TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara

" በአማራ ክልል ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ አራዝመዋል። ትምህርት ከፓለቲካ ነጻ መሆን አለበት " - የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት

በአማራ ክልል በ " ፋኖ " ታጣቂዎችና በመንግስት መካከል ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረው የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ ጊዜ ማራዘማቸው ይህም ደግሞ በተማሪዎች ላይ ጭንቀት መደቀኑ ተሰምቷል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የተማሪዎቻቸውን የቅበላ ጊዜ ማራዘማቸውን እንደተረዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ነው።

የህብረቱ ፕሬዚዳንት ሓየሎም ስዩም፣ " አራት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ አራዝመዋል " ብሎ ተማሪዎች በጭንቀት ውስጥ በመሆናቸው ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትከረት እንዲሰጡ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

በጸጥታው ችግር የተማሪዎቻቸውን የቅበላ ጊዜ ያራዘሙት፣ " ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ ፣ ደብረ ታቦር እና ኢንጅባራ ዩኒቨርሲቲዎች " መሆናቸውንም  ተናግሯል።

" ወሎና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች አሁን መንገድ ስለተከፈተ ይቀበላሉ " ያለው የህብረቱ ፕሬዚዳንት ደባርቅ ዩኒቨርቲንም ቅበላውን ሳያራዝም እንዳልቀረ፣ " ሀፋ፣ ሀፋ " የሆነ ሀሳብ ላይ እንደሆነ አስረድቷ።

ህብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " ትምህርት ከፓለቲካ ነጻ መሆን አለበት " ሲል አሳስቧል።

በአንጻሩ ወልዲያ እና ወሎ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ተቀብለው እያስተማሩ መሆኑ ሲነገር ተስተውሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የተማሪዎቹን ቅበላ አራዝሟል ወይስ አላራዘመም ? ተማሪዎቹን ተቀብሎ እያስተማረ ነው ወይስ አልተጀመረም ? ሲል ወልዲያ ዩኒቨርሲቲን ጠይቋል።

ዩኒቨርሲቲው በምላሹ፣ " አላራዘመም። ተማሪዎቹ እስኪገቡ ድረስ እንጠብቃለን። የመንገድ መዘጋጋቱ ስለሚታወቅ እንደ ሀገር በይፋ ባናራዝምም የቻሉ እየገቡ ነው ያልቻሉ ይገባሉ በፈለጉት ሰዓት " ብሏል።

" በውስጥ ኮሚዩኒኬት ስላደረግን ከተማሪው ከተለያዩ ቅርብ ቦታ (ለምሳሌ ደሴ) እየመጡ  ስላሉ አላራዘምንም " ሲልም አክሏል።

ትምህርት ተጀምሯል ? ስንል ላቀረበነው ጥያቄ " ትምህርት አልተጀመረም " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንለት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ፣ " ተማሪዎችን ተቀብለን እያስተማርን ነው። የኛ ተማሪዎች ገብተዋል። ሲኔር ተማሪዎች በሙሉ ግቢ ነው ያሉት " ብሏል።

" የአዲስ ገቢዎችን በተመለከተ ግን ትምህርት ሚኒስቴር አልመደበም ገና። እንደመደበ እንጠራለን። እኛ ምንም የምናራዝምበት ምክንያት የለም " ነው ያለው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዎቹን ቅበላ ያራዘሙ ዩኒቨርሲቲዎችን በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉት ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር)፣ ' ዩኒቨርሲቲዎቹ የራሳቸው ስኬጁል አለ። እኛም የሰጠነው ስኬጁል አለ። ዩኒቨርሲቲዎቹ ይጠየቁ " ከማለት ውጪ ማብራሪያ ለመስጠት ተቆጥቧል።

#TikvahEthioiaFamilyAA

@tikvahethiopia