TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ውጤት

የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #1

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
👆የቀጠለ

የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #2

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ውጤት : የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል። በሚከተሉት አማራጮች ውጤታችሁን ተመልከቱ፦ ► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et ► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284 ► በቴሌግራም ቦት 👉 https://t.iss.one/EAESbot ከውጤት መግለጫ ፖርታል እና ቴሌግራም…
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

ተማሪዎች እና ወላጆች የፈተናውን ውጤት ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ።

ውጤት የሚታየው ፦

► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et

► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

► በቴሌግራም ቦት 👉 https://t.iss.one/EAESbot ላይ ነው።

ከፍተኛ የኔትዎርክ መጨናነቅ ስለሚኖር በትዕግስት ይሞክሩት።

በ2016 ዓ / ም ለፈተናው ከተቀመጡት ከ684 ሺህ በላይ ተማሪዎች 36,409 ተማሪዎች (5.4 በመቶ) ናቸው በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን 50% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡት።

ምንም እንኳን በተማሪ ቁጥር ደረጃ ከአምናው የቀነሰ ቢሆንም በቀጣይ የትምህርት ዘመንም የሬሜዲያል ፕሮግራም ይኖራል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
👏

በሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከ600ው በተፈጥሮ እና በማህበራዊ ሳይንስ (575 እና 538) ከፍተኛውን ውጤት አምጥተው የሰቀሉት ሴት ተማሪዎች ናቸው።

ከዚህ ባለፈ እጅግ በርካታ ሴት ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት በማምጣት የዘንድሮውን ፈተና ሰቅለዋል።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል በተሰጠው ከ700 ፈተናም ሴቶች ከፍተኛ አኩሪ ውጤት ነው ያስመዘገቡት።

ከላይ ለማሳያ የተወሰኑ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ፎቶ ይያዝ እንጂ ሌሎችም በርከታ ሰቃይ ሴት ተማሪዎች አሉ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ " ዜጎች በሕገ ወጥ ደላሎች ማታለያ ወደ ማይናማር እና ታይላንድ ከመጓዝ ሊታቀቡ ይገባል " ሲል አሳስቧል። ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች በይነ መረብን በመጠቀም በርካታ ዜጎች ችግር ላይ እንዲወድቁ ማድረጋቸውን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ተናግረዋል። " ዜጎች ባልተረጋገጡ አማላይ ማስታወቂያዎች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው " ብለዋል። "…
🔈#ይነበብ

(በድጋሚ የተለጠፈ)

ወጣቶችን ወስደው ምንድነው የሚያሰሯቸው ?

በኦንላይን ወይም በደላሎች አልያም በኤጀንሲዎች " እዚህ ሀገር ጥሩ ስራ አለ ፤ ክፍያውም ከፍ ያለነው " ተብለው ብዙ ወጣቶች ከተለያዩ ሀገራት ይዘዋወራሉ።

ለአብነት ያህል ወጣቶች ከሚዘዋወሩባቸው ሀገራት መካከል የሳይበር ማጭበበር ( Cyber Scam) ማዕከላት ተብለው ወደ ሚታወቁት ፦
• ማይናማር ፣
• ካምቦዲያ፣
• ላኦስ
• ማይናማር ታይላንድ ድንበር
• ቻይና ማይናማር ድንበር በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

እነዚህ አካባቢዎች ባሉ የተለያዩ ቦታዎች በኦንላይን ማጭበርበር ላይ የተሰማሩ በርካታ ድርጅቶች አሉ።

በእርግጥ መጀመሪያ ላይ ወጣቶቹን " እልካችኋለን " የሚሏቸው ሌሎች በኢኮኖሚና ደህንነት እጅግ ጠንካራ ፣ ጠንካራ ባይሆኑም እንኳን ያን ያህል የከፋ ሁኔታ ላይ ወደማይገኙ ሀገራት ነው።

እዛ ቦታ ከደረሱ በኋላ ግን የሚልኳቸው ወደ ጎረቤት ድሃ እና የህግ ስርዓት ወዳልጠነከረባቸው ሀገራት ይሆናል።

የሚሰራው ማጭበርበር ምንድነው ?

ስራ ብለው የሚልኳቸው መጀመሪያ ፦
- የኦላንይ ግብይት ስራ ማቀላጠፍ
- የኦንላይን ሴልስ ስራ
- የሆቴል እንግዳ ተቀባይ
- የማርኬቲንግ ስራ ... ሌላም ሌላም ነው።

ነገር ግን ስራ አለበት ወደ ተባለው ስፍራ ሲሄዱ የሚሰሩት ስራ መጀመሪያ ላይ ከተነገራቸው ተቃራኒ ነው።

የየራሳቸው ጋንግ አለቆች ባላቸው እጃቸውም ረጅም በሆኑ ሰዎች በሚመሩ የማጨበርበር ተግባር ላይ ወደ ተሰማሩ ድርጅቶች ያስገቧቸዋል።

እነዚህ ሰዎች ስልክ / ኮምፒየተር የሚያቀርቡላቸው ሲሆን በዛም ዓለም አቀፍ የማጨበርበር ስራ ላይ ያሰማሯቸዋል።

🔴 ዴቲንግ 🔴

የመጀመሪያ ስራቸው ከኢንተርኔት ላይ ውብ የሆኑ ሴቶችን / ስኬታማ ሴቶችን / ስኬታማ ወንዶችን ታዋቂ ሰዎችን ፎቶ በማውረድ የውሸት አካውንት መክፈት ነው።

በመቀጠል የሚያጭበረብሩትን ሰው ማናገር ይጀምራሉ። ምናልባትም በቅርብ የሚያውቋቸውን ሰዎችንም ሊሆን ይችላል።

እነዛን ሰዎች ልክ እንደ ኖርማል ሆነው ያለ ማቋረጥ ጊዜ ወስደው ያናግሯቸዋል።

የትኛውንም ጊዜ ይፍጅ ማናገራቸውን ይቀጥላሉ።

ስለ ውሸት ስራቸው፣ ስለ ህይወታቸው እየፈጠሩ ያወራሉ። በዚህ ውስጥ ምንም ምልክት አያሳዩም።

ወደ ፍቅር ከወሰዷቸውና ከጣሏቸው እምነትም ካገኙ በኃላ መጨረሻው ወደሆነው ዓላማቸው ገንዘብ ማስላክ ይገባሉ።

" ለምን እኔ ምሰራው ስራ ላይ ኢንቨስት አታደርም / አታደርጊም " በማለት ለምሳሌ ክሪፕቶ  ላይ ብለው ገንዘብ ይቀበላሉ።

በቃ አለቀ ! ገንዘባችሁ ተበልቶ ይቀራል። በኃላም ብሎክ አድርገው ይሸኟችኋል። ቀጣይ ሌላ ሰው ታርጌት ያደርጋሉ።

ወጣቶቹ ይሄን ካላደረጉ ምናልባትም ኢ-ሰብአዊ ቅጣት ሊፈጸምባቸው ይችላል።

⚫️ በጎ አድራጎት ⚫️

የውሸት ማንነት ፎቶ ተጠቅመው አካውንት ከፍተው (ሴትን በወንድ ወንድ ደግሞ በሴት ማንነት) አንድ ታርጌት ያደረጉትን ሰው ረጅም ጊዜ ያናግሩ እና ለእርዳታ / ለእርዳታ ድርጅታቸው ገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ያሳምኗቸኣል።

እነዛ ሰዎች ላይ እምነት የጣሉባቸው ተጨበርባሪዎች በሀዘን ተሰብረው ገንዘባቸውን ይልካሉ። ቀልጦ ይቀራል። ብሎክ ይደረጋሉ።

🟡 ባለሃብት መምሰል 🟡

የውሸት ማንነት በመፍጠር ፣ ፎቶዎችን በመጠቀም በኦንላይን ሰው ያናግራሉ።

እንዲታመኑ ረጅም ጊዜ ሊወስዱም ይችላሉ።

ሰዎቹ ካመኗቸው በኃላ ገንዘባቸውን በጋራ አፍስሰው ስለሚሰሯቸው ስራዎች በማናገር ገንዘብ ያስልካሉ። ከዛማ ቀልጦ ይቀራል። ብሎክ ያደረጋሉ !

🟤 ደንበኞችን ማነጋገር 🟤

ይህም በተመሳሳይ በሀሰተኛ ማንነትና ስራ ከተለያዩ ሰዎች እያነጋገሩ በማጭበርበር ገንዘብ መቀበል ነው።

ለምሳሌ ፦ እቃ የሚሸጡ አስመስለው ብር ካስላኩ በኋላ የውሃ ሽታ ሆነው ይቀራሉ።

🔵 ' ኮሜንት/ሬት በማድረግ ገንዘብ አግኙ ' 🔵

እነዚ አጭበርባሪዎቹ የውሸት ማንነት ተጠቅመው በቴሌግራም ፣ ዋትስአፕ ወይም በሌላ መንገድ ተጠቅመው የሚያጭበረብሩትን ሰው ማናገር ይጀምራሉ።

" ጎግል ላይ ግቡና ስለዚህ ድርጅት ጥሩ አስተያየት ጻፉ ይከፈላችኋል " ይላቸዋል።

ከዛም የመጀመሪያውን ክፍያ በመፈጸም እምነት ያሳድራሉ።

" ይሄን ያህል ብር ከላካችሁ ይሄን ያህል ታገኛላቹ " በማለት የሰዎቹን ማንነት ይገመግማሉ። እስከዛ ድረስ ግን ገንዘብ መላካቸውን አያቆሙም።

የሚጭበረበረው ሰው ብዙ ብር ካስላኩት በኋላ የውሃ ሽታ ይሆናሉ።


በተጨማሪም ...

እንደ ፖሊስ፣ደህንነት፣ ባንክ ሰራተኛ ፣ እንደ ድርጅት ኃላፊ ሆነው የሚያስመስሉ አጭበርባሪዎችም አሉ።

ስራውን የሚሰሩት ሰዎችም ተጠቂዎች ናቸው።

ስራውን ካልሰሩ አሰቃቂ ጥቃት ሊደርስባቸው ይችላል።

እንደ ባሪያ ለረጅም ሰአትም ያሰሯቸዋል።

እንደ ቅርብ ጊዜ ሪፖርት ፥ በማይናማር፣ ካምቦዲያ፣ ላኦስ፣ ቻይና በመሳሰሉ ሀገራት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች በኦንላይ ማጭበርበር ላይ ተሰማርተዋል።

ስራዎቹንም የሚያሰሯቸው ሰዎች እጃቸው በጣም ረጅም ነው።

#TikvahEthiopia
#CyberScam

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ቀረጥ_ነጻ

ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ ከተጣለው የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን ገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ አውጥቷል።

ይኸው መመሪያ " መመሪያ ቁጥር 1023/2017 " ይሰኛል።

በዚህ መመሪያ መሰረት ፥ ለህብረተሰቡ በነጻ የሚሰጡ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እንዲሁም በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ለመርዳት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች የማህበራዊ ልማት ቀረጥ የተጣለበትን አላማ ለማሳካት የሚያግዙ በመሆኑ ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል።

ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የተደረጉ እቃዎች ?

የሚከተሉት እቃዎች ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ሆነው ወደ ሀገር ይገባሉ፡፡

1. ለሚከተሉት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች :-

ሀ/ በመንግስት ባለቤትነት ስር ያሉ ወይም ለህብረሰሰቡ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ :

- የትምህርት ተቋማት፣
- የጤና ተቋማት፣
- የሕጻናት፤ የሴቶች፤ የአረጋውያን፣ የአእምሮ ህመምተኞች እና የአካል ጉዳተኞች መርጃ ድርጅቶች

ለ/ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚሰጡ ድርጅቶች ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች

2. ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ሆነው ወደአገር እንዲገቡ የተፈቀደ እቃዎች።

3. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ተቋሞች፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት እና ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሕግ በተፈቀደው መሰረት ወደ አገር የሚያስገቧቸዉ የመከላከያ እና የህዝብ ደህንነት መሳሪያዎች፣ ለነዚሁ አገልግሎት የሚዉሉ ክፍሎችና እና አክሰሰሪዎች፡፡

4. በብሔራዊ ባንክ ወደ ሀገር የሚገቡ ሳንቲሞች፣ የገንዘብ ኖቶች እንዲሁም የብርና የወርቅ ጠገራዎች፡፡

ከቀረጥ ነፃ #የማይሆኑ እቃዎች ምንድናቸው ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎች ከማህበራዊ ቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ
#አይችሉም

ሀ/ ከ8 መቀመጫ በታች ያላቸው አውቶሞቢሎች  እና የእነዚህ መለዋወጫዎች።

ለ/ ባለአንድ ወይም ባለሁለት ጋቢና ፒካፕ ተሽከርካሪዎች እና የእነዚህ መለዋወጫዎች።

ሐ/ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችና መሣሪያዎች።


በዚህ መመሪያ መሰረት ከቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ የሚችሉ እቃዎች ማስረጃዎች ማቅረብ የግድ ይላል።

ምን አይነት ማስረጃዎች መቅረብ አለባቸው ?

1. እቃዎቹ በእርዳታ የተገኙ መሆኑን የሚያረጋግጥ የእርዳታ የምስክር ወረቀት።

2. የእቃዎቹን ዝርዝር እና ዋጋ የሚያሳይ ኢንቮይስ፣

3. እቃዎቹ ለተገለጸው አላማ የሚውሉ መሆኑን እንዲሁም ስለእቃዎቹ አጠቃቃም ለገንዘብ ሚኒስቴር እና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሪፖርት የሚቀርብ መሆኑ የሚያረጋግጥ አግባብ ባለው ከመንግስት መስሪያ ቤት የተጻፈ የድጋፍ ድብዳቤ።

#TikvahEthiopia #MinistryofFiance

@tikvahethiopia
ቤንዚን ?

በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል።

ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል።

በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው።

በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።

በሜትር ታክሲ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ዜጎችም ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት ተቸግረዋል። ቀናቸውን ሁሉ በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ናቸው።

በክልል ከተሞችም የቤንዚን ነገር ብሶበታል።

ቀድሞውንም ቤንዚን በማደያ እንደልብ በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የማይቻልባቸው የክልል ከተሞች አሁንም ችግሩ እንዳለ ነው።

በክልል ከተሞች አሽከርካሪዎች ቤንዚን በማደያ " የለም " የሚባሉ ሲሆን በጀርባ ግን በየቦታው በህገወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸበቸብ ይታያል።

ይህ ህዝብን እያማረረ ያለው የጥቁር ገበያ የነዳጅ ሰንሰለት መቼ እንደሚበጠስ አይታወቅም። ከዚህ ጀርባ እጃቸው የረዘመ አካላት መኖራቸውን ግን አሽከርካሪዎች ይናገራሉ።

ቤንዚን በክልል ከተሞች ከማደያ ውጭ በእጥፍ ዋጋ ነው የሚቸበቸበው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DV2026 የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከነገ ጀምሮ ክፍት ይደረጋል። ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አዘጋጅታለች። ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም። አሜሪካ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አማካኝነት እንደምትቀበል ይታወቃል። በነገው ዕለት ዝርዝር መረጃ የምንልክላችሁ…
#DV2026

የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት ተደርጓል።

ለ2026 DV ለማመልከት https://dvprogram.state.gov/ ይጠቀሙ።

ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።

ማመልከቻው እስከ ህዳር 5 /2024 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ከፍተኛ የመሙላት ፍላጎቶች ድረገጹ ላይ መዘግየቶችን ሊያስከትል ስለሚችል ለመሙላት እስከ የምዝገባው ጊዜ የመጨረሻ ሳምንት ድረስ ባይጠብቁ ይመከራል።

ዘግይተው የሚገቡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

ህጉ ለአንድ ሰው አንድ ጊዜ ብቻ እንዲያመለክት ነው የሚፈቅደው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የሚጠቀመው የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ደጋግሞ የሚገቡ ማመልከቻዎችን የሚለይ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ አንድ ሰው ካመለከተ ሁሉንም የዛን ሰዎች ማመልከቻዎች ይሰርዛል።

ያልተሟላ ማመልከቻም ተቀባይነት የለውም።

ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ከቪዛ አማካሪዎች ፣ ' እንሞላለን ' ከሚሉ ወኪሎችና ከሌሎች አካላት እገዛ ሳይጠይቁ ራስዎ እንዲሞሉ ይመከራል።

ማመልከቻውን እንዲሞላሎት የሰው እርዳታ ካስፈለገ ጥያቄዎችን በትክክል ለመመለስ በሚሞላበት ስፍራ መገኘት ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪም የ ' ልዩ ማረጋገጫ ቁጥሩ ' ን ለመያዝ በስፍራው መገኝት ያስፈልጋል።

አንዳንድ የሚሞሉ ሰዎች ይህን ቁጥር ይዘው በመቀየር ተጨማሪ ብር የሚጠይቁ ስላሉ እንዳይታለሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

የማረጋገጫ ቁጥሩ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ በጥንቃቄ መያዝ አለበት።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራት ሁሉ የሚጠቃልል ነው።

ኢትዮጵያውያንም ለማመልከት ብቁ ናቸው።

አሜሪካ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አማካኝነት እንደምትቀበል ይታወቃል።

🇺🇸 ለአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ 2026 ለማመልከት ይህንን dvprogram.state.gov ሊንክ ይጠቀሙ !🇺🇸

(ተጨማሪ ማብራሪያ እና እንዴት መሙላት እንደሚቻል የሚገልጽ መመሪያ በቀጣይ እናያይዛለን)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለአንድ ዓመት ሞከርኩት " ዛሬ በይፋዊ የፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የX ገጽ ላይ የወጣው ፅሁፍ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ፅሁፉ " እነ ጥላሁን ገሠሠ : ቴዲ አፍሮ : አሊ ቢራ : ማህሙድ አህመድ ... ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው " ይላል። ቀጥል አድርጎ ፥ " ' የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው : መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው ' ማህሙድ ' ዝምታ ነው መልሴ'…
#ኢትዮጵያ

ዛሬ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ትልቅ መነጋገሪያ የሆነው በፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ X ኦፊሻል ገጽ ላይ የሰፈረው ፅሁፍ ነው።

ፅሁፉ ላይ የማህሙድን ዘፈን ' ዝምታ ነው መልሴ 'ን በማንሳት " የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው: መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው " የሚለው ግጥም ተጋርቷል። መጨረሻ ላይ " ለአንድ አመት ሞከርኩ " የሚልም ሰፍሯል።

ፅሁፉ ስለምን ጉዳይ እንደሆነ ፤ ለምንስ ይህንን ግጥም ነጥሎ እንደተጻፈ በግልጽ የሚያብራራው ነገር የለም።

ያም ሆኖ ግን ፅሁፉን ላይ በርካቶች የየራሳቸውን አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ።

አንዳንዶች ፤ " አሁን ባለው ስርዓት በከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቀው ነው እየሰሩ ያሉት ፤ በተለያዩ ጉዳዮች አለመግባባት ውስጥም እንደነበሩ ብዙ ጊዜ በሚዲያ ይሰማ ነበር ፤ ለመናገር እንኳን እድል የላቸውም ፤ ባገኙት አጋጣሚ ግን በገደምዳሜው ስሜታቸውን ስለ ሀገራቸው ይናገሩ ነበር ፤ አሁንም ቦታውን ሲለቁ ስለዚህ ስርዓት ብዙ የሚናገሩት ይኖር ይሆናል " የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

አንዳንዶች፤ " በዚህ ልክ ትልቅ የስልጣን እርከን ይዘው ህዝብን ግራ የሚያጋባ ድፍንፍን ያለ ፅሁፍ በገጻቸው መጋራቱ ሳያንስ እውነትም እሳቸው መሆናቸውን በግልጽ አለማብራራታቸው ትክክል አይደለም ፤ ችግር ካለም እውነታውን ለህዝብ ማሳወቅ አለባቸው እንዲህ የዘፈን ግጥም ከሚያስቀምጡ " ብለዋል።

ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ " የ6 ዓመት የስልጣን ዘመናቸው ሲያበቃ ይህን አይነት ነገር በገጻቸው መፃፋቸው የህዝብ ተቀባይነት ለማግኘት ነው እስከዛሬ በሀገሪቱ ብዙ ነገር ብዙ ግፍ ሲፈጠር ባላየ ሲያልፉ ነበር ፤ አንዳንዱን ደግሞ እየመረጡ ሲናገሩ ነበር ፤ ለምን አሁን ? በዚህ ስልጣን እንደማይቀጥሉ ስለሚያውቁ ነው ፤ ስልጣንም መልቀቅ ከነበረባቸው ቀድሞ ተናግሮ እንጂ አሁን ላይ ይህን አጀንዳ ለህዝብ መስጠት ትክክል አይደለም ፤ ጊዜያቸው አብቅቷል ይሰናበታሉ ፤ እሱንም ስለሚያውቁ ነው " ሲሉ ፅፈዋል።

በኢትዮጵያ የፕሬዜዳንት ስልጣን ዘመን 6 ዓመት ሲሆን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ወደ ስልጣን የመጡት ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ/ም ላይ ነበር።

ሌሎች ደግሞ " እንዲያው በደፈናው ድምዳሜ ላይ ከመድረስ የእሳቸውን ሙሉ ሀሳብ በትዕግስት ጠብቆ መስማት ይገባል " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ግን ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬዝዳንትነት የስልጣን ድርሻው ምንድነው ? ፕሬዝዳንት የሚኮነው እንዴት ነው ? ምን ምን ይሰራል በዝርዝር ? ሲሉ የጠየቁ አሉ።

ለዚህ ምላሽ ይሆን ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህገ መንግስቱ ስለ ፕሬዜዳንቱ የሚለውን ከዚህ በታች አቅርቧል።

የኢፌዲሪ ህገ መንግስት ስለ ሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ስልጣንና ተግባር ምን ይላል ?

(የኢፌዴሪ ህገ መንግስት)

ምዕራፍ ሰባት
ስለ ሪፐብሊኩ ኘሬዚዳንት
አንቀጽ 69
ስለ ኘሬዚዳንቱ

ኘሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔር ነው፡፡

አንቀጽ 70
የፕሬዜዳንቱ አሰያየም
1. ለፕሬዜዳንትነት ዕጩ የማቅረብ ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።
2. የቀረበው ዕጩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ከተደገፈ ፕሬዜዳንት ይሆናል።
3. የምክር ቤት አባል ፕሬዜዳንት ሆኖ ከተመረጠ የተወከለበትን ምክር ቤት ወንበር ይለቃል።
4. የፕሬዜዳንቱ የሥራ ዘመን 6 ዓመት ነው። አንድ ሰው ከሁለት ጊዜ በላይ ለፕሬዜዳንትነት ሊመረጥ አይችልም።

አንቀጽ 71
የኘሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባር
1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰበባ ይከፍታል፡፡
2. በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቃቸው ሕጐችና ዓለምአቀፍ ስምምነቶች በነጋሪት ጋዜጣ ያውጀል፡፡
3. ሀገሪቷን በውጭ ሀገሮች የሚወክሉትን አምባሳደሮችና ሌሎች መልክተኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ይሾማል፡፡
4. የውጭ ሀገር አምሳደሮችንና የልዩ መልዕክተኞችን የሹመት ደብዳቤ ይቀበላል፡፡
5. በሕግ መሰረት ኒሻኖች እና ሽልማቶችን ይሰጣል፡፡
6. በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕግ በተወሰነው መሰረት ከፍተኛ የውትድርና ማዕረጐችን ይሰጣል፡፡
7. በሕግ መሰረት ይቅርታ ያደርጋል፡፡

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
🔈 #የዜጎችድምጽ

" ስራ መስራት ... ቤተሰብ ማስተዳደር አልተቻለም ! " - አሽከርካሪዎች

በክልል ከተሞች የሚታየው ቤንዚን የማግኘት ፈተና አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ስራ ሰርቶ መግባትና ቤተሰብ ማስተዳደር ፈተና ከሆነባቸው ቢቆይም አሁን ላይ ሁኔታው ይበልጥ እየከበዳቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

" ቤንዚን እንደልብ ማግኘት ከቆም በርካታ ወራት አልፈዋል " የሚሉት መልዕክታቸውን የላኩ ዜጎች " ልጆቻችንን ለማስተዳደር፣ እኛም በልተን ለማደር ስንል አንድ ሊትር  ቤንዚን ከ120 ብር በላይ ስንገዛ ከርመናል አሁን ጭራሽ ቤንዚን ጨመሯል ተብሎ እሱም ጠፍቷል ፤ ሲገኝ ደግሞ ብሩ ጨምሯል " ብለዋል።

ባሉበት አካባቢ ማደያዎች ቢኖሩም ቤንዚን እንዲሁ መቅዳት ቅንጦት ከሆነ መቆየቱን ተናግረዋል።

" 1 ቀን መስራት 1 ቀን ደግሞ ሰልፍ ተሰልፎ መዋል ነው ፤ እንዲህ እየሆንን እንዴት ነው ይህንን ከዕለት ወደ ዕለት እየናረ ያለውን ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መቋቋም የምንችለው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" ልጆቻችንን የምናሳድገው ፤ ከሰው እንዳያንሱ ጥሩ ትምህርት እንዲማሩ የምንለፋው መስእዋትነት የምንከፍለው በዚሁ ባለችን ስራ ነው ይሄን ለመስራት ፈተና ከሆነ ምን ተስፋ ይኖረናል ? እንደው ግራ ተጋብተናል " ብለዋል።

የሞተር አሽከርካሪዎችም የስራና የተለያዩ የግል ጉዳዮች ለሚፈጽሙበት የሞተር ሳይክል እንኳን የሚሆን ቤንዚን ለማግኘት በብዙ ይሰቃያሉ።

ቤንዚን በሰልፍ በሚኖርበት ወቅት ከጥበቃ እስከ ቀጂ ድረስ በመመሳጠር ሰው በፀሀይ ተንገላቶ ተሰልፎ እያለ ካለሰልፍ የሚያስቀዱት ብዙ ነው ፤ ከዚህ ሲያልፍም ለህገወጥ ሽያጭ የሚያውሉ ሰዎችን ደጋግመው እንዲቀዱ በማድረግ የችግሩ አካል ሲሆኑም ይታያል።

በክልል ከተሞች ቤንዚን እንደልብ አይገኝም ፤ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ማግኘቱ ቅጦት ወደመሆን ተሸጋግሯል።

በየከተማው እንደ አሸን የፈሉት ማደያዎች ሲጠየቁ " ቤንዚን የለም ፤ ካለም አገልግሎት የምንሰጠው በፈረቃ ነው "  የሚል መልስ ነው የሚመልሱት።

ከጥዋት 2:30 በፊት አይከፈይም ፤ ከምሽት 12:00 በኃላ ደግሞ የቤንዚን ሽያጭ ጥርቅም ተደርጎ ይዘጋል።

ማደያዎች 24 ሰዓት መስራት ቢጠበቅባቸውም ፤ እንኳን 24 ሰዓት ሊሰሩ ቀኑን እንኳን " ቤንዚን የለም " የሚል ምንም ምክንያቱ የማይገለጽ ምላሽ በመስጠት ነው የሚውሉት።

ይህ ሁሉ ሆኖ ግን በህገወጥ መልኩ ቤንዚን በየቦታው በውሃ መያዣ ፕላስቲኮች ልክ እንደ ህጋዊ ነገር ከእጥፍ በላይ በሆነ ዋጋ ሲቸበቸብ ይታያል። ያውም በየቦታው በየስርቻው።

በአንዳንድ ቦታዎች ማደያዎች በጥቅም ለተሳሰሯቸው አካላት በምሽት በህገወጥ መንገድ ቤንዚን በበርሜል እንደሚሸጡ ይነገራል።

ማደያ ሲጠየቅ " የለም " የሚባለው ቤንዚን በጥቁር ገበያ በህገወጥ መንገድ በየመንደሩ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ዋጋ ነው የሚሸጠው።

ከዋናዎቹ አካላት በአቅርቦት ጉዳይ ላይ ምንም ችግር እንደሌለ በተደጋጋሚ ይነሳል ፤ ነገር ግን ክልል ከተሞች ላይ ቤንዚን ማግኘት ፈተና እንደሆነ ይኸው አመታት አልፏል። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ መዘዙ ብዙ ሊሆንም ይችላል።

° እንዴት ይሄን ሁሉ ጊዜ ዜጋው ሲቸገር ዝም ተብሎ ታየ ?
° እንዴት ይሄን ሁሉ ጊዜ መፍትሄ አይገኝም ?
° በክልል ከተሞች ያለው ህገወጥ የቤንዚን ሽያጭና ስርጭት ሰንሰለት የሚቆረጠው መቼ ነው ?
° በሀገር ደረጃ የሚገባ መጠን ላይ ችግር ከሌለ ለሚታየው ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂ ማን ነው ?  የሚሉ ጥያቄዎች መልስ ይሻሉ።

ከክልል ከተሞች ውጭ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ቤንዚን አንዳንድ ወቅቶች ላይ ካልሆነ በስተቀር በከተማው ባሉ ማደያዎች በቀንም በማታም ይገኛል።

የክልሎቹ ግን ልዩ ነው ማደያ ውስጥ የለም ፤ በየስርቻው በችርቻሮ እንደጉድ ይቸበቸባል።

በአሁን ሰዓት በማደያዎች የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ 91 ብር ከ14 ሳንቲም ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ። የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል። የመቁረጫ ነጥቡ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል። @tikvahethiopia
የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 እና ከዚያ በታች፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 137 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 142 እና ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 179 እና ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 167 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 170 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤

⬇️

የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 140 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 136 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 172 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 164 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 165 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 160 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤


#TikvahEthiopia🇪🇹

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የ5 ሚኒስትሮችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጸድቋል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመት እንፀድቅላቸው በደብዳቤ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው ሹመቱ በምክር ቤቱ እንዲጸድቅ የተደረገው። ሹመታቸው የፀደቀው ፦ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዎስ(ዶ/ር)፣…
#HoP

" የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታችን (immunity) ሳይነሳ እንደ ሽፍታ ተጎትተን ስንታሰርና ለወራት ስንቀመጥ ምን ሰሩ ? " - ደሰለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዬስ (ዶ/ር) ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ሰነዘሩ።

የቀድሞው የፍትህ ሚኒስትር አሁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ላይ ጥያቄ አንስተዋል።

" የፍትህ ዘርፉን ከፍተኛ ችግር ውስጥ የከተቱ ስለሆኑ ትራክሪከርዳቸው የውጭ ጉዳይን ለመምራት ብቁ ሊያደርጋቸው አይገባም " ብለዋል።

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፥ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ዶ/ር ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ሲመጡ ከፍተኛ ተስፋ አድርገው እንደነበር ጠቁመዋል።

ነገር ግን ከሳቸው በፊት ከነበሩት ሚኒስትሮች ምን የተለየ ነገር አሳኩ ? ሲሉ ጠይቀዋል።

በህግ ከውጭ ዩኒቨርሲቲ ፒኤችዲ ይዘው መምጣታቸውና እዚህም ትልቁ የሀገራችን ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማስተማራቸው ላይ ምን ለውጥ አመጡ የሚለው አልተገመገመም ብለዋል።

በፍትህ ሚኒስትርነት ያላቸው ትራክሪከርድ / የሰሯቸው ስራዎች ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ብቁ ያደርጋቸዋል የሚለውም አልተገመገመም ሲሉ ተናግረዋል።

" እኔ በግሌ ቅሬታ አለኝ " ያሉት ደሳለኝ (ዶ/ር) " በፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን የእውቀት ችግር አለባቸው ብዬ አይደለም ፤ በተለያዩ መድረኮች አይቻቸዋለሁ ሞያቸውን በጣም ጠንቅቀው ያውቃሉ ፤ ነገር ግን አፈጻጸማቸውን ካየነው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ሲጠይቅ የነበረውን የፍትህ ጥማት ከማስታገስና ያን ከማርካት ይልቅ አሁንም የፍትህ ስርዓቱ የፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን አድርገዋል " የሚል ወቀሳ አቅርበዋል።

" በሀገራችን በተለይ በኢህአዴግ ዘመን የፍትህ ስርዓቱ ተቃዋሚዎችን ማጥቂያ፣ የፖለቲካ መሳሪያ፣ የገዢው ፓርቲ አንድ አርም ተደርጎ ሲሰራ ነበር አሁንም ያ ተቀይሯል ብዬ አላስብም " ብለዋል።

" የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታችን (immunity) ሳይነሳ እንደ ሽፍታ ተጎትተን ስንታሰርና ለወራት ስንቀመጥ ሌሎች የምክር ቤት አባላት የፌዴሬሽን ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተገቢ ፍትህ ሳያገኙ ለአመታት ሲንገላቱ የፍትህ ሚኒስትር ምንም የሰራው ነገር የለም። ከሳሹ እራሱ የፍትህ ሚኒስትር ነው። " ሲሉ ተናግረዋል።

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) " እንደኔ እንደኔ ዶክተር ጌዲዮን የእውቀት ችግር የለባቸው ግን የፍትህ ሚኒስትር ላይ ያላቸው ትራክሪከርድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሀገሪቱን ለመምራት የሚያስችላቸው አይደለም። የፍትህ ዘርፉን ከፍተኛ ችግር ውስጥ የከተቱ ስለሆነ ለዛ ቦታ ሊቀርቡ አይገባቸውም " ብለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ጉዳይ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት ማብራሪያ ሰጥቷል። ቢሮው እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከአውድ ውጪ በተተረጎመ መንገድ እንደሆነ ጠቁሟል። " የ1997 የጋራ መኖርያ ቤት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው የተሳሳተ መረጃ ትክክል ባልሆነ መልኩ  ከአውድ ውጪ ተተርጉሞ…
List of Names.pdf
4.8 MB
" የተሰጠው ማብራሪያ ከእውነት የራቀ ነው " - የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች

ሰሞኑን ከ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ወይም ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ዝርዝር ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህም ማብራሪያው ፥ " ብቁና ንቁ የነበሩ የ1997 ተመዝጋቢዎች  በ14ኛው ዙር ዕጣ ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል " ነበር ያለው።

ዝርዝር ማብራሪያው በዚህም ይገኛል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/91710?single

ማብራሪያውን የተመለከቱ ቆጣቢዎች ግን ማብራሪያ " ከእውነት የራቀ ነው " ሲሉ ግብረ መልስ ሰጥተዋል።

" እኛ የ1997 ነባር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት አክቲቭ ተመዝጋቢዎች ሰሞኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሰጠው መግለጫ ከእውነታ የራቀ ነው ስንል አንገልፃለን " ብለዋል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት።

" እኛ የ1997 አክቲቭ ቆጣቢዎች የሆንን በ14ኛው ዙር 25 ሺህ ለእጣው አክቲቭ ናቸው ተብለን ለ18,650  ቤቶች ተወዳድረን እጣው ያልወጣልን ወደ 8,000 የምንሆን የተረፍን አክቲቭ ቆጣቢዎች መሆናችን ቢሮው በደንብ ያውቃል ሰነዳችንም በግልፅ በቤቶች ኤጀንሲም ሆነ በንግድ ባንክ አለ " ብለዋል።

" ቢሮው ' ብቁ እና ንቁ የነበሩ የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች በ14ኛው ዙር ዕጣ ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል ' ማለቱ እጅግ ግራ የሚያጋባ ነው የሆነብን " ሲሉም አክለዋል።

አሉን ያሏቸውን ዶክመንቶችንም የላኩ ሲሆን ከላይ ተያይዟል።

ጉዳያቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም እንደያዘው አስታውሰው ተቋሙ መፍትሄ እስኪያገኙ ድረስ እንዲገፋበት ጥሪ አቅርበዋል።

ዜጎቹ " አሁንም ድምፃችን ይሰማ ፤ መፍትሄ ይሰጠን " ሲሉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia