TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#OROMIA #PEACE

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ እንደመከሩ ተነግሯል።

በምክክሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ውይይቱ ልማትና ጸጥታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

በውይይቱ ፦

- የልማት ስራ ያለ ሰላም ውጤት አልባ እንደሆነ / ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ ፤

- ሰው ሰርቶ የሚበላው ፣ ወልዶ የሚስመው ሰላም ሲኖር እንደሆነ አጽንኦተ ተሰጥቶበታል ብለዋል።

" ሰላም ለመንግሥት ብቻ የተተወ ስላልሆነ እንዴት ነው አብሮ መስራት የሚቻለው ? " የሚለውም መነሳቱን አስረድተዋል።

" መንግሥት እና ሸኔ የጀመሩት ድርድር ፤ በተለያየ ምክንያት አኩርፈው ጫካ የገቡ ነፍጥ ያነገቡ ጓዶች አሉ ፤ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ዛሬ ነገ ሳይል እነዚህን አካላት ጠርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር አለበት ይህ ሲደረግ ደግሞ ለሰዎቹ እውቅና ተሰጥቶ የህግ ከለላ ተሰጥቶ ነው ውይይት መደረግ ያለበት " የሚለውም መነሳቱን ገልጸዋል።

" በመንግሥት በኩል ' ዛሬም ቢሆን ክፍት ነው እንነጋገራለን ፣ ችግሮችን በጋራ ተነጋግረን እንፈታለን ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አሁንም ቢሆን የክልሉ መንግሥት በውይይት ያምናል ብለዋል።

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ሙሉ ትኩረታችን ወደ ሰላም ማምጣት ነው ያለብን። የፈለግነውን ነገር በአዳራሽ መወያይት ይቻላል። ጥረቶች ብዙ ነው ያደረግነው አሁንም ለሰላም ክፍት ነን እኛ 3ኛ ዙር ይሁን፣ 5ኛ ዙር ይሁን ፣ 10ኛ ዙር ድርድሮች እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " ብለዋል።

#Ethiopia
#Oromia #VOA

@tikvahethiopia