TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray🚨 " የጊዚያዊ አስተዳደሩን ስልጣን ለመንጠቅ የመሞከር እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ብለን እንጠብቃለን " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንትና የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ዛሬ ነሀሴ 11/2016 ዓ.ም መገለጫ ሰጥተዋል። በጋዜጣዊ መግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ምንድናቸው ? - የህወሓትና ሌሎች ህገ-ደንቦች ያላሟለና ተጨባጭ የትግራይ…
#Tigray

" ጊዚያዊ አስተዳደር ተቆጥረው የተሰጡት ስራዎች አሉት ፤ ስራዎቹን ፍፅሞ ስልጣኑ ያስረክባል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ትናት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ ከነሀሴ 9 አስከ 11/2016 ዓ.ም  " ትግራይ ከአስከፊውና ደም አፋሳሽ  ጦርነት ወደ ከፍታ ወይስ ወደ ብዥታ ጉዞ !! " በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የትግራይ ሙሁራን ማህበር ያዘጋጀው የውይይት መድረክ የመዝግያ ስነ-ስርዓት ተገኝተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፥ " በትግራይ የሃሳብ ብዙህነት ማበብ አለበት ፤ የተለየ ሃሳብ ያቀረበ እንደ ጠላትና አፍራሽ አድርጎ ማሰብና መፈረጅ መቆም አለበት " ብለዋል።

" አሁን ላይ ትግራይ ውስጥ በመታየት ላይ ያለውን ተስፋ አስቆራጭ የሚመስል ሁኔታ ከትግራይና ከትግራዋይ የመፈፀም አቅም በታች ነው " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ችግሮቹ ይፈታሉ " በማለት ተናግረዋል። 

" ፈረንሳዮች ' ልዩነት ለዘልአለም ይኑር ! ' የሚል የሃሳብ ብዙህነት እንደ ዳበረ ባህልና ልምምድ የሚቆጥር አባባል አላቸው ይህንን አባባል እንደ ጥሩ ልምድ በመቅሰምና በመተግበር በሃሳብ ልዩነት የሚያምን የሰለጠነ ፓለቲካዊ ባህል ማጎልበት አንዱ የመልካም አስተሳብና የእድገት መለኪያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው " ብለዋል።

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሃላፊነት ላይ ሲቀመጥ ፦ 
- ሰላም ፍትህና ፀጥታ እንዲያረጋግጥ
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መልሶ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲያስከብር 
- የትግራይ መልሶ ግንባታ አስመልክተው የሚካሂዱት እንቅስቃሴዎች እንዲመራ
- ለቀጣዩ ምርጫ ምቹ ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ እንዲፈጥር የሚሉ ተግባራት ለመስራትና ለመፈፀም ነው " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " እነዚህ ተቆጥረው የተሰጡት ሰራዎች ፈፅሞ ስልጣኑ ያስረክባል " በማለት አክለዋል።

በመካሄድ ያለው የህወሓት 14 ኛው ጉባኤ ትናነት ነሀሴ 11/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፥ " በህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) ስም ማንኛውም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም " ብሏል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ጉባኤው በማካሄድ ላይ የሚገኘው " የህወሓትን ደንብና አሰራር በጣሰ ቡድን " ብለው " የጊዚያው አስተዳደሩ ስልጣን ለመንጠቅ የመሞከር እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ብለን እንጠብቃለን " ማለታቸው ይታወሳል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ  " የድርጅቱ ህገ-ደንብና አሰራር በጣሰ ጉባኤ አልሳተፍም ያለው "  በእነ አቶ ጌታቸው የሚመራው የህወሓት ሃይል ዛሬ ነሀሴ 12/2016 ዓ.ም በመቐለ የውይይት መድረክ ጠርቶ ውይይት እያካሄደ ነው።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
376👏49😡34🤔32😭29🕊25😢11😱6🥰4🙏3
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " ጊዚያዊ አስተዳደር ተቆጥረው የተሰጡት ስራዎች አሉት ፤ ስራዎቹን ፍፅሞ ስልጣኑ ያስረክባል " - አቶ ጌታቸው ረዳ ትናት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ ከነሀሴ 9 አስከ 11/2016 ዓ.ም  " ትግራይ ከአስከፊውና ደም አፋሳሽ  ጦርነት ወደ ከፍታ ወይስ ወደ ብዥታ ጉዞ !! " በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የትግራይ ሙሁራን ማህበር ያዘጋጀው የውይይት መድረክ…
#አሁን : በመቐለ ከተማ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ በወቅታዊ የህወሓት የፓለቲካ ሁኔት ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ መድረኩ ላይ " 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ህጋዊ አይደለም " ብለው የተቃወሙ ፦
➡️ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ፣
➡️ የድርጅቱ የማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን ፣
➡️ የክልል ፣ የዞን ፣ የወረዳና ሌሎች አመራሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ፥ " የውይይት መድረኩ ህወሓትን ለማዳንና ትግራይን ወደ ነባራዊ ሁኔታዋ ለመመለስ ወሳኝ ነው " ማለታቸውን ከድምጺ ወያነ ቴሌቪዥን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ተጨማሪ ይኖረናል።

የፎቶ ባለቤት ፦ ድምጺ ወያነ

@tikvahethiopia
1.04K🕊217😡118🤔117😭71🙏60👏54🥰48😱37😢30
#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር
Yonatan BT Furniture

ከ15% እስከ 20% ቅናሽ የተደረገባቸውን የተለያዩ የቤት ዕቃዎች እድሉ ሳያመልጥዎ አሁኑኑ ይግዙ!
የውበት እና የጥራት ዳር ድንበር!

አድራሻችን፦
1.ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251995272727
2.ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251957868686
3.ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251993828282

👉 Telegram:  https://t.iss.one/yonatanbt_furniture
👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
49👏8🥰6😢5😡5😱4🙏3🕊1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ሞጆ ቅርንጫፍ እየተጉላላን ነው። ትላንት የተላከውን ደብዳቤ ስራ አስኪያጅ ‘አልመራበትም’ ተብሎ ” - አስመጪዎች “ ደብዳቤው ትላንትና ከመሸ ነው እኛ ጋ የደረሰው ከዋና መስሪያ ቤት፡፡ ተመርቶ ለሚመለከተው ክፍል ሰጥጠናል ” - ሥራ አስኪያጅ ክፍሉ አስመጪዎች የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በጉምሩክ እያጋጠማቸው ስላለው ሁኔታ ፤ ክፈሉ ስለተባሉትም ከፍተኛ ቀረጥ በተመለከተ ለቲክቫህ…
#ጉምሩክ

" ሰርኩለሩ በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " - አስመጪዎች

በርካታ የመኪና አስመጪዎች ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አስመጪዎቹ በጋራ ፈርመው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባላኩት ደብዳቤ ፤ " መንግስት በሀምሌ 22/2016 ዓ.ም በስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ ያስተላለፈው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከዚህ በፊት የነበሩ ውስብስብ የንግድ መዛባቶችን እና ብሮክራሲዎችን እንደሚያስቀር እንተማመናል " ብለዋል።

ነገር ግን የኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ነሐሴ 03/2016 እና ነሐሴ 10/2016 ያወጣቸው ሰርኩላሮች ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

" ይህም ሰርኩላር ይዞ ሊመጣ የሚችለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ከግምት ውስጥ ያላስገባ እና ከጉምሩክ ትራንዚት እና መጋዘን አስተዳደር የሚጣረስ በመሆኑ ነው " ብለዋል።

አስመጪዎቹ " የኢትዮያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር FXD/01/2024 ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን ከ22/11/2016 በፊት የተመዘገቡ እና ተቀባይነት ያገኙ ሰነዶች ላይ በደብዳቤ ቁጥር 4/0/04/17 ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ስርኩለት የተላከ ሲሆን ነገር ግን ሰርኩለር በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " ነው ብለዋል።

ጉዳዩን ሲያብራሩም ፦

" በጉምሩክ ደንቡ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው የቀረጥ ማስከፈያ የሚወሰነው ዲ/ዬን. በተመዘገበበት እለት ያለው የብሔራዊ ባንክ ምንዛሬ ተመን በመጠቀም ነው።

ይህ ማለት በዮኒሞዳል አሰራር ሕጋዊ ዶክሜንት አሟልተን ዲ/ዬን ሞልተን ክፍያ ፈፅመን ሰነዱን የተሟላ መሆኑን ለጉምሩክ ኦፊሰር ተረጋግጦ ትራንዚት ተፈቅዶልናል፡፡

ትራንዚት ካስፈቀድን በኋላ ደግሞ ሕጉ በሚፈቅደው በአንድ ወር የትራንዚት ጊዜ ገደብ ውስጥ ኘሮሰስ ጨርሰን እቃዎቹን ወደ አገር ውስጥ አስገብተናል የጉምሩክ ሪስክ የሚጣለው ደግሞ እቃዎቹ አገር ውስጥ / መድረሻው ጣቢያ / ሲደርሱ መሆኑን ከግምት ያላስገባ ውሳኔ ነው።

እቃዎቹ ተጓጉዘው በድሬዳዋ መስመር /ደወሌ/ ለሚገቡ በድሬዳዋ ድልድይ ተሰብሮ ከ3 ሳምንት በላይ መቆማቸው ግምት ውስጥ ያላስገባ ውሳኔ ነው " ብለዋል።


" የጉምሩክ ኮሚሽን ከላይ የተገለጸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአስቸኳይ የውሳኔ ማሻሻያ እንዲደረግልን እና በአዋጁ መሰረት እንድንስተናገድ " ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ፤ " ጉምሩክ  ኮሚሽን አዋጅን በሴኩላር በማሻር የማይሆን ስራ እየሰራ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀረቡ አስመጪዎች አሁንም ተሻሻለ ተብሎ የወጣው ሴኩርላር ያለውን ችግር የሚፈታ አይደለም።

አሁንም ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ አስገንዘበዋል።

ጉዳዩ  በገበያና ስራው ላይ ሚያመጣውን ከፍተኛ ተፅእኖ በመረዳት እውቀትን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ በውይይት መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

#Customs #Ethiopia

@tikvahethiopia
184🙏26🕊11👏10🤔10😱8🥰4😢4😭4😡2
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " - የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህር ዳር ከተማ የመሀል ሜዳው ተጫዋች አለልኝ አዘነ ለህልፈት መዳረጉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ  በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ የቅርብ ግንኙነት…
የእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ጉዳይ የት ደረሰ ?

የባህር ዳር ከነማው የመሀል ሜዳ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከወራት በፊት አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ " የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን አካላት ይዤ ምርመራ ጀምሪያለሁ " ያለው የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ " ጉዳዩን በፍጥነት በማጣራት በቅርብ ለኢትዮጵያ ህዝብ የደረስኩበትን አደርሳለሁ " በማለት ቃል ገብቶ ነበር።

ይሁንና በጉዳዩ ላይ ሀምሌ ወር ውስጥ መግለጫ ይሰጣል መባሉ በተጨማሪ ለእስር የተዳረጉት የተጫዋቹ የቅርብ ሰዎች መሆናቸውን ተከትሎ ጉዳዩ የት ደረሰ ? የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ያቀረበለት የጋሞ ዞን ፍ/ቤት ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት አለመመራቱንና ክስ ባልተከፈተበት በጉዳዩ ላይ መረጃ መስጠት እንደማይችል ገልጾልናል።

ይህንንም ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅቱ ጉዳዩን እንደያዙትና ከምርመራ በኋላ የተደረሠበትን ጉዳይ ለህዝብ እንደሚያደርሱ ቃል የገቡልን በወቅቱ የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የነበሩትን ኢንስፔክተር አብርሀምን አነጋግረናቸው ነበር።

አዛዡ በወቅቱ የሟችን ቤተሰቦች በቁጥጥር ስር አድርገው ምርመራ እያካሄዱ እንደነበር አስታውሰው አሁንም ጉዳዩ ምርመራ ላይ እንደሆነ በመግለጽ ከቦታው በመነሳታቸው እንዲሁም የፖሊስ አሰራር በዚህ ሰአት መረጃ መስጠትን ስለሚከለክል ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን አሁንም ይከታተላል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
301😭225😡68😢39🙏34👏29🕊17😱11🤔8🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን : በመቐለ ከተማ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ በወቅታዊ የህወሓት የፓለቲካ ሁኔት ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱ መድረኩ ላይ " 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ህጋዊ አይደለም " ብለው የተቃወሙ ፦ ➡️ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ፣ ➡️ የድርጅቱ የማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን ፣ ➡️ የክልል ፣ የዞን ፣ የወረዳና ሌሎች አመራሮች…
#TPLF

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

ዛሬ መቐለ ሁለት ስብሰባ ሲካሄድ ውሏል።

አንዱ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚገኙበት 14ኛ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን ሌላኛው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ጉባኤውም የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በርካታ የክልል፣ የዞን እና ወረዳ አመራሮች የተገኙበት ነው።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

-  ያለ ልዩነት (በአመራሮች መካከል) " ጉባኤ ይደረግ አይደረግ " የሚል ሳይሆን እንዴት ይደረግ የሚል ነው።

- የእውቅናው ጉዳይ ከፌደራል መንግስት ጋር በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት መፍትሔ እንዲገኝለት ሁሉም ተግባብቶ እያለ፥ የተወሰኑ ግለሰቦች በጎን በመንቀሳቀስ ወደ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወረቀት በማስገባት ከመግባባቱ ያፈነገጠ ስራ ከውነዋል።

- የተፈጠረው አለመግባባትና ክፍፍል፥ የፕሪቶሪያ ስምምነት ያለባለቤት የሚቀርበት ዕድል የሚፈጥር ነው። ይህን አደጋ ለመቀልበስ ጥረት ይደረጋል።

- ሁኔታው የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ሂደት ባለቤት አልባ ሊያደርግ የሚችል ነው። ይህን ጉባኤ የፌደራል መንግስት አልተቀበለውም። ፌደራል አለመቀበሉ የራሱ ትርጉም አለው። ዋናው ነገር ግን በፓርቲያችን ውስጥ አንድነት እና መቀራረብ፣ በሐሳቦች ዙርያ አብሮ መስራት ሳይሆን መከፋፈል እና መራራቅ የሚያስከትል አደገኛ መድረክ ነው።

- የተፈጠረው ልዩነት አስጊና 'ጠላቶች' ሊጠቀሙበት የሚችል ነው።


ትላንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ ፥ " የህዝብ የሰላም ፍላጎት ወደጎን በመተው፣ ለግዜው ማን መሆኑ በግልፅ ከማይታወቅ እና እነሱ ደጀን ይሆነናል ያሉት የውጭ ኃይል ተማምነህ፥ ያልሆነ ዝግጅት፣ የተወሰነ ግለሰቦች ጠባብ ፍላጎት ሲባል የትግራይ ህዝብን ዳግም ወደ አደጋ ለመዳረግ የሚደረግ እንቅሰቃሴ ነው እየተካሄደ ያለው " ብለው ነበር።

ለዚህ ቃላቸው የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ቃል አቀባይ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ አማኑኤል " ይህ አገላለጽ ትክክል አይደለም። ህወሓት እምነቱ በትግራይ ሕዝብ፣ በፕሪቶሪያው የሰላም ሥምምነት በተቋማዊ አሰራር ነው። ሁሉም ችግሮች በሰላማዊ ፖለቲካዊ መንገድ ይፈታሉ ብለን ነው የምናምነው " ነው ያሉት። #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
375🕊108🤔71😡59👏32🙏23😭23😢21🥰14😱10
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? ዛሬ መቐለ ሁለት ስብሰባ ሲካሄድ ውሏል። አንዱ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚገኙበት 14ኛ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን ሌላኛው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ጉባኤውም የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በርካታ የክልል፣ የዞን እና ወረዳ አመራሮች የተገኙበት…
#Update

በህወሓት ምትክል ሊቀመንበር እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራው የዛሬው የመቐለው ስብሰባ ቁጥራቸው አንድ ሺህ መሆኑ የህወሓት አባላትና አመራሮች ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት የአንድ ቀን ስብሰባቸውን ከምሽቱ 2:30 አጠናቀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ካወጡዋቸው ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አራቱ ነጥቦች የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የፈጠረው አንፃራዊ ምቹ ሁኔታ እንዲቀጥል የሚያስታውስ ነው።

" ሰላም አማራጭ የሌለው አማራጭ መሆኑ በመቀበልና በመረዳት ማንኛውም ወደ ግጭትና ጦርነት የሚመራ የውስጥና የውጭ ተንኮል በፅኑ እንቃወማለን " ይላል።

በአቋም መግለጫው ከተገለፁ አራት ነጥቦች  በህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው ጉባኤ ኢ-ህጋዊነት የሚያትት ሆኖ " ተደናግረው በጉባኤው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የህወሓት አባላት ወደ ቀልባቸው በመመለስ ከህዝባቸው ጎን እንዲሰለፉ " ሲል ያሳስባል።

ዘጠነኛው ነጥብ ደግሞ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኘው የክልሉ ተወላጅ ፣ የድርጅቱ አባልና ደጋፊ ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ ማህበራት ፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ምርጫ ተካሂዶ መንግስት እስኪቋቋም ድረስ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ደግፈው እንዲቆሙ ጥሪ ያቀርባል።

" የተከበራችሁ የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች በድርጅታችን ውስጥ የተፈጠረው የሃሳብ ልዩነት እንደ ሁሉ ጊዜ በጥሞና በማየት በማያዳላ መንገድ የህዝቡ ፀጥታና ሰላም ማስከበር ይገባል " ያለው የውይይቱ ተሳታፊዎች አስረኛ ነጥብ የአቋም መግለጫ የፀጥታ ሃይሎች አሁን የያዙት የማያዳላ አቋም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀርበዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

Via @tikvahethiopiatigrigna

@tikvahethiopia
742👏140🕊79🙏57😡50🤔36🥰15😱13😭12😢5
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል። ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል። " በአፍሪካ ህብረት ፓናል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት…
ትግራይን ዳግም ወደ ጦርነት የሚያስገባ ተጨባጭ ስጋት አለ ?

" ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው። ወደ ጦርነት የሚያስገባ ምንም ነገር የለም " - አቶ አማኑኤል አሰፋ

በሊቀ - መንበሩ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ቃል አቀባይ አማኑኤል አሰፋ ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ነገር የለም ብለዋል።

አቶ አማኑኤል ፥ " በአንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ተሰብስቦ ስለ አንድ ድርጅት ውስጣዊ ጉዳዮች መወሰን ወደ ጦርነት የሚያስገባ አንድም ምክንያት የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

" ጦርነት በዚህን ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ ርካሽ አይደለም " ብለዋል።

" ጦርነት አስፈላጊ ሆኖ አማራጭ ቢሆን ኖሮ ትግራይ ውስጥ ያሉት ችግሮች ሌላ ጦርነት ይጋብዙ ነበር " ሲሉ ተደምጠዋል።

እንዚህ ችግሮች ለተፈጸሙ ወንጀሎች የተጠያቂነት አለመረጋገጥ ፣ በህገመንግስት ላይ የተቀመጠው የክልሉ ግዛት አለመመለስ ፣ የተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው አለመመለስ ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ ...ወዘተ እንደሆኑ ነው የጠቆሙት።

" ዛሬም ትግራይ ውስጥ ብዙ ችግሮች አሉ። ህዝቡ መስእዋትነት እየከፈለባቸው ነው ግን የተጀመረውን የሰላም ተስፋ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲሸጋገር ህዝቡ መስእዋትነት እየከፈለ እየኖረ ነው " ብለዋል።

" ያሉ ችግሮች ወደ ጦርነት ሳያስገቡ አንድ ህወሓት የሚባል ድርጅት በፕሪቶሪያ ስምምነት አካል የሆነ ባለቤት የሆነ ውስጣዊ ችግሮች አጋጥመውት ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል ስራ በመስራቱ ወደ ጦርነት ሊገባ አይችልም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደዚህ ብለዋል ... እንዲህ ብለዋል ተብሎ የተለያየ ትርጉም ከተሰጠው በኃላ ይሄን በሚመለከት ህወሓት ጠቅላይ ሚኒስትሩን engage አድርጓል። " ብለዋል።

" በዚህ ደረጃ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባን ነገር እንደሌለ ግልጽ ሆኗል " ሲሉ አክለዋል።

" ህወሓት አንድ ድርጅት ነው " ያሉት አቶ አማኑኤል አሰፋ ፥ " የተለያዩ ስራዎች ሊሰራ ይችላል ፤ ያን ስራ በሚመለከት መወያየትና መነጋገር ይቻላል። ችግሮች ካሉ ለመወያየት እና አብሮ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የተጀመረ የሰላም ማዕቀፍ አለ ያን መሰረት አድርጎ መወያየት እና መፍታት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ኢትዮጵያ ውስጥ በተከታታይ የተደረጉ ጦርነቶች ናቸው የዛሬውን ችግር ያመጡት " የሚሉት አቶ አማኑኤል " ብዙ ችግር ባለበት ሀገር ሆነን አሁንም ጦርነት ውስጥ ለመግባት የሚያስችል ምንም ምክንያት የለም " ብለዋል።

" ስለተሰበሰብን ፣ አንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ህወሓት የሆነ ነገር ስላደረገ ጦርነት አይመጣም ፤ እንዴት ጦርነት በዚህ ልክ ርካሽ ይሆናል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው ፤ ውስጣዊ ችግሩን ለመፍታት ነው ጉባኤ የሚደረገው " ሲሉ ለወይን በሰጡት ቃለ መጠየቅ ተናግረዋል።

#TPLF #TIGRAY

@tikvahethiopia
724🕊248😡123🤔78👏69🙏45😭44😢32🥰29😱25