TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Mekelle

" የሴቶች ጥቃትና እገታ ይቁም ! " በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

ሰላማዊ ሰልፉ በራስ ተነሳሽነት በተነሳሱ ወጣት ሴቶች የተደራጀ ሲሆን ዛሬ ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በመቐለ ዋና ዋና መንዶች ተካሂዷል።

የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች ፦

➡️ የሴቶች ጥቃት በቃል ሳይሆን በተግባር ይቁም !!

➡️ ፍትህ የማይሰጥ ፍትህ ቢሮ ይዘጋ !! 

➡️ የሴቶች ጥቃትና እገታ ይቁም !!

➡️ መንግስት አጥፊዎች የሚቀጣ ጥርስ ይኑርህ !!

➡️ የእምነት ተቋማት የሴቶች ጥቃትና እገታ አውግዙ !!

➡️ ፆታ ተኮር ጥቃት ይቁም !!

➡️ የዘውዲና የማህሌት ገዳዮች ወደ ፍርድ ይቅረቡ !!

➡️ የሴቶች መብት ይከበር !! 

የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

የሴቶች ጥቃትና እገታ እንዲቆም በራስ ተነሳሽነት በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱት ወጣት ሴቶች፣ ልጃገረዶች ፣ እናቶች አርቲስቶችና ታዋቂ ሴቶች ሲሆኑ በቂ የፀጥታ አካላት ጥበቃና እጀባ እንደተደረገላቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከቦታው ዘግቧል።

በትግራይ ከጦርነቱ ወዲህ ሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃትና እገታ መባባሱ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ሲሆን በቅርቡ ከ91 ቀናት እገታ በኃላ ተገድላና ተቀብራ የተገኘችው የተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ ብዙዎችን ያስቆጣ እንደሆነ ይታወሳል።

Photo Credit - DW TV

@tikvahethiopia            
#Tigray #Mekelle

ባለፉት 11 ወራት ብቻ በመቐለ 12 ሴቶች ሲገደሉ 80 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል።

የመቐለ ፓሊስ ከሀምሌ 2015 ዓ/ም እስከ ሰኔ 2016 ዓ/ም ባሉት 11 ወራት ግድያ ጨምሮ 4,340 ከባድና ቀላል የወንጀል ተግባራት በከተማዋ እንደተፈጸሙ አሳውቋል።

የተፈፀሙት ከባድና ቀላል ወንጀሎች በቁጥር ፦
 
➡️ የሴቶች ግድያ 12 

➡️ አስገድዶ መድፈር 80

➡️ ስርቆት 1,953

➡️ ድብደባ  583

➡️ ዝርፍያ 349

➡️ የመገደል ሙከራ 178

➡️ እገታ 10 

ፖሊድ ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ 170 የፓሊስ ኮሚኒቲዎች መቋቋማቸውን ገልጿል።

እየተፈፀሙ ያሉ የወንጀል ተግባራት ያልተለመዱ ናቸው ያለው ፖሊስ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ለመቆጣጠር ከወትሮው በተለየ የህብረተሰብ ተሳትፎ እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተሰማ።
 
በተለያዩ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት የተሳተፉ አካላት እና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አሳውቋል።

በትግራይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመንግስት እና ለህዝብም ድህንነት አስጊ የሆኑ ኢ-ህጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስተዳደሩ አመልክቷል።

ይህን ለመቆጣጠር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ በማጣራት ላይ መቆየቱን አሁን ላይ አብዛኞቹ የማጥራት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን አመልክቷል።

በዚህም መሰረት ፥ በተለያዩ ህገወጥ ተግባራት ላይ " እጃቸው አለበት " የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እርምጃ ወደመውሰድ መግባቱን ገልጿል።

በተለይ ዛሬ የብረታ ብረት ስርቆት በመሳሰሉ ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትን መያዝ መጀመሩን አስታውቋል።

ለጊዜው ምን ያህል ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ በዝርዝር አልታወቀም።

#Tigray
#Mekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተሰማ።   በተለያዩ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት የተሳተፉ አካላት እና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አሳውቋል። በትግራይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመንግስት እና ለህዝብም ድህንነት አስጊ የሆኑ ኢ-ህጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስተዳደሩ አመልክቷል። ይህን ለመቆጣጠር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ በማጣራት…
#Mekelle

መቐለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ 14 የመኪና የማደሪያ ቦታዎች (ፓርክ የሚደረግበት) 140 ባለቤትነታቸው ያልታወቁ ተሽከርካሪዎች ማግኘቱ የመቐለ ከተማ ፓሊስ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል።

ፖሊስ በመቐለ ከተማ የመኪና ማደሪዎች ድንገተኛ ፍተሻ አድርጎ ነበር።

በዚህም140 ባለቤታቸው ያልታወቁ ተሽከርካሪዎች ሊገኙ እንደቻሉ ገልጿል።

የተገኙት ተሽከርካሪዎች ባለቤትነታቸው ለማወቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሆነ አመልክቷል።

" ባለንብረት ነኝ " የሚል አካል ማረጋገጫ ማስረጃ ይዞ መቅረብ ይችላል ተብሏል።

የመቐለ ፓሊስ ከተሽከርካሪ ፣ ብረታብረትና ሌሎች ንብረቶች ጋር ተያይዞ የማጣራት ስራ በመስራት ላይ እንደሆነ ገልጿል።

የሚካሄደው ምርመራ ግኝቶች በየጊዜው ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሐምሌ 4 ባወጣው መግለጫ በክልሉ በቀላል እና ከባባድ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የማዋል ኦፕሬሽን መጀመሩ መግለፁ መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
 
#Mekelle

° " መንግስት ቃሉና መመሪያው ማክበር አለበት " - የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች

° " ወደ ላይ እንጂ ወደ ጎን የሚሰጥ የቤት መስሪያ ቦታ የለም " - የትግራይ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ


በመላ ትግራይ በተለይ በመቐለ የሚገኙ የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች ከቤት መስሪያ ቦታ ጋር በተያያዘ ከአንድ ሳምንት በላይ ወደ ክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት ምላሽ ለማግኘት ቢመላለሱም ሰሚ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

ትላንት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፅ/ቤት የተሰባሰቡት የ 3043 የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች ለጥያቄያቸው ምላሽ ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀርተዋል።

በቦታው የተገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮችና ጥያቄና የክልሉ መንግስት ምላሽ ተመልክቷል።

60,860 አባላት ያቀፉት 3,043 የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበራት ከጦርነቱ በፊት ተደራጅተው ህጋዊ እውቅና በማግኘት ለቤት መስሪያ የሚሆን ገንዘብ በባንክ ሲቆጥቡ መቆየታቸው ይናገራሉ።

ማህበራቱ ቢያንስ በአንድ ቤተሰብ 5 አባላት ቢኖሩ መንግሰት ቃሉ እንዲጠብቅ እየቀረበለት ያለው ጥያቄ የ300 ሺህ ሰዎች መሆኑን ጠቁመዋል።

ተወካዮቹ ፤ " እኛ በሦስተኛ ዙር የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር ስንደራጅ በክልሉ መመሪያ 4/2011 መሰረት ከኛ በፊት በሁለት ዙር እንደተስተናገዱት 70 ካሬ ለቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጠን ተሰማምተን ነው " ብለዋል።

የክልሉ አስተዳደር ግን ከጦርነቱ በኋላ ጥያቄያቸውን ላለመለስ ጀሮ ዳባ ልበስ ማለቱ እንዳሰዘናቸው በአደባባይ ወጥተው ገልፀዋል።

" የክልሉ አስተዳደር በመመሪያ 4/2011 የገባው ቃል ይተግብር " ተወካዮቹ ፥ በሚሰጣቸው 70 ካሬ ቦታ ቤት ለመስራት እንጂ ኮንደሚንየም ማለትም የጋራ መኖሪያ ቤት ለመስራት ቃል እንዳልፈፀሙ አስረድተዋል።

የማህበራቱ አመራሮች ከቀናት በፊት ለጥያቄያቸው ተገቢ ምላሽ ለማግኘት ለክልሉ ምክትል ጊዚያዊ አስተዳደር ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ጥያቄ አቅርበው ከክልሉ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በመነጋገር መልስ እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ቢሆንም አስከ አሁን የተሰጣቸው ምላሽ እንደሌለ ተናግረዋል።

ከአንድ ሳምንት በፊት የክልሉ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ አልማዝ ገ/ፃድቕ ለድምፂ ወያነ ትግራይ ጉዳዩ በማስመልከት በሰጡት ማብራርያ ፤ ማህበራቱ ከጦርነቱ በፊት ለእንያንዳንዱ አባል 70 ካሬ መሬት ለቤት መገንብያ እንዲሰጥ በሚፈቅደው መመሪያ መደራጀታቸው አምነዋል።

"ይሁን እንጂ ከአሁን በኋላ ወደ ላይ እንጂ ወደ ጎን የሚሰጥ የቤት መስሪያ ቦታ የለም ፤ ስለሆነም ማህበራቱ የሚሰጣቸው ቦታ G+4 ወደ ላይ የሚገነባ የጋራ መኖሪያ አፓርታማ ነው " ብለዋል።

የማህበራቱ ተወካዮች በቢሮ ሃላፊዋ መልስ እንደማይስማሙ ገልጸዋል።

ለፍትሃዊ ጥያቄያቸው ፍትሃዊ ምላሽ ለማግኘት በማለምም ትላንት ቅዳሜ ቀኑን ሙሉ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፅ/ቤት ጠብቀው የሚያናግራቸው የመንግስት የስራ ሃላፊ ባለመገኘቱ ነገ ሰኞ ጥያቄቸውን በሰላማዊ ሁኔታ ማቅረብ እንደሚቀጥሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle

የኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
 
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) ስርዓተ ቀብር ዛሬ በመቐለ ተፈጽሟል።

የቀብር ስነስርዓቱ በመቐለ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን የአርበኞች የመቃብር ቦታ ነው የተፈጸመው።

በቀብር ስነስርዓቱ የሟች ቤተሰቦች፣ የመቐለ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች ፣ የህወሓትን ጨምሮ የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም የትግል ጓዶቻቸው ተገኝተው ነበር።

የ3 ሴት ልጆች አባት የሆኑት ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) ባደረባቸዉ ህመም ምክንያት ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው መስከረም 24 / 2017 ዓ.ም በተወለዱ በ60 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

Photo Credit - Tigrai Communication & Demtsi Woyane

@tikvahethiopia