TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

" ሰራተኞቹ ከሥራ ፈቃድ ወስደው ቤተሰብ ለመጠየቅ ሃና ማሪያም ተብሎ ወደ ሚጠራው ሰፈር ሲጓዙ ነበር " - የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 3 የሆቴል መስተንግዶ ሠራተኞች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው " ቀይ አፈር " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቀን 8፡20 ላይ ነው እንደደረሰ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

አንድ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ መንገድ ሲጠቀሙ የነበሩ እግረኞችን ገጭቶ ባደረሰው አደጋ ነው የ3ቱ ሰራተኞች ህይወት ያለፈው።

ሟቾቹ ሶስቱም ሴቶች ሲሆኑ ዕድሜያቸው ከ25-30 ይገመታል።

ሰራተኞቹ ከሥራ ፈቃድ ወስደው ቤተሰብ ለመጠየቅ " ሃና ማሪያም " ተብሎ ወደ ሚጠራው ሰፈር ሲጓዙ ነበር።

ከሟቾቹ ጋር አብራ ስትጓዝ የነበረች አንዲት ሴት እራሷን ስታ ሕክምና እየተከታተለች ትገኛለች።

በበዓል ወቅት መሰል አደጋ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እና በእርጋታ እንዲያሽከረክሩ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ፍ/ቤት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቀደ። " የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ፤ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግር እና ወከባ ፈጥረዋል " ተብለው የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱ ተሰማ። የፌደራል መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ቡድን፦ - ዮሃንስ ዳንኤል - አማኑኤል መውጫ፣…
ክስ ተመሰረተባቸው።

" የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል " በተባሉ 6 ግለሰቦች ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ክስ ተመሰረተ።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ የመሰረተው ክስ ምን ይላል ?

- አውሮፕላንን ያለአግባብ መያዝ ወንጀል፣
- የመንግስት ሰራተኛ የስራ ግዴታውን እንዳይፈጽም መቃወምና አለመታዘዝ የሚል የወንጀል ክስ ነው።

በተጨማሪም በ1ኛ ተከሳሽ ዮሃንስ ዳንኤል ላይ ብቻ " የአየር መንገዱን መልካም ስም ለማጉደፍ ተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒውተር ስርዓት አማካኝነት ማሰራጨት ወንጀል የሚል ክስ " አቅርቧል።

ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ፦
- ዮሃንስ ዳንኤል
- አማኑኤል መውጫ፣
- ናትናኤል ወንድወሰን፣
- ኤልያስ ድሪባ፣
- ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ናቸው። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ክስ ተመሰረተባቸው። " የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል " በተባሉ 6 ግለሰቦች ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ክስ ተመሰረተ። የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ የመሰረተው ክስ ምን ይላል ? - አውሮፕላንን ያለአግባብ መያዝ ወንጀል፣ - የመንግስት ሰራተኛ የስራ ግዴታውን እንዳይፈጽም መቃወምና አለመታዘዝ የሚል…
#Update

የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ታዘዘ።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ ክስ የቀረበባቸው 6 ግለሰቦች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ።

ግለሰቦቹ ፦
- ዮሃንስ ዳንኤል
- አማኑኤል መውጫ፣
- ናትናኤል ወንድወሰን፣
- ኤልያስ ድሪባ፣
- ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ናቸው።

ዐቃቤ ህግ በ6ቱ ግለሰቦች ላይ የወንጀል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

የቀረበባቸው ክስ ለተከሳሾች ከደረሰ በኋላ በተከሳሾች ጠበቆች በኩል ደንበኞቻቸው " የተከሰሱበት ድንጋጌ በመርህ ደረጃ ዋስትና ሊያስከለክል አይችልም " በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድ ጠይቀዋል።

ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ፤ የወ/መ/ስ/ህግ ቁጥር 67/ለ ጠቅሶ በልዩ ሁኔታ ዋስትና ሊያስከለክል ስለሚችል በሰበር ሰሚ ችሎት ትርጉም የተሰጠባቸው ማለትም ፦
➡️ ከወንጀሉ ከባድነትና ከክሱ ተደራራቢነት፣
➡️ ከጉዳዩ ባህሪና ከከባቢያዊ ሁኔታዎች አንጻር ዋስትና ሊያስከለክሉ የሚችሉበትን ትርጉም የተሰጠባቸው የሰበር ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥሮችን ጠቅሶ የዋስትና መብታቸው እንዲታለፍ ጠይቆ ነበር።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት የግራ ቀኝ የዋስትና ክርክሩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ብይን ሰጥቶበታል።

በዚህም ተከሳሾቹ ከቀረበባቸው ተደራራቢ ክስ አንጻር ቢወጡ የዋስትና ግዴታቸውን አክብረው ሊቀርቡ አይችሉም በማለት የጠየቁት የዋስትና ጥያቄን ውድቅ ተደርጎ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ታዟል።

ክሱን ለመመልከትም ለጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡ #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፐርፐዝብላክ ° " ሥራ ላይ የነበሩ ሱቆችም የቤት ኪራይ መክፈል ስላልተቻለ ሊዘጉ ነው " - የፐርፐዝ ብላክ ባለአክሲዮኖች ° " በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ስላለ ምንም  አይነት መግለጫ አንሰጥም " - ድርጅቱ የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ባለአክሲዮኖች፣ የድርጅቱ አካላት መታሰራቸውን ተከትሎ ድርጅቱ ላይ ባላቸው ሼር ላይ ሥጋትና ቅሬታ እንዳደረባቸው፣ ለቅሬታቸው አፋጣኝ ምላሽ  እንዲሰጣቸው በቲክቫህ…
በእነ ፍስሐ እሸቱ (ዶ/ር) ላይ የተመሰረተው ተደራራቢ ክስ ምንድነው ?

የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ በ10 ግለሰቦች እና ሁለት ድርጅቶች ላይ ክስ መስርቷል።

ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ ፦
1ኛ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱ (ዶ/ር)፣
2ኛ የተቋሙ ም/ስራ አስፈጻሚ ኤርሚያስ ብርሃኑ (ዶ/ር)፣
3ኛ የተቋሙ ቺፍ  ኦፕሬሽን ኦፊሰር እና የቦርድ አባል ወ/ሮ ኤፍራታን ነጋሽን ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ግለሰቦች እንዲሁም ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ እና ኖትር ዲዛይን ሃ/የተ/የግ/ማህበር ናቸው፡፡

ተከሳሾቹ ፦

➡️ በአዲስ አበባ ከተማ መሃል ሜክሲኮ ላይ በ100 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ  ባለ 3 መኝታ ቤት መኖሪያ ቤት በ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚሸጥ መሆኑን በሚዲያ በማስተዋወቅ ሰዎች ቤት ለመግዛት ሲሄዱ "መጀመሪያ ገንዘቡን አስገቡና ውሉን ትመለከታላችሁ " በማለት ከሌሎች ግብረዓበሮቻቸው ጋር በመሆን አሳሳች ቃላቶችን በመጠቀም፣

➡️ ሰዎች ገንዘቡን ካስገቡ በኋላ ደግሞ የአክሲዮን ግዢ ውል እንዲፈርሙ በማድረግ ምንም አይነት የግንባታ ቦታ ባልተረከቡበት ሁኔታ 2 ቢሊየን 234 ሚሊየን 200 ሺህ ብር በመሰብሰብ፣

➡️ ቤቱን ሰርተው ሳያስረክቡ በመቅረት

➡️ ግማሹን ገንዘብ ወደ ውጭ እንዲሸሽ በማድረግ፣

➡️ ኮሚሽን በመቀበልና በማታለል  ወንጀል ተጠርጥረው በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ሲከናወን ነበር።

በዚህ መልኩ ፖሊስ ሲያከናውነው የቆየው የምርመራ ማጣሪያ ሥራ መጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ዝርዝር ክሶችን በየደረጃቸው  አቅርቦባቸዋል።

ከቀረቡ ክሶች መካከል በአንደኛው ክስ ላይ ከ1ኛ - 9ኛ ባሉ ተከሳሾች ላይ እንደተመላከተው በኢፌዲሪ የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና (ለ) እንዲሁም  የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32 (2) ላይ የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል ክስ ይገኝበታል።

እንደ አጠቃላይ በቀረበው ተደራራቢ ክስ ዝርዝር ችሎት ለቀረቡ 4 ተከሳሾች ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን የተከሳሾቹ ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበውን ክስ ዝርዝር ተመልክተው ዋስትና ላይ ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ዋስትና ላይ የሚደረገውን የግራ ቀኝ ክርክር ለመከታተል ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ተዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾችን ፖሊስ በአድራሻቸው አፈላልጎ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ መስጠቱን #ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ፍስሕ እሸቱ (ዶ/ር) ሀገር ጥለው አሜሪካ ሀገር መግባታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia