመወዝ አለመከፈል ቅሬታ ሰምቷል? ስንል ጥያቄ ያቀረብንለት የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር (ኢመማ) ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማኅበሩ ፦

" በአካባቢው ካለው ችግር አንጻር ፎርማል ሆኖ የመጣልን ነገር የለም። ግን በወግዲ ወረዳ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አካባቢዎችም እስከ ለሁለት ወራት እየተከፈለ አይደለም ከባንክም ከሌላም  ኬዝ ጋር በተያያዘ።

እንደተባለው መምህራን እየተጎዱ ነው። በይበልጥ ጉዳዩ የክልሉን መምህራን ማኅበር ይመለከታል። ፎርማል ሆኖ ወደኛ ቢመጣ ወደ ፌደራል መንግስትም ልንወስደው እንችላለን፡፡

ፎርዛትማተር መንግስት 'የክልሎቹ ማንዴት ነው' ነው የሚለን፡፡ ከዚህ ቀደም የትግራይ ክልል መምህራን መጥተው ያን ያህል ሲንገላቱ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ነበር ለሻይ ሲላቸው የነበረው።

አማራ ክልል አይነት የጦርነት ሁነት ላይ ስለሆነ ፎርማሊ በሕግ አግባብ የሚጠየቅ ድርጅት የለም፡፡ በዚህ ነው የተቸገርነው "
ነው ያለው።

በጸጥታው ችግር ትምህርት ቤቶች ስለተዘጉ ሳያስተምሩ ደመወዝ እንደማይፈጸምላቸው እንደተነገራቸው ነው መምህራኑ የሚገልጹት፤ ይህ አግባብ ነው ? በሚል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ የማኀበሩ ፣ " ልክ አይደለም " የሚል መልስ ሰጥቷል።

" ተማሪ እስከመጣላቸው ድረስ አላስተምርም ያሉ መምህራን ካሉ ነው እንጂ መምህራኑ ትምህርት ቤት ቁጭ ብለው ተማሪ እየጠበቁ ነገር ግን በጸጥታ ችግር ተማሪ ካልመጣላቸው ማንን ነው የሚያስተምሩት ? " በማለት ጉዳዩ ልክ ያልሆነበትን ምክንያት በመጠይቅ አስረድቷል፡፡

" ጸጥታውን ማስከበር ያለበት እኮ የመንግስት አካል ነው " ያለው ማኀበሩ፣ " የራሱን ሥራ እንዴት መምህራን ላይ ይጥላል? ትክክል የማይሆነው ይሄ ነው፡፡ መምህራን ትምህርት ቤት ላይ ከሌሉ ትክክል ነው ደመወዛቸው መክፈል አይገባም የት እንዳሉ አይታወቅምና " ብሏል።

" ነገር ግን ማኀበረሰቡ ልጆችን ትምህርት ቤት ልጆቹን አልክም ብሎ ከሆነ መምህራን ደግሞ ትምህርት ቤታቸው ላይ ሆነው እንዴት ነው የማይከፈሉት። ይሄ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን መቱት አይነት ነገር ነውና ትክክል አይደለም " ሲል አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የመምህራንድምጽ

🔵 " ያለ ፍላጎት እና ያለ አግባብ 'በልማት ሰበብ' ደሞዝ ተቆርጦብናል " - የጎባ ወረዳ መምህራን

🔴 " ከነሱ ጋር ተነጋግረን የምንግባባ ከሆነ እንግባባለን፤ ካልሆነም ብራቸው ይመለሳል " - የጎባ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት


በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ክልል ጎባ ወረዳ ያሉ መምህራን ለልማት በሚል ሳቢያ " ያለ ፍላጎታችን እና አላግባብ " ደሞዝ ተቆርጦብናል በማለት ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

34 ገደማ ይሆናሉ የተባሉት መምህራን በዚህ ምክንያት ስራቸውን አቁመው ከትላንት በስቲያ ተቃውሞአቸውን ለማሰማት ወደ ሚመለከተው አካል በሰልፍ እንደሄዱ የጎባ ወረዳ መምህራን ተወካይ የሆኑት መ/ር ሀብታሙ ታደሴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የመምህራኑ ቅሬታ ምንድነው ?

- መምህራኑ እንዲቆረጥ የተወሰነባቸው ደሞዝ በአንድ አመት ውስጥ የአንድ ወር ደሞዝ ሲሆን ደሞዛቸው ያለፍቃድ በጥቅምት መቆረጥ ተጀምሯል።

- የወረዳውን መምህራን ከአንድም ሁለቴ በዚህ ጉዳይ ተወያይተዋል ነገር ግን " በወቅቱ የኑሮ ሁኔታ ምክንያት በየወሩ ከብድር ወደ ብድር እየተሻገርን ባለንበት ወቅት ደሞዝ እንዲቆረጥ አንፈልግም " ብለው ነበር።

- " እኛ ልማት ጠል አይደለንም " ያሉት መምህራኑ " በራሳችን ፍላጎት ልማቱን እንደግፍ እንጂ በግዴታ አይደለም " ሲሉ ነው የገለጹት።

- ከዚህ ቀደም ወረዳው በዚህ ጉዳይ መምህራንን ባወያየበት ወቅት እንደ ወረዳ መምህራን የራሳችን የአቋም መግለጫ አውጥተናል ሲሉ የመምህራኑ ተወካይ መ/ር ሀብታሙ ተናግረዋል።

ተወካዩ አክለው " ወደው፣ ፈቅደው፣ ፈርመው የሰጡት መምህራን እንዲቆረጥባቸው፤ ያልተስማሙት ደግሞ መብታቸው ተከብሮ እንደፍላጎታቸው እንዲደረግ አሳውቀናል" ሲሉም አስረግጠዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመምህራኑ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ የጎባ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ አስፋቸዉ አቱሞን አነጋግሯል።

አቶ አስፋቸው ምን አሉ ?

በወረዳው ከ400 በላይ መምህራን እንዳሉ የገለፁት አቶ አስፋቸው ወደ ሰባ ደገማ የሚሆኑት  በደሞዝ ቆረጣው እንዳልተስማዉ ገልፀዋል።

" የወረዳ ልማት ተብሎ ሁሉም መንግስት ሰራተኛ ተስማምቶ እየተቆረጠባቸው ነበር " ያሉት አቶ አስፋቸው " የተወሰኑ መምህራኖች ናቸው ችግር እየፈጠሩ ያሉት " ብለዋል።

መምህራኑ የተቆረጠባቸውን ደሞዝ በተመለከተ ከሚመለከተው ክፍል ጋር መነጋገራቸውንም ያስረዱት ኃላፊው " ከነሱ ጋር ተነጋግረን የምንግባባ ከሆነ እንግባባለን፤ ካልሆነም ብራቸው ይመለሳል እንጂ ልማቱ ምንም የሚሆንበት የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

ውሳኔውን ብቻቸውን መወሰን እንደማይችሉ የገለፁት ኃላፊው ከሌሎች የወረዳው ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚነጋገሩ አስረድተዋል።

" ከወረዳ ጋር ተነጋግረን መምህራኑ ሊስማሙ ይችላሉ። ካልተስማሙም መመለስ ይችላል " ያሉት አቶ አስፋቸው " ያን ያህል የተጨቆኑበት እኛ ያረግነው የሚካበድ አይደለም። ቀላል ነው። ትንሽም ስለሆኑም የነሱን ባንቆርጥም ልማቱን ወደ ኃላ ሊጎትት አይችልም " ሲሉ ገልፀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የመምህራንድምጽ

🔴 “ ‘ለምን ደመወዛችን ተቆረጠ’ ብለው የጠየቁ 66 መምህን  ታስረዋል” - የኮሬ ዞን መምህራን ማኀበር

🔵 “የታሰሩት በመምህራን ላይ ድንጋይ በመወርወር ሌሎቹን በመበጥበጣቸው ነው” - የዞኑ ትምህርት መምሪያ

🟢 “ምቹ ሁኔታ ላይ አይደለሁም። ሥራ ላይ ነኝ ስንት ሰዓት እንደምጨርስ አላውቅም”  - የዞኑ ሰላምና ጽጥታ ቢሮ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው በመቆረጡ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑና የክልሉ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የዞኑ መምህራን ማኀበር ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ጭበጮ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል፣ “‘ደመወዛችን ለምን ተቆረጠ’ ብለው የጠየቁ 66 መምህራን ታስረዋል” ብለዋል።

“‘የተቆረጠው ደመወዝ ከኛ ፈቃድና ስምምነት ውጪ ስለሆነ ይመለስልን’ የሚል ጥያቄ አቅርበው ነው የታሰሩት። ያለፈቃዳቸው ደመወዛቸው መቆረጡ፤ መታሰራቸው አግባብ አይደለም። አግባብ አለመሆኑን ለሚመለከተው አካል አሳውቀናል” ነው ያሉት።

“ከዞኑ መምህራን ማኀበር የታሰሩትን ለማነጋገር ሂደው የወረዳ አመራሮች የታሰሩት እንዳይጠየቁ ጭምር ከልክለዋል” ያሉት ሰብሳቢው፣ “ጥያቄያቸውን በውይይት መመለስ ሲገባችሁ ማሰር፣ መደብደብ፣ ማንገላታቱ ስህተት ነው” በሚል እየሞገቱ መሆኑን አስረድተዋል።

ስለጉዳየለ ማብራሪያ የጠየቅነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኀበር በበኩሉ፣ የመምህራኑ መታሰር ከዞኑ መምህራን ማኀበር ሪፓርት እንደተደረገለት በመግለጽ፣ “ያለአግባብ ማንም ተነስቶ ደመወዝ ቆርጦ መውሰድ ሕገወጥነት ነው” ሲል ወንጅሏል።

ከላይ ላሉት ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቃችኋል? በማለት የጠየቅናቸው የማኀበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ፣ የመምህራኑን መታሰር አረጋግጠው፣ “ትላንት ነው ከዞኑ ሪፖርት የተደረገልን። ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀናል” ብለዋል።

ያለፈቃዳቸው ደመወዝ መቁረጥና ለምን? ብለው የጠይቁ መምህራኑን ማሰር አግባብ ነው? የሚል ጥያቄ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ የቀረበላቸው የኮሬ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰረበ አሻግሬ፣ “ደመወዛቸው የተቆረጠው በፈቃዳቸው” ነው ሲሉ አስተባብለዋል።

ማኀበሩ ለእናንተም እንዳሳወቀ፤ ያለፍቃዳቸው እንደተቆረጠ፣ መምህራኑ እንደታሰሩ ነው የገለጸው፣ ፤ ይሄ ለምን ሆነ? በሚል ላቀረበሰነው ጥያቄ፣ “የሰርማሌ ወረዳ መምህን ጋር ተገናኝቻለሁ። ደመወዛቸው የተቆረጠው አሁን አይደለም፤ ፈቅደውም ነው” ብለዋል።

የኃላፊው ዝርዝር ምላሽ ምንድን ነው?

“ አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ የሚል በሁሉም አካባቢ ወላጅም፣ ሠራተኞችም፣ ተማሪም እንዲተባበር የሚል አገር አቀፍ ጉዳይ አለ። የዞኑ አመራሮች ተስማምተው ነው ወደ ታች የወረደው።

የትምህርት ቤቱ መምህራን ባለሉበት ውይይት ተካሂዷል። ተስማምተው ደመወዛቸው ከተቆረጠ ቆይቷል። ሐምሌና ነሐሴ አካባቢ ነው የተቆረጠው። በተቆረጠ ጊዜ ነበር መቆረጡ ልክ አይደለም ብለው ማመልከት የነበረባቸው።

ተስማምተው ከተቆረጠ በኋላ የሳርማሌ ወረዳ ብቻ ይህንን ተግባሪዊ ሲያደርግ የከተማ አስተዳደርና ጎርካ አላደረገም። ግን ዞን ማዕከሉም ተግባራዊ አድርጓል 25 ፐርሰንቱን።

በመምህራኑ ‘እንዴት ሌሎች አካበቢ ያሉ መምህራን ሳይቆርጡ የኛ ብቻ ተቆረጠ? ስለዚህ ገንዘባችን ይመለስ’ የሚል ጥያቄ ነው የተነሳው መጀመሪያ። ገንዘብ ይመለስ የሚለው ነገር በጋራ እንነጋገራለን።

መምህራን በሁለት ነው የተከፈሉት። ግማሹ ‘እያስተማርን እንጠይቅ’፤ ግማሹ ‘ሙሉ ለሙሉ ትምህርት እናቁም’ የሚል ነው። የተወሰኑት ለማስተማር ክፍል ሲገቡ የተወሰኑት ደግሞ ድንጋይ ይዞ የሚሄድ፤ ተማሪ ይውጣ የሚል አለ።

በመምህራን መካከል ግጭት ተፈጠረ። የተቆረጠው ገንዘብ ይመለስ በመባሉ ሳይሆን በመምህራኑ መካከል በተፈጠረው ግጭት ነው የታሰሩት። ችግር የፈጠሩ ሰባት መምህራን ነበሩ ትላንት የታሰሩት። 

መምህራኑ የታሰሩት ችግር ፈጥረው ነው ሳይፈጥሩ? የሚለውን  እንዲያረጋግጡ ለአራት ዞኑን መምህራን ማኀበር ወደ ታች እንዲወርዱ አሳይመንት ሰጥቻሁ። ትላንት ነበር አሳይመንት የሰጠሁት እነርሱ ግን የወረዱት ዛሬ ነው።

‘እንደገና ደግሞ ሌሎች መምህራን ታስረዋል’ ሲባል በምን ምክንያት ? ስል በፊት የታሰሩት መምህራን ለምን ታሰሩ ? ብለው ሊረብሹ መጥተው ነው የሚል መረጃ አለ። 

አሁን የዞኑን መምህራን ማህበር፣ ትምህርት ጽሕፈት ቤትንም አግኝታለሁ ውይይት ላይ ናቸው። 

የታሰሩት በመምህራን ላይ ድንጋይ በመወርወር ሌሎቹን በመበጥበጣቸው ነው እንጂ ያ በውይይት የሚፈታ ነው። በዚህ ተስማምተናል።
” ብለዋል።

መምህራኑ ለምን ታሰሩ ? በሚለው ጉዳይ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የኮሬ ዞን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንደሮ፣ “ ምቹ ሁኔታ ላይ አይደለሁም። ሥራ ላይ ነኝ ስንት ሰዓት እንደምጨርስ አላውቅም ” በማለት ለማብራሪያ ቀጠሮ ከመስጠትም ተቆጥበዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን፣ ምላሽ ሲሰጥ፣ ጉዳዩንም እስከመጨረሻው በመከታተል ተጨማሪ መረጃ የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የመምህራንድምጽ 🔴 “ ‘ለምን ደመወዛችን ተቆረጠ’ ብለው የጠየቁ 66 መምህን  ታስረዋል” - የኮሬ ዞን መምህራን ማኀበር 🔵 “የታሰሩት በመምህራን ላይ ድንጋይ በመወርወር ሌሎቹን በመበጥበጣቸው ነው” - የዞኑ ትምህርት መምሪያ 🟢 “ምቹ ሁኔታ ላይ አይደለሁም። ሥራ ላይ ነኝ ስንት ሰዓት እንደምጨርስ አላውቅም”  - የዞኑ ሰላምና ጽጥታ ቢሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ…
🔈 #የመምህራንድምጽ

#Update

የተደበደቡ ስድስት መምህራን ህክምና ተከልክለዋል። ከታሰሩት አንድም የተፈታ የለም ” - የዞኑ መምህራን ማኀበር

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ ከ60 በላይ መምህራን ከደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው የተቆረጠ ገንዘብ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑ መምህራን ማኀበር ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ፣ መምህራኑ ከእስር እንዳልተፈቱ፣ እየታሰሩ በነበረበት ወቅት ድብደባ የተፈጸመባቸው መምህራን እንዳይታከሙ መከልከላቸውን ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

የማኀበሩ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ጭበጮ ለበሰጡት ቃል፣ “ በሚያስሩበት ወቅት የተደበደቡ ስድስት መምህራን ህክምና ተከልክለዋል። ከታሰሩት ውስጥ አንድም የተፈታ የለም ” ብለዋል።

ተጎጂዎቹን እንዲያዩ የማኀበሩን ሰዎች ወደ እስራት ቦታው ልኮ እንደነበር የገለጹት አቶ ተስፋዬ፣ “ አሁን ባለው ሂደት ብዙዎቹ እንደተገጎዱ ናቸው። እንዲያውም የአንዱ በጆሮው ሁሉ መግል እየወጣ ነው ህክምና ተከልክለዋል ” ብለው፣ ለማሳከም ቢጠይቁም እንደከላከሏቸው ተናግረዋል።

መምህራኑ ከታሰሩ ስንት ቀናት አስቆጠሩ ? የተቆረጠባቸው ምን ያህል ገንዘብ ነው ? ለሚለው ቲክቫህ ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ደግሞ፣ “ ረቡዕ ነው እስራቱ የተጀመረው ፤ ዛሬ አራተኛ ቀናቸው ነው። 25 በመቶ ነው የተቆረጠባቸው ” የሚል ነው።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ፣ መምህራኑ ደመወዛቸው የተቆረጠው በፈቃዳቸው እንደሆነ፣ የታሰሩትም ገንዘብ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው ሳይሆን፣ “ ድንጋይ ወርውረው ሌሎችን በመበጥበጣቸው ” መሆኑን ነው የገለጸው፣ እውነትም እንደዛ ነው የሆነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ?

“ ይሄ ትልቅ ውሸት ነው። ቢነጋገሩ፣ ተስማምተው ቢሆን ኖሮ መምህራኑ ቅሬታ አያቀርቡም ነበር።

መምህራኑ ለትምህርት መምሪያው በፅሑፍ ያቀረቡት ‘አልተስማማንበትም፤ ባልተስማማንበት ጉዳይ የተቆረጠብን ገንዘብ ይመለስልን’ የሚል ነው።

‘ያልተስማማንበት ስለሆነ ገንዘቡ ይመለስ’ ብሎ እያንዳንዱ መምህር ትምህርት መምሪያውን ጠይቋል። መምሪያው ይሄን ሁሉ ክዶ ነው ለመሸፈን የሚሞክረው። ባወጣው መግለጫም እርምት ቢደረግ መልካም ነው።

ትምህርት መምሪያው መምህራኑ ‘ድንጋይ ወርውረዋል’ ማለቱ ውሸት ነው። አንድም የወረወረ የለም። አንድ መምህር ለስህተት ድንጋይ የሚባል ነገር አላነሳም። ይህን ወርዶ ማረጋገጥ ይቻላል ”
ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ፕሬዜዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ በበኩላቸው፣ “ ‘አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ’ በሚል ነው መምህራኑን ሳያወያዩ ‘በዞን ደረጃ ተወስኗል’ በሚል ከደመወዛቸው እየቆረጡ ያሉት ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ ደመወዝ ያለስምምነት መቆረጥ እንደሌለበት አቅጣጫ ቢቀመጥም ይሄን የሚያደርጉ አካላት ምንም ሲያደርጉ አይታዩም ” ሲሉም ተችተዋል።

“ ከዚህ በፊት ሌላ ዞንና ወረዳ ላይ እንደዚህ አይነት ነገር ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎች ተመልሰው የተሻለ ሹመት እንዲያገኙ ነው የሚደረገው እንጂ ‘ይሄን አጥፍተሃል’ ተብሎ የማጠየቅ አካል የለም ” ነው ያሉት።

ስለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ታምራት፣ ለጊዜው የማይመች ቦታ እንደሆኑ ገልጸው፣ ቀጠሮ ሰጥተው የነበረ ሲሆን፣ በቀጠሩት ሰዓት በተደጋጋሚ ቢደወልም ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ትላንት በሰጠን ማብራሪያ፣ የመምህራኑ ደመወዝ የተቆረጠው በስምምነታቸው መሠረት እንደሆነ፣ የታሰሩትም፣ ድንጋይ ስለወረወሩ እንደሆነ፣ ቅሬታው እንዲፈታ እየሰራ ስለመሆኑ ገልጾ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የመምህራንድምጽ #Update “ የተደበደቡ ስድስት መምህራን ህክምና ተከልክለዋል። ከታሰሩት አንድም የተፈታ የለም ” - የዞኑ መምህራን ማኀበር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ ከ60 በላይ መምህራን ከደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው የተቆረጠ ገንዘብ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑ መምህራን ማኀበር ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ፣ መምህራኑ…
🔈#የመምህራንድምጽ

#Update

" ሰባቱን ፍርድ ቤት ዋስትና እያስሞሉ ነው። ሌሎቹን ደግሞ ፈተዋቸዋል " - የኮሬ ዞን መምህራን ማኀበር

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ያለፈቃዳቸው ከደመወዛቸው የተቆረጠ ገንዘብ እንዲመለስ በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑና የክልሉ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

በአጠቃላይ ታስረው የነበሩት ከ66 በላይ እንደነበሩ፣ 22 የሚሆኑት መምህራን እስከዛሬ ድረስ በእስር ላይ እንደቆዩ፣ ቀሪዎቹ ግን ሰሞኑን እንደፈቷቸው የዞኑ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲገልጽ ነበር።

ከእስራት ያልተፈቱት ቀሪ 22ቱ መምህራን ዛሬ እንዲፈቱ ውይይት እየተደረገ እንደነበርም ማኀበሩ ጠቁሞ ነበር።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ በበኩሉ፣ 22ቱ መምህራን እንዲፈቱ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ገልጾ፣ ዛሬ እንደሚፈቱ ለቲክቫህ ተናግሯል።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰርበ አሻግሬ ዛሬ ከሰዓት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ደመወዛቸው የተቆረጠው ተስማምተው ስለመሆኑ ስም ዝርዝር እንዳላቸው ፤ በእስር ላይ ያሉትም እንደሚፈቱ  ገልጸዋል።

ጥያቄያቸው ወይ የእነርሱ ይስተካከል ወይ የእኛ ይመለስ የሚል ቢሆን እኔም ከጎናቸው ነኝ ብለዋል።

አቶ ሰርበ አሻግሬ ምን አሉ ?

“ ተስማምተው ከቆረጡ በኋላ እኔም ጋ የመጡት ‘እኛ ቆርጠን ሌሎቹ አልቆረጡም፤ ልክ አይደለም ተነጋገሩ’ ብለው ነበር። እኔም ስልጠና ላይ ስለነበርኩ ነው የቆየነው።
 
መምህራኑ ይፈታሉ። ማታ ለሁለት በድን ነግሬአለሁ። የመጀመሪያዎቹ ዋና በጥባጮቹ ሰባት ናቸው። ‘እነርሱ ለምን ታሰሩ?’ ብለው የገቡት 15 ናቸው። 15ቱ ከትላንትና ወዲያም ይውጡ ተብሎ ‘አንድ ላይ ነው የምንወጣው’ ብለው ነው።

የእናንት የሁለታችሁ ኬዝ የተለያዬ ስለሆነ ነው። የእናንተ ከፓሊስ ጋር በመጋጨት ነው ውጡ ተብለው እኮ 15ቱ መምህራን አንወጣም ነው እኮ ያሉት።

የታሰሩት 22 መምህራን ናቸው። ሰባቱ ተማሪዎቹን አባረው መምህራንንም የጠበጡ ናቸው። አሁን 66 ታሰሩ የሚለው ውሸት ነው። ሰባቱ መጀመሪያ ተያዙ፤ 15  በኋላ ገቡ። ትላንት ውጡ ተብለው እምቢ ብለው ነው። ዛሬ ይወጣሉ። ”
ብለዋል።

መምህራኑ ተፈተዋል ?

የዞኑ መምህራን ማኀበር ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ጭበጮ ምሽት 12 ሰዓት ገደማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት፣ መምህራኑ ከእስር ተፈትተዋል።

የማኀበሩ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ ሰባቱን ፍርድ ቤት ዋስትና እያስሞሉ ነው። ሌሉሎቹን ደግሞ ፈትተዋቸዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ሁሉም ተፈትተዋል ማለት ይቻላል? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ "ኦረዲ አዎ ለሰባቱ ብቻ ተያዢ ፈልገው ነው፡፡ ተያዦቹም ኦረዲ እየጨረሱ ናቸው" ብለዋል።

ተደበደቡ የተባሉት ምህራን እስከዛሬ ህክምና አግኝተው ነበር ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፣ ሳያገኙ እንደቆዩ የሚታከሙት ገና ካሁን ወዲያ እንደሆነ ምላሽ ሰጥተዋል።

የተፈቱት በምን ተስማምታችሁ ነው ? ለተሚለው የቲክቫህ ጥያቄ የሰጡት ማብራሪያ ደግሞ፣ መምህራኑና ትምህርት መምሪያው እንዲወያዩ፣ መምህራኑ ይመለስ ካሉ ገንዘቡ እንዲመለስ መወሰኑን ነው የገለጹት።

#Update - መምህራኑ ከእስር ተፈተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM