TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የኢሬቻ ' ሆራ ፊንፊኔ ' በዓል አከባበር በአዲስ አበባ #Irreechaa2017

Photo Credit - Vist Oromia & Social Media

#AyyaanaGaari ! #HappyIrreechaa !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " የህወሓትን ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል ሲል " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ገለጸ። በህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የሚመራው ህወሓት ከመስከረም 20 አስከ 22 /2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ያካሄደውን የማእከላዊ ኮሚቴ እና የከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባ ማጠቃለሉ በማስመልከት የአቋም መግለጫ አውጥቷል። …
#TPLF

" ህዝብ በማደናገር ላይ ይገኛሉ " - በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማዕከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን

በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ክፍፍል ተቀራርቦ ከመፈታት ይልቅ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየተካረረ መጥቷል።

" ከህወሓት አባልነት የተባረሩ በማንኛውም ቦታና ጊዜ በህወሓት ስም ፓለቲካዊ ስራና እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም " ሲል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን አሳውቋል።

የቁጥጥር ኮሚሽኑ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፥ ጉባኤ ያካሄደው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት " ህጋዊ ነው " ብሏል።

" የህወሓት መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 8 ቁጥር 4 በውሳኔ አሰጣጥ ላይ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው በብዙሃን ተገዢ መሆን እንዳለባቸው ያስቀምጣል " ያለው መግለጫው " በዚሁ መሰረት በ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ከጠቅላላ ተሳታፊ 83 በመቶ ጉባኤተኛ የተገኘበት " ህጋዊ ነው !! " ብሎታል።   

ስለሆነም " ህጋዊ አለመሆኑን እያወቀ ህጋዊ መስሎ ማደናገር አግባብነት እና ተቀባይነት ያለው አይደለም " ሲል በምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት ከሷል።

" ከጉባኤ ራሳችን አግልለናል ወይም ወደ ጉባኤ አንገባም ያሉት በድርጅቱ መተዳደሪያ ህገ ደንብ መሰረት ከድርጅት አባልነታቸው እንደተባረሩ እውነት ነው ፤ በተግባር ግን የህወሓት ስም ፣ አርማ ፣ ሎጎ እና የድርጅቱ ሃላፊነት በመጠቀም ህዝብ በማድናገር ላይ ተጠምደዋል " ብሏል የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን መግለጫ።  

" ከጉባኤ በመሸሽ ሁሉም አይነት ክህደት በድርጅቱ ላይ ፈፅመህ ስታበቃ እኔ ህወሓትን ነኝ የሚል የከሰረ የማደናገር  ፓለቲካ ማራመድ ህጋዊ ፣ ፓለቲካዊ ፣ ሞራላዊ እና ታሪካዊ ተጠያቂነት የሚያስከትል ሆኖ አግኝተነዋል " ሲል አክሏል።

" የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ከድርጅቱ የተባረሩት አካላት #ከያዙት_ፓለቲካዊ_ስልጣን_እንዲነሱ ፤ በህወሓት ስም የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ የማድረግ ሃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን " ብሏል።

ቁጥጥር ኮሚሽኑ ፥ " ህዝብ በማድናገር ላይ ይገኛሉ " ሲል ክስ ያቀረበባቸው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን የህወሓት ቡድን " ህዝብ እንዲታገላቸው " ሲል ጥሪ አስተላልፏል። 

" ህወሓት ለ2 እንደተከፈለ ተደርጎ የሚቀርበው ተረክ ከህወሓት አልፎ ህዝብ ስለሚጎዳ በፍጥነት መታረም አለበት " ብሏል።

በምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት  መስከረም 23 /2017 ዓ.ም ባወጣው  መግለጫ  " የህወሓት ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል " ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ የተከበረው የ2017 ዓ/ም የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፥ " በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብና አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች እንዲሁም የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች የታደሙበት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል " ሲል ገልጿል፡፡

ለበዓሉ በሰለም መጠናቀቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ ፦
- ለአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች፣
- ለበዓሉ ታዳሚዎች፣
- ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣
- ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎች
- ለሰላም ሠራዊት ወጣቶች
- ስምሪት ተሰጥቷቸው ኃላፊነታቸውን በትጋት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት አካላት ምስጋና አቅርቧል።

ነገ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ የሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል ይከበራል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

መንገዶች ተከፍተዋል።

ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ተከፍተዋል።

@tikvahethiopia
" ለአንድ ዓመት ሞከርኩት "

ዛሬ በይፋዊ የፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የX ገጽ ላይ የወጣው ፅሁፍ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

ፅሁፉ " እነ ጥላሁን ገሠሠ : ቴዲ አፍሮ : አሊ ቢራ : ማህሙድ አህመድ ... ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው " ይላል።

ቀጥል አድርጎ ፥ " ' የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው : መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው ' ማህሙድ ' ዝምታ ነው መልሴ' ን ሲያዜም " ሲል ይገልጻል።

መጨረሻ ላይ " ለአንድ ዓመት ሞከርኩት " የሚል ያልተቋጨ ፅሁፍ ታክሎበታል።

ፕሬዜዳንቷ ገጽ ላይ ፅሁፉ ስለምን ጉዳይ እንደሆነ በግልጽ የተብራራ ነገር አልሰፈረም።

በተረጋገጠው አካውንታቸው የወጣውን ፅሁፍ ግን በርካቶች እየተቀባበሉት ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
ኮሚሽነር ግርማይ ማንጁስ !

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና ህይወታቸው እስካላፈበት ጊዜ ድረስ የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ኮሚሽነር ግርማይ ባደረባቸዉ ህመም ምክንያት ህክምናቸውን ሲከታተሉ በቢቆዩም በተወለዱ በ60 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል።

ከነሐሴ 01 ቀን 1994 ዓ/ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ከዋና መምሪያ እስከ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ኃላፊነት ሠርተዋል።

እስከ ህልፈታቸው ጊዜ ድረስም የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ህዝባቸውን ሲያገለግሉ ነበር።

ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) የ3 ሴት ልጆች አባት ነበሩ።

ዛሬ አስክሬናቸው በልዩ ወታደራዊ አጀብ እና ሃይማኖታዊ ስነርዓት ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ተሸኝቷል።

የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ነገ እሁድ ከጠዋቱ  3፡00 ሰዓት በመቐለ ጽርሃ አርያም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

#FederalPolice #Tigray #CommissionerGirmayKebede

@tikvahethiopia