#Ethiopia 🇪🇹 #Africa #China
የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ቻይና ውስጥ ተሰባስበዋል።
በቻይና የተሰባሰቡት ለቻይና አፍሪካ የመሪዎች መድረክ ነው።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ሉዑካቸው ቻይና ይገኛሉ።
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፥ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ደማቅ አቀባበል እንዳደሩጉላቸው ገልጸዋል።
ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውንም አመልክተዋል።
" ኢትዮጵያ የቻይናን ያልተቋረጠ ዘርፈብዙ ድጋፍ በእጅጉ ታደንቃለች። " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ " እንደ ሀገር የተለያዩ ተግዳሮቶችን ብናስተናግድም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንደስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና ሌሎች ዘርፎች ትርጉም ያላቸው የለውጥ ርምጃዎች ተራምደናል " ብለዋል።
" በዚህ የእድገት ጎዳና የቻይና ኢንቨስትመንቶች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ፤ በቱሪዝም ብሎም በወረቀት እና እንደ ፐልፕ ያሉ ተያያዥ ግብዓቶች ኢንደስትሪንም ለማሳደግ እምቅ አቅም አለ። " ሲሉ ገልጸዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
@tikvahethiopia