TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የዜጎችድምጽ

ችግሩ ቢነገር ቢነገር መፍትሄ ያልተገኘለት በክልሎች ያለው የቤንዚን ጉዳይ !

በክልል ከተሞች ነዳጅ በተለይም ቤንዚን ማግኘት ፈተና እንደሆነ ቀጥሏል።

በርካታ በትራንስፖርት ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ባለው ችግር ምክንያት ሰርቶ መግባት ቤተሰብ ማስተዳደር ከባድ ሆኖባቸዋል።

ከክልል ከተሞች አንዷ የሲዳማ መዲናዋ ሀዋሳ ናት።

በዚህች ከተማ ነዳጅ እንደልብ ማግኘት ከቆመ ዓመታት አልፈዋል።

ያለው ችግር በተደጋጋሚ ቢነገርም በክልል መዲናይቱ ምንም የተቀየረ ነገር የለም። አሁንም ችግሩ እንደቀጠለ ነው። እንደልብ ነዳጅ ማግኘት አይቻልም።

አሽከርካሪዎች " ነዳጅ ማግኘት ከፍተኛ መከራ ሆኖብናል " ሲሉ ድምጻቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።

" ብላክ በኃይላድ እየተሞላ እንደሸቀጥ ዕቃ በየሱቁ አንድ ሊትር  ከ160 እስከ 180 ከዛም በላይ እየተሸጠ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በከተማው በርካታ ማደያዎች ቢኖሩም ነዳጅ ማግኘት ስቃይ ነው።

ነዳጅ በፕሮግራም ማሸጥ ከተጀመረም በርካታ ወራት አልፈዋል።

ምንም እንኳን በየማደያው ቤንዚን የለም ይባል እንጂ ባጥቁር ገቢያ ነጋዴዎች በከፍተኛ ብር እንደጉድ ይቸበቸባል።

ቤንዚን ከከተማ እስከ ገጠር ድረስ ከጥቁር ገበያው ጠፍቶ አያውቅም።

ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉት የሥራ ኃላፊዎች " ችግሩ ይቀረፋል እየሰራን ነው " እያሉ ተደጋጋሚ ቃል ከመስጠት ውጪ ያመጡት መሬት ላይ የሚታይ ለውጥ እንደሌለ ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ባለው ሁኔታ ምክንያት " ሰርቶ መኖር በጣም ችግር ሆኖብናል " ብለዋል።

ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ሌሎች ክልሎችም ብንመለከት የቤንዚን ችግር እንደዚሁ ነው።

በየማደያው የለም የሚባለው ቤንዚን ከጥቁር ከገበያ እንደልብ ሲገኝ ይታያል።

ቃላቸውን የሰጡን ነዋሪዎች " ቤንዚን በየሱቁ ፤ በየመንደሩ እንደጉድ ይቸበቸሻል ነዳጅ ማደያ ሲኬድ የለም ነው መልሳቸው " ብለዋል።

" ህዝብ እየተሰቃየ ነው። በተለይ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች መከራቸውን እያዩ ነው። ችግሩ በርካታ ጊዜ ቢያልፈውም ለምን ማስተካከል እንዳልተቻለ ሊገባን አልቻለም " ሲሉ አክለዋል።

ከነዳጅ ማደያዎች ሌሊት በሲኖትራክ ሳይቀር ነዳጅ ተጭኖ እንደሚወጣ ፤ በዚህ የጥቁር ገበያና የነዳጅ ሽያጭ ሰንሰለት እጃቸው የረዘመ በመዋቅር ውስጥ ያሉ አካላት ሊኖሩ እንደሚችላ ጠቁመዋል።

በየመዋቅሩ ተጠቃሚ ሰዎች ባይኖሩ እንዴት ይሄን ያህል ጊዜ ችግሩ ይቀጥላል ? ሲሉም ጠይቀዋል።

ለአብነት ወላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ ቤንዚን ማግኘት አይታሰብም።

በጥቁር ገበያ እስከ 200 ብር ድረስ ይቸበቸድረስ

ከዚህ ባለፈ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከነዋሪዎች እንደሰማው አንዳንድ ከከተማ የወጡ ማደያዎች ሳይቀሩ ነዳጅ በድብቅ ይሸጣሉ።

አንድ ሊትር ቤንዚን 92 ብር መሸጥ ሲገባው ከጀርባ በትውውቅ እስከ 220 ብር ድረስ ለመሸጥ የሚደራደሩ አሉ።

ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የመፍትሄ እርምጃ ሲወሰድ እና ማስተካከያ ሲደረግ አይታይም።

በአጠቃላይ በክልል ከተሞች በቤንዚን ምክንያት ስራ መስራት ፈተና እንደሆነ ነው። ከከተማ ወጥቶ ለመስራትም እየተቻለ አይደለም።

የዚህ ሁሉ ችግር መጨረሻ የሚወርደው ህዝብ ላይ ነው። " ነዳጅ የለም ተወዷል " በሚል በትራንስፖርት ተገልጋዩ ዜጋ ላይ የሚጨመረው ዋጋ ከፍተኛ ነው ፤ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ይሄ ተጨምሮ የሚያሳድረው ተፅእኖ እንዲሁ በቃላት የሚገለጽ አይደለም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM