TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ 320 የትግራይ ተዋጊዎች ትጥቅ አውርደው አስረክበዋል። የቀድሞ ትግራይ ተዋጊዎች ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊትም ታጣቂዎች ያወረዷቸውን ትጥቆች ርክክብ አድርጓል። በዛሬው ዕለት 320 የትግራይ ተዋጊዎች ቀላል መሳሪያዎችን አውርደው በማስረከብ ወደ ተሃድሶ ያስልጠና ማዕከል አቅንተዋል። …
#DDR
" ትጥቅ መፍታት መሸነፍ ፣ መዋረድ ወይም ራስን ዝቅ ማድረግ ማለት አይደለም። ትጥቅ መፍታት ማለት የሀገር አንድነትና ሰላም በፅኑ መሰረት ላይ ከማቆም አንፃር መታየት አለበት " - የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር
የመጀመሪያ ዙር የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝድ በማድረግ ወደ ተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማስገባት ስራ በይፋዊ ስነስርዓት ተጀምሯል።
ዛሬ በተካሄደ ይፋዊ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያው ፤ " የዴሞብላይዜሽን አሰራር ሴት ተዋጊዎችን ፣ አካል ጉዳተኞችን እና በአደረጃጀት ውስጥ ያሉ አመራሮችን በማስቀደም ይፈፀማል " ብለዋል።
በዴሞብላይዜሽን አሰራር በየቀኑ 320 ታጣቂዎች ወደ ስልጠና ማእከላት የማስገባት ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በመጀመሪያ ዙር 75 ሺህ ታጣቂዎች እንደሚስተናገዱ አክለዋል።
" ማንኛውም ትጥቅ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ መያዝ የሀገሪቱ ህገ-መንግስት ይከለክላል ስለሆነም በትግራይ እየተፈፀመ ያለው የዴሞብላይዜሽን አፈፃፀም ህግና ስርዓት ተከትሎ የሚፈፀም ነው " ሱሉ ተናገረዋል።
ብ/ጄነራሉ ፤ " ትጥቅ መፍታት መሸነፍ ፣ መዋረድ ወይም ራስን ዝቅ ማድረግ ማለት አይደለም። ትጥቅ መፍታት ማለት የሀገር አንድነትና ሰላም በፅኑ መሰረይ ላይ ከማቆም አንፃር መታየት አለበት " ብለዋል።
" ትጥቅ ማስረከብ ማለት ያለችን እንዲት ሀገር ከሚጋረጡባት የውጭ ስጋቶች መታደግ መሆኑን መገንዘብ ያሻል " ያሉት ጀነራሉ " ትጥቅ የማስፈታት ተግባሩ የትግራይ እና በክልሉ ደንበር አከባቢ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተፈፃሚ ይሆናል " ሲሉ አሳውቀዋል።
የትግራይ የፀጥታ እና የሰላም ቢሮ ሃላፊ ጀነራል ፍስሃ በበኩላቸው ፤ " ትጥቅ የመፍታቱ ተግባር እርምጃ ለትግራይና ለሀገር ሰላም የተከፈለ ውድ እና ሁሌ በታሪክ ድምቆ የሚታወስ ፍፃሜ ነው " ብለዋል።
ዛሬ ትጥቃቸው ያስረከቡ 320 የቀድሞ ተዋጊዎች ሲሆኑ ወደ ተዘጋጀላቸው የስልጠና ማእከላት ማምራታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ስነ-ስርዓቱ ከተከናወነበት ቦታ በላከው መረጃ ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia