TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE : በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ መደረጉንም ይፋ አድርጓል። " ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር…
#MoE
በወጥነት ይተገበራል የተባለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምግብ ሜኑ ምን ይመስላል ?
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 (መቶ ብር) እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑም ሁሉም ጋር ወጥ እንዲሆንብ እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ አይዘነጋም።
ይህንን ተከትሎ ፤ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በወጥነት እንዲከናወን ትምህርት ሚኒስቴር ከምግብ ተመን ማሻሻው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል።
የምግብ ሜኑው ዝቅተኛውን መስፈርት መሠረት በማድረግ መዘጋጀቱን የገለጸው ሚኒስቴሩ ተቋማት ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ተማሪ ሳምንታዊ ወጪው ከ700 (ሰባት መቶ) ብር ባልበለጠ መልኩ ስራ ላይ መዋል እንዳለባቸው ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
ለዩኒቨርሲቲዎች በተላከው የምግብ ሜኑ ከላይ የተያያዘ ሲሆን ፦
👉 ቁርስ ላይ ፦ እንጀራ ፍርፍር / ሩዝ + ዳቦ + በሻይ ፣ ቅንጬ ፣ ስልስ ፣ ማካሮኒ ተካተለዋል።
👉 ምሳ ላይ ፦ ምስር/አተር ክክ/ሽሮ / አተር / ባቄላ / ድንች / አትክልት ማለትም ጎመን ፣ድንች፣ ካሮት የመሳሰሉ / ፓስታ / + እንጀራ / ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪም በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።
👉 እራት ላይ ፦ ምስር/ክክ/ፓስታ / ሽሮ + በእንጀራ/ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪ በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።
🔵 ለበለጠ መረዳት ከሰኞ እስከ እሁድ የተከፋፈለውን የምግብ ሜኑ ከላይ መመልከት ይቻላል።
አጠቃላይ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች በላከው የምግብ ሜኑ መሰረት ለቁርስ ፣ ለምሳ፣ ለእራት ለአንድ ተማሪ የተመደበው 100 ብር ነው።
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የተመደበው ዕለታዊ የምግብ በጀት በየጊዜው እየጨመረ ያለውን የምግብ ዋጋ ንረት ሊሽፍን ባለመቻሉ መንግሥት በፊት የነበረውን ዕለታዊ የተማሪ ምግብ ወጪ 22 ብር ወደ 100 ብር ከፍ አድርጎታል።
(በትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ሰርኩላር ከላይ ተያይዟል)
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia

#NGAT
ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከታህሳስ 21 እስከ 25/2017 ዓ.ም ይከናወናል፡፡
ለመመዝገብ 👇
HTTPS://NGAT.ETHERNET.EDU.ET
ከምዝገባው ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ [email protected] ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 (Enatnesh Gebeyehu) እና 0911335683 (Fasil Tsegaye) ማብራሪያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል።
የመፈተኛ ' USER NAME ' እና " PASSWORD ' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈጸም ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡
ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
#MoE
Via @tikvahuniversity

የመውጫ ምዘና ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12 /2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ተገለጸ።
በክረምት በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ሲከታተሉ ቆይ የመውጫ ምዘና ለሚጠባበቁ መምህራን የመውጫ ምዘና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደርጓል።
በዚህም የመውጫ ምዘናው ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን መምህራኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዳያድረጉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
ሚኒስቴሩ ምዘናው በየአቅራቢያ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጥ መሆኑን ገልጾ " በቀጣይ ክልል / ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮዎች በኩል የምናሳውቃችሁ ይሆናል " ብሏል።
#MinistryofEducation

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ከትላንት ጀምሮ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ምዝገባው እስከ ጥር 14/2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ታውቋል።
ከተጠቀሰው ቀን ውጭ ምዝገባ ማድረግ አይቻልም።
ምዝገባው በ https://exam.ethernet.edu.et ላይ የሚካሄድ ሲሆን ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ በቀጣይ ይፋ ይደረጋል።
የመፈተኛ User Name እንዲሁም Password በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም እንዳለበት ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ማንኛውም አይነት ጥያቄ ዘውትር በሥራ ሰዓት በኢሜል [email protected] በስልክ ቁጥር 0911824528 / 0913678404 / 0913949676 / 0910076453 / 0923106826 / 0913866717 / 0911335683 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ተብሏል።

#EthiopianDefenceUniversity
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፥ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት አሳውቀዋል።
ሚኒስትሩ ይህንን ያሳወቁት ከከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው።
#MoE
@tikvahuniversity

" የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ ማስረጃ እንዳትሰጡ " - ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡ ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ አሳስቧል፡፡ በሚኒስቴሩ የመምህራን ትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ከሳምንት በፊት የተጻፈው…
#MoE
በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በክረምት መርሐግብር ሲከታታሉ ለቆዩ መምህራን የመውጫ ምዘና ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓ.ም ይሰጣል።
የምዘና ፈተናው መምህራኑ በሚኖሩባቸው አቅራቢያ ባሉ አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንደተጠናቀቀ ማለትም ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል።
ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ ማሳሰቡ ይታወቃል።

" በዚህ ዓመት 150 ሺህ የሚደርሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በበየነ መረብ (ኦንላይን) ይወስዳሉ " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ
ባለፈው ዓመት ወደ ተግባር የገባው የኦንላይን ብሔራዊ ፈተና ዘንድሮም እንደሚቀጥል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ዓመት 150 ሺ የሚደርሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በበየነ መረብ (ኦንላይ ) እንዲወስዱ ቅድመ ዝግጅ እየተደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።
ይህንን ያሉት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ላይ ነው።
ከዚህ ባለፈ በመድረኩ " ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥራት ያለው ትምህርት በማግኘት ረገድ እኩል እድል እንዲኖረው ፤ በድሃና ሃብታም መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ ሥራ መስራት አለብን " ብለዋል።
" ይችን ሀገር መለወጥ የሚቻለው የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር ሲቻል " ነው ሲሉም ገልጸዋል።
በመንግስት ትምህርት ቤቶች የተሻለ የመማር ማስተማር እንዲኖር ማድረግ ላይ መሥራት እንደሚገባና ' በትምህርት ለትውልድ ' የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል የተጀመረው ንቅናቄ ግለቱን ጠብቆ እንዲሄድ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በሌላ በኩል ፤ የመምህራንን አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከተመረቁ ዜጎች ውስጥ ልዩ የማስተማር ሙያ (pedagogy) ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ወደ ሙያው እንዲገቡ እንደሚደረግ ይፋ አድርገዋል።

" በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ ይገባል " - ትምህርት ሚኒስቴር
የካቲት 21/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፤ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ እና የሠራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻል።
የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ያትታል።
በዚህም በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ እንደሚገባ / እንደ ቅደመ ሁኔታ መቀመጡን አሳስቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙበትን ዓላማ እንዲያስፈፅሙ አሳሰበ።
የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፥ * የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙበትን ዋና ዓላማ መዘንጋት የለባቸውም " ሲሉ አሳሰቡ።
ሚኒስትሩ ይህን ማሳሰኒያ የሰጡት ዛሬ ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።
" ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ችግር ፈቺ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቅባቸዋል " ያሉት ፕ/ር ብርሃኑ ፥ ተቋማቱ በአካባቢ ሳይታጠሩ ለተመሠረቱበት ዓላማ መኖር አለባቸውም ብለዋል፡፡
- የሙስና መንሰራፋት፣
- ግብረ-ገብነት ማጣት
- ዕውቀት የመቀያየር ባሕል በምሁራን ዘንድ መቀዛቀዙን አንስተዋል
እነዚህ ችግሮች ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የዕውቀት ማዕከል እንዳይሆኑ አድርገዋል ብለዋል።
" ሀገራችን በዘርፈ-ብዙ ችግሮች ውስጥ በመሆኗ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የመፍትሔ ሐሳብ ማመንጨት ይጠበቅባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት እና የእውነት ማዕከል እንዲሆኑየሪፎርም ሥራ እየተከናወነ ነው " ሲሉም አመልክተዋል።
ተቋማቱ፤ ጥራት ባለው ትምሕርት ትውልድን መቅረጽ እና የማሕበረሰቡን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችሉ ምርምሮችን በማድረግ ሀገራዊ ግዴታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም በአጽንኦት አሳስበዋል።
Credit - #FMC

#MoE #NGAT
ትምህርት ሚኒስቴር የሶስተኛውን ዙር የ2017 ዓ.ም የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ አደረገ።
ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ በ https://ngat.ethernet.edu.et/registration የመመዝገቢያ ሊንክ በኩል እንደሚከናወን አሳውቋል።
ከምዝገባው ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ [email protected] ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 እና 0911335683 ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚቻልም አመልክቷል።
የመፈተኛ ' USER NAME ' እና " PASSWORD ' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል ይላካል ያለው ሚኒስቴሩ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 እንደሆነና በቴሌብር በኩል ብቻ እንደሚፈጸም ገልጿል።
ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል። ተፈታኞች በፈተና ወቅት የተሰጣቸውን User Name እና Password፣ እንዲሁም ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል ብሏል።

#MoE #NGAT ትምህርት ሚኒስቴር የሶስተኛውን ዙር የ2017 ዓ.ም የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ አደረገ። ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ በ https://ngat.ethernet.edu.et/registration የመመዝገቢያ ሊንክ በኩል…
#Update #MoE
" እስከምሽት ድረስ እየሞከሩ መቆየት ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር
ሀገር አቀፍ የ2017 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የአመልካቾች ምዝገባ ከ የካቲት 27/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ እንደሚከናወን የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ዛሬ በሚያበቃው የአመልካቾች የምዝገባ ሂደት ለመመዝገብ የሞከሩ ተፈታኞች የመመዝገቢያው ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንክ እየሰራ አይደለም የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
ከምዝገባ ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሚል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስቀመጣቸው ስልኮች ቢኖሩም እየሰሩ አለመሆኑንም ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ዶ/ር ኤባ ሚጀናን ማብራሪያ ጠይቋል።
በምላሻቸውም " የኔትወርክ ችግር ይሆናል እንጂ ሲስተሙ ይሰራል ደጋግማቹ ሞክሩ " ብለዋል።
አክለውም " ሁሉም ሳይሆን የተወሰኑ ሰዎች ናቸው ለመመዝገብ እክል የገጠማቸው በርካታ ሰዎች አሁንም እየተመዘገቡ ነው " ያሉ ሲሆን እስካሁን ባለው 8 ሺ የሚጠጋ ሰው መመዝገቡን ጠቁመዋል።
" ፕሮሲጀሩን መከተል ግድ ይላል ከዘለሉ ላይሰራ ይችላል ነገር ግን ሁል ጊዜ ብዙ ሰው በመጨረሻ ነው የሚመዘገበው ፣መጨናነቅ ይኖራል እንዳይዘጋ በሚል በርካታ ሰዎች በአንድ ላይ ስለሚሞክሩ ጫና ይኖራል በዚህ ምክንያት ካልሆነ በቀር ምንም ችግር የለበትም " ነው ያሉት።
ሊራዘም የሚችልበት አጋጣሚ ይኖራል ወይ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄም " መራዘም ሳይሆን እስከምሽት ድረስ እየሞከሩ መቆየት ይችላሉ ኔትወርክ ያለበት አካባቢ በመሆን ደጋግመው ይሞክሩ " ብለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የተፈታኞች የመፈተኛ 'User Name' እና 'Password' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ መሆኑን እና የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም እንደሚጠበቅባቸው ማስታወቁ ይታወሳል።
ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቀጣይ እንደሚገልጽ አሳውቋል፡፡
መመዝገቢያ ፦ https://ngat.ethernet.edu.et/registration
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#Update #MoE " እስከምሽት ድረስ እየሞከሩ መቆየት ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የ2017 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የአመልካቾች ምዝገባ ከ የካቲት 27/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ እንደሚከናወን የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ዛሬ በሚያበቃው የአመልካቾች የምዝገባ ሂደት ለመመዝገብ…
#Update #NGAT
የብሄራዊ ድህረ-ምረቃ (NGAT) መግቢያ ፈተና መጋቢት 5 እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ዙር የNGAT አመልካቾች ምዘገባ መጠናቀቁን ገልጿን።
ፈተናው የሚሰጠው ዓርብ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ መሆኑንም አሳውቋል።
ተፈታኞች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በሚመደቡበት የፈተና ማዕከላት እንዲገኙ ብሏል።
➡️ ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከል በሚሄዱበት ወቅት ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።
➡️ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከመጀመሩ 3 ደቂቃ በፊት በፈተና ማዕከል መገኘት ይጠበቅበታል፡፡
➡️ የሞባይል ስልክ ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
➡️ የፈተና ማዕከላት ምደባ በምዝገባ ፕላትፎርም የሚገለጽ ይሆናል፡፡

#Update #NGAT የብሄራዊ ድህረ-ምረቃ (NGAT) መግቢያ ፈተና መጋቢት 5 እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ዙር የNGAT አመልካቾች ምዘገባ መጠናቀቁን ገልጿን። ፈተናው የሚሰጠው ዓርብ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ መሆኑንም አሳውቋል። ተፈታኞች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በሚመደቡበት የፈተና ማዕከላት እንዲገኙ ብሏል።…
የNGAT ፈተናና ምዝገባ ቀን ተራዘመ።
የብሄራዊ ድህረ-ምረቃ (NGAT) መግቢያ ፈተና እና ምዝገባ ቀናት ተራዘመ።
ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ዙር የNGAT አመልካቾች ምዘገባ መጋቢት 01/2017 መጠናቀቁ እና ፈተናው መጋቢት 05/2017 ከ3፡00 ጀምሮ እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ በአንዳንድ ተፈታኞች ጥያቄ መሰረት ምዝገባው እስከ መጋቢት 04/2017 ዓ.ም እስከ ምሽቱ 12:00 የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል።
ፈተናው ደግሞ መጋቢት 12/2017 ከ3:00 ጀምሮ እንደሚሰጥ ገልጿል።
በተለያየ ምክንያት ምዝገባ ያመለጣቸው አመልካቾች ምዝገባቸውን ወደ https://ngat.ethernet.edu.et/registration በመግባት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

#ExitExam የመውጫ ፈተና ወስደው ለወደቁ ተማሪዎች Special Diploma ሊሰጥ ነው። የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተከታታይ ውይይት ሲያደርግ መቆየቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ይህን ተከታታይ ውይይት ተከትሎ የመውጫ ፈተና መሰጠት ከተጀመረበት ሐምሌ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናውን ወስደው ለወደቁ ዕጩ ተመራቂዎች ልዩ ዲፕሎማ…
#MoE
ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ሊከናወን ነው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፉት ሰርኩላር " በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ዲግሪዎች ህትመት ወጥ በሆነ መልኩ ደህንነታቸው ተጠበቆ የዲግሪ ማስረጃ / ሰርተፍኬት ህትመት በማዕከል ለማሳተም መታሰቡን " ገልፀዋል።
በመሆኑም ተቋማቱ በዲግሪ የምስክር ወረቀቱ ላይ ሊካተትላቸው የሚፈልጉትን ሎጎ እና ሌሎች መካተት አለበት የሚሉትን እንዲያካትቱ እንዲሁም በየተቋማቱ በዚህ ዓመት የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉና ለምርቃት የተዘጋጁ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር እንዲልኩ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
የህትመት ሥራው በ2017 ዓ.ም ከሚመረቁ ተማሪዎች ጀምሮ የሚፈፀም መሆኑንም ገልፀዋል።

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ታስቧል።
ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።
ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ ጥናት አቅርበዋል።
ውይይትም ሲደረግ ነበር።
በዚህም ወቅት በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።
ላለፉት ዓመታት (እሳቸው በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ) ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።
ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
'' የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ '' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ " በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።
ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።
ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።
በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።
ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ " የመምህራን ባንክ " ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።
ባንኩ " በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን " ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

#MoE የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ታስቧል። ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ። ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም…
#MoE
" ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)
በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ሳይገቡ በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ጠቁመዋል።
ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፤ " በሚቀጥለው ዓመት ላይደርስልን ይችላል ግን ህጋዊ ስርዓቱን በሙሉ ጨርሰን በ2019 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች ከ2019 ጀምሮ 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይድረጋል " ብለዋል።
" ከዚህ በፊት የነበረ ነው አዲስ አይደለም በጃንሆይ ጊዜ (በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ማለታቸው ነው) የነበረ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሁለት ጥቅም አለው ብለን ነው ይሄን የምናደርገው አንደኛ ልጆቹ ዝም ብሎ የቀለም ትምህርት ብቻ ተምረው ሳይሆን ተግባራዊ የሆነ ትምህርትም ለአንድ ዓመት ሄደው የሚሰሩበት ከማህበረሰቡ ጋር የሚተዋወቁበት ነው። ሁለተኛ የአስተማሪዎች እጥረትም ስላለ ልጆችን ወደ አስተማሪነት ለአንድ አመት ቢሆንም ለማስገባት ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

በሰኔ 2017 የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና #ዳግም ለመፈተን እየተጠባበቁ ያሉ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ሚያዝያ 14 /2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
የመመዝገቢያ ቅፅ https://exam.ethernet.edu.et ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ገልጿል፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡
ፈተናውን ለመውሰድ የብሔራዊ (ፋይዳ) መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሲሆን ፤ የአገልግሎት ክፍያ (500 ብር) በቴሌብር በኩል ብቻ የሚፈፀም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ውጤት በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚመወሰድ ተገለፀ።
ይህ የተገለጸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ውጤት ከ25 በመቶ በታች የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል እርምጃ እንደሚወሰድ አመላክተዋል።
የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በብቃትና በችሎታ እንዲመደቡ እየተደረገ መሆኑን አንስተው " አሰራራቸውን ለማዘመንም የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ማሰልጠኛ ተቋም ለማቋቋሞ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

#MoE #AAU #ExitExam
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ሰኞ ይፋ ባደረገው የተሻሻለ የአካዳሚክ ካላንደር በሰኔ ወር ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የ2017 ዓ/ም ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ጠቁሟል።
ተማሪዎቹንም ሰኔ 21 እንደሚያስመርቅ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተቋሙ ስም ይፋ ተደርጎ የተሰራጨውን የአካዳሚክ ካላንደር ትክክለኝነት ከሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው አመራር ማረጋገጥ ችሏል። አንድ የተቋሙ አመራር " ከመጨረሻው ሐምሌ 2 ከሚለው ውጪ ሁሉም ትክክል ነው። የመጨረሻው ሐምሌ 8 ነው የሚሆነው " ብለዋል።
ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ይፋ ባደረገው ካላንደር የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ባለው ጊዜ እንደሚሰጥ ቢጠቁምም ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ስለ ፈተናው ቀን በይፋ ያሳወቀው ቀን የለም።
በሌላ በኩል የመውጫ ፈተና በድጋሜ የሚፈተኑ ተፈታኞች በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " አሁን ላይ የመወጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ተፈታኞችን የምዝገባ ሁኔታ እየገመገምን እንገኛለን " ሲል ገልጿል፡፡
በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚፈተኑት ጋር አብረው ፈተናውን እንደሚወስዱም አመልክቷል።
ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዳግም ተፈታኞች ምዝገባ ነገ ግንቦት 05 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡
እስካሁን ድረስ ምዝገባ ያልፈጸሙ ተማሪዎች የመመዝገቢያው አድራሻ / ሊንክ https://exam.ethernet.edu.et በአግባቡ እየሰራላቸው እንዳልሆነ በጠቆም የምዝገባ ጊዜው እንዲራዘም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት ጠይቀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ከምዝገባ ጋር በተያያዘ ገምግሞ ይፋ የሚያደርገው አዲስ ነገር ካለ የምንከታተለው ይሆናል።
ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ " በዲሲፕሊን ምክንያት የመውጫ ፈተና ውጤታቸው ተሰርዟል " የተባሉ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ማዕከል ድጋሚ ተፈታኞች ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ ምዝገባ ማድረግ አለባቸው።

#MoE #AAU #ExitExam አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ሰኞ ይፋ ባደረገው የተሻሻለ የአካዳሚክ ካላንደር በሰኔ ወር ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የ2017 ዓ/ም ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ጠቁሟል። ተማሪዎቹንም ሰኔ 21 እንደሚያስመርቅ ገልጿል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተቋሙ ስም ይፋ ተደርጎ የተሰራጨውን…
#ExitExam
" ፈተናው የሚሰጠው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን " - ትምህርት ሚኒስቴር
በ2017 ዓ.ም በሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ እስከ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ብቻ የተራዘመ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
እስከ አሁን ያልተመዘገቡ የድጋሚ ተፈታኞች (resitters) ከዚህ በፊት ለምዝገባ በተከፈተውና በተገለጸው መመዝገቢያ ፕላትፎረም https://exam.ethernet.edu.et በኩል ገብተው ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ ብሏል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውጫ ፈተና የሚቀመጡ ተፈታኞችም በተቋሞቻቸው በኩል መመዝገባቸውን እንዲያረጋግጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
ፈተናው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።
ለመውጫ ፈተናው የሚያመለክቱ አመልካቾች ለመመዝገብ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) ሊኖራቸው እንደሚገባና ፤ ከግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በኋላ ምዝገባ እንደማያስተናግድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።