TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማይናማር🚨 🔴 “ ልጆቻችን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት። መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርልን ” - የወላጆች ኮሚቴ 🔵 “ ከአገራቱ ጋር የስራ ሥምሪት ስምምነት ባለመኖሩ፣ ሰዎቹም ያቀኑት በህገ ወጥ መንገድ በመሆኑ ያሉበት ቦታና ቁጥራቸውን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ አዋቅረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልጆቻቸው ካሉበት አስከፊ ሁኔታ…
#Myanmar (Burma) #ማይናማር

" በህይወት እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር " - ሽኩር  (የአይን ምስክር)

" ስሜ ሽኩር ይባላል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዓለምን ባመሰቃቃላ ግዜ እኔ ሥራ ካጡ ሰዎች አንዱ ነበርኩ።

በአገራችን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ጉዳዩን የበለጠ አባብሶት የነበረ ቢሆንም ለመኖር ሲባል ለ 7ወር የህል በመምህርነት አገልግያለሁ። ነገር ግን ገቢዬ ፍላጎቴን ለማሟላት በቂ አልነበረም።

አንድ ቀን በታይላንድ ውስጥ የውሂብ ማስገቢያ ኦፕሬተር ለመሆን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የስራ ማስታወቂያ አየሁ።

በጣም ማራኪ መስሎ ታየኝ። በወር 1,000 ዶላር ቃል ገቡልኝ።

ማረፊያ ቦታ እና በቀን 8 ግዜ የምግብ ሰዓት እንደለው    ተነገረኝ።

ቤተሰቤን እና ራሴን ከድህነት ለማላቀቅ እና የተሻለ ህይወት ለመኖር ወደ ታይላንድ መሄድ  እንዳለብኝ አሰብኩ።

በማስታወቂያው ላይ ያለውን ቁጥር አግኝቼ የመፃፍ ችሎታዬን እና የእንግሊዝኛ ችሎታዬን በቪዲዮ ገመገሙ። 

ከዛም ታይላድ ከሄድኩ በኃላ ተወዳደርኩ እና ፈተናውን አልፌ በመቀጠሬ ኩራት ተሰማኝ።

🛬 ስራው ለህልሜ መልስ ይሆናል ብዬ ነበር 🛬

በታይላንድ ውስጥ ያለው ስራ ለህልሜ መልስ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር ፤ ለቤተሰቤ እና ለጓደኞቼ የተሻለ ህይወት ይሰጥልኝ ይሆን ብዬም ነበር።

ነገር ግን ያሰብኩት ነገር ቅዠት ሆኖ ተገኘ።

ባንኮክ አየር ማረፊያ ስደርስ አንድ ሰው ወደ መድረሻው በር ወሰደኝና ሹፌሩን እንድጠብቅ ነገረኝ።

ሹፌሩ እኔንና ሌላ ሠራተኛ ጨምሮ እዞን ሄደ።

እዞን የሄደው ማይ-ሶት ወደምትባል የታይላንድ ትንሽ ከተማ (ማይናማር  ጋር ትዋሰናለች) ወደዛ ነው።

ያኔ ጨለማ ስለነበር ምን እየሆነ እንዳለ ሙሉ በሙሉ አላውቅም ነበር። 

ጥቂት ሰዎች ወደ እኛ መጡ፣ እና በጀልባ እንድንገባ አስገደዱን። ሳንፈልግ ወደ ማይናማር ወሰዱን። ማይናማር  ወዳለው ግቢ ስንደርስ ደነገጥኩ፣ ፈራሁ ፤ አቅመ ቢስ ሆንኩኝ።

🏦 አሰሪዎቻችን ህይወታችንን ተቆጣጠሩት 🏦

ግቢው ሰፊና በህንጻዎች የተሞላ ነበር።

እያንዳንዱ ሕንፃ አራት ፎቆች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱ ወለል 16 ክፍሎች አሉት። እያንዳንዱ ክፍል አራት ተደራቢ አልጋዎች አሉት።

በግቢው ውስጥ አሠሪዎቻችን ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት።

በሳምንት ሰባት ቀን እስከ 16 ሰአት እንድንሰራ አድርገውናል።

በሥራ ላይ እያለ እንቅልፍ ከተሰማን ወይም እግሮቻችንን ትይዩ ካላደረግን እንቀጣለን።

በግቢዎቹ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ነበሩ። 

በጣም ብዙ ኢትዮጵያዊያን ፣ ህንዶች፣ ፊሊፒኖዎች፣ ፓኪስታናውያን፣ ቻይናውያን፣ ኢንዶኔዥያውያን፣ ሩሲያውያን፣ ዩክሬናውያን፣ ታይላንድ፣ ጃፓናውያን፣ አፍሪካውያን ከኡጋንዳ እና ኬንያ እና የአካባቢው  ማይናማር ሰዎች ጭምር ይገኙበታል።

👨‍💻 ስራው ማጭበርበር ነበር 👨‍💻 

በግቢው ውስጥ የነበረው ስራ አሰቃቂ ነበር።
 
ዋናው ሥራው በCrypto-currency ማጭበርበሮች በዓለም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ገንዘብ መስረቅ ነበር።

አሰሪዎቻችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የውሸት መገለጫዎችን (ፌክ ፕሮፋይል የሴት / የወንድ) እንድንፈጥር አስገድደውናል።

የተዘጋጀውን ስክሪፕት ተከትዬ፣ ከአሜሪካ ፣ ከጃፓን እንዲሁም ከታይዋን የውጭ ዜጎች እንዲወዱኝ አድርጌአለሁ።

አመኔታቸዉን ካገኘሁ በኋላ ብዙ ገንዘብ ማግኘት እንዲችሉ የCrypto-currency መድረክን አስተዋውቄያለሁ። 

ግን ሁሉም ውሸት ነበር።

እስከ ዛሬ ድረስ የተገደድኩበትን ሥራ ከቤተሰብ ወይም ከጓደኞቼ ጋር ለመካፈል አፍራለሁ።

ሰዎችን በማጭበርበር ተጸየፍኩኝ ነገር ግን ምንም ምርጫ አልነበረኝም ፤ ለህይወቴ እፈራ ስለነበር ነው።

🪖 ቦታው በታጠቁ ሰዎች ነው የሚጠበቀው 🪖

ከዚያ ቦታ ለማምለጥ ምንም መንገድ አልነበረም። 10 ጫማ ከፍታ ያላቸው ግድግዳዎች በላዩ ላይ ሽቦዎች ነበሯቸው።

ቦታው በታጠቁ ሰዎች ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግለት ነበር። 

ከግቢው ለማምለጥ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ የሞት ምኞት ነው።

ሰዎችን ማጭበርበር አለመቻል ማለት አካላዊ ጉዳት ወይም ሞትንም ያስከትላል።

አንድ ጓደኛችን ለቅጣት ወደ ‘ ውሃ እስር ቤት ’ ተላከ። ተደብድቦ ወደ ቢሮው ተመለሰ ከዛ በኃላ ማውራትም ሆነ መሄድ አልቻለም።

ሞባይል ስልኮቻችንን፣ ፓስፖርቶቻችንን እና ሁሉንም የግል ማህደሮች የባንክ ካርዶችን ጨምሮ ነው የተወሰደው።

የሚሉንን ያህል ብንሰራም ቃል የገቡትን ገንዘብ በፍጹም አይከፍሉም።

💰 3000 ዶላር ከፈልን 💰

ወደ ቤት ሀገሬ ለመምጣት በጣም ፈለኩኝ።

ነገር ግን አጋቾቼ ለመልቀቅ 5,000 ዶላር መክፈል እንዳለብኝ ነገሩኝ።

የሌለኝ እና ማድረግ የማልችለው ገንዘብ ስለሆነ   ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን ከአለቃው ጋር በድጋሚ ለመደራደር ሞከርን። 

3000 ዶላር ከፈልኩኝ፣ በመጨረሻም ለቀቁኝ።

ማይናማር ወደ ባንኮክ መሻገር በጣም አስፈሪ ነበር ነገር ግን የአለህ ፊቃድ ሁኖ ከዛ እስር ቤት ወጣሁ።

ከዚያ መከራ በመትረፌ እፎይታ ተሰማኝ።

በህይወት እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። ለዚህ እድል እና እንዲወጣ ለረዱኝ ሰዎች የዘላለም አመስጋኝ እሆናለሁ።

ወደፊት እየሄድኩ፣ አዲስ ጅምር እፈልጋለሁ። አሁን ቤተሰቤን ለማስተዳደር ጥሩ ሥራ እየፈለግኩ ነው።

💻 በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የውሸት ማስታወቂያ አያለሁ 💻

አሁንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የውሸት የስራ ማስታወቂያዎችን እያየሁ ነው። ይህን ሳይ በግቢው ውስጥ የታሰሩትን ሰራተኞች አስባለሁ። 

የሀገራት መንግስታት እንዲሁም ሌሎች ኤጀንሲዎች ሰዎችን ከህገወጥ ዝውውር እና ከግዳጅ የጉልበት ስራ ለመጠበቅ ስለዚህ ጉዳይ የበለጠ ግንዛቤ እንደሚገነቡ ተስፋ አደርጋለሁ።

ይህ መቆም አለበት !

ህብረተሰባችን ከህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ህገ ወጥ ጉዞ ራሱንና ልጆቹን መጠበቅ አለበት። "

(ሽኩር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM