TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.5K photos
1.59K videos
216 files
4.34K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sidama

" በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰና እያስመረረ የሚቀጥል አመራር አይኖርም " - አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ

በሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት ግምገማ መደረጉን ተከትሎ በርካታ የፖሊስ አዛዥች ከስልጣን ሲነሱ በጥቂቶች  ላይ ከህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ምርመራ እንደተጀመረባቸው ተሰምቷል።

ከሰሞኑ በክልሉ ሲካሄድ የሰነበተውን የግምገማና የውይይት መድረክ አሰመልክተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ኃላፊዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ " በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰና እያስመረረ የሚቀጥል አመራር አይኖርም " ብለዋል።

" በዚህ መሰረት በተደረገ ግምገማ በክልሉ በተለያዩ ዞን ወረዳና ከተማ አስተዳደር ውስጥ
ባሉ መዋቅር ይሰሩ ከነበሩ አመራሮች ውስጥ ሰባት የፖሊስ አዛዦችና ሙሉ የአንድ ክፍለ ከተማ የማኔጅመንት አባላት ላይ ከህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ምርመራ እንዲጀመር ታዟል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ከተደረጉ አመራሮች መካከል ፦
- የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ፣
- የሆኮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ
- የጨቤ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ይገኙበታል።

የዳዬ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ከኃላፊነታቸው ታግደው ከመልካም አስተዳደር ችግሮችና ከህገወጥ ንግድ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩባቸው ጉዳዮች እንዲጣራ ታዟል።

በተጨማሪም ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ በዞኑ ህገ-ወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ እየተበራከተ በመምጣቱና መቆጣጠር ባለመቻላቸው ከኃላፊነታቸው ሊነሱ ችለዋል።

በወረዳ ደረጃ ደግሞ የሁላ ወረዳ፣ የአለታ ጩኮ ወረዳ፣ የቡርሳ ወረዳና የጠጢቻ ወረዳ ፖሊስ አዛዦች የተነሳባቸው ጉዳዮች ተጣርቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

በሀዋሳ ከተማ ምስራቅ ክፍለ ከተማ ያሉ ጠቅላላ ማኔጅመንቱ ከኃላፊነት እንዲነሱ መደረጋቸው ተነግሯል።

በመድረኩ በርካታ ችግሮች የተነሱ ሲሆን ለአብነትም ኪራይ ሰብሳቢነትና ባለጉዳይን ማማረር ጎልተዉ የተነሱ ክፍተቶች ናቸው።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
252👏120🕊22🤔20😡14😱7🙏6😭5😢4🥰2
#Sidama

🔴 " በብልፅግና ፓርቲ መዋጮ ምክንያት አባላትና አመራሮች እየታሰሩብኝ ነው " -የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ሲህአዲድ)

🔵 " በፓለቲካ አቋሙና አመለካከቱ የታሰረ የፖለቲካ ፓርቲ አባልና አመራር የለም " - የሲዳማ ክልል ፖለቲካ ፖርቲ የጋራ ምክር ቤት

🚨" የታሰርነዉ ለሁለት ፖርቲዎች መዋጮ አናዋጣም ስላልን ነው " - የሲህአዲድ አባላትና አመራሮች


የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል አቶ ሠለሞን ቡሮዳ የፓርቲያቸው አባላትና አመራሮች " ለብልፅግና  ፖርቲ መዋጮ አናዋጣም " በማለታቸዉ እየታሰሩና በሐሰት እየተወነጀሉ ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቀረቡ።

በክልሉ ከጥቅምት ወር መገባደጃ ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች አባላትና አመራሮቻቸው ሰበብ እየተፈለገ ሲታሰሩና ሲፈቱ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ደግሞ በአባላቶቻቸው ላይ ሐሰተኛ ክስ እየተፈበረከባቸዉ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአንዳንድ ወረዳዎች ማሸማቀቅ ተበራክቷል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ለአብነትም ፦
- ወንሾ፣
- ጠጥቻ፣
- ጎርቼ፣
- ቦና ዙሪያ፣
- ቡርሳ፣
- ጫቤ ጋምቤልቱ፣
- ሸበዲኖ፣
- ጭሬና በንሳ ወረዳዎች አባላትና አመራሮቻቸው " የብልፅግና ፓርቲ መዋጮ ለምን አታዋጡም " በሚል ለእስር ተዳርገዉ እንደነበር አንስተዋል።

አቶ ሠለሞን ፤ " አሸናፊዉ ፓርቲ ብልፅግና ነዉ፤ ሁሉም ለብልፅግና ፓርቲ የህንፃ ግንባታ  መዋጮ የማዋጣት ግዴታ አለበት " የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ በአንዳንድ ወረዳዎች በግልፅ እየተስተዋለ ነው ብለዋል።

" በዚህ ሁኔታ የሚደረጉ ኢ-ሕገ መንግስታዊና የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ በሚፃረርር መልኩ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የኢሶዴፖ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የደቡባዊ ቀጠና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በለጠ ሲጄቦ አነጋግሯል።

ቅሬታ መቅረቡን አልሸሸጉም።

ቅሬታውን ተከትሎ ምክር ቤቱ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ በማድረግ ኮሚቴ ተሰይሞ የማጣራት ሥራ መስራቱን ገልጸዋል።

በዚህም የታሰሩት ግለሰቦች በደረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ አንጂ በፖለቲካ አቋማቸዉና አመለካከታቸዉ ምክንያት እንዳልሆነ መረጋገጡን አሳውቀዋል።

ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ የፓርቲው የወረዳ አባል መሆናቸውን የሚገልጹት የጠጥቻ ወረዳ ነዋሪ አቶ አስራት ወርሶ ግን " ለሁለት ፓርቲ መዋጮ አላዋጣም በማለቴ ታስሬ ነበር " ሲሉ ስለእስራቸው ምክንያት ይገልጻሉ።

ከአንድ ቀን እስር በኋላም የፓርቲው አመራሮች ባቀረቧቸዉ መረጃዎች ምክንያት ከእስር መለለቃቸዉን አስረድተዋል።

የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የሁላ ወረዳ ስራ አስፈፃሚ መ/ር ሀንሳሶ በበኩላቸው " እኔም አባላቶቻችን ለምን ታሰሩ " በሚል ልንጠይቃቸዉ በሄድንበት ከሁለት አባላት ጋር ታስረን ነበር ሲሉ " ተጨማሪ ምስክርነት ሰጥተዋል።

አክለውም " ለብልፅግና ፓርቲ የሕንፃ መሰሪያ መዋጮ ካላዋጣችሁ በሚል በአባላትና አመራሮቻቸዉ ላይ በበርካታ ወረዳዎች እየደረሰ ያለዉ ጫና ስጋት ዉስጥ ከቶናል " ሲሉ ገልጸዋል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ እና የገዢዉ ብልፅግና ፓርቲ ሃሳብ ለማካተት ያደረግነዉ ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን ኃሳባቸውን እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
😡20180😭19🙏14🕊14🤔10🥰5👏3😢3😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
ፊቼ ጨምበላላ መቼ ይከበራል ? " የሲዳማ አያንቱዎች በተፈጥሮ የቆጠራ ጥበብ ተመርተዉ የ2017/18 የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል የፊታችን መጋቢት 18 እና 19 እንዲሆን ወስነዋል " - የሲዳማ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል የፊታችን መጋቢት 18 እና 19 እንዲከበር የባህል አባቶች(አያንቱዎች) መወሰናቸውን የክልሉ ባህና ቱሪዝም ቢሮ…
#Sidama #Hawassa

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበዉ የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ " ፊቼ ጫምበላላ " በዓል የፊታችን መጋቢት 18 እና 19 በሀዋሳ ከተማ ይከበራል።

" የፍቼ ጫምበላላ በዓል ቅድመ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል " ሲል የሲዳማ ክልል ባህልና ተሪዝም ስፖርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ደግሞ " ከበዓሉ እሴት እና ከተቀመጡ መረሃግብሮች ዉጪ በየትኛዉ መልኩ የበዓሉን ድባብ ለማጠልሸት የሚሞክሩ አካላትን የፀጥታ መዋቅሩ አይታገስም " ሲል አሳስቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
159😡83🤔19🙏14🥰8😭6😱4😢2
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama #Hawassa በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበዉ የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ " ፊቼ ጫምበላላ " በዓል የፊታችን መጋቢት 18 እና 19 በሀዋሳ ከተማ ይከበራል። " የፍቼ ጫምበላላ በዓል ቅድመ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል " ሲል የሲዳማ ክልል ባህልና ተሪዝም ስፖርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የክልሉ ኮሚኒኬሽን…
#Sidama #Hawassa

ለፊቼ ጨምበላላ በዓል ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆነዋል። ከዋዜማው እስከ መጋቢት 19 ድረስ ሞተር ማሽከርከርም ታግዷል።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መልካሙ አየለ ፥ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በሀዋሳ የሚከበረውን የፊቼ ጨምበላላ በዓልን ምክንያት በማድረግ ገደብ የተጣለባቸዉ ተሽከርካሪዎች እና የሚዘጉ መንገዶች ስለመኖራቸው ተናግረዋል።

ለበዓሉ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ሰዎች የሚታደሙ እንደመሆኑ መጠን የትራፊክ መጨናነቅና አደጋዎች እንዳይከሰቱ በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የገለጹት አዛዡ ከዋዜማዉ መጋቢት 18 እስከ 19 የባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ላይ ገደብ እንደተጣለ ገልጸዋል።

በዓሉ ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ለሁሉም ተሽከርካሪዎች የሚዘጉ መንገዶች ስለመኖራቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

በዚህም መሠረት ከነገ መጋቢት 18/2017 ዓ/ም ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ :-

➡️ ከሱሙዳ አደባባይ (ቅዱስ ገብርኤል) ፊት ለፊት እስከ ፒያሳ ዳሽን ባንክ ሕንፃ ድረስ፤
➡️ ከኬራዉድ እስከ ታቦር ትራፊክ መብራት፤
➡️ ከሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል እስከ ጉዱማሌ ደሴት፤
➡️ ከዳሽን ሕንፃ እስከ የቀድሞ ማዘጋጃ (ሻፌታ አደባባይ)
➡️ ከፒያሳ ቴሌ እስከ እስከ ሴንትራል ሆቴል ደሴት
➡️ ከሮኪን እስከ ሴንትራል ሆቴል ያሉ መንገዶች በዓሉ ተከብሮ እስኪጠናቀቅ መሉ በሙሉ ለሁሉም ተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ አስታዉቀዋል።


@TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
259🤔75😡71🕊32😭22😱12🙏6💔6👏4🥰1😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Sidama

ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አዲስ ፖሊስ አዛዥ ተሹሟል።

የምስራቅ ሲዳማ ዞን ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ማቴዎስ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሆነዉ ተሹመዋል።

በፀጥታ ዘርፉ ዉስጥ ሪፎርም ዉስጥ እንደሆነ በሚነገረው የሲዳማ ክልል ፖሊስ ተቋም ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ በተፃፈ ደብዳቤ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ማቴዎስ ከዛሬ ሐምሌ 2/2017ዓ/ም ጀምሮ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሆነዉ ተሹመዋል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ኮማንደር መልካሙ አየለ በምን ምክንያት እንደተነሱ እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
449🕊29😢23💔18🤔14🙏13😡11😭10😱7🥰6👏2