ኢትዮጵያ ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር ያለባት ሀገር ናት።
ካለው ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር አንጻር ያለው የስራ እድል አነስተኛ ነው። የስራ እድል ቢገኝ እንኳን የሚከፈለው ክፍያ ዝቅተኛ በሆኑ ህይወትን መቀየር እና ያሰቡትን ማሳካት ፈተና ነው።
በዚህ ምክንያት ብዙ ወጣቶች የተሻለ ኑሮና ገቢ ፍለጋ ከሀገር ለመውጣት ይፈልጋሉ።
ወጣቶቹ ያደጉ ሀገራት / በኢኮኖሚ የተሻሉ ሀገራት ሄደው ሰርተው ፣ ጥሩ ገቢ አግኝተው ለራሳቸው ተርፈው ፤ ዋጋ ለከፈለላቸውና ተቸግሮ ላሳደጋቸው ቤተሰባቸው እንዲሁም ለህብረተሰባቸው መድረስ እና ' አለሁላችሁ ' ማለት ይፈልጋሉ።
እድሜ ቆሞ አይጠብቅምና ፈጣሪ በሰጣቸው የወጣትነት ጊዜ ጉልበትና እውቀታቸውን ተጠቅመው ቢያንስ እነሱ ባይደላቸው ለልጆቻቸው የሚሆን ነገር ማስቀረት ትልቁ ምኞታቸው ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወጣቱ ዘንድ ከሀገር ወጥቶ ለመስራት የሚታየው ፍላጎት እጅግ በጣም መጨመሩን በተለያየ መንገድ ለመገንዘብ ችሏል።
በተለይ ወደ ካናዳ፣ ጣልያን፣ አሜሪካ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሳዑዲ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ሮማኒያ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ... ሌሎችም የውጭ ሀገራት በትምህርት እና በስራ ለመሄድ ፕሮሰስ የሚያደርጉ በርካታ ወጣቶችን ማነጋገር ችለናል። ሀሳባቸውንም ተቀብለናል።
አንድ ካናዳ ለመሄድ በዝግጅት ላይ ያለ ወጣት ፥ " እኔ ከዩኒቨርሲቲ በትልቅ ውጤት ከተመረቅኩ አንስቶ ባለፉት 3 ዓመታት ያልሞከርኩት የስራ ሙከራ የለም ባለሁበት አካባቢ አጠቃላይ የቅጥር ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ሆኖብኝ በግሌ ለመንቀሳቀስ ሞክሬ አይደለም ህይወቴን ላሻሻል ዳግም የቤተሰብ እጅ ጠባቂ ሆኛለሁ " ሲል ገልጿል።
" በዚህም ምክንያት ከሰዎች ብር አፈላልጌ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ያለውን ነገር ሁሉ ለመስራት እየጣርኩኝ ነው " ብሏል።
ሌላኛዋ ወጣት በተመሳሳይ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ስትሆን " በተግባር የስራ እድል ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ ነው ፤ የሚሰራው በትውውቅ በብሄር እና በዝምድና ነው እንዴት ይሄንን ማለፍ እንዳለበኝ አላውቅም " ብላለች።
ለበርካታ ወራት እዚሁ ሀገር ውስጥ ሆኖ ሰርቶ ለመቀየር በሚል ብዙ ሙከራ ብታደርግም ስላልተሳካ የውጭ ሀገር እድል እየሞከረች እንደሆነ አመልክታለች።
ሌላኛው ቃሉን የሰጠ ክሩቤል የተባለ ወጣት ፥ ምንም እንኳን በስራ ላይ በሚገኝም በወር የሚያገኘው ገቢ አነስተኛ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ትዳር ይዞ፣ የራሱን ሃሳብ አሳክቶ፣ ለቤተሰብ ፣ ለወገን ተርፎ መኖር የማይታሰብ ስለሆነበት ውጭ ሀገር ሰርቶ የመመለስ ፍላጎት እንዳለውና ይህን ለማድረግ እየሞከረ እንደሆነ ጠቁሟል።
ሌሎች ያናገርናቸው ወጣቶችም ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ፣ ስራም ለማግኘት የሚያደርጉት ጥረት ተስፋ ስላስቆረጣቸው ውጭ ሀገር ለመሄድና ማንኛውም ስራ ለመስራት ሲሉ እድላቸውን እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል።
" ማንኛውም ሰው ሀገሩን ጥሎ የሚወጣው ሀገሩን ጠልቶ ሳይሆን የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ነው " የሚሉት ወጣቶቹ በዚህ እድሜ ካልሰራን መቼ ልንሰራ ነው ? ሲሉ ጠይቀዋል።
ቃላቸውን የሰጡት ወጣቶች ፦
- በሀገር ውስጥ ያለው የስራ እድል እንዲሰፋ ፣
- በትውውቅ፣ በብሄር፣ በዝምድና የሚፈጸም ቅጥር እንዲቆም
- በገንዝብ የሚፈጸም ቅጥር እንዲቀር ካልተደረገ ወጣቱ እዚህ ሰርቶ የመለውጥ ተስፋው እንደሚሞት አስገንዝበዋል።
ሌላው " በሙስና የሚዘረፈው ብር ብዙ ነው እሱን ተከላክሎ ለወጣቶች አንዳች ነገር እንኳ ማድረግ ይቻላል ፤ ግን ዘራፊው የበለጠ ሃብቱን እያካበተ ወጣቱ የበለጠ ተስፋ እየቆረጠ ነው " ብለዋል።
አሁን ላይ በየመስኩ ሙስና መንሰራፋቱን ስራ ለመቀጠር፣ ጉዳይ ለመጨረስ እጅ መንሻ ካልተሰጠ እንደማይሆን በተግባር እንደተመለከቱ ጠቁመው ይሄ እያደር መዘዙ የከፋ ይሆናል ሲሉ አሳስበዋል።
" በሙስና በየአመቱ የሚዘረፈው የዚህች ሀገር ሃብት ለስንት ወጣቶች ህወይት መቀየሪያ ይበቃ ነበር ? " ሲሉም ጠይቀዋል።
ወጣቶች በሀገራቸው ላይ ሰርተው እንዲቀየሩ ምቹ ሁኔታ ከሌለ፣ እድሎችና ለስራ ለፈጠራ የሚሆን ሀቀኛ መደላደሎች ካልተፈጠሩ በሀገር ሰርቶ መቀየር አስቸጋሪ ስለሚሆን ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል።
" ፖለቲከኞችም ሆኑ ለሀገር እናስባለን ተፅእኖ ፈጣሪ ነን የሚሉ ሰዎችም የወጣቶችን የኢኮኖሚ ጉዳይ አጀንዳ ሊያደርጉ ይገባል ዘውትር እነሱን የሚጠቅም ነገር ካልሆነ የመናገር እና ተፅእኖ የመፍጠር ፍላጎት የላቸውም " ሲሉ ተችተዋል።
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ አ/አ)
#ቲክቫህኢትዮጵያ #የወጣቶችድምጽ
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#SafaricomEthiopia
⭐ የሙዚቃ ኮከቦቹን በላይካችን ምርጥ 20 ውስጥ እናስገባቸው! 👏🏽
እስከ መስከረም 20 ብቻ! ⏳
የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ #Safaricomet ታግ እናድርግ
እንዝፈን! እንፖስት! እናሸንፍ!
መልካም ዕድል!
#1Wedefit #FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge

ፎቶ፦ ከአዳማ ወደ ጂቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል፡፡
የባቡር ትራንስፖርት ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ውስጥ ገቢ ምርቶችን ለማስገባት ብቻ የሚያገለግል ነበር።
የአገልግሎቱ መጀመር ወደ ውጭ ሀገራት ጥራት ያለውን የስጋ ምርት የመላክ አቅምን ይጨምራል ፤ የትራንስፖርት መጨናነቅን ይቀንሳል ብለዋል።
#Ethiopia #EngTakelUma

TIKVAH-ETHIOPIA
NGAT_EXAM_SCHEDULE_FFF1.xls
#NGAT
የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የማለፊያ ነጥብ 50% እና ከዚያ በላይ እንደሆነ ተገልጿል።
የፈተናው ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።
በ2017 ዓ.ም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለሚማሩ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።
የተፈታኞች ውጤት ዛሬ ይፉ የሆነ ሲሆን ተፈታኞች የምዝገባ ቁጥር / Username በማስገባት ውጤታቸው በተከታዩ ሊንክ መመልከት እንደሚችሉ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ውጤት መመልከቻ - https://result.ethernet.edu.et/ngat_result
Via @tikvahuniversity

የግብፅ ነገር #2 ? ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር በባህር በር ጉዳይ የመግባቢያ ስምምነት በተፈራረመች ወቅት ሰዓታት ሳይቆጠር ተቃውሞ ያሰማችው ግብፅ ነበረች። ከሶማሊያ ጋር ተደዋውላም " አይዞሽ እኔ አለሁልሽ፤ በማንኛውም መንገድ አብሬሽ ቆማለሁ " ብላት ነበር። ባለስልጣናቶቿም ኢትዮጵያ ለሶማሊያን ስንትና ስንት የደም ዋጋ እንዳልከፈለች ዛሬ ደፍረው " ኢትዮጵያን እንዳለመረጋጋት ምንጭ "…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግብፅ ?
ግብፅ፣ ሶማሊያን እያስታጠቀች ነው።
ሶማሊያ የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ከግብፅ እንደተሰጧትና ተጨማሪ መሳሪያዎችን በቀጣይነት እንደምትጠብቅ አንድ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ተናግረዋል።
ስማቸው ሳይጠቀስ ለቢቢሲ ሶማሊኛ የተናገሩ ባለሥልጣን ባለፉት ቀናት በመርከብ ተጭነው ወደ ሞቃዲሾ ወደብ የደረሱት የጦር መሳሪያዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።
እነዚህ መሳሪያዎች የሶማሊያ መንግሥት ጦር የሚታጠቃቸው ነው ብለዋል።
ወደ ሶማሊያ የገቡት የጦር መሳሪያዎች ፦
- ፀረ አውሮፕላን ሚሳኤሎች፣
- መድፎች
- ሌሎች አነስተኛ የጦር መሳሪያዎች መሆናቸውን ባለሥልጣኑ ጨምረው ተናግረዌ።
ይህንን ከፍተኛ የሆነ መጠን ያለውን የጦር መሳሪያ በሞቃዲሾ ወደብ በኩል ወደ ሶማሊያ መግባቱን በተመለከተም የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ናቸው።
በርካታ የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን የጦር ማሳሪያዎቹ ወደ ሞቃዲሾ ወደብ ደርሰው የተራገፉት #በግብፅ መርከብ አማካኝነት መሆኑን ዘግበዋል።
በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ከትናንት እሁድ ጀምሮ የተለያዩ ዓይነት ያላቸው ከባድ መሳሪያዎች እና በጭነት መኪና ተሸፍነው የሚጓዙ ወታደራዊ ቁሶች በሞቃዲሾ ጎዳናዎች ላይ ሲተላለፉ ታይተዋል።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣን አሁን ከገባው የጦር መሳሪያ ጭነት በተጨማሪ በቀጣይነት ታንኮችን እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።
ይህ እየሆነ ያለው ግብፅ ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነት ደርሳ ሠራዊቷን በአገሪቱ ውስጥ ለማሰማራት ፍላጎት እንዳላት መግለጿን ካሳወቀች በኃላ ነው።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሁለት የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች የጦር መሳሪያ ጭነው ሞቃዲሾ መግባታቸው የሚዘነጋ አይደለም። #ቢቢሲሶማሊ

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ !
የመጀመሪያው የሞሐ የቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ፣ በአዲስ አበባ ኮተቤ 02 አካባቢ ለዕድለኛ ወጥቷል፡፡
ዕድለኛዋ አሸናፊ ወ/ት ሕይወት ተካ፣ ሽልማታቸውን ቅዳሜ መስከረም 11 ቀን 2017ዓ.ም. በተከናወነ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም ተረክበዋል፡፡
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ፣ አሁንም ደንበኞቹን በጣዕም እያስደሰተ በሽልማት ማንበሽበሹን ቀጥሏል፡፡
በርካታ ሽልማቶች አሁንም ዕድለኞቻቸውን ይጠብቃሉ፡፡ ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና ሰቨን አፕን እያጣጣምን ዕድላችን እንሞክር - እናሸንፍ!
#Pepsi #7Up #Mirinda
#MohaSoftDrinksIndustry

ግብፅ ? ግብፅ፣ ሶማሊያን እያስታጠቀች ነው። ሶማሊያ የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ከግብፅ እንደተሰጧትና ተጨማሪ መሳሪያዎችን በቀጣይነት እንደምትጠብቅ አንድ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ተናግረዋል። ስማቸው ሳይጠቀስ ለቢቢሲ ሶማሊኛ የተናገሩ ባለሥልጣን ባለፉት ቀናት በመርከብ ተጭነው ወደ ሞቃዲሾ ወደብ የደረሱት የጦር መሳሪያዎች እንዳሉ ጠቁመዋል። እነዚህ መሳሪያዎች የሶማሊያ መንግሥት ጦር የሚታጠቃቸው…
" ... የጦር መሣሪያ አቅርቦቱ በመጨረሻ ሀገሪቱን አሸባሪዎች እጅ ላይ እንድትወቅድ በር ሊከፍት ይችላል " - ታዬ አጽቀሥላሤ (አምባሳደር)
" በሶማሊያ ባልተረጋጋ የደህንነት ሁኔታ ውስጥ በውጭ ሃይላት የሚደረግ የጦር መሣሪያ አቅርቦት በመጨረሻ ሀገሪቷ አሸባሪዎች እጅ ላይ እንድትወድቅ በር ሊከፍት ይችላል " ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሤ ተናግረዋል።
ይህን ያሉት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ግንባታ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።
አምባሳደር ታዬ የሶማሊያ ጉዳይ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ " ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች " ሲሉ አረጋግጠዋል።
" በሶማሊያ ድህረ የአፍሪካ ህብረት ሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ (አትሚስ) የሚኖረው የኃይል ስምሪት ተገቢውን ጊዜ ወስዶ የተልዕኮዎን የኃላፊነትን ፣ መጠን፣ የፋይናንስ ምንጭ እና ቅንጅት በአግባቡ መሠራት አለበት " ሲሉ አስረድተዋል።
" ሶማሊያ ባልተረጋጋ የደህንነት ሁኔታ ውስጥ በውጭ ኃይላት የሚደረግላት የጦር መሣሪያ አቅርቦት አሸባሪዎች እጅ ላይ ሊወደቅ ይችላል " ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ሮዝማሪ ዲካርሎ " በቀጣናው እና ከቀጣናው ባሻገርም ተመድ ከኢትዮጵያ ጋር በሰላም ግንባታ ዙሪያ የሚያደርገውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል " ብለዋል።

#Tigray አዲሱ የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው አነሱ። በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ ፊርማ መስከረም 8/ 2017 ዓ.ም የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የዞኑ የመንግስታዊ አገልግሎት ዘርፍና የልማታዊ ዘርፍ አግልግሎት ሃላፊዎች ከስራ ተነስተዋል። ለሃላፊዎቹ ከዞኑ መንግስታዊ የስራ ሃላፊነት መነሳት የጊዚያዊ አስተዳደሩ…
#Tigray
" የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ እና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ አንቀበልም ፥ መንግስት ለዚህ መሰል እንቅስቃሴ ህጋዊ የሆነ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ አስጠንቅቋል።
ከሰሞኑን ካቢኔው ስብሰባ አድርጎ ነበር።
ይህን ተከትሎ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ እና ስለ ህወሓት አመራሮች ክፍፍል እና ስለ ጸጥታ ኃይሉ ተነስቷል።
ካቢኔው " ከጊዚያዊ አስተዳደር እውቅና ውጪ ፦
- መንግስታዊ የስራ ምደባ ማካሄድ ፣
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ማፍረስ
- የመንግስት መዋቅር ለመረበሽና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም " ብሏል።
" መንግስት ለዚህ መሰል ተቀባይነት የሌለው እንቅስቃሴ ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል አስጠንቅቋል።
ከህወሓት ክፍፍል ጋር በተያያዘ ካቢኔው " በአሁኑ ወቅት በህወሓት አመራሮች ዙሪያ የተፈጠረው መከፋፈል በህወሓትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረ ተደርጎ መወሰዱ ልክ አይደለም " ብሏል።
" ክፍፍሉ በጥቂት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የተፈጠረ ነው " ያለው ካቢኔው " ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከህወሓት ከሙሁራን ከፀጥታ አካላትና ከተፎካካሪ ድርጅቶች በተወጣጡ አካላት የተደራጀ መሆኑ ከግምት ውሰጥ በማስገባት ከህወሓት ክፍፍል ጋር አቆራኝቶ መግለፅ ልክ አይደለም " ሲል ገልጿል።
ካቢኔው ስለ ፀጥታ ኃይሎች ባነሳው ነጥብ " የፀጥታ አካላት ሁሉም ዓይነት ችግሮችና ፈተናዎች ተቋቁመው የህዝብ ፀጥታ ለማስከበር እያደረጉት ያለውን ጥረት አወንታዊ እና እውቅና የሚቸረው ነው " ብሏል።
" ስራዎቻቸው ከማንኛውም የፓለቲካ አስተሳሰብ ነፃ በማድረግ ገለልተኛ አቋም ይዘው እንዲሰሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ይደግፋል ያበረታታል " ሲል አመልክቷል።
#TikvahEthiopiaMekelle

#Tigray " የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ እና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ አንቀበልም ፥ መንግስት ለዚህ መሰል እንቅስቃሴ ህጋዊ የሆነ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ አስጠንቅቋል። ከሰሞኑን ካቢኔው ስብሰባ አድርጎ ነበር። ይህን ተከትሎ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። በዚህም የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ እና ስለ ህወሓት…
#Tigray
" እኔ ድርድር ያስፈልጋል በሰላም ይፈታ ስል ፤ እሱ ግን ' ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ? ' ነበር ያለው " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)
ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድና የቆየ ቂም ለመወጣት በሚል ከሰሱ።
በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባሳለፍነው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት መቐለን ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ህዝባዊ የተባሉ ስብሰባዎች አካሂዷል።
በእነዚህ መድረኮች የፖርቲው አመራሮች ክፍፍል በስፋት ተነስቷል።
ህወሓትን ለማጥፋት፣ ስልጣን ለመጠቅለል የሚንቀሳቀሱ ተብለው የተገለፁ አመራሮች በስም እየተጠቀሱ ወቀሳ ሲሰነዘርባቸው ተሰምቷል።
ቅዳሜ በመቐለ በተካሄደና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮንን (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የፖርቲው አመራሮች እና የተመረጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የታደሙበት መድረክ ነበር።
በዚሁ መድረክ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን፥ ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድ፣ የቆየ ቂም በመወጣት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በማንሳት እንዲሁም ከዚህ በፊት በይፋ ያልተሰሙ መረጃዎች በመግለፅ ሲተቹ ተደምጠዋል።
በንግግራቸው እርሳቸው የሚመሩትን ህወሓት ሰላም የማይፈልግ አድርጎ የማቅረብ የተሳሳተ ፍረጃ ከትግራይ ባለስልጣናት በኩል እየቀረበበት መሆኑ ገልጸው " ይህ ውሸት ነው " በማለት አጣጥለዋል።
ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ " ለምሳሌ በደቡባዊ ዞን በተደረገ መድረክ ጀነራል ጻድቃን እኛ ሰላም እንፈልጋለን፣ እነሱ የሚሹት ጦርነት ነው ሲል ሰምታችሁታል። በጦርነቱ ወቅት ደሴ ተሻግረን ሰሜን ሸዋ ስንጠጋ፥ ድርድር ያስፈልጋል ወይ ሲባል እኔ አዎን ያስፈልጋል ነው ያልኩት። በሰላም ሊፈታ ስለሚገባው። እሱ ግን ከማን ጋር ነው የምንደራደረው፣ ውጊያው አልቋል ሲል የነበረ ነው። አሁን ግን እኔ ሰላም ነኝ እነሱ ጦርነት ናቸው የሚፈልጉ ማለት ጀመረ " ብለዋል። #ዶቼቨለ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የመስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡
እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉ፡፡
እርስዎም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
[Telegram] [Facebook]
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
https://t.iss.one/LionBankSC

#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!
የአዲስ አመት ልዪ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ፣ ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማህበራዊ ገጾት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮችን እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡
የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡
- Tag ሲያደርጉን ለ Facebook @ TecnoEt ፣ ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia እና ለ TikTok @ TecnoEt ን ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።)
- በተጨማሪም #TecnoEt2017 ን keyword መጠቀም እንዳይረሱ)

" ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ ከሁለት ዓመት በላይ የተስፋ እንጀራ ብቻ ሆኖብናል " - አቶ አባይነህ ጉጆ
የአካል ጉዳተኞችን ዘርፈ ብዙ የሆኑ ችግሮች ይፈታል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል የተባለው " ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ " በታቀደለት ወቅት አለመውጣቱ አካል ጉዳተኞችን ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበር ፌደሬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ ምን አሉ?
“የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ሲነሳ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ ሆኖም ብዙ ችግሮቻችንን ሊቀርፍልን ይችላል ብለን እየጠበቅን ያለነው ጠቃላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ ይወጣል ብሎ መንግስት ተስፋ ሰጥቶናል።
በተስፋ ብቻ አላበቃም ሕጉ ድራፍት ተደርጎ የጋራ ምክክር ሕጉ ላይ አካል ጉዳተኞችም ተሳትፎ ከተረጋገጠበት በኋላ ለፍትህ ሚኒስቴር ሂዶ ነበር።
ፍትህ ሚኒስቴር አንዳንድ በእኛ በኩልም ተቀባይነት የሌላቸውን ኮመንቶች በመስጠት ወደኋላ መልሶታል። ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው ሕጉን በባለቤትነት የሚያረቀው።
ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ሕግ ከሁለት ዓመት በላይ የተስፋ እንጀራ ብቻ ሆኖብናል፡፡
እሱ ሕግ ቢወጣ የተሻለ ነገር ሊያመጣ ይችላል።
ሕጉ ቢወጣ እውነት ለመናገር በርካታ ችግሮቻችንን ይቀርፋል ብለን እናምናለን" ብለዋል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-09-24
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#Telegram
" አዲሱ ደንብ መተግበሪያውን ለወንጀል የሚጠቀሙት ሰዎችን ቅስም የሚሰብር ይሆናል " - ዱሮቭ
ቴሌግራም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የደንበኞቹን መረጃዎች ለሕግ አካላት አሳልፎ ሊሰጥ ነው።
በዚህም የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ፦
➡️ ስልክ ቁጥሮች፣
➡️ የኢንተርኔት አድራሻ
➡️ ሌሎችንም መረጃዎች በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት በመሳሰሉ የሕግ ተርጓሚዎች በሚፈለግበት ጊዜ ሊሰጥ እንደሚችል ቴሌግራም አሳውቋል።
የቴሌግራም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፔቨል ዱሮቭ ይህ አዲስ ደንብ እንደሆነው አመልክተዋል።
ይህ አዲስ ደንብ " መተግበሪያውን ለወንጀል የሚጠቀሙት ሰዎችን ቅስም የሚሰብር ይሆናል " ብለዋል።
" 99.999% የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ከወንጀል ጋር የሚያያይዛቸው አንዳችም ነገር የለም። 0.001% የሚሆኑት ግን ለድብቅ ወንጀል እየተጠቀሙበት የቴሌግራምን ዝና እና ክብርን እያጎደፉት ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ቢሊዮን የሚጠጉ ጨዋ ተጠቃሚዎቻችን የሚጎዳ ነው " ብለዋል።
ዱሮቭ ባለፈው ወር በፈረንሳይ ፣ ፓሪስ ኤርፖርት በቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበር አይዘነጋም።
በፖሊስ ከተያዙ በኋላ የቀረበባቸው ክስ " መተግበሪያው ለወንጀለኞች መፈንጫ እንዲሆን ፈቅደዋል " የሚል ነበር።
" ሕገ ወጥ የሕጻናት ምስሎች ዝውውርና የአደገኛ እጽ አዘዋዋሪዎችን በሚያበረታታ መልኩ መተግበሪያው ለወንጀል ተግባር እንዲውል ፈቅደዋል " በሚል የተከሰሱት ዱሮቭ ከሕግ አካላት ጋር ባለመተባበርም ተወንጅለው ነበር።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በበኩላቸው ሌሎች ለፈጸሙት ወንጀል እሳቸው ተከሳሽ መሆናቸው " አስደናቂ እና ግራ የሚያጋባ " ነገር ነው ሲሉ የፈረንሳይ ባለሥልጣናትን ወርፈው ነበር።
በኃላ ፍ/ቤት ዱሮቭ በዋስ ወጥተው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ማዘዙ ይታወሳል።
#Telegram #BBC