TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አክሱም

🧕" እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው። ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን " - ተማሪዎች

➡️ " የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ከትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል " - የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

👉 " ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም " - የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

በትግራይ ፣ አክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላለፉት 2 ሳምንታት የራስ መሸፈኛ ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት መግባት እንደተከለከሉና በዚህም ከትምህርት ገበታ መውጣታቸውን የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ከሂጃብ መልበስ ጋር በተያያዘ በአክሱም በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውዝግቡ የጀመረው ጥቅምት ወር ነው።

ተቋሙ ለክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቆ አውንታዊ ምላሽ ቢሰጠውም በተግባር የተቀየረ ነገር ግን የለም።

የምክር ቤቱ ፀሀፊ ሓጂ መሓመድ ካሕሳይ ምን አሉ ?

" ፀጉራቸውን ሸፍነው ትምህር ቤት እንዲሄዱ ማየት ያልተፈቀደበት መታየት የለበትም ፀጉሯ የአንድ ሴት ይሄ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው።

ሃይማኖት ውስጥ ፖለቲካ አይገባም፣ ፖለቲካ በሃይማኖት አይገባም እየተባለ በአንቀጽ ተቀምጦ እያለ አሁን ፖለቲካ በሃይማኖት እየገባ ነው።

ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል የፀጉር መሸፈኛ ሂጃብ መጠቀም እንደሚችሉ በ2000 ዓ/ም የወጣ ሀገር አቀፍ መመሪያ አለ።

ስለዚህ ዝም ብለን የምናየው ነገር አይሆንም።

በአሁኑ ጊዜ በአራት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ወጥተዋል።

ዋናው ደግሞ 3 ወር ሲማሩ የነበሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና የኦንላይ ምዝገባ የሚደረግበት ወቅት ነው በዚህ ሳምንት ያልቃል የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች እስካሁን አልተመዘገቡም።

የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል፤ አልገቡም እስካሁን።

ችግሩ እንዲፈታ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ እና ከአክሱም ከተማ አስተዳደር ትምህርይ ፅ/ቤት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው " ብለዋል።


ተማሪዎች ምን ይላሉ ?

" በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመታት ከሌሎች  ተማሪዎች ወደኃላ ቀርተናል አሁን ደግሞ በሂጃብ ምክንያት ፈተና ሊያመልጠን ነው።

ፎርሙ እያመለጠን ነው። ሌሎች ተማሪዎች በሂጀብ ፎርም እንደሞሉ ነው የምናውቀው። እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው።

ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም ፤ መፍትሄው ደግሞ በጣም አስቸኳይ እና ዘላቂ መሆን አለበት። እስካሁን መብታችን እየተከበረ አይደለም " ብለዋል።

NB. የክልል ትምህርት ቢሮ እና የአክሱም ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምን አለ ?

ምክትል ርዕሰ መምህር ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሔር ፦

" ' ትምህርት ቤቶች ከሃይማኖት እና ከፖለቲካ ነጻ መሆን አለባቸው ' ይላል የትግራይ ክልል የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም።

ክርስቲያኑ መስቀል ወይም መጠምጠሚያ ፤ ሙስሊሙም ሂጀብ ወይም ኮፍያ ማድረግ አይፈቀድም። የትምህርት ቤቱ መለያ ዩኒፎርም ብቻ ነው መልበስ የሚገባው።

የተወሰኑ ተማሪዎች ሂጃባቸውን አናውልቅም ብለው ነበር አሁን ግን ተማሪዎች የትምህት ቤቱን መመሪያ ተከትለው እየገቡ ናቸው።

አሰራሩ ለዓመታት የቆየ ነው " ብለዋል።


አንድ በጉዳዩ ላይ ቃላቸው የሰጡ የክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኛ ፤ " በክልሉ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እየሆነ ያለው በ1995 የወጣ መመሪያ ነው በዚያ መመሪያ ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን መተዳደሪያ ማውጣት እንደሚችሉ ይደነግጋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ትግርኛ አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia