TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ እና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ አንቀበልም ፥ መንግስት ለዚህ መሰል እንቅስቃሴ ህጋዊ የሆነ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ አስጠንቅቋል። ከሰሞኑን ካቢኔው ስብሰባ አድርጎ ነበር። ይህን ተከትሎ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። በዚህም የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ እና ስለ ህወሓት…
#Tigray

" እኔ ድርድር ያስፈልጋል በሰላም ይፈታ ስል ፤ እሱ ግን ' ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ? ' ነበር ያለው " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)

ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድና የቆየ ቂም ለመወጣት በሚል ከሰሱ።

በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባሳለፍነው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት መቐለን ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ህዝባዊ የተባሉ ስብሰባዎች አካሂዷል።

በእነዚህ መድረኮች የፖርቲው አመራሮች ክፍፍል በስፋት ተነስቷል።

ህወሓትን ለማጥፋት፣ ስልጣን ለመጠቅለል የሚንቀሳቀሱ ተብለው የተገለፁ አመራሮች በስም እየተጠቀሱ ወቀሳ ሲሰነዘርባቸው ተሰምቷል።

ቅዳሜ በመቐለ በተካሄደና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮንን (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የፖርቲው አመራሮች እና የተመረጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የታደሙበት መድረክ ነበር።

በዚሁ መድረክ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን፥ ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድ፣ የቆየ ቂም በመወጣት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በማንሳት እንዲሁም ከዚህ በፊት በይፋ ያልተሰሙ መረጃዎች በመግለፅ ሲተቹ ተደምጠዋል።

በንግግራቸው እርሳቸው የሚመሩትን ህወሓት ሰላም የማይፈልግ አድርጎ የማቅረብ የተሳሳተ ፍረጃ ከትግራይ ባለስልጣናት በኩል እየቀረበበት መሆኑ ገልጸው " ይህ ውሸት ነው " በማለት አጣጥለዋል።

ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ " ለምሳሌ በደቡባዊ ዞን በተደረገ መድረክ ጀነራል ጻድቃን እኛ ሰላም እንፈልጋለን፣ እነሱ የሚሹት ጦርነት ነው ሲል ሰምታችሁታል። በጦርነቱ ወቅት ደሴ ተሻግረን ሰሜን ሸዋ ስንጠጋ፥ ድርድር ያስፈልጋል ወይ ሲባል እኔ አዎን ያስፈልጋል ነው ያልኩት። በሰላም ሊፈታ ስለሚገባው። እሱ ግን ከማን ጋር ነው የምንደራደረው፣ ውጊያው አልቋል ሲል የነበረ ነው። አሁን ግን እኔ ሰላም ነኝ እነሱ ጦርነት ናቸው የሚፈልጉ ማለት ጀመረ " ብለዋል። #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የመስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡

እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉ፡፡


እርስዎም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
[Telegram] [Facebook]
                              
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ    
    የስኬትዎ አጋር!

https://t.iss.one/LionBankSC
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ አመት ልዪ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ፣ ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማህበራዊ ገጾት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮችን እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡
- Tag ሲያደርጉን ለ Facebook @ TecnoEt ፣ ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia እና ለ TikTok @ TecnoEt ን  ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።)
- በተጨማሪም #TecnoEt2017 ን keyword መጠቀም እንዳይረሱ)
" ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ ከሁለት ዓመት በላይ የተስፋ እንጀራ ብቻ ሆኖብናል " - አቶ አባይነህ ጉጆ

የአካል ጉዳተኞችን ዘርፈ ብዙ የሆኑ ችግሮች ይፈታል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል የተባለው " ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ " በታቀደለት ወቅት አለመውጣቱ አካል ጉዳተኞችን ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበር ፌደሬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ  ምን አሉ?

“የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ሲነሳ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ ሆኖም ብዙ ችግሮቻችንን ሊቀርፍልን ይችላል ብለን እየጠበቅን ያለነው ጠቃላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ ይወጣል ብሎ መንግስት ተስፋ ሰጥቶናል።

በተስፋ ብቻ አላበቃም ሕጉ ድራፍት ተደርጎ የጋራ ምክክር ሕጉ ላይ አካል ጉዳተኞችም ተሳትፎ ከተረጋገጠበት በኋላ ለፍትህ ሚኒስቴር ሂዶ ነበር።

ፍትህ ሚኒስቴር አንዳንድ በእኛ በኩልም ተቀባይነት የሌላቸውን ኮመንቶች በመስጠት ወደኋላ መልሶታል። ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው ሕጉን በባለቤትነት የሚያረቀው።

ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ ከሁለት ዓመት በላይ የተስፋ እንጀራ ብቻ ሆኖብናል፡፡

እሱ ሕግ ቢወጣ የተሻለ ነገር ሊያመጣ ይችላል።

ሕጉ ቢወጣ እውነት ለመናገር በርካታ ችግሮቻችንን ይቀርፋል ብለን እናምናለን"
ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-09-24

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Telegram

" አዲሱ ደንብ መተግበሪያውን ለወንጀል የሚጠቀሙት ሰዎችን ቅስም የሚሰብር ይሆናል " - ዱሮቭ

ቴሌግራም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የደንበኞቹን መረጃዎች ለሕግ አካላት አሳልፎ ሊሰጥ ነው።

በዚህም የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ፦
➡️ ስልክ ቁጥሮች፣
➡️ የኢንተርኔት አድራሻ
➡️ ሌሎችንም መረጃዎች በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት በመሳሰሉ የሕግ ተርጓሚዎች በሚፈለግበት ጊዜ ሊሰጥ እንደሚችል ቴሌግራም አሳውቋል።

የቴሌግራም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፔቨል ዱሮቭ ይህ አዲስ ደንብ እንደሆነው አመልክተዋል።

ይህ አዲስ ደንብ " መተግበሪያውን ለወንጀል የሚጠቀሙት ሰዎችን ቅስም የሚሰብር ይሆናል " ብለዋል።

" 99.999% የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ከወንጀል ጋር የሚያያይዛቸው አንዳችም ነገር የለም። 0.001% የሚሆኑት ግን ለድብቅ ወንጀል እየተጠቀሙበት የቴሌግራምን ዝና እና ክብርን እያጎደፉት ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ቢሊዮን የሚጠጉ ጨዋ ተጠቃሚዎቻችን የሚጎዳ ነው " ብለዋል።

ዱሮቭ ባለፈው ወር በፈረንሳይ ፣ ፓሪስ ኤርፖርት በቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበር አይዘነጋም።

በፖሊስ ከተያዙ በኋላ የቀረበባቸው ክስ " መተግበሪያው ለወንጀለኞች መፈንጫ እንዲሆን ፈቅደዋል " የሚል ነበር።

" ሕገ ወጥ የሕጻናት ምስሎች ዝውውርና የአደገኛ እጽ አዘዋዋሪዎችን በሚያበረታታ መልኩ መተግበሪያው ለወንጀል ተግባር እንዲውል ፈቅደዋል " በሚል የተከሰሱት ዱሮቭ ከሕግ አካላት ጋር ባለመተባበርም ተወንጅለው ነበር።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በበኩላቸው ሌሎች ለፈጸሙት ወንጀል እሳቸው ተከሳሽ መሆናቸው " አስደናቂ እና ግራ የሚያጋባ " ነገር ነው ሲሉ የፈረንሳይ ባለሥልጣናትን ወርፈው ነበር።

በኃላ ፍ/ቤት ዱሮቭ በዋስ ወጥተው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ማዘዙ ይታወሳል።

#Telegram #BBC

@tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም !

እነሆ የመጀመሪያው የ130 ዓመታት ክብረ በዓል ገጸ-በረከት !

ኢትዮ 130 ፕሮሞ

በቴሌብር ወይም በአየር ሰዓት ጥቅል ሲገዙ በሚሰበስቧቸው ጎልድ እና ዲጂታል መጫወቻ ሳንቲሞች በመጠቀም በዕድል ጨዋታ ወይም የጠቅላላ ዕውቀት ጥያቄዎችን በመመለስ ሽልማቶችን ያግኙ!

🚘 3 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች
🛺 6 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች
💰 በየቀኑ የ20 ሺህ እና በየሳምንቱ የ100 ሺህ ኢ-የገንዘብ ሽልማቶች በቴሌብር
📱 91 ዘመናዊ ስማርት ስልኮች
🎁 130 ሺህ የሞባይል ጥቅሎች

💁‍♂️ ከእርስዎ የሚጠበቀው አገልግሎቶቻችን እየተጠቀሙ በ130 ጨዋታዎች እየተዝናኑ ዕድልዎን መሞከር ብቻ ነው!
በቴሌብር ሱፐርአፕ በ130 ፕሮሞ መተግበሪያ ወይም *130# በመደወል በሚላክልዎት ድረ-ገጽ ወደ ጨዋታው ይግቡ።

ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት አላቸው

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/4e9O7Sb

በሌላ ፌሽታ የ130 ላኪ ስሎት ጨዋታም እናበስራችኋለን፤ ይጠብቁን!

#130_ዓመታትን_በጽናት_ታላቅ_አገርና_ሕዝብ_በማገልገል_ላይ

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#MesiratEthiopia

አስፈላጊ መረጃ! የሐዋሳ ኢንፎ ሴሽን የቦታ ለውጥ
📍 አዲሱ አድራሻ፦ ሳውዝ ስታር ሆቴል (South Star Hotel)፣ ሐዋሳ
🗓 መስከረም 20, 2017 ዓ.ም
🕒 ከጠዋቱ 3:30 እስከ 6:30 ሰዓት

የመስራት ፕሮግራም ንግድዎን እንዴት ማጎልበት እንደሚችል፣ ስለ ሥራ ፈጠራ ፕሮግራማችን ቁልፍ ግንዛቤዎች እና ስለ ቴሌግራም ቦት ስልጠና ጥቅሞች ምንመለከትበት ዝግጅት ነው።

ከታች ባለው ሊንክ ተመዝገቡ!
https://forms.gle/RFt2RTUhznLSi7np9

#Mesirat #Entrepreneurship #Hawassa #BusinessGrowth
“ 21 ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል፡፡ አያገለግሉም፤ መልሶም ለማልማትም በጣም አስቸጋሪ ነው ” - የደሴ ከተማ አስተዳደር

በአማራ ክልሏ ደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ/ም ሌሊት ባተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰዎች ሕይወት ላይ ጉዳት ባይደርሰም በመኖሪያ ቤቶች ላይ ውድመት እንደደረሰ ከተማ አስተዳደሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

የከተማዋ የኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ነስረዲን ኃይሌ “ ቄራ የሚባል አካባቢ ነው የመሬት መንሸራተቱ የተከሰተው ” ብለዋል፡፡

“ መንሸራተቱ ተፈጥሯዊ በሆነ ምክንያት ከክረምቱ ክብደት ጋር ተያይዞ የተከሰተ ነው፡፡ እስካሁን 21 አባወራዎች (በቤተሰብ አባላት ደረጃ 116 ግለሰቦች) ከቦታቸውና ከንብረታቸው ላይ ተፈናቅለው ወደ ካምፕና ዘመድ ቤት ተጠግተዋል ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ 21 ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል (እስከ ትላንትና ምሽት ድረስ ዳሜጅ ሆነዋል)፡፡ ኦረዲ አያገለግሉም፡፡ መልሶም ለማልማትም በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በሰዎች ሕይወት ግን ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ” ነው ያሉት፡፡

ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት አደጋ ተከስቶ ያውቃል እዚሁ አካባቢ ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ፣ “ እንደከተማ ሦስተኛ ቦታ ላይ ነው ይሄ የመሬት መንሸራተት የተከሰተው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የአሁኑ የመንሸራተት አደጋ እንደቀጠለ ነው ወይስ ቆሟል ? ምንስ እየተሰራ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ፣ “ ችግሩ በመሠረቱ ጨምሯል አሁን፡፡ እዛ አካባቢ ላይ ያሉ ነዋሪዎችን የማንሳት ሥራም የከተማ አስተተዳደሩ ሰርቷል ” ብለዋል።

“ ትላንት ከተከሰተ በኋላ ዛሬ አዳር ላይ ሊከሰት ይችላል ብለን በሰጋንባቸው ቦታዎች ሙሉ ለሙሉ ግለሰቦችን አንስተን በቅርብ ዘመድ ያላቸው ወደ ዘመድ ቤት እንዲሄዱ፤ ካልሆነ ደግሞ ከተማ አስተዳደሩ ካምፕ አዘጋጅቶ እዚያ ካምፕ ላይ እንዲያድሩና አሰፈላጊውን ጊዜያዊ ድጋፍ እያደረግን ነው ” ብለዋል፡፡

" የመሬት መንሸራተቱ የሚያሰጋቸውን
አካባቢዎች የግለሰቦችን ንብረት ጭምር የማሸሽ ሥራ ትላንት ተሰርቷል ” ሲሉ አክለዋል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-09-24-2

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቤንዚን ? በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል። ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል። በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው። በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።…
#ቤንዚን

° " ቤንዚን ማግኘት ፈተና ሆኖብልናል " - አሽከርካሪዎች

° " የቤንዚን አቅርቦት ችግር የለም " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን

አሁን ላይ በአዲስ አበባ ቤንዚን ማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነባቸው አሽከርካሪዎች እየገለጹ ናቸው።

የተለያዩ ማደያዎች ላይ " ቤንዚን የለም " የሚል የተለጠፈ ሲሆን ቤንዚን አለባቸው የሚባሉና የሚቀዳባቸው ማደያዎች ላይ እጅግ በጣም ረጅም ሰልፎች ነው ያሉት።

አሽከርካሪዎች ቤንዚን ለመቅዳት ሰዓታትን ለመሰለፍ እየተገደዱ ነው። በዚህም ቀናቸውን በሰልፍ እያሳለፉ በመሆኑ ስራቸው እየተበደለ ነው።

ምንም እንኳን ከሰሞኑን ችግሩ ብሶ ቢታይም ባለፉት ሣምንታት አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰልፎች ይታዩ ነበር።

ለመሆን ምንድነው የተፈጠረው ?

በዚህ ጉዳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን መ/ቤትን ማብራሪያ ጠይቋል።

የተፈጠረው ነገር ምንድን ነው ? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላቸው የባለስልጣኑ አንድ አካል በሰጡን አጭር ማብራሪያ፣ " የቤንዚን እጥረቱ የለም " ብለዋል፡፡

በከተማዋ ያለውን ችግር በተመለከተ ፤ " የእኛ ልጆች ኢስፔክሽን ሲወጡ ያዩት ነገር አሁን የቴሌ ብር አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ነው፡፡ ምክንያቱም በካሽ ግብይት መፈጸም አይቻልም ፤ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ስለሆነ አብዛኛው ሰው ያንን ሲስተም ሳይጠቀም ቆይቶ በካሽ ትራንሰፈር እያደረገ ነበር፡፡ በዚያ ምክንያት አንዱ ከማደያ ላይ ነዳጅ ቀድቶ ለመውጣት ረጅም ሰዓት ይወስዳል " ብለዋል፡፡

" እናም ረጃጅም ሰልፍ የሚፈጠረው በዛ ነው እንጅ በእጥረት አይደለም " ብለው ለተጨማሪ መረጃ ወደ ሌላ የሚመለከተውን የተቋሙ አካልን የመሩን ሲሆን ሌላኛው አካል ማብራሪያ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ቢሰጡም በቀጠሮ ሰዓት በተደጋጋሚ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

በሌላ በኩል ፥ ባለስልጣን መ/ቤቱ ለካፒታል ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፥ በአዲስ አበባ ከተማ በአማካይ እስከ 1.4 ሚሊየን ሊትር ቤንዚን እያቀረበ መሆኑን አመልክቷል።

" በአዲስ አበባ ከሰሞኑ በነዳጅ ማደያዎች ላይ የተስተዋለው ያልተለመደ ሰልፎች ባለፈው ሣምንት በነበሩት ሁለት ቀናት ከበዓላት ጋር በተያያዘ የአቅርቦት መቀነስ በመኖሩ ነዉ " ብሏል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ፥ " በከተማዋ በቀን በአማካይ እስከ 1.4 ሚሊየን ሊትር ቤንዚን የሚቀርብ ቢሆንም የማደያዎቹ አገልግሎት አሰጣጥ ዝግታ መኖሩ እና የቤኒዚን ምርት ላይ ከፍተኛ የጥቁር ገበያ ፍላጎት መኖር ሠልፎችን ምክኒያት በማድረግ የአቅርቦት ዕጥረት ያለ በማስመሰል አጋጣሚውን ለትይዩ ገበያዉ ለመጠቀም መሞከር ይታያል " ሲል አስረድቷል።

" ከነዳጅ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ያለው ሁኔታ በአፋጣኝ እንዲስተካከል የተደረገበት እርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል " ያለዉ መ/ቤቱ " በዚህም በመዲናዋ ከመደበኛ ኮታ ተጨማሪ ቤንዚን እንዲቀርብ ሆኗል " ሲል አስታዉቋል።

" የየቤኒዚን ተጠቃሚ አሽከርካሪዎች አቅርቦት በበቂ ሁኔታ መኖሩን ተረድተው በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ ማደያዎችን በመጠቀም መገልገል ይችላሉ " ሲል አሳስቧል።

#AddisAbaba #Benzine

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara “ የእኛ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶቻችን ደረጃ 2 ላይ ያሉ ናቸው፡፡ ደረጃቸው ዝቅተኛ ግን መማር ማስተማሩን ማስኬድ የሚችሉ እንደማለት ነው ” - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በአማራ ክልል በተለይ በጸጥታ ችግር ሳቢያ የግብዓት እጥረት ያለባቸው ትምህርት ቤቶች እንዳሉ፣ ይህም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ማነቆ እንደሆነባቸው ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገጸዋል፡፡ ለአብነትም እንደ…
#Amhara #Education

" ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ገብተው እንዲማሩ ሁሉም ይተባበር " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

ለ2017 ትምህርት ዘመን ምን ያህል ተማሪ ተመዘገበ ?

በአማራ ክልል ፣ ባለፈው ዓመት ት/ቤት መግባት ከነበረባቸው 6 ሚሊዮን ተማሪዎች መካከል ግማሽ ያክሉ በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት እንዳልተከታተሉ በወቅቱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመልክቷል።

በተለይም በጎጃም ቀጠና የሚገኙ አብዛኛዎቹ የ6ኛ፣ የ8ኛና የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና መውሰድ አልቻሉም።

እስካሁን በ2017 ወደ ትምህርት ቤት የመጡ ተማሪዎች በጣም ጥቂቶች ናቸው።

ችግሩ ሳይቃለል በዚህ ዓመት ቢሮው 7 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለማስተማር ቢያቅድም ከነሐሴ 20/2016 ዓ ም ጀምሮ ባደረገው ምዝገባ ግን እስካሁን የተመዘገቡት 2 ሚሊዮን አይሞሉም።

➡️ እድሜያቸው ከ4 እስከ 6 ዓመት የሆናቸውን 1 ሚሊዮን 760 ህፃናትን ለመመዝገብ ታቅዶ የተመዘገቡት 324 ሺህ ያክሉ ናቸው፡፡

➡️ ከ1ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል 4 ሚሊዮን 800 ሺህ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ቢባልም ባለፉት 20 ቀናት የተመዘገቡት ግን ከ1 ሚሊዮን 300 ሺህ አይበልጡም።

➡️ በሁለተኛ ደረጅ ትምህርት ቤት 1 ሚሊዮን 200 ሺህ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ የታቀደ ሲሆን ወደ ትምህርት ቤት የመጡት ግን 300 ሺህ ያክሉ ናቸው።

ተማሪዎች ለምን ወደ ትምህርት ቤት አልመጡም ?

ለአፈፃፀሙ ዝቅተኛ መሆን ፦
- በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ፣
- ተማሪዎች ዘግይቶ የመመዝገብ ልማድ፣
- ፖለቲካን ከትምህርት ጋር የማያያዝ ጉዳዮችና ሌሎች ምክንያቶች እንደሚጠቀሱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጠው ቃል አመልክቷል።

የክልሉ የትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፥ " ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ፦
° የሀገር ሽማግሌዎች፣
° የሐይማኖት አባቶች፣
° ተፅዕኖ ፈጣሪዎች
° መንግስትና ኃላፊው
° በጫካ ያሉ ወንድሞች ጭምር ሊተባበሩ ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ወላጆች በሰጡት ቃል የልጆች ወደ ትምህርት ቤት አለመሄድ እንዳሳሰባቸው እና ጉዳዩ ከባድ እንደሆነ ጠቁመዋል። በአንዳንድ የገጠሩ ክፍል " ትምህርት ቅንጦት እየሆነ ነው " ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

አማራ ክልል በብዙ ፈተና ውስጥ እያለፈ ያለ ክልል ቢሆንም በተለይ በብሔራዊ ፈተና በየዓመቱ እጅግ ምጡቅ ልጆች የሚወጡበትና ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብበት ነው። ለአብነት እንኳን ባለፈው ዓመት በብሔራዊ ፈተና ሁለተኛው የሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በዚሁ ክልል ነው።

#Amhara #Education

@tikvahethiopia
" የተፈጸመው ወንጀል ጭካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ወንጀል ነው " - ፖሊስ

በጫጉላ ምሽት ሚስቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የሃላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ሟች ሪባቴ ትባላለች።

ሟች እና ወንድሟ በግድያ ተጠርጣሪው ግለሰብ አማካኝነች ቁርዓን እንደሚቀሩ ከሟች እህት አመደልሃዲ አንደበት ለመስማት ተችሏል።

ተጠርጣሪው ሟችን ማግባት እንደሚፈልግና ለሟች ወንድም በጓደኛው አማካኝነት ሃሳቡን ይገልጽለታል።

የሟች ወንድም አብዱልሃዲም ሟች እህቱን " ተስማምተሻል ወይ ? " በሚል መጠየቁንና ከሀፍረት መግለጽ ብትፈራም እንደተስማማች በመረዳቱ ወደ ጋብቻ ቅድመ ሁኔታው ማለፋቸውን ይገልጻል።

ከዚያም ወደ ጥሎሽና ኒካህ ተኪዷል።

ኒካህ ከታሰረ በኃላ ከለሊቱ 10 ሰዓት ገደማ ስልክ ተደወለልኝ የሚለው ወንድሟ " ሪባቴ ታማለች ና " ተብሎ ተነገረኝ ሲል ሁኔታውን አስታውሷል።

ወደ ቤታቸው ሲሄድ ግን ቤቱ በፖሊስ ተከቦ ነበር።

ሌላኛው የሟች ወንድም በርገና  " አባቴ ኒካህ እሰር ብሎ ከወከለኝ ቀን ጀምሮ ያለው ነገር ብቻ ነው ማውቀው ከዚያም ወንድሜን ወከልኩት ኒካሀው ታሰረ አለኝ ከዛ ለሊት 10 ሰዓት ስልክ ተደወለልኝ ቦታው ስንደርስ ቤቱ በፖሊስ ተከቧል " ሲል ገልጿል።

" በጭራሽ ያልገመትነው ነገር ሆኖ አገኘን " የሚለው የሟች ወንድም " ፖሊሶች እኛ ወደ አስክሬኑ እንዳንጠጋ አድርገው አስክሬኑን ወደ ሆስፒታል ወስደው እሱን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስዱት " በማለት አስረድቷል።

" ለሟች እህታችን ተገቢው ፍትህ ተሰጥቶን ተጠርጣሪው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ እንፈልጋለን " ብሏል።

የሃላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ በበኩሉ ድርጊቱ ከተፈጸመበት ሰዓት አንስቶ ተጠርጣሪውን በህግ ጥላ ስር አውሎ 5 አባላት ያለው መርማሪ ቡድን በማዋቀር ምርመራ እያካሄደ መሆኑን አመልክቷል።

የተፈጸመው ወንጀል " ጭካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ወንጀል ነው " ሲል ገልጿል።

ፖሊስ የተጠርጣሪውን የእምነት ክህደት ቃል እንደተቀበለና በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርመራው አልቆ  ውሳኔ እንዲያገኝ እንደሚሰራ አመልክቷታ።

የሃላባ ህዝብ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና መረጃ በመስጠት ላደረገው ርብርብ ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሀሩን ሚዲያ ነው። #HarunMedia

@tikvahethiopia
#USA

ዶላንድ ትራምፕ በቅርብ በሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉና ፕሬዜዳንት ከሆኑ ፥ " በአስቸኳይ የስደተኞችን ወረራ አስቆማለሁ፣ ማንኛውም አይነት የህገወጥ ስደተኞችን በረራ እንዲቆም እንዲሁም በማንኛውም መንገድ ወደ አሜሪካ ምድር እንዳይገቡ አደርጋለሁ " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ በስልጣን ዘመናቸው በአሜሪካ ታሪክ ትልቅ የተባለ ዲፖርቴሽን (ከሀገር የማስወጣት) ስራ እንደሚሰሩ ከወዲሁ ተናግረዋል።

" ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ያሏቸው ዶክመንት አልባ ህገወጥ ስደተኞችን ነው።

በስድተኞች ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም ከዚህ ቀደምም የሚታወቀው ትራምፕ አሁን ስመጣ " አጠነክረዋለሁ " እያሉ ለደጋፊዎቻቸው ቃል በመግባት ላይ ናቸው።

" ከተሞቻችን አድንላችኋለሁ " እያሉ ያሉት ትራምፕ ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ህገወጥ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው ተብሏል።

ምናልባትም ተመርጠው ፕሬዜዳንት ከሆኑ በኃላ ይሄን ሁሉ የሰው ቁጥር እንዴት ከአሜሪካ ዲፖርት እንደሚያደርጉ ለጊዜው በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

#USA #deport

@tikvahethiopia