TIKVAH-ETHIOPIA
ነዳጅ (ቤንዚን) በክልሎች ላይ ችግር ከሆነ እጅግ በርካታ ጊዜያት ያስቆጠረ ነው።
ከአዲስ አበባ ውጭ ነዳጅ እንደልብ ማግኘት አዳጋች ነው።
ለተለያዩ ጉዞ ወደ ክልሎች የሚወጡ መንገደኞች ይህንን ነገር ያውቁታል።
በአንድ በኩል ነዳጅ የለም እየተባለ በጥቁር ገበያ እስከ 150 ብር ከዛም ከፍ ብሎ ለጉድ ይቸበቸባል።
ይህንን ችግር ማስተካከል ፤ ጥቁር ገበያውን መቆጣጠር ለምን አልተቻለም ? የብዙሃን ጥያቄ ነው።
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ነዳጅ ለማግኘት ሰዓታትን መሰለፍ ግድይላቸዋል ፤ ጾማቸው ላለማደር ልጆቻቸውን ላለማስራብ የዕለት ጉርሳቸውን ይዘው ለመግባት ከማደያ ውጭ ይገዛሉ።
በየጊዜው በየማደያው " የለም " ይባላል ውጭ ላይ ለጉድ ይሸጣል። ይህ ሰንሰለት ከላይ እስከ ታች መሆኑ እሙን ነው። ዘላቂ መፍትሄ ያስፈልጋል።
ነዳጅ በአግባቡ ለተጠቃሚው እንዲደርስ ያሉት ችግሮች ተፈትሸው መታረም ግድ ይላለቸዋል።
በየጊዜው በነዳጅ ጉዳይ ዜጎች መማረር የለባቸው።
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" የማህበሩ ይዞታ አለአግባብ ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ ተሰጥቷል " - የሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች
በአዲስ አበባ ከተማ የሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ ህንጻ ቤቶች ባለቤቶች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር የነዋሪዎች ይዞታ (600 ካ/ሜ በላይ) አለአግባብ ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ እንደተሰጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳወቀ።
ጉዳዩ ፍርድ ቤት ድረስ የደረሰና ፍርድ ቤትም ውሳኔ ያሳለፈበት ነው።
ጉዳዩ ምንድነው ?
ማህበሩ ይዞታው እንደሆነ የገለጸውና በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠበት እንዲሁም በሳይት ፕላን ሳይቀር በግልጽ የማህበሩ ይዞታ መሆኑ የታወቀ መሬት ተወስዶ ለግለሰብ ተሰጥቷል።
ማህበሩ በሳይት ፕላኑ መሰረት የነዋሪዎች ይዞታውን አጥሮ የበለጠ እንዲለማና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርግ ፍቃድ አግኝቶ አልምቶት ነበር።
ልማቱ የሕጻናት ስፖርት ማዘውተሪያ መጫወቻና የመኪና መተላለፊያ እና ፓርኪንግ ውሎ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም ይህ ቦታ የተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች እንደ ደመራ ፣ ሀዘንና ሰርግ ማከናወኛ ቦታ የነበረ ነው።
ለዚህ የልማት ስራ ግምቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ከማህበሩ ወጪ ተደርጓል።
ከዚህ ባለፈ ለህበረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ የጋራ መጠቀሚያ ፣ የሕጻናት ማቆያና የስፖርት ማዘውተሪያ የእርድ አገልግሎት መፈጸሚያ በከፍተኛ ወጪ አሰርቶ ለፍቃድ ሲጠባበቅ ነበር።
ነገር ግን ያለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ከክፍለ ከተማው (ልደታ) የመሬት ልማት አስተዳደር " ታዘዘ ነው " በሚል አንዳችም ደብዳቤ ሳይዙ በቃል ብቻ በፖሊስ ኃይል በመታገዝ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ የማህበሩን ይዞታ ጥሰው በመግባት ልኬት ወስደዋል።
ከዛ በኃላም ያለ ምንም የፅሁፍም ሆነ የቃል ማስጠንቀቂያ በግልጽ የማህበሩ ይዞታ እንደሆነ እየታወቀ ኮርዲኔት ተቀይሮ ለግለሰብ መሰጠቱን ማህበሩ እንደደረሰበት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ማህበሩ ፥ በአንድ የጋራ መኖሪያ ክልል ውስጥ የሚገኙ የጋራ መጠቀሚያዎች በተለይም በ' ግሪን ኤርያ ' የተከለሉ ቦታዎችን ህብረተሰቡን ሳያማክሩ እና የከተማ ፕላንና ልማት መመሪያን ጥሶ አረንጋዴ ቦታዎችን ለግለሰብ እያነሱ መስጠት አግባብ አይደለም ሲል ወቅሷል።
ከዚህ ባለፈ ከአካባቢው የግንባታ ስታንዳርድ አንጻር ቦታውን ለግለሰብ ከመስጠት ይልቅ ለህብረተሰቡ ለልጆች መጫወቻ፣ ለእርድ ቦታ፣ ለኮሚኒቲ ፖሊሲንግ ፣ ለተለያዩ የማህበራዊ ክንዋኔዌች እንዲሁም ለመኪና ማቆምያ ቢውል የተሻለ እንደሆነ አስገንዝቧል።
ይህ የይዞታ ጉዳይ 2014 ዓ/ም ላይ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶም ነበር።
ከሰሽ ደግሞ ይዞታው የራሱ እንዳልሆነ የታወቀው አካል ሲሆን " ቦታውን ለመንጠቅ አጠሩብኝ ፤ ሁከትም ፈጥረዋል " የሚል ክስ ነው ያቀረበው።
ጉዳዩን የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲከታተለው ከቆየ በኃላ ክርክር የተነሳበት ይዞታ የከሳሽ አለመሆኑን ወስኗል።
ነገር ግን ጉዳዩ የተረሳሳ አስመስሎ በቅርቡ ቦታው ታጥሯል። ማህበሩም ለሶስተኛ ወገን እንደተሰጠ እንደደረሰበት ጠቁሟል።
መፍትሄ ፍለጋ ብዙ ቢደክምም ሰሚ አላገኘም።
(የፍርድ ቤት ሂደቱን ከታች ይቀርባል)
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" በሰው ላይ ጨዋታ ነው እንዴ የያዙት ? " - ነዋሪዎች
በአዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ' ጨፌ ሜዳ ' ነዋሪዎች በመብራት መቆራረጥ እንዲሁም ጠፍቶ እስከወዲያኛው መቅረት እጅግ በጣም ተማረዋል።
በተደጋጋሚ ቅሬታ ቢያቀርቡም መፍትሄ አላገኙም።
ነዋሪዎች ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
➡️ ከአምትና ከሁለት ዓመት በፊት እንዲሁ ይጠፋል ይቃጠላል መጥተው ይቀይራሉ ፤ የሚቀይሩት ኃይሉ የተመጣጠነ አይደለም ወዲያ ይጠፋል።
➡️ ሰው ላይ ጨዋታ ነው እንዴ የያዙት ? ለምንድነው እንዲህ የሚደረገው ? ሰራን ብለው እንደሄዱ ወዲያው ይጠፋል። እነሱ ደመወዛቸውን እየበሉ ነው ፤ እንጀራ ጋግሮ መብያ ይጠፋል እንዴ ?
➡️ ከ30 እና 40 ዓመት በፊት ስንገለገልበት በነበረበት መጠን እንድንገለገል እየተደረገ ሰው ጭለማ ውስጥ ነው ያለው።
➡️ ፍሪጅ ተበላሽቷል አይሰራም ፤ ቴሌቪዥን ተበላሽቷል ለሰራተኛ ብር እየሰጠን ነው የምናሰራው። ለፍተን ደክመን አጠራቅመን በእርጅና ጾም እንፈታበታለን ያለው ነገር ሁላ እየተበላሸብን ነው። ባለፈው ብዙ ነገር ተበላሽቶ ጥለናል።
➡️ ፍሪጅ የሚፈልግ መድሃኒት አለ ያ ሁሉ ከንቱ ቀረ ሰው ይሙት እያሉ ነው ?
➡️ ህጻናት ፣ ልጆች ፣ አቅመ ደካማ አለ ስንት ጣጣ ነው ያለው። ቤት ውስጥ ብዙ ነገር ነው ያለው። ቢደወልላቸው አይመጡ ፤ መጣን መጣን እያሉ ያሾፋሉ። ሲመጡ ደግሞ ምኑን ነክተውት እንደሚሄዱ አይታወቅም ኬላ እንኳን ሳያልፉ ወዲያው ይጠፋል።
➡️ የተቦካ እህል እየተበላሸ ነው የት ይጋገር ?
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ኃላፊ ዳይሬክተር ይሄይስ ስዩም ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ቃል ፤ ቅሬታው እውነትነት እንዳለው ገልጸዋል።
" ለፈጠርንባቸው ችግር ደንበኞቻችንን ይቅርታ ጠይቃለሁ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለት ሳምንት ሳይሞላ ወይም ከዛም ባነሰ ጊዜ መፍትሄ እንሰጣቸዋለን " ብለዋል።
#ፈረንሳይለጋሲዮን #ጨፌሜዳ
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የከንቲባዋ ቃል አሳዝኖናል " - የ97 ተመዝጋቢዎች
" የ1997 ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች 20 አመት ሙሉ የጠበቅነዉን ተስፋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ' 97 ሰጥተን ጨርሰናል ' ማለታቸዉ በጣም አሳዝኖናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ቁጠባችንን በአግባቡ እየቆጠብን የነበርን በሺዎች የምንቆጠር ዜጎች አለን " ብለዋል።
" እኛም ዜጎች ነን በኪራይ ቤት እድሜችን አለቀ " ሲሉ አክለዋል።
ነዋሪዎቹ ፥ " ለሕዝብ ዕንባ ጠበቂ ተቋም ደብዳቤ አስገብተናል አዲስ አበባ ቤቶች ኤጀንሲ ግን መልስ አልሰጣቸውም " ሲሉ አስታውሰዋል።
" ከዚህ ባለፈ የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮም መፍትሄ እንዲፈልግልን ብለን ነበር ጋር ግን ምላሽ ተነፍጎናል " ብለዋል።
" ወዴት እንደምንሄድ ጨንቆናል ፍትህ ተጓሎብናል ፤ አሁን ካለው የኑሮ ጫና አንጻር የቤት ኪራይ ትልቁ ፈተና ነው እባካችሁ መፍትሄ ፈልጉልን " ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM