TIKVAH-ETHIOPIA
" የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት መዘዙ ለአጎራባች ሃገራትም ተርፏል " - ካተሪን ፓቲሎ የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በሱዳን ላይ ካስተለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ባሻገር ኢትዮጵያን ጨምሮ በአጎራባች ሃገራት ላይ ብርቱ ኤኮኖሚያዊ ጉዳት ማድረሱን የዓለም የገንዘብ ድርጅት አስታወቀ። በድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ካተሪን ፓቲሎ " የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት መዘዙ ለአጎራባች…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Sudan
ዛሬም ድረስ አሸናፊ ያልተገኘለትና ዳፋው ለጎረቤቶች ሀገራት ጭምር የተረፈው የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት የብዙ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።
በርካቶችም ጦርነትን ሽሽት ሀገር ጥለው ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል።
የሱዳን ከተሞች ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል።
ሀገሪቱ ያሏት መሰረተ ልማቶች እንዳልነበሩ ሆነዋል።
ኢኮኖሚው ደቋል፤ ሞቷል።
የሚበላ የሚላስ የሚቀመስ ያጣው ሱዳናዊ እጅግ ብዙ ነው።
ተፋላሚዎቹ ቁጭ ብለው እንዲነጋገሩ ብዙ ቢሞከረም እምቢኝ እንዳሉ ናቸው። ጦርነቱንም አፋፍመው ቀጥለዋል።
ከዓመት ባለፈው የእርስ በርስ ጦርነት አንድም አሸናፊ አልተገኘም። ይልቁንም ሱዳን እንዳልነበረች ሆናለች። ዳግም ለማንሰራራት በርካታ አመታት ይወስድባታል።
ከላይ የተያያዘው ቪድዮ በአንድ ከተማ ያለውን አስከፊ ገጽታ የሚያሳይ ነው።
@tikvahethiopia