TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ለ2017 የበጀት አመት ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ይጸድቃል። የዘንድሮ በጀት 1.8 ትሪሊየን ብር እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህ መጠን ባለፈው ሰኔ ወር ለ2017 በጀት አመት ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር አንጻር በእጥፍ የሚጨምር ነው፡፡ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ድጋፍ ማግኘት የጀመረው መንግስት ለውጡን ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጫናዎችን ለመከላከል…
#Ethiopia
የፌደራል መንግሥት 551 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ተናግረዋል።
ከዚህ ውስጥ 240 ቢሊዮን ብሩ " ለማኅበራዊ ድጋፍ " የሚውል ነው ብለዋል።
ተጨማሪ በጀቱ የፌደራል መንግሥቱን ሰኔ ወር ላይ ያጸደቀውን የ2017 ዓ.ም. በጀት 1.5 ትሪሊዮን ብር ገደማ ያደርሰዋል።
የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀትም ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ትሪሊዮን እንዲሻገር ያደርገዋል።
ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ምን አሉ ?
➡ የህህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከአንድ ወር በፊት አንድ ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት ማጸዕደቁን ያታወሳል።
➡ አሁን 551 ቢሊዮን አካባቢ የሚሆን ተጨማሪ በጀት ለምክር ቤቱ ይቀርባል።
➡ በተጨማሪ በጀት መልክ ለፓርላማ ከሚቀርበው ግማሽ ትሪሊዮን ብር ውስጥ 240 ቢሊዮን የሚሆነው ፦
° ለማኅበራዊ ድጋፍ፣
° ለሴፍቲኔት፣
° ለሠራተኛ ደመወዝ ጭማሪ፣
° ለመድኃኒት ድጎማ፣
° ለዘይት ድጎማ፣
° ለነዳጅ ድጎማ የሚውል ነው።
➡ ከወጪው በተጨማሪ የገቢ በጀትንም ለሕ/ተወ ምክር ቤት አቅርበን እናሳውጃለን።
➡ 563 ቢሊዮን የነበረው የፌደራል መንግሥት ገቢ ተከልሶ 851 ቢሊዮን ይሆናል። ይሄ የሚሆነው ግን አንድም የታክስ መጠን ሳይጨምረ ነው።
ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ፦
" ይሄንን ስናደርግ ተጨማሪ ታክስ በመጣል ወይም የታክስ ምጣኔ በመጨመር አይደለም መጨመር ያሰብነው። ኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን distortion ዝንፈት በማስተካከል ነው።
ታክስ ሳይከፍል ይከብር የነበረ ባለሃብት አሁን ቶሎ ወደ መስመር መግባት አለበት። ይሄንን የሚፈቅድ ነገር አይኖርም። ጠንካራ የሆነ enforcement ሥራ ይሠራል። "
#Ethiopia #FBC #BBC
@tikvahethiopia

#AddisAbaba
"መታወቂያ አምጡ" በማለት በመሳሪያ በማስፈራራት ዘርፈዋል የተባሉ ሁለት የፖሊስ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ረዳት ሳጅን ሬድዋን ሁሴን እና ኮንስታብል ሳሙኤል ድጉማ ይባላሉ።
ሰዎቹ የፖሊስ አባላት / ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የሐርቡ ፖሊስ ጣቢያ አባል ናቸው።
"ስልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል" ወንጀል ተከሰው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።
ሌሊት ላይ ለወንጀል መከላከል ሥራ በተሰማሩበት ቦታ ላይ ግለሰብን አግተው #በሽጉጥ_አስፈራርተው ንብረት ወስደዋል ነው የተባለው።
የክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መርማሪ እንዳለው ፥ ተጠርጣሪዎቹ ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ሌሊት በወንጀል መከላከል ሥራ ላይ ተመድበው ሲሠሩ መንገድ ላይ ያገኙዋቸውን አንድ የግል ተበዳይ " መታወቂያ አምጡ " በማለት ፖሊስ ጣቢያ እንደወሚወስዷቸው ገልጸው ግለሰቡ በኪሳቸው የያዙትን ሁለት ዘመናዊ ሞባይሎች በሽጉጥ አስፈራርተው በመደብደብ እንደወሰዱባቸው ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ከግለሰቡ የተወሰዱትን ስልኮች 2ኛ ተጠርጣሪ በመኖሪያ ቤቱ በሚተኛበት ፍራሽ ውስጥ ደብቆ መገኘቱን ጠቅሷል።
በዚህም መርማሪ " ስልጣንን ያለ አግባብ መገልገል " ወንጀል ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።
ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን ገልጸው ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።
መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ምርመራው ሳይጠናቀቅ በዋስ ቢወጡ የግል ተበዳዩን ሊያስፈራሩ ይችላሉ በማለት የዋስትና ጥያቄውን ተቃውሟል።
ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤት የ7 ቀን የምርመራ ማጠናቀቂያ ጊዜ ለመርማሪ ፖሊስ ፈቅዷል።
#AddisAbaba #FBC #JournalistTarikAdugna

#ጉምሩክ ➡️ “ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የኮንቴነር ዲመሬጅ በየቀኑ እየጨመረብን ነው ” - አስመጪዎች ➡️ “ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ” - ጉምሩክ ኮሚሽን አስመጪዎች ፣ ተግባራዊ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን የሚተካ ' አዲስ መመሪያ ' በማውረድ እስከዛሬ ሲከፍሉት ከነበረው ቀረጥ ከእጥፍ በላይ ካልከፈሉ እቃቸውን መውሰድ እንዳይችሉ እያደረጋቸው መሆኑን ለቲክቫህ…
#Update
" ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " - ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ
ጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ናቸው።
በዚህም ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።
ጉምሩክ ፤ " የሠነድ ምዝገባ እና ማጣራት ሂደቱን በአግባቡ እየሠራ ይገኛል " ብለዋል።
" የብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " ሲሉ አረጋግጠው " የቀረቡ ሠነዶች ያልተሟሉ እና ቀሪ ጉዳዮች ኖረው ተቀባይነት ያላገኙ ሠነዶች የሚስተናገዱት በዕለቱ የምንዛሪ ተመን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ ባለው የአሠራር መመሪያ መሠረት የገቢ ዕቃዎችን ሠነድ በመፈተሽ ወደ ሀገር እንዲገቡ እያደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።
" በምንዛሪ ግብይቱ ላይ ባለው ለውጥ ምክንያት የተለያዩ ጥያቄዎች አሉ " ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ " ከሕግና መመሪያ ውጭ የተሠራም ሆነ የሚሠራ ሥራ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።
" እኛ #የሥራ_መመሪያዎችን ለደንበኞቻችን ሁሉ የማሣወቅ ሥራ እየሠራን ነው ፤ በአሠራር ሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል " ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
#EthiopianCustomsCommission #FBC