#AddisAbaba
" የህዝቡን ኑሮ አይታችሁታል ? ይሄ ማህበረሰብ ከኮሪደር ልማቱ ይልቅ የዕለት ጉርሱን ሸፍኖ የሚበላበት ነገር አያስፈልገውም ? " - ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ
የኮሪደር ስራው ላይ የሚነሱት ጥያቄዎች ምንድናቸው ?
የአዲስ አበባ ከተማን ገጽታ ይቀይራል የተባለው የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
አሁን ላይ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ስራ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ ነው።
የአሁኑን ጨምሮ ከቀደመው (የተጠናቀቀው) ስራ ጋር በተያያዘ ግን ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ።
ሰሞኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት አንድ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር። በዚህም ወቅት የተለያዩ ጥያቄዎች ተጠይቀዋል። ከንቲባዋን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን ተጠየቀ ? ምንስ ተመለሰ ?
በውይይቱ ተሳታፊ ከነበሩት አንዱ ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ ናቸው።
አቶ አበበ " የትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ ይሄ የኮሪደር ልማትን አይቃወምም። እኛ የአሮጌ ከተማ ፍቅር የለብንም። ቡቱቶ የሆነ ከተማ ፍቅር የለብንም። urbanization እየሰፋ ነው የሚሄደው ፤ ከተሜነት እየሰፋ ሲሄድ የህዝብ ቁጥር ሲጨምር ከዓለም ጋር መዘመን አለብን። ምንም ጥርጥር የለውም። እኛም እኮ የምንዝናናበት ነው የተሰራው ኮሪደር። ነገር ግን የሚሰሩት ልማቶች የሚሰሩት ለሰው ነው ፤ ስለዚህ ምን ያክል ነው የተጠናው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
በተጨማሪ ለከንቲባዋ ፦
➡ ለመሆኑ ከኮሪደር ስራ ጋር ተያይዞ ለአዲስ አበባ ህዝብ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የለም ? የአዲስ አበባ ህዝብ ኑሮ አያሳስበውም ? አሁን ያለበት የኑሮ ደረጃ አያሳስበውም ?
➡ የህዝቡን ኑሮ አይታችሁታል ?
➡ ' እዬዬም እኮ ሲደላ ነው ' ለምን ኑሮው አይታይም የህዝቡ ?
➡ ይሄ ማህበረሰብ ከኮሪደር ልማቱ ይልቅ የዕለት ጉርሱን ሸፍኖ የሚበላበት ነገር አያስፈልገውም ?
➡ ፒያሳ ተነሳ ጥሩ ስራ ተሰርቷል በጣም ውብ ነው ደስ ይላል ፤ የተሰራው ውስጥም ነው ተቀምጠን የምንወያየው ግን በዚህ ፍጥነት አልተቻኮለም ?
➡ በየመንገዱ የሚሰሩ ፣ ጀብሎ የሆነው የሚቸረችሩ ወጣቶች የት ሄዱ ? ሁሉም ነገር ዝግ ተደርጎባቸዋል። ... ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?
" የኮሪደር ስራ ቅድሚያ ልንሰጠው ይገባል ወይ ? እንዲህ መቸኮልስ ለምን አስፈለገ ፤ በርካታ የከተማው ህዝብ ጥያቄዎች የሉም ወይ ? የሚለው መነሳቱ ጥሩ ነው።
የኮሪደር ልማት ስራ ሲሰራ ሌሎች ስራዎችና አገልግሎቶች ወደኃላ ተብለዋል ማለት አይደለም። አስማምተን ነው እየሰራን ያለነው።
በተናበበ መንገድ አቅደን ፤ ሌሊትም ቀንም ለመስራት ራሳችንን አሳምንነን ነው እየሰራን ያለነው። ስራም ተከፋፍለን ነው። ቢሮ ማገልገል ያለበት ቢሮ ነው። እኛም ሙሉ ጊዜያችን ኮሪደር ብቻ አይደለም። ኮሪደር እያስተባበርን ሌሎች ስራዎችም እንሰራለን።
የኑሮ ውድነት ተነስቷል ፤ ችግሩ ስለገባን ነው የአዲስ አበባ ህጻናት ባዶ ሰሃን ያለ ሃጢያታቸው ምግብ ሳይኖራቸው ምግብ ያላቸው እንዲመስሉ ተደርጎ ያለ እድሜያቸው እንዲዋሹ ያለ ጥፋታቸው ፤ ከመራባቸው በላይ ምግብ ያላቸው እንዲመስሉ ባዶ ሰሃን ይዘው ትምህርት ቤት የሚወደቁበትን ታሪክ አይደል እንዴ የቀየርነው ?
ለ800 ሺህ ተማሪዎች ዩኒፎርም እናቀርባለን፣ ደብተርና የትምህርት ቁሳቁስ እናቀርባለን ፤ ምግብ በቀን ሁለት ጊዜ ጥዋት ቁርስ ይበላሉ ምሳቸውን በልተው ወደቤት ይሄዳሉ ፤ ቤት ውስጥ ያለውን ገመና ስለምናውቅ ነው።
ትውልድ መገንባት አለበት ሀገራቸውን እየጠሉ እያማረሩ ማደግ ስለሌለባቸው። የአዲስ አበባ እናቶችን የኑሮ ጫና በሚገባ አይተነው ነው። ጓዳቸውን አይተን ነው።
ሁለተኛ በየቦታው ቦታ አመቻችተን ከ190 በላይ የእሁድ ገበያ የፈጠርነው ከስግብግብ ነጋዴዎች ነዋሪዎችን ለማስጣል የሰራነው የኑሮ ውድነቱ ስለሚገባን አይደለም ?
እነኛህ የአዲስ አበባ ከተማ የመግቢያ በሮች ላይ 5 ትልልቅ የገበያ ማዕከላት በቢሊዮን ልክ እንደ ኮሪደር ልማት በፍጥነት የገነባነው የኑሮ ውድነት ጫናው ስለሚገባን አይደለም ? ለምን አልተደረገም ከዚህ በፊት።
ገበሬው ቀጥታ አምጥቶ ምርት እንዲሸጥ ደላላው ከመሃል እንዲወጣ አላደረግንም እንዴ ?
አረጋውያን በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ማግኘት አቅቷቸው አልተመለከትንም ፤ ' ተረጂነትን ታስፋፋላችሁ ' እየተባለን ስንተች ትችቱን ወደጎን ብለን በቀን አንድ ጊዜ ምግብ የሚያገኙበትን 21 የምገባ ማዕከላት ገንብተን እየመገብን ነው።
ከመንግሥት በጀት ውጭ 30,000 ቤቶች ገንብተን በነጻ ድሆችን አንስተን ዝቅ ብለን ያስገባንበት የህግ ግዴት አለብን እንዴ ? 30,000 ከመንግሥት በጀት ውጭ ነው። ውሃ የሚያፈስባቸው ከመጸዳጃ ቤት ጋር የሚኖሩ አንስተን አስገብተናቸዋል።
የኮሪደር ስራ በሰራንበት 2016 ዓ/ም ላይ ብቻ 18,000 ከትንሽ ፕሮጀክቶች እስከ አድዋ ድረስ ሰርተን ለህዝባችን ክፍት አድርገናል። የት የት እንደሆኑ ዳታ እንሰጣለን ሂዱና እዩ።
አጠቃላይ የከተማው ችግር እና ያለንበት ጥልቅ ድህነት በ1 ፣ በ3 ፣ በ5 ዓመት ተስርቶ አያልቅም የዘመናትን ውዝፍ በአንድ ጊዜ አልጨረሳችሁም ከሆነ ትክክል አይደለም። ሊያልቅ አይችልም።
በአንድ በኩል እኚህን ቶሎ ቅረፉ በሌላ በኩል አትቸኩሉ አብሮ አይሄድም።
ኮሪደር ስራ በባለሞያዎች በደንብ ተጠንቶ ነው የተጀመረው። መነሻው መዋቅራዊ ፕላን ነው። ያጠናንባቸውን አካባቢዎች ዶክመንቱ ይፋዊ ስለሆነ ማየት ይቻላል። የፕላን ጥሰቱ ልክ የለውም።
በየሰፈሩ ያሉ የፍሳሽ መስመሮች የተዘጉ ናቸው፣ እሳት አደጋ ሲፈጠር እንኳን ገብተን ማጥፋት አቅቶናል። ይቃጠሉ ይለቁ ? ከቆሻሻ ጋር መኖር የኢትዮጵያውያን ክብር ይመጥናል ? ጠረኑን አይታችሁታል ? እንዲህ ባልናገር ጥሩ ነበር ግን እውነታው ይሄ ነው።
ሰው ፍሳሽ ከላይ እየወረደበት እንዲተኛ፣ እናቶች ቆጥ ላይ እንጀራ እንዲጋግሩ ፣ እናቶች ከስር ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን ይዘው ያድራሉ ከላይ ቆጥ ሰርተው ያከራያሉ። እነዚህ አካባቢዎች ታሪካቸው ይኸው ነው።
ቤቶቹ አርጅተዋል። በጭቃና በእንጨት ነው የተሰሩት አረጁ ግዜያቸው አለፈ ወደቁ በቆርቆሮ ቢለበዱ፣ ላስቲክ ቢታሰርባቸው ችግር መከላከል አይችሉም።
ወቀሳ የምታነሱ ሰዎች ፒያሳ ዶሮ ማነቂያ በሴት እህቶቻችን እና እናቶች ላይ የሚፈጸመው ወንጀል ለምን አያማችሁም ? ወይስ አታውቁም ? የዜግነት ክብራችንን አይመጥንም ነበር። ስለዚህ ክብራችንን በሚመጥን መንገድ ማልማት ይገባል።
ወደው አልነበረም ከቆሻሻ ጋር ሲኖሩ የነበሩት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አልፈው መጥተው ያ እንዲቀጥል የሚቀርበው ጥያቄ ፍጹም ተቀባይነት የለውም።
- ገቢያችን እንዲያድግ
- የስራ እድል በስፋት እንዲፈጠር
- ዜጎች ንጹህ ፅዱ ቦታ እንዲገበያዩ፣ እንዲሰሩ ፣ እንዲኖሩ ለማስቻለው ስራዎችን እየሰራን ያለነው።
የምንቸኩለው ጊዜ ስለሌለን ነው። ጉስቁልና ድህነት ውስጥ ነው ያለነው። ውርደት አለ ከዚህ ውስጥ መውጣት አለብን። አንዳንዶች የኛ ኑሮ ሻል ስላለ የድሃው አይታየን ይሆናል ! ከዚህ በላይ እንቸኩላለን " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba #ኮንዶሚኒየም
🔵 " ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ? ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " - አቶ አበበ አካሉ
⚫ " የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከአዲስ አበባ የኮሪደር ስራ ጋር በተያየዘ በርካቶች በልማት ተነሺነት ከኖሩበት አካባቢ ተነስተው ወደ ተለያዩ ጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲገቡ እየተደረገ ነው።
ምንም እንኳን ተነሺዎቹ መግባታቸው ላይ ቅሬታ ባይፈጥርም ከ97 አንስቶ ሲቆጥቡ የኖሩ ነዋሪዎች መፍትሄ ሳያገኙ መቅረታቸው እና አሁን ላይ አስተዳደሩ ቤት የተሰጠ መሆኑ ቅሬታ አሳድሯል።
ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በተካሄደ የኮሪደር ስራውን በሚመለከት የውይይት መድረክ ላይ ይኸው ቅሬታና ጥያቄ ተነስቷል።
ጥያቄውን ካነሱት አንዱ ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ ናቸው።
" ሲቆጥቡ የኖሩ ሰዎች ጉዳይ ምን ደረሰ ? አሁን ማህበረሰቡ ምን ያማል ከተማ አስተዳደሩን ' እኛ በቆጠብነው ገንዘብ ነው የልማት ተናሺዎችን እያሰፈረ ያለው ' የሚል ሮሮ አለ።
ለዚህ ምንድነው ምላሻችሁ ?
ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " ሲሉ ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?
" የኮንዶሚኒየም ቤት እስኪ ከየት አምጥታችሁ ነው በዚህ ደረጃ ያላችሁ ኃላፊዎች ' በቆጡት ገንዘብ ነው የሚሰራው ' የምትሉት።
እነ ንግድ ባንክ ናቸው ብሩን የሚያቀርቡት እስቲ እንነጋገር ትንሽ ወደ መረጃው ጠጋ ብላችሁ ብናወራ ምናለበት።
ኮንዶሚኒየም በብድር ነው የሚሰራው። የከተማ አስተዳደሩ በጀቱን አስይዞ ነው የሚበደረው።
ለምንድነው የሚቆጥቡት ? ከተባለ ዕጣ የደረሳቸው ዕለት የሚከፍሉትን እንዳያጡ ነው። እንጂ ቤቱን መገንቢያ አይደለም። ልክ ቤቱ ሲገነባ ብሩን ይከፍሉታል።
ሁለተኛ እንዴት ነው እኛ ብቻችንን የምንጠየቅበት ? ቤት ባልተዘጋጀበት በሚሊዮኖች መዝግቦ ቆጥቡ ብሎ ኃላፊነት ወስዶ የሰራ አካል እያለ ለምንድነው እኛ የምንወቀሰው ?
ቤት ሳያዘጋጅ ዜጎችን ልክ እንደ ማታለያ በሚሊየን መዝግቦ የበተነ እያለ ለምንድነው እኛ የምንወቀሰው ?
የኮንዶሚኒየም ቤት አጠቃላይ አንድ ቦታ እጅብ ብሎ ስለተሰራ ብዙ ይመስላችኋል እንጂ እስካሁን እስካጠናቀቅነው ያለው 300,000 ነው። የተመዘገበው በሚሊዮን ነው። በየጊዜው ተስፋ ቆርጦ፣ ተጣርቶ ተጣርቶ እኛ የደረስንበት 600,000 ነው። አክተቭ ይቆጥብ የነበረው። ግን ቤት ማግኘት እንዳለባቸው እናምናለን። ቤት ማግኘት አለባቸው።
ካለቁት ኮንዶሚኒየሞች ብራቸው ተዘርፎ፣ ቀድሞ ተከፍሎ ያልተሰራ 80 ህንጻ ብር ተከፍሎበት ጥለው ሄደዋል። በብዙ ውጣውረድ ነው 139,000 ቤቶችን የጨረስነው። የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ብቻ።
አሁንም ቢሆን ግን የከተማችን ነዋሪዎች ቤት ማግኘት አለባቸው። ለዚህም በኮንዶሚኒየም ብቻ አይደለም እንደ ቀድሞ በሚፈለገው ደረጃ ብድር ማግኘት አልቻልንም ከባንክ። ኮንዶሚኒየም መጥፎ ስለሆነ አላቆምነውም።
ከተማ አስተዳደሩ ዕዳ እየከፈለ ነው። ንግድ ባንክ የሚያበድረው የባለሃብትን ገንዘብ ነው አይደል ? 56 ቢሊዮን የኮንዶሚኒየም ዕዳ ነው የተረከብነው ዋስትና የሚሰጠው ከተማ አስተዳደሩ ስለሆነ ክፈሉ ተባልን ተገደድን በለውጥ ዘመኑ 30 ቢሊዮን ከፍለናል የኮንዶሚኒየም ዕዳ።
ይህ ሁሉ ዕዳ አንደኛ በከፍተኛ ሰብሲዲ ስለሚሰራ ነው ፤ ሌላው ያልተሰሩ ቤቶች የተከፈለባቸው አሉ። ሳይከፍሉ ሲሸጡ በተለያየ መንገድ ሲተላለፉ የነበሩ ቤት ውስጥ ያገኘናቸው ሰዎች ከግለሰብ የገዙ ናቸው፤ ሊገደዱ አይችሉም የኮንዶሚኒየም ክፈሉ ተብለው። አጣርተን እኮ በሚዲያ ነግረናችኋል ፤ ያጋጠመንን።
አሁን በግልና በመንግሥት አጋርነት ወደ 100,000 ቤቶች አስጀምረናል። የቁጠባ ቤቶችንም እየሰራን እያከራየን ነው። በሪስልቴትም በግል የሚሰሩትን እንደ ከተማው ፕሮጀክት ጠጋ ብለን እያገዝን ቶሎ እንዲጨርሱ እያደረግን ነው።
እስካሁን የቆጠቡትን አሁን በግልና መንግሥት ትብብር ከምንሰራው ውስጥ ቅድሚያ ሊያገኙ የሚችሉበትን አግባብ እየተከተልን ነው። ሁለተኛ ደግሞ ተደራጅተው በማህበር እንዲሰሩ ...እስካሁን ለተደራጁት መሬት አስረክበናል።
መነገጃ አታድርጉት፤ ከእውነታው ውጭ መነጋጃ ማድረጉ አይጠቅምም።
የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል። ባለፈው ያስጨረስናቸውን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቅድሚያ 97 አክቲቭ ቆጣቢዎች ሁሉ ዕጣ እንዲወጣላቸው ተደርጓል።
እነሱ ከወጣላቸው በኃላ ዲአክቲቬት ያደረገውን አካውን አክቲቬት ያደረገ ካለ እሱ ስለቆጠበ ቤት ስለሚፈልግ ለሚቀጥለው ጊዜ ሊታይ ይገባል ፤ እንጂ በዚህ መንገድ መቅረብ የለበትም " ሲሉ መልሰዋል።

#AddisAbaba " ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ " በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየሰራው ነው " ሲል ገልጿል። ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ…
የዛሬው የመርካቶ ገበያ ውሎ ምን ይመስላል ?
በዛሬው እለት በመርካቶ የሚገኙ የተለያዩ የገበያ ማዕከላት ተዘግተው መዋላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባደረገው ቅኝት ማየት ችሏል።
የመርካቶ ገበያም ከዚህ ቀደም ከነበረው የንግድ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ መዋሉን ነጋዴዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ተዘግተው ከዋሉት የገበያ ማዕከላት መካከል
ሚሊተሪ ተራ ፤ ዱባይ ተራ ፤ አድማስ እና አመዴ ገበያ አካባቢ የሚገኙ ሱቆች ይገኙበታል።
ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን የዘጉት ከደረሰኝ ጋር በተገናኘ ውዝግብ መሆኑ ታውቋል።
ነጋዴዎቹ ዛሬ ጠዋት በርካታ የንግድ ሱቆች ዝግ እንደነበሩ የተናገሩ ሲሆን በከሰአቱ የገበያ ሁኔታ አንዳንድ ሱቆች እንደተከፈቱ ገልፀዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከሰዓት በኋላ ባደረጉት ቅኝት የጣና ገበያ ፣ ሲዳሞ ተራ እና ቦምብ ተራ አካባቢ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደታዩበት ታዝበዋል።
በተወሰነ መልኩም ወደ ሸማ ተራ እና መሃል መርካቶ አካባቢዎች መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴዎችን መመልከት ተችሏል።
ሆኖም ግን በሸማ ተራ ፣ ድር ተራ እና ሰሀን ተራ አካባቢዎች የነበረው የንግድ እንቅስቃሴ የተቀዛቀዘ መሆኑን ነጋዴዎች ነግረውናል።
በዛሬው እለት በሰሀን ተራ አካባቢ በግምት 8 ሰዓት ገደማ ላይ ነጋዴዎች " አነስተኛ ነው " ያሉት እሳት ተነስቶ እንደነበር ጠቁመዋል። ነገር ግን እሳቱ ሳይስፋፋ ወዲያው በነጋዴው ርብርብ እንደጠፋ ጠቅሰዋል።
በሰሀን ተራ አካባቢ የሚገኙት ሱቆች በአክሲዮን የገበያ ማዕከልን ለመገንባት ሱቆቻቸውን ለቀው እየወጡ እንደሆነም ካነጋገርናቸው ነጋዴዎች ተረድተናል።
በዚህ አካባቢ የሚገኙት ነጋዴዎች ሱቃቸውን የለቀቁት በስምምንነት መሆኑንም ተናግረዋል።
የተለቀቁትም ሱቆች ከወረዳው የመሬት የልማት አስተዳደር ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበት " ታሽጓል " የሚል ጽሑፍ ተለጥፎባቸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የተለያዩ የመርካቶ ነጋዴዎች በሸማ ተራ ከተከሰተው የእሳት አደጋ በኋላ " ስራ የለም " ሲሉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ያለ ደረሰኝ ሲነግዱ የተገኙ ነጋዴዎች ላይ ይጣላል የተባለው ቅጣት የተጋነነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሱቆቹ የተዘጉት " ግብይቶች ሁሉ በደረሰኝ ይካሄዱ " የሚለው ተቃውሞ እንዳልሆነ አንድ ስሙ እንዳይገለፅ የጠየቀ የመረጃ ምንጭ ገልጿል።
የመረጃ ምንጩ " ግብይቶች በደረሰኝ የሚደረጉ ቢሆንም ተቆጣጣሪ አካላት የተሸጡ እቃዎችን የሚያሳይ ደረሰኝ በሚጠይቁበት እና በምናሳያቸው ወቅት ከሚገባው በታች ነው የቆረጣችሁት በማለት በ6 ወር ሰርተነው የማናቀውን 100 ሺህ ቅጣት ጥለውብን ይሄዳሉ " በማለት አማረዋል።
በአንፃሩ አንድ ሌላ ነጋዴ እንደገለፁት ከንግድ ስራ መንግስት ማግኘት የሚገባው ገቢ ቢኖርም ይህ አሰራር የማይመቻቸው እና ደረሰኝ የማይቆርጡ ነጋዴዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።
ከዚህ ቀደም ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኢንተለጀንስ እና የምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ " መርካቶ በባህሪው ብዙ የክልል ግብር ከፋዮች የሚያለቅሱበት ቦታ ነው የሌሎች ክፍለ ከተሞች ግብር ከፋዮችም ቅሬታ ያቀርባሉ ደረሰኝ አይሰጡም በሚል ትልቅ ችግር ስላለበት ትኩረት ተደርጎበት ያለ ነው እንጂ አዲስ አይደለም " የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።
ዳይሬክተሩ አክለውም " ቦታው በልዩ ሁኔታ (በግብር አሰባሰብ) በመንግስት ትኩረት ተደርጎበት ሊሰራበት የሚፈለግ አካባቢ ነው ነገር ግን ከአሰራር አንጻር በሚፈለገው ልክ ማሳካት አልተቻለም " ማለታቸው ይታወሳል።