TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SavetheChildren #MoH

የህፃናት አድን ደርጅት (Save the children) በኢትዮጵያ በ3 ክልሎችበ16 ወረዳዎች የክትባት ተደራሽነትን ለማስፋፋት የሚረዳ “ቡስት” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ድርጅቱ ፕሮጀክቱን ይፋ ያደደረገው ከጂኤስኬ ተገኘ በተባለ የገንዘብ ድጋፍ ፣ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው።

ፕሮጀክቱ በአማራ፣ ኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች በሚገኙ 16 ወረዳዎች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ክትባት በሚስጥበት ወቅት ገጠራማ በሆኑ ቦታዎች ለትራንስፓርት አገልግሎት የሚረዱ 50 ታብሌቶች የተገጠሙላቸው 52 ሞተር ሳይክሎችን ድርጅቱ አበርክቷል።

ድርጅቱ ፥ “ በዚህ ፕሮጀክት ከ200 ሺሕ በላይ ልጆች እንዲከተቡ ይደረጋል ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ቲክቫህ ለህጻናቱ የሚሰጡት ክትባት የምን በሽታ መከላከያ ነው ? ሲል ላቀገበው ጥያቄ “ በጤና ሚኒስቴር የተቀመጡትን 13ቱንም ክትባቶች ሳፓርት እናደርጋለን ” የሚል መልስ ከድርጅቱ ተሰጥቷል።

ክትባቱ ፦
- ሚዝልስ፣
- ፓሊዮ፣
- ዲያሪያ፣
- ኒሞኒያና ከመሳሰሉ ህመሞች የሚከላከል ነው ተብሏል።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴዔታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ “ በኢትዮጵያ ውስጥ ክትባት በአግባቡ ያልወሰዱና ጭራሽም ያልወሰዱ በርከት ያሉ ህፃናት አሉ ” ሲሉ ጠቁመዋል።

እኚህም ከ1 ሚሊዮን በላይ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

እነዚህም ራቅ ያሉ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ናቸው።

ምንም ክትባት ያላገኙና ጀምረው ያቋረጡ ህፃናት በአብዛኛው በአማራ፣ ኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች እንደሚገኙ በጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-01

 #TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ERMP 2024 List of Matched Candidates (1).pdf
947.6 KB
#MoH
#ERMP_2024_Matching

የጤና ሚኒስቴር የ2024 የብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) አመልካቾች ምደባ (Matching) ለቋል።

በምደባው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በሚኒስቴሩ ነጻ የስልክ መስመር 952 በሥራ ሰዓት ብቻ እስከ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

" የተቋም/የፕሮግራም/የስፖንሰር ለውጥ አድርጉልኝ ጥያቄ እንደ ቅሬታዎች የማይወሰዱ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም " ብሏል።

Via @tikvahuniversity