TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ክብርን ተቀዳጀ።

በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ' የአቪዬሽን ኦስካር ' ተብሎ በሚጠራው የስካይትራክስ መድረክ ነው ይህን ክብር የተቀዳጀው።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት፣

🏆 በአፍሪካ የኢኮኖሚ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በመባል ተደራራቢ ድልን ተጎናጽፏል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በነገው ዕለት በኬንያ ምድር አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሏል። ይህ ሰልፍ የሀገሪቱ መንግስት ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅን የሚቃወም ነው። የተቃውሞ ሰልፉ አይቀሬ እንደሆነ ያወቀው የሀገሪቱ መንግሥትም በአገር ውስጥ ጉዳይ እና ብሔራዊ አስተዳደር ካቢኔ ሚኒስትር በኩል ሰልፉ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል። ዛሬ በሰጠው ይፋዊ መግለጫ ማንኛውም ተቃዋሚ የመንግስትም…
#ኬንያ

" ዉጡ ! ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ወጥታቹ መቃወም ትችላላችሁ " - ኪቱሬ ኪንዲኪ

የኬንያ መንግሥት፤ ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን የሚቃወም የተቃውሞ ሰልፍ " ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ መካሄድ ይችላል " ብሏል።

የኬንያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ' ሰላማዊ ይሁን ብቻ ወጥታችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ' ብሏቸዋል።

' ያልተለመደ ነው ' በተባለው እርምጃ ፤ የሀገር ውስጥ የደህንነት ካቢኔ ሚኒስትር ኪቱሬ ኪንዲኪ ፥ " ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ የህግ የበላይነትን እና ህዝባዊ ስርዓቱን እስካከበሩ ድረስ በእቅዳቸውን መሰረት መቀጠል / ወጥተው መቃወም / ይችላሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" የኬንያ መንግስት ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ በሰላማዊ መንገድ ፤ ትጥቅ ሳይታጠቅ ፦
° የመሰብሰብ ፣
° ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ፣
° የመምረጥ
° አቤቱታዎችን ለባለስልጣናት የማቅረብ የማይገረሰስ ህገ መንግስታዊ መብቱን ያከብራል ፤ እንዲፈጸምም ያደርጋል " ብለዋል።

ሰልፈኞቹ ወደ ሀገሪቱ ቤተ መንግስት ፣ በኃይል ወደ ፓርላማ ህንጻ እንዲሁም ወደ ሌሎችም የመንግሥት አካባቢዎች ለመጠጋት እንዳይዳፈሩ አስጠንቀቀዋል።

- ህግና ስርዓት አክብሩ ፤
- ህዝባዊ ስርዓቱን አክብሩ ፤
- የግል ፣ የመንግስት ንብረት አታውድሙ ፤
- መሰረተ ልማት አካባቢ አትጠጉ ፤
- የተከለከሉ ቦታዎች ጋር አትሂዱ፤
- የህዝባዊ አገልግሎት አታስተጓጉሉ፣
- እናተን የማይደግፏችሁ የተቃውሞ ሰልፍ መውጣት የማይፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን አታስፈራሩ፣ አታዋክቡ፣ አታስጨንቁ
- የጸጥታ ኃይል አባላትን አትተንኩሱ ... ከዚህ ውጭ ግን እንደልባችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ብለዋቸዋል።

ሚኒስትሩ ፤ የጸጥታ ኃይል ጥበቃ እና እጅባ ለማድረግ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሰልፍ ለማድረግ የሚሄዱበትን አቅጣጫ ቀደም እያሉ ማሳወቅ እንዳለባቸው ገልጸው ፀሃይ ከመጥለቋ በፊት ተቃውሞው እንዲያበቃ አደራ ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyKenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ " ዉጡ ! ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ወጥታቹ መቃወም ትችላላችሁ " - ኪቱሬ ኪንዲኪ የኬንያ መንግሥት፤ ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን የሚቃወም የተቃውሞ ሰልፍ " ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ መካሄድ ይችላል " ብሏል። የኬንያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ' ሰላማዊ ይሁን ብቻ ወጥታችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ' ብሏቸዋል። ' ያልተለመደ ነው ' በተባለው እርምጃ ፤ የሀገር ውስጥ የደህንነት…
#ኬንያ

ናይሮቢ፣ ሞምባሳን ጨምሮ በተለያዩ የኬንያ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መደረግ ጀምረዋል።

በወጣቶች መሪነት እየተካሄዱ ባሉት በነዚህ ሰልፎች ላይ መንግሥት ተጨማሪ ታክስ ለመጣል ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅ ሙሉ በሙሉ እንዲተወው እየተጠየቀበት ነው።

መንግሥት በረቂቁ ላይ አንዳንድ ማሻሻያ አደረጋለሁ ቢልም ተቃዋሚዎች ግን " የምን አንዳንድ ነው ? ሙሉ ረቂቁን ተወው " የሚል አቋም እንደያዙ ተሰምቷል።

ከዛሬው ሀገር አቀፉ የተቃውሞ ሰልፍ ጋርም በተያያዘ በናይኖቢ ያለው ሰልፍ ጥሩ እንዳልሆነ እና ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ሰው መጎዳቱ ተሰምቷል።

ባለስልጣናት የተቃውሞ ሰልፉን ለመበተን በ' ኬንያታ ጎዳና ኢመንቲ ህንፃ ' አጠገብ የአስለቃሽ ጭስ ማዘጋጀታቸው ፤ የአድማ ብተና ኃይሎችም ዱላ  እና አስለቃሽ ጭስ ተጠቅመው ተቃዋሚዎችን ሲያባርሩ እንደነበሩ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት እና ምክትል ፕሬዜዳንት በጋራ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ።

ስራ መልቀቂያውን ያስገቡት ፤ " በፍትህ እና የዳኝነት ሰርዓቱ ለውጥ ለማምጣት ያሰብናቸው ፣ ያቀድናቸው የጀመርናቸው ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚያስችል ሁኔታ ማግኘት ስላልቻልን ነው " ብለዋል።

ሰኞ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም የተፃፈው የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ በበርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ፤ ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የተፃፈው የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ ትክክለኛ መሆኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የፕሮቶኮል ሹምን በመጠየቅ አረጋግጧል።

የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዜዳንትና ምክትላቸው ከደም አፋሳሹ ጦርነት በኃላ በክልሉ በተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር  መሾማቸውን የገለፀው የፕሮቶኮል ሹሙ "  የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ ጥያቄው የቀረበላቸው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለጥያቄው ገና መልስ አልሰጡም  " ብሏል።   

የከፍተኛ ፍርድ ፕሬዜዳንት ፀጋይ ብርሃነ ገ/ተኽለ (ዶ/ር ) እና ምክትላቸው ገብረ ኣምላኽ የዕብዮ በላይ ባቀረቡት ስራ መልቀቅያ ደብዳቤ ፥

" በፍትህና የዳኝነት ስርዓቱ ለውጥ ለማምጣት ያሰብናቸው ፣ ያቀድናቸው የጀመርናቸው እና ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ማግኘት አልቻልንም።

በአጠቃላይ የፍትህ እና የዳኝነት የአስተዳደር ስርአት እያጋጠሙን ያሉ  ያልተሻገርናቸው ችግሮችና ማነቆዎች ለመቀነስ በሌላ መንገድ የበኩላችን እንደምንወጣ በመተማመን ፍላጎታችን ስራችንን ለመልቀቅ መወሰናችንን በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን።

ያቀረብነው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ እስከሚወሰድ በስራ ገበታችን እንደምንቆይ እናረጋግጣለን "
ብለዋል።

ለ14 ዓመታት የወረዳ የዞን እና የከፍተኛ ፍርድ ዳኛ በመሆን አገልግለው ከወራት በፊት ከከፍተኛ ፍርድ ቤት የስራ ገበታቸው የለቀቁ ዓወት ልጃለም የተባሉ የህግ ምሁር በቅርቡ TPM ለተባለ ሚድያ በሰጡት ቃለመጠይቅ ፥ " መንግስታዊ ፍርድ ቤቱ ጠንካራና ነፃ አይደለም ፤ ነፃና ጠንካራ የዳኝነት አካል የለም " ያሉ ሲሆን ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኃላ በቻ እሳቸው ጨምሮ ከ 50 በላይ ዳኞችና አቃቤ ህጎች ስራ መልቀቃቸው ተናግረዋል።

አሁን ላይ ፕሬዜዳንቱ እና ምክትላቸው በአንድ ጊዜ የስራ መልቀቅያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ በማህበራዊ የትስስር ገፆች " ፓለቲከኞቹ አላሰራ ካሉዋቸው ስራ መልቀቅ መብታቸው ነው " የሚሉና " ክልሉ ከጦርነት ማግስት በማገገም ሂደት እያለ ይህ መሰል ተግባር ከሙሁራን አይጠበቅም ፣ መታገስና መታገል ነበረባቸው " የሚሉ አስተያየቶች በመንሸራሸር ላይ ናቸው።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#Mekelle

" የሴቶች ጥቃትና እገታ ይቁም ! " በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

ሰላማዊ ሰልፉ በራስ ተነሳሽነት በተነሳሱ ወጣት ሴቶች የተደራጀ ሲሆን ዛሬ ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በመቐለ ዋና ዋና መንዶች ተካሂዷል።

የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች ፦

➡️ የሴቶች ጥቃት በቃል ሳይሆን በተግባር ይቁም !!

➡️ ፍትህ የማይሰጥ ፍትህ ቢሮ ይዘጋ !! 

➡️ የሴቶች ጥቃትና እገታ ይቁም !!

➡️ መንግስት አጥፊዎች የሚቀጣ ጥርስ ይኑርህ !!

➡️ የእምነት ተቋማት የሴቶች ጥቃትና እገታ አውግዙ !!

➡️ ፆታ ተኮር ጥቃት ይቁም !!

➡️ የዘውዲና የማህሌት ገዳዮች ወደ ፍርድ ይቅረቡ !!

➡️ የሴቶች መብት ይከበር !! 

የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

የሴቶች ጥቃትና እገታ እንዲቆም በራስ ተነሳሽነት በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱት ወጣት ሴቶች፣ ልጃገረዶች ፣ እናቶች አርቲስቶችና ታዋቂ ሴቶች ሲሆኑ በቂ የፀጥታ አካላት ጥበቃና እጀባ እንደተደረገላቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከቦታው ዘግቧል።

በትግራይ ከጦርነቱ ወዲህ ሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃትና እገታ መባባሱ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ሲሆን በቅርቡ ከ91 ቀናት እገታ በኃላ ተገድላና ተቀብራ የተገኘችው የተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ ብዙዎችን ያስቆጣ እንደሆነ ይታወሳል።

Photo Credit - DW TV

@tikvahethiopia            
#Ethiopia

የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት ፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት አዋጅ በ4 ተቃውሞ በ6 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።

አዋጁ ፤ ከዚህ በፊት በልማት ተነስተው የካሳ ክፍያ ያላገኙትን እና አሁንም ድረስ እየጠበቁ ያሉ የልማት ተነሺ ሰዎችን እንደማያካትት ተሰምቷል።
 
ከምክር ቤት አባላት ምን ተጠየቀ ? ምን ምላሽ ተሰጠ ?

Q. ከዚህ በፊት በርካታ የካሳ ክፍያዎች አዲሱ የካሳ ክፍያ እና ተነሺዎች መልሶ የሚቋቋሙበት አዋጅ እስከ ሚፀድቅ ድረስ እንዲቆዩ ተደርገዋል ይህ አዋጅ እንዴት ሊያስተናግዳቸው አስቧል ?
 
Q. ካሳ የመክፈሉ ኃላፊነት ለክልሎች በአዲሱ አዋጅ መስጠቱ ለሰራተኞቻቸው እንኳን ደሞዝ መክፈል ያልቻሉ ክልሎች ባሉበት ሰዓት እንዴት እንዲህ አይነት ክፍያ ሊከፍሉ ይችላል ?

Q. አንዳንድ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች በተመለከተ ለፌደራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት መስጠቱ አግባብነት የለውም። ይህ እንዴት ሊታይ ታስቦ ነው ለከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ችግሮችን ለማየት ስልጣን የተሰጠው ?


ሌላው ፤ ከዚህ በፊት ከፍተኛ የሆነ ምዝበራ ይፈፀም የነበረው በክልሎችና በወረዳዎች በሚጣሉ የካሳ ተመኖች ነበር አዋጁ ይህ እንዲባባስ ሊያደር ይችላል የሚል ስጋት ተነስቷል።
 
በተ/ም/ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፥ ከዚህ በፊት ከልማት ጋር በተያያዘ ያልተከፈሉ ክፍያዎች የሚዳኙት በቀድሞ አዋጅ መሰረት ነው ብለዋል።

አዲሱ አዋጅ የሚመለከተው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ያሉ የካሳ ክፍያዎች ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
 
በክልሎች ያለው በጀት ጉድለት እንዳለ ሆኖ ለልማት ተነሺዎች የሚከፈለው የካሳ ክፍያ የሚፈፀመው የፌደራል መንግስት ለክልሎች በሚሰጠው የበጀት ድጎማ እንደሆነ ተመላክቷል።

በክልሎች አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሲታቀዱ ለክልሎች የሚመደበው በጀት ላይ የካሳ ክፍያ ታሳቢ ይሆናል።
 
ከዳኙነቱ ጋር በተያያዘም ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሌላኛው የቋሚ ኮሚቴ አባል ፤ " ውሳኔውን ለመስጠት የተፈለገው ልማቶች ሲካሄዱ ፈጣን ፍርድ ለማሰጠትና ሀብትን ከምዝበራ ለመታደግ በማሰብ ነው " ብለዋል።

#ShegerFM
#HoPR
 
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ የአሜሪካንን ገመና ለዓለም ሁሉ ያጋለጠው ' ዊክሊክስ ' የተሰኘው ድረገጽ መሥራች ጁሊያን አሳንጅ ለዓመታት ከዘለቀው የፍርድ ቤት ሙግት በኋላ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በደረሰው ስምምነት ከእስር ተለቋል።

አሳንጅ ለአምስት ዓመታት ያህል በዩናይትድ ኪንግደም እስር ላይ የነበረ ሲሆን አሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጣት ስትሞግት ነበር።

ከፍተኛ ምስጢራዊ ወታደራዊ መረጃዎችን ለዓለም ይፋ በማድረግ ክስ የቀረበበት አሳንጅ ጥፋተኝነቱን ማመኑን ተከትሎ ከዩኬ ከእስር ቤት በነጻ ተሰናብቷል።

ዩኬን ለቆም ወደ አውስትራሊያ ሄዷል።

ዊክሊክስ ከጦርነት ፣ ከስለላና ከሙስና ጋር የተያያዙ ምሥጢራዊ እንዲሁም መንግሥታዊ ሪፖርቶችን ጨምሮ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰነዶችን ለዓለም ይፋ አድርጓል።

#StellaAssange
#BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ ናይሮቢ፣ ሞምባሳን ጨምሮ በተለያዩ የኬንያ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መደረግ ጀምረዋል። በወጣቶች መሪነት እየተካሄዱ ባሉት በነዚህ ሰልፎች ላይ መንግሥት ተጨማሪ ታክስ ለመጣል ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅ ሙሉ በሙሉ እንዲተወው እየተጠየቀበት ነው። መንግሥት በረቂቁ ላይ አንዳንድ ማሻሻያ አደረጋለሁ ቢልም ተቃዋሚዎች ግን " የምን አንዳንድ ነው ? ሙሉ ረቂቁን ተወው " የሚል አቋም እንደያዙ…
#Update

በኬንያ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ።

የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግሥት ያረቀቀውን አዲስ የታክስ ሕግ የተቃወሙ ኬንያውያን የአገሪቱን ፓርላማ ቅጥር ጊቢ ጥሰው ገብተዋል።

ፖሊስ በከፍተኛ ቁጥር የወጡ ተቃዋሚ ወጣቶችን ለመበተን ጥይት እና አስቀሽ ጭስ ተኩሷል።

እስካሁን ድረስ ቢያንስ 5 ሰዎች በጥይት የተመቱ ሲሆን ሁለቱ ሕይወታቸው አልፏል።

ከጥቂት ሰዓታት በፊት የአገሪቱ ም/ ቤት አባላት ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ገጥሞት የነበረውንና በተለያዩ ምርት እና አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ የሚጥለውን ረቂቅ ሕግ አጽደቀዋል።

" አዲሱ የቀረጥ ሕግ ኑሯችንን ያስወድድብናል " ሲሉ የቆዩት ኬንያውያን ወጣቶች ከአገሪቱ ፓርላማ ፊት ለፊት የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት በከፍተኛ ቁጥር ወጥተዋል።

ከፖሊስ ቁጥጥር አቅም በላይ የሆኑ አብዛኛዎቹ ወጣቶች የሆኑ ተቃዋሚዎች የፓርላማውን በር ጥሰው ገብተዋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ የፓርላማ አባላት ከምክር ቤቱ ምድር ቤት ለመደበቅ ሲሯሯጡም ተይተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፥ ተቃዋሚዎች አንደኛውን የፓርላማውን ክፍል በእሳት ማያያዛቸውን ቢቢሲ እና የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በኬንያ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ። የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግሥት ያረቀቀውን አዲስ የታክስ ሕግ የተቃወሙ ኬንያውያን የአገሪቱን ፓርላማ ቅጥር ጊቢ ጥሰው ገብተዋል። ፖሊስ በከፍተኛ ቁጥር የወጡ ተቃዋሚ ወጣቶችን ለመበተን ጥይት እና አስቀሽ ጭስ ተኩሷል። እስካሁን ድረስ ቢያንስ 5 ሰዎች በጥይት የተመቱ ሲሆን ሁለቱ ሕይወታቸው አልፏል። ከጥቂት ሰዓታት በፊት የአገሪቱ ም/ ቤት አባላት…
ፎቶ ፦ በኬንያ ናይሮቢ የተቆጡ ተቃዋሚዎች የሀገሪቱን ፓርላማ ጥሰው በመግባታቸው በርካታ የምክር ቤቱ አባላት ምድር ቤት (ግራውንድ) ለመደበቅ ሲሯሯጡ ታይተዋል።

የተ/ምክር ቤት አባላቱ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት የነበረውንና በተለያዩ ምርት እና አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ የሚጥለውን ረቂቅ ሕግ አጽድቀው ነበር።

ተቃውሞ የቀሰቀሰው የፋይናንስ ሕግ በ195 የምክር ቤት አባላት ድጋፍ ፣ በ106 የም/ ቤት አባላት ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ነው የጸደቀው።

በቀጣይ ወደ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ይመራል።

#Kenya
#KenyaParliament

@tikvahethiopia