TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Axum የአክሱም ኤርፓርት ሰኔ 2/2016 ዓ/ም ዳግም የበረራ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።  በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ  የሆነ ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ  ኤርፖርት ሰኔ 2 የመጀመሪያ ዳግም በረራውን ያደርጋል። እሁድ ሰኔ 2 በኤርፓርቱ ዳግም መደበኛ የበረራ  አገልግሎት ስነ-ሰርዓት ማስጀመሪያ ጥሪ የተደረገላቸው የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት እንደሚገኙ ቲክቫህ…
#Axum #Update
 
የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ ከሶስት ዓመት በኃላ ዛሬ እሁድ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት የመጀመሪያውን ይፋዊ የአውሮፕላን  በረራ አስተናግዷል።

የዳግም በራራ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት የክልል እና የፌደራል ባለስልጣናት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በቦታው የሚገኘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በላከው መረጃ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን አዲስ አበባ ተነስቶ ከቀኑ 6:00 ላይ አክሱም የደረሰው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-700 አውሮፕላን 140 ተጓዦች ይዟል።

ከተጓዦቹ ውስጥም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ፣ የፌደራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች ይገኙበታል።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ  አስተዳደር ፕረዜዴንት አቶ ጌታቸው ረዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

#Axum #Ethiopia #Tigray

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Axum

" በአሁኑ ሰዓት የተለየ አዲስ መመሪያና ክልከላ ባልወጣበት ፤ የነበረውን የአለባበስ ስርዓት የሚቀይር አዲስ ጥያቄ ባልቀረበበት ሁኔታ የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም " ሲል የትግራይ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮ ለአክሱም የትምህርት ፅህፈት ቤት በፃፈው ደብዳቤ ፤ " ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ምን ዓይነት አለባበስ መከተል እንዳለባቸው የሚያዝ የቆየ መመሪያ እና አሰራር አለን " ብሏል።

" ነባሩ የአለባበስ መመሪያ እና አሰራር እያለ የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም በከተማው በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ተለይቶ ያልነበረ የአለባበስ ህግ እንዲተገበር ያቀረበው ጥያቄ ልክ አይደለም "  ሲል ገልጿል።

" ከመ/ቤታችን የተላኩ ባለሙያዎች ለተነሳው ጥያቄ መፍትሄ ለማምጣት መግባባት ላይ ቢደርሱም ምክር ቤቱ ጥያቄውን እልባት እንዳላገኘ አድርጎ ቅሬታ ማቅረቡ ትክክል አይደለም " ሲል አመልክቷል።

በአሁኑ ሰዓት የተለየ አዲስ መመሪያና ክልከላ ስለሌለ የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው የአለባበስ ስርዓቱ በነበረው እንዲቀጥል ቢሮው አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ " ሙስሊም ተማሪዎች ከተፈቀወድ አለባበስ ውጭ ለብሰው (ሂጃብ አድርገው) መግባት ተከልክለዋል ፤ ከትምህርታቸውም ተሰተጓጉለዋል " ከተባለባቸው ትምህርት ቤቶች የአንዱን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ለማነጋገር ስልክ ቢደውልም በጉዳዩ ላይ ለሚድያ መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ገልፀዋል።

ትናንት የትግራይ አስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለሚዲያ መግለጫ ሊሰጥ ዝግጅት አድርጎ የነበረ ሲሆን ከላይ ያለውን የትምህርት ቢሮን መገለጫ ተስፋ በማድረግ ሊሰጠው ያሰበውን መግለጫ ለሌላ ጊዜ አስተላልፏል።

ይሁን እንጂ ዛሬም ተማሪዎች " ከተፈቀደው አለባበስ ውጪ ለብሳችኋል " በሚል ምክንያት ወደ ትምህርት መአድ እንዳይገቡ ተደርገዋል።

ጉዳዩ ብዙዎችን እንዳስቆጣ የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #Axum

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማሳሰቢያ ፥ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።

" ያልተመዘገበ አይፈተንም " ማለቱ ይታወሳል።

ከሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ ጋር ተያይዞ በአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተነሳው ውዝግብ ባለመግባባት ተቋጭቷል።

159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አገር አገር አቀፍ ፈተና ለማሳተፍ የሚያስችላቸው ፎርም ሳይሞሉ የተሰጠው የምዝገበ ቀነ ገደብ ዛሬ አልቋል።

ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተለው የቆየው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ጥር 6 ቀን 2017 ከሰዓት በኋላ ወደ አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር  ስዩም ካሕሳይ ደውሎ አግኝቷቸዋል።

ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" - በትምህርት ቤታችን ከተለመደው የአለባበስ ስርዓት የተለየ የተሰጠ የአለባበስ ትእዛዝ የለም።

- ሴት ሙስሊም ተማሪዎቻችን እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከትምህርት ቤቱ አመራር በአካል በመምጣት እንዲወያዩ ማስታወቅያ በመለጠፍና ስልክ በመደወል ጥረት ተደርጓል ለመምጣት ፍቃደኛ ኣይደሉም።

- የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮች ጉዳዩ እንዲረግብ ከትምህርት ቤታችን ፣ ከከተማዋ ከንቲባ ከአገር ሽማግሌ እና ከክልል ትምህርት ቢሮ ሰላማዊ ልመና ቢቅርብላቸውም ጉዳዩ ለማርገብ ፍቃደኛ አልሆኑም።

- በአጠቃላይ የፈተና ፎርም ያለ መሙላትና ያለ መፈተን ፍላጎቱ ከተማሪዎቻች ፍላጎት ውጪ የውጭ ተፅእኖ እና ግፊት አለበት።

- ልጆቻችን በቀላሉ በመግባባት ሊፈታ በሚችል ጉዳይ ከፈተና ውጪ መሆናቸው እንደ ርእሰ መምህርና ወላጅ እጅግ እሞኛል አበሳጭቶኛል " ... ብለዋል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ታህሳስ 22 ቀን 2017 ከህገ-መግስት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ክልከላ ውጪ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " ሂጃብ " እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ባወጣው ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ  ፥ " ፍትሃዊ ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልላችን የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የምንወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎችን ለህዝባችን እናሳውቃለን " ማለቱ ይታወሳል። 

ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ መሰረት ጥያቄዎቹ በሚመለከተው አካል ጀሮ ዳባ ልበስ መባላቸውን በማረጋገጡ በታህሳስ 30 ቀን 2017 ባወጣው አጭር መግለጫ ጉዳዩ በህግ እንዲታይ ክስ መመስረቱ ግልጽ አድርጓል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አመራሮች ስለ ጉዳዩ አሁናዊ ሁኔታ ተጨማሪ ማብራርያ እንዲሰጡ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

ከ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጭ የሆኑት 159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳይ ወዴት ያመራ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።

@tikvahethiopia