TIKVAH-ETHIOPIA
" የ6 ሰዎችን ማግኘት አልተቻለም "- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ኪንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰዉን የመሬት መንሸራተት አደጋ በተመለከተ ክልሉ ዛሬ ወቅታዊ መረጃ ሰጥቶ ነበር። በዚህም መግለጫ " የቀበሌዉን ማህበረሰብ ቁጥር ለመለየት በተደረገ የቤት ለቤት ቆጠራ ስድስት ሰዎች አልተገኙም " ብሏል። አሁንም አስክሬን ፍለጋዉን እንደቀጠለ ጠቁሟል። በሌላ በኩል ፤ እስካሁን…
#Update
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የቀሪ ሰዎችን አስክሬን የማፈላለጉ ሥራ ማብቃቱን ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አሳውቋል።
ያልተገኙ ሟቾችን የመፈለጉ ሥራ ያበቃው አደጋው ከተከሰተበት ከባለፈው ሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የቁፋሮ ሥራው ሲካሄድ ከቆየ በኋላ እንደሆነ ጠቁሟል።
በፍለጋው የ243 ሰዎች አስክሬን በማግኘት በክብር እንዲያርፍ ሲደረግ፤ የ6 ሰዎች እስክሬን ግን እስከ ትናንት ተፈልጎ አለመገኘቱን አሳውቋል። #DW
@tikvahethiopia

#Ethiopia #USA
አሜሪካ በአማራ ክልል እየተባባሰ የሄደው ግጭት እንዳሳሰባት ገለጸች።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊንከን " የርስ በርስ ግጭቶች እልባት ያገኙ ዘንድ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ አለባቸው " ብለዋል።
አንቶኒ ብሊንከን ይህንን ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት እንደሆነ ተነግሯል።
ብሊንከን "በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ያሳስበኛል" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶችን ጨምሮ የውስጥ ግጭቶችን ለመፍታት የፖለቲካ ውይይት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ " በፕሪቶሪያው ስምምነት እና አፈጻጸሙ ዙሪያ " መነጋገራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት የሀገራቸው እገዛ እንደማይለያት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊነክን በአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና እየተባባሰ ነው ያሉት ውጥረት እንዲረግብም በዚሁ ጊዜ መጠየቃቸውን ተዘግቧል።
#AFP #DW