TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኮሬ “ ባለፉት ዓመታት ከ300 በላይ ንጹሐን በታጣቂዎች ተገድለዋል ” - ኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን  “መንግስት ቸልተኛ ሆኗል የሚል ግምገማ አለን። ዛሬ ጠዋትም ሰው ተገድሏል” - የክልሉ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ  ንጹሐን ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች፣ ዞኑና የክልሉ ተወካዮች ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በዞኑ ጎርካ ወረዳ ዳኖና ኬረዳ…
#ኮሬ

🛑 “ አሁንም ግድያው እንደቀጠለ ነው። ዛሬም 3 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል” - ኮሬ ዞን

🔵 “ ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል” - በፌደራል ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኮሬ ህዝብ ተወካይ

ዛሬ (ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም) ሦስት ንጹሐን ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ከምዕራብ ጉጂ በተነሱ ታጣቂዎች መገዳላቸውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮሬ ዞን አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል።

“ ችግሩን ማስቆም የሚችል መንግሥት አካል አልተገኘም ” ያሉት አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ በዞኑ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ አካል፣ በሁለተኛው ዙር የመኸር ወቅት ብቻ 11 ሰዎች ሲገደሉ አራት ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

“ ጉዳቱ የደረሰባቸው ቀበሌዎች ዳኖ፣ ጎልቤ፣ ጋሙሌ፣ ኬረዳ፣ ሻሮ ናቸው። በአጠቃላይ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት በታጣቂዎች ተዘርፏል ” ነው ያሉት።

በአካባቢው ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ የሚፈጸመው ግድያ ለምን ይሆን መቋጫ ያጣው ? ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ጥያቄ ያቀረብንላቸው በፌደራል ተወካዮች ምክር ቤት የኮሬ የህዝብ ተወካይ አምዛዬ አወቀ (ዶ/ር) ምላሽ ተሰጥተዋል።
 
“ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ምንም መቋጫ አላገኘም። እኛም በተደጋጋሚ ለመንግስት አመልክተናል። ግን ምንም መፍትሄ የለም። በየቀኑ ግድያ እንሰማለን ” ብለዋል።

“ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እኛም ሁሉም በዬቦታው እየጮኸ ነው ግን መፍትሄ የለም። ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ነው ” ሲሉም አክለዋል።

የኮሬን ህዝብ የወከሉት በፌደራል ደረጃ እንደመሆንዎ ለመንግስት ቅርብ ነዎትና ጉዳዩን በግልጽ ለመንግስት አንስታችሁ ነበር? ከሆነስ የመንግስት ምላሽ ምንድን ነው? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ፦

“ በየጊዜው ነው የሚነሳው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ በተገኙበት ጊዜ ኦፊሻሊ ጥያቄ ሁሉ አንስቼ ነበር በ2016 ዓ/ም። ‘ሁኔታውን ለማርገብ የተወሰነ የመከላከያ ኃይል ይላካልና ሁኔታው ይረጋጋል’ ብለው ነበር።

ከዚያ በኋላ የተወሰነ ኃይል ሂዶ ነበር። እሱም አሁን በአገሪቱ ባለው ሁኔታ ይመስለኛል ተቀነሰ። ከዚያ በኋላ ግን ሁኔታው እየተባባሰ ነው የሄደው።

ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ህዝቡ በዬቀኑ ይዘረፋል። መንገድም የለም። የዲላ ህዝብ ጋር ነው የኮሬ ዞን የሚገናኘው ይሄ መንገድም ከተዘጋ ዘጠኝ ዓመት ሆኖታል።

ይሄን ሁሉ በማመልከታቸም አመልክተናል። ሽማግሌዎች ወጥተው ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት፣ ለሰላም ሚኒስቴር አመልክተዋል፤ ለክልሉ መንግስት በዬጊዜው የሚቀርብ ጉዳይ ነው። 

ነገር ግን ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል ”
ሲሉ መልሰዋል።

ስለዚህ የመፍትሄው ጉዳይ ምንም እየተሰራበት አይደለም ማለት ነው ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ ምላሻቸው፣ “ ምንም መፍትሄ የለም ” የሚል ነው።

“ አንዳንድ ጊዜ ‘እርቅ ተደርጓል’ ይባላል፤  አምና እርቅም ለማድረግ ተሰብስበው የነበሩት የብልጽና ፓርቲ ኃላፊም ጭምር የተገደሉበት ሁኔታ አለ። መንግስት የራሱ ፓርቲ አባል ሲገደል እንኳ ገዳዮች እነማን ናቸው ብሎ ተከታትሎ ሊያቀርብ አልቻለም ” ሲሉም ተናግረዋል።

በመሆኑም መንግስት፣ ሚዲያዎችም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ህዝቡን እንዲታደጉ በህዝቡ ስም ጥሪ አስተላልፈዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኮሬ 🛑 “ አሁንም ግድያው እንደቀጠለ ነው። ዛሬም 3 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል” - ኮሬ ዞን 🔵 “ ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል” - በፌደራል ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኮሬ ህዝብ ተወካይ ዛሬ (ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም) ሦስት ንጹሐን ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ከምዕራብ ጉጂ በተነሱ ታጣቂዎች መገዳላቸውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮሬ ዞን አስተዳደር ለቲክቫህ…
#ኮሬ

🛑 " ከትላንትና በስቲያም ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች ቆስለዋል። የአርሶ አደሩ ስጋት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው " - ኮሬ ዞን

🔵 " እዛ አካባቢ ያለውን ህዝብ በማጽዳት መሬቱን መውሰድ ነው የተፈለገው " - የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ዳኖ ቀበሌ ከትላንት በስቲያ ሁለት አርሶ አደሮች በታጣቂዎች ጥቃት እንደቆሰሉ ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ተወካይ አቶ አማረ አክሊሉ፣ ጉዳዩ በመንግስት ልዩ ትኩረት ስላልሰጠው አርሶ አደሮች በከፍተኛ ስጋት ላይ በመሆናቸው የፌዴራሉ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ጥቃቱን እንዲያስቆም ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ አማረ በዝርዝር ምን አሉ ?

" በጎርካ ወረዳ ዳኖ ቀበሌ ትላንትም ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች ቆስለዋል። የአርሶ አደሩ ስጋት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው። አገዳደላቸው ራሱ ዘግናኝ ነው። 

አንድ ሰው ላይ እስከ 30 ጥይት ነው የሚያርከፈክፉት አጥንቱ እስኪታይ።

አሁን የመኸር እርሻ ወቅት በመሆኑ የአረም ሥራ ላይ ባሉ አርሶ አደሮች ነው ጥቃት እየደረሰ ያለው።

በአብዛኛው ጥቃቱ የሚሰነዘረው ጋላና ወረዳ ነው። ጥቃቱን የሚያደርሱት እዛው አካባቢ የመሸጉ ታጣቂዎች ናቸው።

ከምዕራብ ጉጂ ተነስተው ነው ጥቃት የሚፈጽሙት። በአካባቢው ላይ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱ ናቸው።

በዋነናነት ‘ወደ 18 ቀበሌዎችን አፈናቅለን ቦታ ካልወሰድን’ የሚሉ አካላት ናቸው። በዚሁ ምክንያት ነው በአርሶ አደሮች ግድያና ድብደባ፣ በንብረት ላይ ዘረፋ እየተፈጸመ ያለው።

የፌደራል መንግስት ካልገባ የአካባቢው ችግር እየተወሳሰበ ነው። ጣልቃ ገብቶ ነጻ ካላወጣ በስተቀር ግድያው ከ6 ዓመታት በላይ አስቆጥሮም አልቆመም። የሸኔ ታጣቂ አለ፤ ጉጂ ላይ የተወሸቀ ሌላ ታጣቂም አለ
" ነው ያሉት። 

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮሬ ህዝብ ተወካይ ሀምዛዬ አወቀ (ዶ/ር) በበኩላቸው ለቲክቫህ ሰጡት ቃል፣ " መንግስት ባለበት አገር ነው ህዝቡ ጥቃት የሚደርስበት። ጥቃት የሚደርስበትም ከኦሮሚያ ክልል ነው " ብለዋል።

" በቁጥሩ ትንሽ ስለሆነ ይሄ ህዝብ ብቻውን መጋፈጥ አይችልም። መንግስት መከታ ካልሆነው በስተቀር የህልውና አደጋ ውስጥ ነው። መንግስት ተገቢውን እርምጃ እየወሰደ አይደለም "  ሲሉ ለቲክቫህ ተናግረዋል።

ለችግሩ መፈጠር መሠረታዊ መንስዔው፤ ታጣቂዎች በግልጽ ከዛ ህዝብ የሚፈልጉት ጉዳይ ምንድን ነው ? ስንል ላቀረብለንላቸው ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

" የችግሩ መሠረታዊ ነገር እውነት እንነጋገር ከተባለ የግዛት መስፋፋት ፍላጎት መኖር ነው። ምንም ሌላ ምክንያት የለውም። ‘ሸኔ’ ምናምን እየተባለ ሰበብ እየተደረገ ይቀርባል እንጂ።

እዛ አካባቢ ያለውን ህዝብ በማጽዳት መሬቱን መውሰድ ነው የተፈለገው። በተለይ ከሁለት ቀበሌዎች ላይ ህዝቡ ከዚያ እንዲፈናቀል፤ እንዲጠፋ ተደርጓል።

ከዚያ በኋላ ግን እንደ አቡካዶ፣ ሙዝ የመሳሰሉ ቋሚ ተክሎች ሁሉ ተነቅለው እንዲጠፉ፣ አካባቢው ወደ ባድማነት እንዲቀየር፣ ባዶ መሬት ነው ተብሎ እንዲሰጥ የተደረገበት ሁኔታ አለ። 

በ20ውም ቀበሌያት ወረራ ሲደረግ ቋሚ ተክሎች ሁሉ ነው የሚነቀሉት። ይሄ የሚደረገው ለምንድን ነው? በሚል ብዙ ጊዜ እንጠይቃለን፤ የደረስንበትም ህዝቡን በማጥፋት መሬት ለመውረስ መሆኑን ነው
" ሲሉ አስረድተዋል።

ችግሩን ለምን ማስቆም እንዳልተቻለ ማብራሪያ እዲሰጡ በፅሑፍ መልዕክት ጭምር የጠየቅናቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ፣ " የአመራር ስልጠና ላይ ነኝ " በማለት ዝርዝር ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል ።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia