TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF
" የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን የላኩት ማስረጃ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ምክትል ሊቀመንበርና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅሬታ ደብደቤ አቀረቡ።
ምክትል ሊቀ-መንበሩ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም በህወሓት " በልዩ ሁኔታ " የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ዙሪያ ነው ለቦርዱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት።
" በህወሓት የምዝገባ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተላከው ደብዳቤ ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው በግለሰቦች የተላከ ነው " ብለዋል።
ም/ ሊቀ መንበሩ አቶ ጌታቸው ፥ " የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን በመሆን የፈረሙት እንጂ እኛ ለምዝገባ ብለን የፈረምነው ማንኛውም ሰነድ የለም " ሲሉ አክለዋል።
ስለሆነም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት አስመልክቶ ለተወሰኑ ግለሰቦች የሰጠው እውቅና የተጭበረበረ በመሆኑ ዳግም ሊያጤነው ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia