TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.7K photos
1.56K videos
216 files
4.28K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ነው የደረሰው ፤ እስካሁን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል " - ፖሊስ በአዲስ አበባ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ' አዲሱ ገበያ ' አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል። አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ መድረሱን ፖሊስ ጠቁሟል። በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ…
የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ቃል ፥ ከሰሜን ሆቴል ወደ አዲሱ ገበያ ይሄድ የነበረ ኮድ 3 43994 ሸገር ባስ ላይ ነው አደጋው የደረሰው።

እስካሁን የ1 ሰው ህይወት አልፏል። እድሜው ከ36 እስከ 40 የሚገመት ነው።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ህክምና ተቋም ተልከዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BRICS+ 16ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በሩሲያ ይጀመራል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ለመሳተፍ ካዛን ከተማ ገብተዋል። ከኢትዮጵያ መሪ በተጨማሪ ፥ - የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን - የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬድራ ሞዲ - የደቡብ አፍሪካው ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሩስያ፣ ካዛን ገብተዋል። የቻይናው…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ካዛን ፦ ከ16ኛው የ #BRICS+ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሀገራት መሪዎች የተናጠል ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፦
° ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ፕሬዜዳንት  ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ፣
° ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ
° ከኢራን ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ... ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ቪድዮ ፦ አርቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray🚨 በሓውዜን ወረዳ በተጣለ ተተኳሽ #የ4_ሰዎች ህይወት ጠፋ።   በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች ፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል። ሰኔ 1/2016 ዓ.ም በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ፤ ሓውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በፈነዳ ተተኳሽ የ4 ወገኖች ህይወት #ተቀጥፏል። ከአራቱ የአደጋው ሰለባዎች ሶስቱ የአንድ…
#ትግራይ

" ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ብቻ ባልመከኑ ተተኳሾች ከ51 በላይ ወገኖች ሲቀጠፉ ፤ ከ286 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ሰለባ ሆኗል " - በትግራይ ማእከላይ ዞን የየጭላ አበርገለ ወረዳ የፀጥታ ፅ/ቤት

በትግራይ በነበረው አውዳሚ እና አሰቃቂ ጦርነት ወቅት ተቀብረው እና ተጥለው ያልመከኑ ተተኳሾች የንፁሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፍና አካል ማጉደል ቀጥለዋል።

በየጭላ አሸርገለ ወረዳ የእምባ ሩፋኤል ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ አርሶ አደር ባልመከነ ተተኳሽ 2 ልጆቻቸው ሲያጡ አንዱ ቆስሎ ተርፎላቸዋል።

ሌላዋ እናት ቁርስ አብልተው ለእንጨት ለቀማ የላኩዋቸው ልጆቻቸው አንዱ በተጣለ ተተኳሽ ሲሞት ሌላኛው የአካል ጉዳተኛ ሆኗል።

በጦርነቱ ወቅት በአከባቢው በነበረው የጦር መሳሪያ ዲፓ የቀሩ የተጣሉና የተቀበሩ በርካታ ያልመከኑ ተተካሾች መኖራቸው የጦቆሙት የጥቃቱ ሰለባዎች ፤ በሰው እና በእንስሳ ከፍተኛ አደጋ በማድረስ የሚገኘው ተተኳሽ እንዲወገድላቸው ጠይቀዋል።

የክልሉ እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት የአደጋው አስከፊነት በመረዳት አከባቢያቸው ከተተካሾች እንዲታደጉላቸውም ተማፅነዋል።

የወረዳው የፀጥታ ፅ/ቤት የአርሶ አደሮቹ አስተያየት በመጋራት ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ከ51 በላይ ወገኖች ባልመከኑ ተተኳሾች ህይወታቸው ሲቀጠፍ ፤ ከ286 በላይ ደግሞ ለአካል ጉዳት እንደተጋለጡ ገልጸዋል።

" ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ነው " ያለው ፅ/ቤቱ ህዝቡ ከስጋት ድኖ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ መንግስትና ለጋሽ ደርጅቶች አከባቢውን ከተተኳሾች ለማፅዳት የበኩላቸው እንዲተባበሩ ጠይቋል።

" ዘላቂው መፍትሄ በአከባቢው ላይ ያለውን ተተኳሽ ማፅዳት ነው ፤ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት የወዳደቁና የተቀበሩ ተተኳሾችን በማስወገዱ በኩል አከባቢያችን ትኩረት ያሻዋል " ሲል ፅ/ቤቱ አስገንዝቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከድምፂ ወያነ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዶላር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዶላር ዋጋ አሽቆለቆለ። ባለፉት በርካታ ቀናት በንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112 ብር ከ3957 ሳንቲም እየተገዛ በ123 ብር ከ6353 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር። ዛሬ ባንኩ ይፋ ባደረገው የዕለታዊ የምንዛሬ ተመን አንዱን የአሜሪካ ዶላር የሚገዛበትን ዋጋ ወደ 113 ብር ከ1308 ሳንቲም አሳድጎ መሸጫውን ወደ 115 ብር ከ3934 ሳንቲም አውርዶታል። እንደ ዛሬው…
#ExchangeRate

የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጭማሪ አሳየ።

ባለፉት ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113 ብር ከ1308 ሳንቲም እየተገዛ በ115 ብር 3934 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር።

ዛሬ ይፋ በተደረገው የምንዛሬ ዋጋ ተመን አንድ ዶላር መግዣው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ  116 ብር ከ6699 ሳንቲም የገባ ሲሆን መሸጫው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ 119 ብር ከ0033 ሳንቲም ገብቷል።

በተመሳሳይ በሌሎችም የውጭ ሀገር የገንዘብ ምዛሬ ላይ ጭማሪ ታይቷል።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ ፦ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የነዳጅ ማደያዎች እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠንን ከትላንት ጀምሮ ይፋ ማድረግ ጀምሯል።

አሁን ላይ በከተማዋ 123 ማደያዎች ግልጋሎት እየሰጡ ነው ተብሏል።

ቢሮው ፤ " በየዕለቱ የነዋጅ ማደያዎችን እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ይፋ ማድረግ የተጀመረው በአገልግሎቱ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የተገልጋች እንግልት ለመቀነስ ነው " ብሏል።

ነዳጅ ማደያዎች የት ቦታ እንደሚገኙ እና በእለቱ የተራገፈው ነዳጅ መጠን እንዲሁም የጥቆማ ስርዓቱ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለጽ አሳውቋል። ሚኒስቴሩ ፤ " በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጸል " ብሏል። ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል። @tikvahethiopia
#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.iss.one/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#DStvEthiopia

ዛሬ ምሽት ማን ዩናይትድ ከቀድሞ አሰልጣኛችው ሞሪኒዮ ጋር ይገናኛሉ!
ወደ ቱርክ ተጉዞ ከፌነርባቼ ጋር ይጫወታል! ይህንን ደማቅ ፍልሚያ በቀጥታ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በቀጥታ በSS Football በ ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ።

ዩናይትድ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ይችላል?

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ይከታተሉ!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ 👇
www.dstv.com/en-et
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
Forwarded from telebirr
ኢትዮ 130 እንደተለመደው በ4ኛውም ዙር 100 ሺህ ብርን ጨምሮ ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች ለዕድለኞች አበርክቷል!!

ዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ!! 🎉🎉

🔥 ሽልማቶቹ ገና አልተነኩም 6ቱን ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎችን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶች አሁንም እርስዎን ይጠብቃሉ!

💡ጥቅልና የአየርሰዓት በመግዛት፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር በመፈጸም እንዲሁም ገንዘብ በመላክና በመቀበል ተጨማሪ የጨዋታ ዕድሎችን ያግኙ!

🚘 6 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች
🛺 9 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች
💰በየቀኑ የ20 ሺህ ፤ በየሳምንቱ የ50 ሺህ እና 100 ሺህ ብር ገንዘብ ሽልማቶች በቴሌብር
📱 ዘመናዊ ስማርት ስልኮች እንዲሁም
🎁 በርካታ የሞባይል ጥቅሎች!

እነዚህን አጓጊ ሽልማቶች የግልዎ ለማድረግ በቴሌብር ሱፐርአፕ ኢትዮ130 መተግበሪያ ወይም ለኢትዮ ፕሮሞ 1 ቁጥርን ወደ 130 በመላክ ለኢትዮ130 ላኪ ስሎት 131 ላይ Ok ብለው በመላክ ይመዝገቡ!

ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/3Y0pGzs ይጎብኙ!

#130_ዓመታትን_በጽናት_ታላቅ_አገርና_ሕዝብ_በማገልገል_ላይ

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#Tigray

" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " - የትግራይ ክልል የፀጥታ እና የሰላም ቢሮ 

የትግራይ ክልል ፀጥታ እና ሰላም ቢሮ ባወጣው መግለጫ ፤ " የህዝብ እና የሰራዊት አንድነት በማላላት የአርስ በርስ ግጭት እንዲከሰት የሚሰሩት ግለሰቦች እና አካላት አንታገስም " ብሏል።

እንዲህ ያለው ተግባር ላይ ስለተሰማሩት ግለሰቦችና አካላት በግልጽ ስም ጠቅሶ ያለው ነገር የለም።

ቢሮው ፥ " በአገር ውስጥ እና በውጭ በመሆን በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በመጠቀም በሬ ወለደ ውሸት በመንዛት በክልሉ የፀጥታ ሃይልና ህዝብ መካከል ያለው አንድነት እንዲላላ እየተሰራ እያየን በትእግስት ለማለፍ መርጠናል " ብሏል።

" ከአሁን በኋላ ህግ እንዲከበር በጥብቅ ይሰራል " ሲል አስታውቀዋል ።  

" በፀጥታ ሃይሉ ጉድለት አለ የሚል አካል ተጨባጭ አሳማኝ መረጃ በማቅረብ ህጋዊ በሆነ መልኩ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል " ያለው ቢሮው " ይሁን እንጂ ፓለቲካ አስታኮ የሚነዛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ውሸት በግለሰብም ሆነ በየትኛውም አካል አያሰጠይቅም ማለት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ሲል አስጠንቅቀዋል። 

" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረውም ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " ሲልም ገልጿል።

ቢሮው ፤ " የፀጥታ ሃይል የማንም የፓለቲካ ቡድን መሳሪያ አይደለም " ሲልም አክሏል።

የፀጥታ ኃይሉ በክልሉ ባለው የፓለቲካ መከፋፈል መካከል ገብቶ የአንዱ ደጋፊ የሌላው ተቃዋሚ እንዲሆን ታልሞ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ መሆኑን የገለጸው ቢሮው " ይህ አይሳካም ፍፁም ተቀባይነት የለውም፤ ይህንን ተላልፎ የሚገኝ ግለስብና አካል በህግ እንዲጠየቅ በማድረግ የህግ ልእልና እንዲከበርና የህዝቡ ሰላምና ፀጥታ እንዲከበር እንሰራለን " ብሏል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ካዛን ፦ ከ16ኛው የ #BRICS+ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሀገራት መሪዎች የተናጠል ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። በተጨማሪም ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፦ ° ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ፕሬዜዳንት  ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ፣ ° ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ…
#BRICS+

በሩስያ፣ ካዛን ሲካሄድ የቆየው የBRICS+ አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።

ስብስቡ 13 ሀገራትን በአጋር (ፓርትነር) አድርጎ ተቀብሏል።

ሀገራቱን የBRICS አጋር (ፓርትነር) አድርጎ የተቀበለው በ2024 ምንም አይነት አዲስ ሙሉ አባል ሀገር ላለመቀበል በመወሰኑ ነው።

13ቱ ሀገራት ወደፊት የስብሰቡ ሙሉ አባል ሀገር ለመሆን እንደሚሰሩ ነው የተነገረው።

የBRICS+ ሙሉ አባል ሀገራት እነማን ናቸው ?

🇧🇷 ብራዚል
🇷🇺 ሩስያ
🇮🇳 ሕንድ
🇨🇳 ቻይና
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ
🇮🇷 ኢራን
🇪🇬 ግብፅ ናቸው።

አሁን BRICS+ን በአጋርነት (ፓርትነር) ሆነው የተቀላቀሉት እነማን ናቸው ?

🇩🇿 አልጄሪያ
🇧🇾 ቤላሩስ
🇧🇴 ቦሊቪያ
🇨🇺 ኩባ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇰🇿 ካዛኪስታን
🇲🇾 ማሌዢያ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇹🇭 ታይላንድ
🇹🇷 ቱርክ
🇺🇬 ዩጋንዳ
🇺🇿 ኡዝቤኪስታን
🇻🇳 ቬዬትናም ናቸው።

በካዛኑ የBRICS+ የመሪዎች ጉባኤ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ፣ የቬንዝዌላው ፕሬዜዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ተገኝተው ነበር።

የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ካዛን ተገኝተው ነበር። ሳዑዲ ምንም እንኳን በይፋ የBRICS ስብስብን ባትቀላቀልም በተጋባዥ ሀገርነት ትሳተፋለች።

የሌሎች ሀገራት መሪዎችና ተወካዮችም በካዛን ተገኝተው ነበር።

#BRICSSummit #Russia

@tikvahethiopia