#ኢትዮጵያ #ረቂቅአዋጅ
በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ማቋረጥን የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ በጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ተካቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደቀረበ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
መሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ማቋረጥ የሚቻለው የታማሚዎችን የልብና የመተንፈሻ አካላት የአሠራር ሥርዓት መመለስ በማይችልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ፣ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ በረቂቅ አዋጁ በአንቀጽ 14 ተደንግጓል፡፡
ዝርዝር አፈጻጸም የጤና ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያ እንደሚወሰን ተመላክቷል፡፡
በማይድን በሽታ የሚሠቃዩና የሕይወታቸውን ፍፃሜ የሚጠባበቁ ሰዎችን ሥቃይ ለመቀነስ የሚሰጥ የጤና አገልግሎት በረቂቅ አዋጁ የተካተተ ሲሆን፣ በጤና ባለሙያ ወይም ሥልጠና ባገኘ ማንኛውም ግለሰብ (አካላት) ሊሰጥ እንደሚችል በረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 13 ተደንግጓል፡፡
" ሆስፒስ " እየተባለ የሚጠራው አገልግሎቱ የሚሰጠው ተገልጋይ የቅርብ ዘመዶቹ ስለታካሚው የበሽታ ክብደት፣ ደረጃና ስለሚያስከትው ውጤት ሊያውቁ እንደሚገባ በረቂቅ አዋጁ ተዘርዝሯል፡፡
በማንኛውም ሁኔታ የተገልጋይን ሕይወት የሚያሳጥር ሕክምና ተግባር መፈጸምን ይከለክላል ይላል፡፡
በረቂቅ አዋጁ የተቀመጠው በክፍል ሦስት በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሥር ከተዘረዘሩት ውስጥ፣ ስለሆስፒስ ወይም በማይድን በሽታ የሕይወታቸው ፍፃሜ የሚጠባበቁ ሰዎች የሚሰጥ አገልግሎትና በመሣሪያ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ በተመለከተ ይገኝበታል፡፡
የጤና አገልግሎቶች አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ በ12 ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን፣ ጠቅላላ ድንጋጌዎች ስለአጠቃላይ የጤና አገልግሎት፣ ስለመብትና ግዴታ፣ ስለጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ ስለልዩ የጤና አገልግሎቶችና ሌሎች 60 አንቀጾች ተካተውበታል፡፡
የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 5/2017 ሆኖ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጤና ማኅበራት ልማትና ባህል ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡
ሆስፒስ ማለት ምን ማለት ነው ?
በሕይወት መትረፍ የማይችሉ ሰዎች የሚሰጣቸው የሕክምና አገልግሎት ነው።
ታካሚው ስለሕመሙ እንዲያውቅ የሚደረግበትና ቤተሰብ (አስታማሚ) እንደሚቀበሉት የሥነ ልቦና ድጋፍና ምክር የሚገኙበትን አገልግሎት ያካተተ ነው።
የጤና ባለሙያዎች ምን አስተያየት ሰጡ ?
- ከዚህ ቀደም በመሣሪያ የታገዙ ታማሚዎች ሕይወታቸው እንደማይተርፍ እየታወቀ፣ መሣሪያውን ለመንቀል ከሥነ ምግባር አኳያ ለመወሰን ይከብድ ነበር።
- በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት የሚቋረጥበት ሁኔታ የሕግ ማዕቀፍ የለውም የተወሰነ የአንጎል ክፍል እየሠራ ነገር ግን መሣሪያው እየተነፈሰላቸው እስከ 2 እና 3 ዓመታት በሕክምና የሚቆዩ ታማሚዎች ይኖራሉ።
- በመሣሪያ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት የሚቋረጥበትን ሁኔታ ውሳኔ ለመስጠት ማረጋገጫ በሚሰጡ ሆስፒታሎች የሥነ ምግባር ኮሚቴ መኖር አለበት።
- ጉዳዩ በባለሙያ ብቻ መወሰን የሌለበት በመሆኑ በየጤና ተቋማቱ ራሱን የቻለ የሥነ ምግባር ኮሚቴ መቋቋም ይገባዋል።
(#ሪፖርተር_ጋዜጣ)
@tikvahethiopia

" ንፁኃንን ያለ አበሳቸው የማይገባቸውን ሰቆቃና ፍዳ እየከፈሉ ነው ! "
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ምን ጠየቀ ?
ከተጀመረ ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረውና በአማራ ክልል በሁለት ተፋላሚ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት እየደረሰ ያለውን የከፋ የመብት ጥሰት፣ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ምርመራ እንዲያደርጉበት በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠይቋል።
ከሰሞኑን ፎረሙ በጦርነት እየታመሰ ባለው የአማራ ክልል የጤና ተቋማትና አገልግሎት ላይ እየደረሰ ነው ላለው ቀውስ ምላሽ መስጫ ስትራቴጂ ይፋ አድርጓል፡፡
ይፋ በተደረገው ባለ 45 ገጽ ስትራቴጂ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ዩኒሴፍ፣ የአለም ጤና ድርጅት፣ የተመድ የሥነ ሕዝብ ድርጅት፣ የአማራ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተሳትፈውበታል፡፡
ፎረሙ በስትራቴጂክ ሰነዱ ምን አለ ?
➡️ የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ተደቅኖበታል።
➡️ በጦርነት ምክንያት በርካታ የጤና ተቋማት ሥራ አቁመዋል።
➡️ ከ1,100 በላይ ሠራተኞች ተፈናቅለዋል ፤ ተገድለዋል።
➡️ ከ5,000 በላይ ሰዎች ለፆታዊ ጥቃት ተጋልጠዋል። ይህ ቁጥር የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት ውስጥ ወደ ጤና ተቋም የመጡትና የተመዘገቡትን ብቻ የሚይዝ ነው።
➡️ በቀጠለው የደኅንነትና የፀጥታ ሥጋት የተነሳ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትና የልማት አጋሮች በክልሉ የሚያደርጉት እንቅስቃሴና ድጋፍ በጊዜያዊነት ለማቆም እየተገደዱ ነው።
➡️ በጦርነቱ በመንገድ መዘጋት ምክንያት ወደ ክልሉ የሚላኩ መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች እንዳይገቡ ከመገደቡ ባሻገር፣ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህር ዳር ወደ ዞንና ወረዳዎች ለመላክ አስቸጋሪ ሆኗል።
➡️ በርካታ የጤና ተቋማት በክልሉ ዝቅተኛውን የጤና አገልግሎት እንኳ ለህዝቡ ማቅረብ ተስኗቸዋል።
➡️ በሱዳን የሚካሄደውን ጦርነት ፈርተው ወደ አማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር መተማ የገቡ ሱዳናውያን ቁጥር ከ140 ሺሕ በላይ ደርሷል። የስደተኞች ቁጥር የጤና አገልግሎት ችግሩን አባብሶታል።
➡️ የኮሌራ በሽታ በክልሉ በ12 ዞኖችና በአራት የከተማ አስተዳደሮች ተከስቷል። የኮሌራን በሽታ ለመቆጣጠር አልተቻለም።
➡️ የአማራ ክልል ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት ውድመት ካለማገገሙ ባሻገር የሱዳን ጦርነት አማራ ክልል የቀጠለው ጦርነት፣ ድርቅ፣ ወባና ኩፍኝ ክልሉን አደጋ ውስጥ ጥለውታል።
➡️ መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ጨምሮ ሁሉም የሰብዓዊ ድጋፎች ያለምንም መስተጓጎልና ክልከላ ለሕዝቡ ተደራሽ እንዲሆን በጦርነት ውስጥ ያሉ ሁሉ ወገኖች ተባባሪ ሊሆኑ ይገባል።
የፎረሙ ዋና ጸሀፊ ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) ለሪፖርተር በሰጡት ቃል ፥ " ንፁኃንን ያለ አበሳቸው የማይገባቸውን ሰቆቃና ፍዳ እየከፈሉ በመሆኑ፣ ሁለቱም ውጊያ ላይ ያሉ ወገኖች ያለምንም መስተጓጎል የጤና እና ሌሎች የሰብዓዊ አገልግሎትና አቅርቦቶችን ለሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንዲደርሱ መፍቀድ አለባቸው " ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ፤ ሰነዱ በውጊያ ላይ ያሉ ሃይሎች ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ሕጎችን እያከበሩ ባለመሆኑ ይህን እንዲያከብሩ የሚጠይቅ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
አክለውም " የሴቶች መደፈር ትልቅ የሆነ ልብ የሚሰብር የመብት ጥሰት በመሆኑ ይህን ጉዳይ የመብት ተቆርቋሪዎች ሊመረምሩት ይገባል " ብለዋል፡፡
" የጤና ባለሙያዎች ደኅንነታቸው ሊከበር ይገባል ፤ የጤና ተቋማት በጦርነቱ ምክንያት በገጠማቸው የግብዓት አቅርቦት የደኅንነት ችግር የትራንስፖርት ችግርና የሰው ኃይል ችግር የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርጓቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" የጤና ተቋማት አምቡላንስ በጣም በሚያሳዝን መንገድ ከተፈለገው ዓላማ ውጭ እየዋለ በመሆኑ ይህ ሊታረም ይገባል " ብለዋል፡፡
" በሰነዱ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ተብሎ የቀረበው ሰነድ በጤና ተቋማት የመጣውን ብቻ የያዘ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው። የሰብዓዊ ቀውሱን ሙሉ መረጃ የማያሳይ ቁንጽል መረጃ በመሆኑ የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች የመብት ጥሰቱን እንዲመረምሩ ጥሪ እናቀርባለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ስትራቴጂክ ሰነዱ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ችግሩን ተረድቶ ጫና እንዲያደርግና ሕጎች እንዲከበሩ በሚል ታስቦ የተዘጋጀ ነው። #ሪፖርተር