TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? " አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ  ላይ ናቸው ? በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው። የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል። መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው። ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት…
#HoPR

" ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል

የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦

" ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት ሪፖርት ሙስና በሀገራችን ከአመት አመት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ።

ይህን ስር የሰደደ መንግሥታዊ ሌብነት ወይም ሙስና ለመዋጋት ብሔራዊ የጸረሙስና ኮሚቴ መቋቋሙን ብንሰማም አርቂ ስራ ሲሰራም ሆነ በሙስና ምክንያት ያንዣበበውን ሀገራዊ አደጋ ለመቀልበስ እርባና ያለው ስራ ሲሰራ አልታየም።

በአጠቃላይ መንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ይሄ ነው የሚባል መፍትሄ እየሰጠ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱም ላይ ጥያቄ ይነሳል።

ምክንያቱም የህዝብ እና የመንግስት ሀብት በዘረፉ ሙሰኛ ባለስልጣናት ላይ መቀጣጫ የሚሆን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ተጨማሪ ሹመት እና የቦታ ዝውውር በመስጠት መንግስት ሙሰኞችን አብሮ አቅፎ ይኖራል ማለት ይቻላል።

ከዚህ የተነሳ ፦

የመንግስት መዋቅር በሌቦች ተጠልፏል።

ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል።

ዜጎች የዕለት ኑሯቸውን ለመግፋት በአደባባይ ገንዘብ እየተጠየቁ ነው።

ከፍተኛ የሀገር ሀብት ከሀገር ወጥቶ እየሸሸ ነው።

የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት እያባከኑ ነው።

በኦዲት ሪፖርት መሰረት በየመ/ቤቱ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ይታያል።

መ/ቤቶች ገንዘብ ያለማስረጃ ወጪ በማድረግ ይጠቀማሉ ፣ ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ በወጪ ይመዘግባሉ፣ ከፋይናንስ መመሪያና ደንብ ውጭ የገንዘብ ክፍያ ይፈጸማል።

እንደሚታወቀው ብዙ ሀገራት ለችግሩ በሰጡት ትኩረት የማያወላውል እርምጃ ስለወሰዱ ችግሩን ማቃለል ችለዋል።

ለምሳሌ በቅርቡ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ለልምድ ልውውጥ የጎበኟቸው የእስያ ሀገራት እነ ሲንጋፖር ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ ስንመለከት ለእድገታቸው ዋናው መሰረት በሙስና ላይ ያላቸው ቁርጠኝነት ነው።

በሀገራችን የሌብነት ችግር ለመቅረፍ አፋጣኝ እና አስተማሪ የሚሆን እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር የጸረ ሙስና ህጋችንን አሻሽለን ቢሆን በሀገራችን አሁን የምናያቸው ፈተናዎች ተደምረው ሙስና የሀገራችንን ህልውና መፈተኑ አይቀርም።

ክቡር ጠ/ሚኒስትር በህዝቡ የሚቀርበው ተደጋጋሚ ቅሬታና የጄነራል ኦዲተር መ/ቤት በማስረጃ አስደግፎ ያቀረበልን ስር የሰደደ የሙስናን ችግር ለመቅረፍ መንግስትዎ ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ?

በተደጋጋሚ እንደታዘብነው ቃል ከመግባት ባለፈ ምን ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ ታስቧል ?

ህዝቡስ ከመንግስትዎ ምን ይጠብቅ ? "

#Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR " ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦ " ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት ሪፖርት ሙስና በሀገራችን ከአመት አመት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ። ይህን ስር የሰደደ መንግሥታዊ ሌብነት ወይም ሙስና…
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦

" የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል።

ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው።

መንግስት በህዝብ ዘንድ እምነት አልገነባም ብለን እናስባለን። ይሄም የሚገናኘው ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር ነው።

ባለፉት 10 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ሰበብ በማድረግ የመንግስት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል።

ከነዚህ ጥሰቶች ውስጥ የጅምላ ግድያ፣ በሰብዓዊ / ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል። በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች።

ጥቂቱን ለመጥቀስ በመርዓዊ ፣ በጅጋ ፣ በደብረ ኤልያስ ፣ በፍትኖተ ሰላም፣ ደብረሲና አካባቢ ፣ ጎንደር እና ወሎም እንዲሁ ተፈጽሟል።

ይህንንም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋማት የዘገቡት የአይን እማኞችም የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው።

ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጾታዊ ጥቃት፣ ድብደባ ፣ ዘረፋ ፣ ንብረት ማውደም ፣ የሲቪል ተቋማት በጤና ፣ በትምህርት ተቋማት ላይ ውድመት እንደደረሰ በርካታ ምስክሮች ገልጸዋል።

ሌላው የሰብዓዊ መብት ችግር በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ምክንያት በርካታ ፖለቲከኞች የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ታስረዋል።

ከዚህ ባለፈ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች፣ አጠቃላይ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በተለይ በአማራ ክልል አማራዎች በጅምላ ለወራት በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።

የምክር ቤት አባላትን ስናነሳ የምክር ቤት አባላችን አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግስት ወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኖ መንግስትን ከምዝበራ ያዳነ በሰላማዊ ትግልም በእጅጉ የሚያምን ሰው ነው አንድ አመት ለሚሞላ ጊዜ በእስር እየማቀቀ ያለው።

ሌሎችም በለውጡ ከእርሶ ጋር አብረው የሰሩ እንደ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ፣ ዶ/ር ካሳው ተሻገርና አቶ ታዬ ደንደአ ያሉም ለውጡ ስህተት ፈጽሟል በትክክለኛው ጎዳና እየሄደ አይደለም ብለው ስለሞገቱ ብቻ ለወራት ታስረዋል።

ከዚህ የከፋው ግን የት እንኳን እንደታሰረ የማይታወቅ አንድ የአብን አባላችን ነው ሀብታሙ በላይነህ ይባላል።

ሀብታሙ በላይነህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ነው። እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ መምህር ነው። ላለፉት 4 ወራት የት እንደገባ አይታወቅም። ይህን ጉዳይ ቤተሰቡም እኔም ለተለያየ የመንግስት ኃላፊዎች አቤት ብለናል ምላሽ አላገኘንም። ዛሬ እርሶ ምላሽ ይሰጡናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ እንማጸናለን።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ልክ እንዳበቃ ህጋዊ አሰራሩ ይቀጥላል ብለን እንገምት ነበር ነገር ግን አዋጁ አብቅቶ በኮማንድ ፖስቱ እየተዳደርን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።

የጅምላ እስር አሁንም አለ፣ ህገመንግስቱ በትክክል እየሰራ አይደለም። በደረቅ ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ብቻ መጠየቅ ሲገባቸው አሁንም በፖለቲካ አመለካከታቸው ዜጎች በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።

ስለዚህ ህብረተሰቡ ስለ ሽግግር ፍትህና ስለ ሀገራዊ ምክክር መንግስት ሲያወራ ይመነው ? እምነት አልገነባንም።

በጅምላ የታሰሩ፣ የህሊና እስረኞች ቢፈቱ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መርምረው አጥፊዎች ተጠያቂ እዲሆኑ ቢደረግ ያኔ እምነት መገንባት ይቻላል።

መንግስት ምን እቅድ አለው እምነት ለመገንባት ? የህሊና እስረኞችን ለመፍታት እና የጅምላ ግድያና ሌሎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማቆም ምን ወስኗል ? "

#TikvahEthiopia
#HoPR

@tikvahethiopia
ተጨማሪ በጀት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ያገኘውን ድጋፍ እና ብድር የያዘ ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ለፓርላማ አቅርቦ እንደሚያስጸድቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል።

ይህ የተናገሩት ዛሬ በነበረው የምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ወቅት ነው።

ተጨማሪ በጀቱ ፦

➡️ ለዝቅተኛ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች ለሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ፣

➡️ ለነዳጅ ድጎማ፣

➡️ ለዘይት ድጎማ፣

➡️ ለማዳበሪያ እና መድኃኒት ድጎማ የሚውል መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ፎቶ፦ ፋይል

#EthiopianInsider #HoPR #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሹመት ሰጥተዋል። በቅርቡ ፕሬዜዳንት ሆነው በተሰየሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የፍትሕ ሚኒስትሩን ጌዴዮን ጢሞቲዮስን (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል። የኢትያጵ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩትን ሃና አርዓያስላሴን ደግሞ የፍትህ ሚኒስትር አድርገው ሹመዋል። በተጨማሪም ፥ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ…
#HoPR

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የ5 ሚኒስትሮችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጸድቋል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመት እንፀድቅላቸው በደብዳቤ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው ሹመቱ በምክር ቤቱ እንዲጸድቅ የተደረገው።

ሹመታቸው የፀደቀው ፦

- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዎስ(ዶ/ር)፣
- የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያ ሥላሴ፣
- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣
-  የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ
- የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ናቸው፡፡

ምክር ቤቱ ሹመቱን በአንድ ተቃውሞ፣ በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጽድቀዋል።

@tikvahethiopia
#HopR

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በስብሰባው ላይ የምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅርበዋል።

አሁን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥያቄዎቹ ላይ ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

@tikvahethiopia
"  ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከኩፖን እና ከቶንቦላ ትኬት አጠቃላይ 23.7 ሚሊዮን ብር ቢሸጥም ባንክ አልገባም " - የፌደራል ዋና ኦዲተር

የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወሎ ተሪሸሪ ኬር የህክምናና ማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከወሎ ዩኒቨርስቲ የሥራ ሀላፊዎች፣ ከፌደራል ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ከተሪሸሪው የቦርድ አባላት ጋር በመሆን ከህብረተሰቡ የተሰበሰበውን ገንዘብ በማስመልከት በኦዲት ግኝት ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ?

ለወሎ ተርሸሪ ኬር የህክምናና  የማስተማሪያ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ የሚውል በየክልሎች ፣በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ቆንፅላ ጽ/ቤቶች በኩል ይሸጣል ተብሎ የተሰራጨው 9.3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የኩፖን ትኬት ጠፍቷል። የሥራ አመራር ቦርዱ አጠቃላይ 17 ሚሊዮን የእዳ ሥረዛ ማድረጉ በኦዲት ሪፖርት ተረጋግጧል።

በህብረተሰቡ ተነሳሽነት የተሰበሰበው ገንዘብ ያለ አግባብ ሲባክንና ለፕሮጀክቱ ለታለመለት ዓላማ ሳይውል መቅረቱ ተገቢ አይደለም።

ሆስፒታሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊና ለምስራቅ አፍሪካ ተስፋ ለነበረው ፕሮጀክት የሚሆን በኢምባሲዎች የተበታተነው የሎተሪ ዕጣዎችም የት እንደደረሱ አልታወቀም።

የኦዲት ግኝቱ መነሻ ህዝቡ ያነሳው ቅሬታ ስለሆነ ተጠያቂ መሆን ያለበት አካል መጠየቅ አለበት።

እስካሁን ባንክ ያልገባው ገንዘብ በማን እጅ እንዳለና ለምንስ ባንክ ገቢ እንዳልተደረገ እንዲሁም የተሸጡ ትኬቶችና ቦንዶች ባንክ ገቢ አልተደረጉም።

የሲቪል ማህበራት እንደገና ሲቋቋም ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ እንደገና መመዝገብ ቢኖርበትም አልተመዘገበም። ወሎ ዩኒቨርስቲ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባራት በቦርዱ የተወሰነውን ውሳኔዎችን መቀበል አለበት።

ቦርዱ ውሳኔ ከወሰነ በኋላ የህዝብ ገንዘብ ወጪ እያደረገ ነበር። ቦርዱ ስልጣን ሳይኖረው 17 ሚሊዮን ብር የእዳ ስረዛ አድርጓል። የተወሳሰቡ ችግርች ናቸው ያሉት።


የፌደራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ምን አሉ ?

🔴 ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከኩፖን እና ከቶንቦላ ትኬት አጠቃላይ 23.7 ሚሊዮን ብር ቢሸጥም ባንክ አልገባም። ቦርዱ የመሰረዝ ስልጣን ሳይኖረው 11.1 ሚሊዮን የሚጠጉ የኩፖን ትኬቶችን የጠፉ በሚል ሰርዟል።

🔴 ባንክ ያልገባው ገንዘብ ለማን እንደተሰጠ ስለሚታወቅ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ከሚፈልገው አካል ጋር በመሆን ገንዘቡን ለህዝቡ ይፋ ለማድረግ ወደ ባንክ መግባት አለበት።

🔴 ከ2010 ዓ.ም. እስከ 2016 ዓ.ም. የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከፕሮጀክቱ 9.1 ሚሊዮን ለተለያዩ የሥራ ማስኬጃዎች ተብሎ የወጣ ገንዘብ አለ ይህ መውጣት አልነበረበትም።

የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሚናስ ህሩይ ምን አሉ ?

🟠 ለፕሮጀክቱ የታቀደው ገንዘብ 3.5 ቢሊዮን ብር ነበር። የተሰበሰበው ግን 50 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው።

🟠 በተለያዩ አካባቢዎች የተበተነው የተንቦላ ሎተሪ ገንዘብ በቸልተኝነት ተረስቷል። ቀጣይ አቅማችን በሚችለው መንገድ ለማስመለስ እንሰራለን።
#HoPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሹመት : የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ መሐመድ እድሪስን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል። @tikvahethiopia
#ሹመት : ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

በዚሁ መሠረት ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) ማናቸው ?

➡️ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን እና አለምአቀፋዊነት ጽህፈት ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል።
   
➡️ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጋዜጠኝነት እና ተግባቦት የትምህርት ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።

➡️ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተማሩበት የትምህርት ክፍል በአስተማሪነት አገልግለዋል።

➡️ በውጭ ቋንቋዎች የማስተርስ ዲግሪ ባገኙበት አምቦ ዩኒቨርስቲ እና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አስተምረዋል። 

➡️ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12 ዓመታት የማስተማር እና የአመራርነት ልምድ አለቸው።

➡️ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ (UNISA) በኮሚዩኒኬሽን አግኝተዋል።

➡️ በተለያዩ የምርምር ህትመቶች ላይ የወጡ ጽሁፎችን በግላቸው እና በጋራ አሳትመዋል።

➡️ በብሉምበርግ የአፍሪካ ሚዲያ ኢኒሼቴቭ ስር የሚሰጠውን የፋይናንስ ጋዜጠኝነት ስልጠናን በስራ አስኪያጅነት መርተዋል በሌሎች ተቋማትም በማማከር ስራዎች ተሳትፈዋል። 

#HoPR #EthiopiaInsider

@tikvahethiopia