TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በነገው ዕለት በኬንያ ምድር አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሏል። ይህ ሰልፍ የሀገሪቱ መንግስት ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅን የሚቃወም ነው። የተቃውሞ ሰልፉ አይቀሬ እንደሆነ ያወቀው የሀገሪቱ መንግሥትም በአገር ውስጥ ጉዳይ እና ብሔራዊ አስተዳደር ካቢኔ ሚኒስትር በኩል ሰልፉ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል። ዛሬ በሰጠው ይፋዊ መግለጫ ማንኛውም ተቃዋሚ የመንግስትም…
#ኬንያ

" ዉጡ ! ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ወጥታቹ መቃወም ትችላላችሁ " - ኪቱሬ ኪንዲኪ

የኬንያ መንግሥት፤ ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን የሚቃወም የተቃውሞ ሰልፍ " ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ መካሄድ ይችላል " ብሏል።

የኬንያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ' ሰላማዊ ይሁን ብቻ ወጥታችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ' ብሏቸዋል።

' ያልተለመደ ነው ' በተባለው እርምጃ ፤ የሀገር ውስጥ የደህንነት ካቢኔ ሚኒስትር ኪቱሬ ኪንዲኪ ፥ " ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ የህግ የበላይነትን እና ህዝባዊ ስርዓቱን እስካከበሩ ድረስ በእቅዳቸውን መሰረት መቀጠል / ወጥተው መቃወም / ይችላሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" የኬንያ መንግስት ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ በሰላማዊ መንገድ ፤ ትጥቅ ሳይታጠቅ ፦
° የመሰብሰብ ፣
° ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ፣
° የመምረጥ
° አቤቱታዎችን ለባለስልጣናት የማቅረብ የማይገረሰስ ህገ መንግስታዊ መብቱን ያከብራል ፤ እንዲፈጸምም ያደርጋል " ብለዋል።

ሰልፈኞቹ ወደ ሀገሪቱ ቤተ መንግስት ፣ በኃይል ወደ ፓርላማ ህንጻ እንዲሁም ወደ ሌሎችም የመንግሥት አካባቢዎች ለመጠጋት እንዳይዳፈሩ አስጠንቀቀዋል።

- ህግና ስርዓት አክብሩ ፤
- ህዝባዊ ስርዓቱን አክብሩ ፤
- የግል ፣ የመንግስት ንብረት አታውድሙ ፤
- መሰረተ ልማት አካባቢ አትጠጉ ፤
- የተከለከሉ ቦታዎች ጋር አትሂዱ፤
- የህዝባዊ አገልግሎት አታስተጓጉሉ፣
- እናተን የማይደግፏችሁ የተቃውሞ ሰልፍ መውጣት የማይፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን አታስፈራሩ፣ አታዋክቡ፣ አታስጨንቁ
- የጸጥታ ኃይል አባላትን አትተንኩሱ ... ከዚህ ውጭ ግን እንደልባችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ብለዋቸዋል።

ሚኒስትሩ ፤ የጸጥታ ኃይል ጥበቃ እና እጅባ ለማድረግ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሰልፍ ለማድረግ የሚሄዱበትን አቅጣጫ ቀደም እያሉ ማሳወቅ እንዳለባቸው ገልጸው ፀሃይ ከመጥለቋ በፊት ተቃውሞው እንዲያበቃ አደራ ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyKenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ " ዉጡ ! ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ወጥታቹ መቃወም ትችላላችሁ " - ኪቱሬ ኪንዲኪ የኬንያ መንግሥት፤ ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን የሚቃወም የተቃውሞ ሰልፍ " ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ መካሄድ ይችላል " ብሏል። የኬንያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ' ሰላማዊ ይሁን ብቻ ወጥታችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ' ብሏቸዋል። ' ያልተለመደ ነው ' በተባለው እርምጃ ፤ የሀገር ውስጥ የደህንነት…
#ኬንያ

ናይሮቢ፣ ሞምባሳን ጨምሮ በተለያዩ የኬንያ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መደረግ ጀምረዋል።

በወጣቶች መሪነት እየተካሄዱ ባሉት በነዚህ ሰልፎች ላይ መንግሥት ተጨማሪ ታክስ ለመጣል ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅ ሙሉ በሙሉ እንዲተወው እየተጠየቀበት ነው።

መንግሥት በረቂቁ ላይ አንዳንድ ማሻሻያ አደረጋለሁ ቢልም ተቃዋሚዎች ግን " የምን አንዳንድ ነው ? ሙሉ ረቂቁን ተወው " የሚል አቋም እንደያዙ ተሰምቷል።

ከዛሬው ሀገር አቀፉ የተቃውሞ ሰልፍ ጋርም በተያያዘ በናይኖቢ ያለው ሰልፍ ጥሩ እንዳልሆነ እና ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ሰው መጎዳቱ ተሰምቷል።

ባለስልጣናት የተቃውሞ ሰልፉን ለመበተን በ' ኬንያታ ጎዳና ኢመንቲ ህንፃ ' አጠገብ የአስለቃሽ ጭስ ማዘጋጀታቸው ፤ የአድማ ብተና ኃይሎችም ዱላ  እና አስለቃሽ ጭስ ተጠቅመው ተቃዋሚዎችን ሲያባርሩ እንደነበሩ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ የቀሰቀሰው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግን እንደሚያስቀሩት / እንደማይፈርሙበት አስታውቀዋል። ሩቶ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሱት ተቃውሞውን ተከትሎ ቢያንስ 20 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው። ፕሬዜዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ " ኬንያውያን በሕጉ ዙሪያ ያሰሙትን ተቃውሞ በደንብ ተከታትያለሁ፤ ስለዚህም ሕጉን እንደማይፈልጉት በግልጽ ተናግረዋል፤…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኬንያ

ምንም እንኳን ትላንትና የኬንያ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ በፋይናንስ ረቂቅ ሕጉ ላይ ፊርማቸውን እንደማያኖሩ እና ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንደተደረገ ቢያሳውቁም ዛሬም ተቃዋሚዎች አደባባይ ወጥተው ነበር።

ናይኖቢ ውስጥ የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጪስ ተኩሰዋል።

ወደ ፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት የሚወስደውን መንገድ ዘግተውታል።

ዛሬም በከተማይቱ በርካታ የንግድ ተቋማት ባደረባቸው ስጋት በራቸውን ሳይከፍቱ ነው የዋሉት።

ከናይሮቢ በተጨማሪ ሞምባሳና ኪሱሙ ተቃዋሚዎች አደባባይ ወጥተው ነበር።

ትላንት ሩቶ ውሳኔያቸው ካሳወቁ በኃላ ተቃዋሚዎች ፦
- ቀጣይ ወዳሉበት ቤተመንግስት እንመጣለን። ይጠብቁን !
- ' ከሃዲ ፣ ወንጀለኞች ' እያሉ በቴሌቪዥን ለተናገሩት ዋጋ ይከፍላሉ
- ስልጣን የህዝብ ነው
- ለውሳኔው አርፍደዋል
- አሁን ደግሞ የስልጣን መልቀቂያ ለማስገባት ይዘጋጁ !
- ስልጣን ለመልቀቅ ይዘጋጁ የሚሉ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሲያሰራጩ ነበር።

ኬንያውያን የፋይናንስ ረቂቁን " ኑሮ ያስወድድብልናል ፣ የስራ አጥነት እጅግ በከፋበት ሰዓት ግብር መጨመር አይገባም ፣ ተደራራቢ ግብር በቃን " በሚል ነበር ተቃውሞ የጀመሩት።

በወጣቶች በተመሩ የጎዳና ላይ ተቃውሞዎች ቢያንስ 20 ሰዎች ህይወታቸውን እጥተዋል። ተቃውሞው እየበረታ ሲመጣም ሩቶ " በቃ ረቂቅ ሕጉን ትቼዋለሁ " የሚል ውሳኔያቸውን አሳውቀዋል።

#Kenya

@tikvahethiopia
#ኬንያ

ባለፈው ሳምንት በኬንያ፣ ናይሮቢ አንድ ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በሚገኝ የቆሻሻ መጣያ ስፍራ የተቆራረጠ የሴቶች አካል በማዳበሪያ ተጥሎ ተገኝቷል።

የተቆራረጠው የሴቶች አካል ከተገኘ በኋላም ከ40 በላይ ሴቶችን መግደሉን ያመነ ግለሰብ መያዙን የኬንያ ፖሊስ ዛሬ አስታውቋል።

ባለቤቱን ጨምሮ 42 ሴቶችን መግደሉን ያመነው የ33 ዓመት ተጠርጣሪ የተያዘው በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ቢያንስ የ8 ሴቶች አስከሬን ከተገኘ በኋላ ነው።

ኮሊንስ ካሃሊሲአ የተባለው ይኸው ተጠርጣሪ እኤአ 2022 ጀምሮ ሴቶችን ብቻ እየለየ ሲገድል እንደቆየ ቃሉን መስጠቱን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪው በሰጠው ቃል " ውብ የሆኑ ሴቶችን " መግደል እንደሚመርጥ ጨምሮ ተናግሯል።

የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት " ለሰው ልጅ ሕይወት ምንም ደንታ የሌለው ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አውለናል " ብሏል።

ፖሊስ እንደሚለው ከሆነ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ያዋለው ከገደላቸው ሴቶች ከአንዷ ሞባይል ወደራሱ ስልክ ገንዘብ ከላከ በኋላ ነው።

ተጠርጣሪው ኮሊንስ የሚኖረው የሴቶቹን አስክሬን ሲጥል ከነበረበት የቆሻሻ መጣያ ስፍራ 500 ሜትር ርቀት ላይ ነው።

የዚህ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋል የተሰማው ባለፉት ቀናት ከቆሻሻ መጣያው ስፍራ የበርካታ ሴቶች የተቆራረጡ አካላት በማዳበሪያ ተጥሎ ከተገኘ በኋላ ነው።

የተገደሉት ሴቶች እድሜያቸው ከ18 እስከ 30 ሲሆን ሁሉም በተመሳሳይ መንገድ ነው የተገደሉት።

ግለሰቡ ወንጀሉን ለምን እንደፈጸመ ፖሊስ እያጣራ ሲሆን የአስክሬን ምርመራም እየተደረገ ይገኛል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia