TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AAU #GAT
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መስከረም 3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡
በተቋሙ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 1/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡
Via @tikvahuniversity

ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት እና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት የፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ የቀብር ስንስርዓት እሁድ ጷጉሜን 3/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን ይፈፀማል።
በዕለቱ ከጠዋቱ 4:00-6:00 ሰዓት ባስተማሩበትና በሰሩበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ራስ መኰንን አዳራሽ የስንበት ስነ-ስርዓትም የሚከናወን ይሆናል።
#AAU
@tikvahethiopia
በዕለቱ ከጠዋቱ 4:00-6:00 ሰዓት ባስተማሩበትና በሰሩበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ራስ መኰንን አዳራሽ የስንበት ስነ-ስርዓትም የሚከናወን ይሆናል።
#AAU
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የመመዝገቢያ ቀናት ከጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም - መስከረም 8/2017 ዓ.ም ድረስ ነው " - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንጋፋዉ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ /ም ለቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች ለመቀበል መዘጋጀቱን አሳውቆናል። ዩኒቨርሲቲው ለ2017 ቅድመ ምረቃ ትምህርት በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል ከፍለዉ ለሚማሩ እንዲሁም በማታ በተከታታይ መርሃ ግብር…
#AAU
ራስ ገዙ አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል በመጀመሪያ ዲግሪ በ2017 ዓ/ም መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ያቀረበው ጥሪ ነገ ያበቃል።
በ2017 ዓ/ም በቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሃ ግብር በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምደባ እንደማይኖር ይታወቃል።
በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍለው በዩኒቨርሲቲው መማር ለሚፈልጉ በሙሉ የአ.አ.ዩ የሚያወጣውን የመግቢያ ፈተና (UAT) እንዲሁም ሌሎች መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲው ድረ ገጾች ፦
➡️ www.aau.edu.et
➡️ https://portal.aau.edu.et ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ ይችላሉ።
የመመዝገቢያ ቀኑ ነገ መስከረም 8/ 2017 ዓ.ም ያበቃል።
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ወደፊት ይገለጻል።
በመንግስት ስኮላርሽፕ ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመማር የሚያያዘው ማስረጃ ምንድነው ?
በቀን መደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለማመልከት ከተጠየቁት መስፈርቶች አንዱ የቤተሰብ የገቢ መጠንን የሚገልፅ ማስረጃ ማያያዝ ነው።
በዚህ መሰረት ፦
1. ከወረዳ/ቀበሌ ወይም መስሪያ ቤት ስለገቢያቸዉ ዝቅተኛነት የሚገልፅ ማስረጃ ከሚመለከተዉ ከወረዳ ወይም ቀበሌ ወይም መስሪያ ቤት ዘርፍ ኃላፊ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የቤተሰቡ ኃላፊ ጡረታ ላይ የሚገኙ መሆናቸዉን የሚገልፅ ደብዳቤ ወይም የታደሰ የጡረተኝነት መታወቂያ ወይም የባንክ ደብተር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
https://t.iss.one/TikvahUniversity/12317
(Addis Ababa University)

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎች በውድድር ነጻ የትምህርት እድል (ሶኮላርሺፕ) ሊሰጥ እንደሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን የመጀመርያው ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን ተወስኖ ተማሪዎችን በራሱ የቅበላ ስርዓት ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ እያከናወነ ነው።
ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ያዘጋጀውን የተማሪዎች መግቢያ ፈተና ይሰጣል። በዚህም ብቃትን፣ ብዝሃነትንና ፍትሐዊነትን ማዕከል አድርጎ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ገልጿል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎችን በውድድር ነፃ የትምህርት እድል ከዶርሚታሪና የካፌ አገልግሎት ጋር እንደሚሰጥ አሳውቋል።
አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ " ብቃትና ተሰጥዖ ያላቸው ተማሪዎች መዳረሻ ለመሆን ያለኝን ቁርጠኝነት እገልጻለሁ " ብሏል።

ተማሪዎች እስከ መቼ ማመልከት ይችላሉ ? የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው መረጃ የማመልከቻው ቀን ከዚህ ቀደም በነበረው ማስታወቂያ ዛሬ መስከረም 08/2017 እንደሚያበቃ ቢገለጽም እስከ ነገ መስከረም 09/2017 ድረስ መራዘሙን አስታውቋል። በዚህም በዩኒቨርሲቲው ድረ ገጾች ፦ ➡️ www.aau.edu.et ➡️ https://portal.aau.edu.et ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር…
#AAU
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ተማሪዎችን ለማስተማር በራሱ መስፈርት አወዳድሮ እንደሚቀበል የምልመላ ፖሊሲ መዘርጋቱን ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል፡፡
ለማስተማር የተቀባላቸውን ተማሪዎች በተመለከተም ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚደንት ዩኒቨርሲቲ ጀይል ዑመር (ዶ/ር) ፣ “ ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃም ሆነ በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የሚከታተሉትን ብቃትና አቅም ለመመልመል የሚያስችል የቅበላ ፖሊሲ በማዘጋጀት ምልመላውን አዘጋጂቷል ” ብለዋል፡፡
“ ለምልመላው ትልቁ መስፈርት በሀገራችን ለቅድመ መረቃ ፕሮግራሞች በአገሪቷ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችል ውጤት ያላቸው ተማሪዎች እንዲወዳደሩ ነው የተደረገው ” ነው ያሉት፡፡
ለምልመላው በጥቅሉ፣ ዩኒቨርሲቲው የሰጠው የአድሚሽን ፈተና ከ50 ፐርሰንት፣ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤት ከ50 ፐርሰንት መያዙ ተነግሯል፡፡
“ በዚህ ዓመት ለከፍተኛ ትምህርት ብቁ ናቸው ተብለው ትምህርት ሚኒስቴር ካረጋገጠላቸው መካካል 11 ሺሕ 939 ተማሪዎች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመመረጥ ለፈተና ቀርበዋል፡፡ የቅበላ ፈተናው የሚለካው ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲው ቢገቡ ያለ ምንም እንከን የቅድሞ ምረቃውን ፕሮግራም ዝግጁነት ኑሯቸው የሚችሉ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የክሪቲካል ቲንኪንግ፣ የቋንቋ ዝግጁነትን፣ የስሌት ብቃቶችን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ጉዳዮችን የቅበላ ፈተናው ማካተቱንም ገልጸዋል፡፡
“ ከ11 ሺሕ 939 ለፈተናው የተቀመጡትን ስናይ፣ በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመጀመሪያው ነው፡፡ የፍሬሽማን ፕሮግራም ዘርፍ አለው፡፡ በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ ተብሎ ይከፈላል ” ነው ያሉት።
“ በተፈጥሮ ሳይንስ ያመለከቱትና ለፈተና የተቀመጡት 7,589 ሲሆኑ፣ በሶሻል ሳይንስ ደግሞ 4,350 ተማሪዎች ናቸው ” ነው የተባለው።
በዚህም በመንግስት ስኮላርሽፕ የሚማሩት 4,402፣ በራሳቸው ከፍለው የሚማሩት ደግሞ 7,537 ተማሪዎች ለፈተና እንደተቀመጡ ተገልጿል፡፡
በዬፕሮግራሞቹ የማስተናገድ አቅምም አንዱ ታሳቢ የሆነ መስፈርት እንደሆነ የገለጸው ዩኒቨርሲቲው፣ “ በዚህ ስሌት በመንግስት ስፖንሰርነት የተመለመሉት 2,660፣ በግል አመልካችነት (ከፍሎ ለመማር) 2,640፣ በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም 5300 ተማሪዎችን ቅበላ አድርጓል ” ነው ያሉት፡፡
በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ተመዝግበው ትምህርትቸውን እንደሚቀጥሉም ተመላክቷል፡፡
በተለይ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መጥተው ለመማር የሚፈልጉ ከመሆናቸው አንጻር ዩኒቨርሲቲው ምልመላውን በምን መልኩ እንደዳሰሰው ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ፣ “ ከየትኛውም የአገሪቷ ኮርነር ላሉት እድሉ ተሰጥቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በዚህ በኩል ነፍጓል የምንለው ነገር የለም ” ብሏል፡፡
ክፍያው ስንት እንደሆነ ከጋዜጠኞች ለቀረበው ጥያቄም፣ ክፍያው የተለያዬ እንደሆነ፣ መንግስት ስፖንሰር ያደረጋቸው የምግብ፣ የመኝታ፣ የትምህርታና ሌሎች ወጪዎው በመንግስት እንደሚሸፈኑ ዪኒቨርሲቲው ምላሽ ሰጥቶበታል፡፡
“ ከፍለው የሚማሩ ደግሞ ምግብም፣ መኝታ ቤትም ያስፈልገኛል ለሚል ኮስት ያደርጋል፡፡ የትምህርት ወጪ የምንለው ስሌቱ በኢሲቲኤስ ነው፡፡
እንደዬየፕሮግራሞቹ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ዝቅተኛ በአንድ ኢሲቲኤስ 600 ብር፣ በኢሲቲኤስ ከፍተኛው እስከ 2000 ብር የሚሄድ ነው ” ብሏል፡፡
#TikvahEthiopiaFamilyAA