TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መምህራን

" ለልማት በሚል ከደመወዛችን እየተቆረጠብን ነው " - መምህራን

" እውነት ነው። ከህግ አግባብ ውጪ የመምህራን ደመወዝ እየተቆረጠ ነው " - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር

የደመወዝ በወቅቱ አመከፈል፣ የጥቅማጥቅም ክፍያ አለማግኘት ችግር ባልተቀረፈበት ሁኔታ፣ ያለፈቃዳቸው ከደመወዝ ለልማት በሚል እየተቆረጠባቸው መሆኑን መምህራን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረሩ።

መምህራኑ በሰጡት ቃል፣ " ለልማት በሚል እስከ 50 በመቶ ከደመወዛችን እየተቆረጠብን ነው። የወር አስቤዛን በቅጡ ከማይሸፍን ደመወዝ ላይ እየተቆረጠ እንዴት ቤተሰብ እናስተዳድር ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

ይህ የመንግስት ድርጊት ሰንበትበት እንዳለ ገልጸው፣ ጭራሽ ቤተሰብ ማስተዳደር አቅቷቸው በብድር እየማቀቁ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

መምህራኑ ያቀረቡት ቅሬታ እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበለት የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር፣ " እውነት ነው ችንሩን በደንብ ነው የምናውቀው "  ብሏል።

የማኀበሩ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አበበ በሰጡት ቃል፣ " በየክልሉ የተለያየ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ። ያለመምህራን ፈቃድ የደመወዝ  ቆረጣም በጣም #ትክክል ያልሆነ፣ #ጉልበተኝነት የበዛበት፣ #ሰሚ ያጣ ነው " ብለዋል።

ታዲያ ለቅሬታው ማኀበሩ ምን እየሰራ ነው ? ለሚለው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " ትክክል አይደለም ብለን እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድርሰናል። ባለፈው ነሐሴ ወር በነበረን ውይይት " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አሁንም በተለይ ዳውሮ ዞን የሚገኙ መምህራን እንደሚያለቅሱ፣ ማኀበሩም ለትምህርት ሚኒስቴር እንዳሳወቀ፣ ትምህርት ሚኒስቴርም ያለፈቃዳቸው ደመወዝ እንዳይቆረጥ ለክልሉ ትምህርት ቢሮ ደብዳቤ እንደጻፈ፣ ክልሉም ደመወዛቸው እንዳይቆረጥ ለሚመለከተው አካል እንዳሳወቀ አስረድተዋል።

" ዞኑ ላይ 'ለማዕከል ግንባታ' በሚል ለዛ ነው ደመወዛቸው እየተቆረጠ ያለው። መምህራኑም እዚህ ድረስ መጡ። እኛም ለእንባ ጠባቂ ተቋም ደብዳቤ ጻፍን። የተለያዩ አካላትን ለመድረስ ጥረት አደረጉ። ግን እንባ ጠባቂም ምን ያህል ኃላፊነቱን እንደተወጣ አላውቅም " ነው ያሉት።

" በእኛ በኩል ያላረግነው ነገር የለም " ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ " ግን አሁን ህግ የሌለ በሚስል ሁኔታ የመምህራን ደመወዝ እየተቆረጠ ነው " ብለዋል።

መምህራኑ ደመወዛቸውን ቀድመው ለተለያዩ ፕሮግራሞች ከፋፍለው የሚጠቀሙበት ብቸኛ ገቢያቸው እንደሆነ ገልጸው፣ " መካከል ላይ ደመወዝ ሲቆረጥ ምስቅልቅል ይወጣል " ሲሉ አስረድተዋል።

" ይህንን የማያይ ምን አይነት የዞን አመራር እንዳለ አይገባኝም በበኩሌ። እጅግ በጣም ጫፍ የወጣ ስልጣን መጠቀም እንደሆነ ነው የምረዳው። መምህራን እየተሰቃዩ ነው የሚያዳምጣቸው አጥተዋል " ሲሉ አክለዋል።

ምን ያህል መምህራን ናቸው ደመወዝ የተቆረጠባቸው ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ሽመልስ፣ " ለምሳሌ ዳውሮ ላይ የዞኑ መምህራን በሙሉ ተቆርጦባቸዋል። ኦሮሚያ ላይ የ230 ሺህ መምህር ይቆረጣል ደመወዙ " ነው ያሉት።

የሚቆረጠው መጠን በሁሉም ቦታ እንደየሁኔታው እንደሚለያይ አስረድተው፣ የክልል መንግስታት በማናለብኝነት ደመወዝ መቁረጥ አግባብነት እንደሌለው ቆም ብለው እንዲያስቡ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመምህራኑን ቅሬታ በተመለከተ ምን ሀሳብ እንዳለው በቀጣይ የመረጃ የምናደርሳችሀ ይሆናል።

#TikvahErhiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#መምህራን

" የአማራ ክልል ከማንም ጋር የሚወዳደር አይደለም ፤ መምህራን ጥይት በላያቸው ላይ እያፏጨ ነው ያስተማሩት " - ማኀበሩ

የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር / ኢመማ / በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ከባድ የሚባል ፈተና ለመጋፈጥ እየተገደዱ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

ቃሉን ለቲክቫህ የሰጠው ማኀበሩ፣ መምህራኑ በከፋ የጸጥታ ችግር ውስጥ ሆነው እየሰሩ ባለበት እንኳ ደመወዛቸው እየተቆረጠባቸው መሆኑን ገልጿል።

" የአማራ ክልል መምህራን የሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ወታደር፣ 'ፋኖ' እየሰፈሩ በዚያ ችግር ውስጥ ሆነው እንኳ መስዋዕትነት ከፍለዋል " ብሏል።

" አማራ ክልል ከማንም ጋር የሚወዳደር አይደለም " ያለው ማኀበሩ፣ ሚዲያዎች ግን ትኩረት እየሰጡት ባለመሆኑ ከአሁን ወዲያ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

በጣም ከአቅም በላይ በሆነባቸው አካባቢዎች ካልሆነ በስተቀር በጸጥታ ችግር ውስጥ የሚገኙት መምህራኑ ትምህርት እንዳይቋረጥ ጥረት ማድረጋቸውን አስረድቷል።

" ሱፐር ቫይዘር በሌለበት፣ የትምህርት መዋቅር እዚህ ግባ በሚባል ደረጃ በማይንቀሳቀስበት ሁኔታ አማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ኮሚትመንት ወስደው እየሰሩ ነው " ሲል አክሏል።

" የአማራ ክልል መምህራን ጥይት በላያቸው ላይ እያፏጨ፣ በላያቸው ላይ የጥይት ሀሩር እየተወረወረ ነው ያስተማሩ። ይሄ በደንብ መታወቅ አለበት " ነው ያለው።

" መምህራን በዚህ ኮሚትመንት ልክ እየሰሩ ደመወዛቸው እየተቆረጠ ነው " ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

" በአንድንድ ምክንያቶች ሁለት ወራት፣ ሦስት ወራት ደመወዝ የተቆረጠባቸው አሉ " ያለው ማኀበሩ፣ " ግን ያ ደግሞ ውዝፉ ጭምር እየተከፈለ ነው " ብሏል።

የ8ኛ ፣ 6ኛ፣ 12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች በቀጣይ የሚወስዱበት መንገድ እንዲመቻችም አሳስቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መምህራን " የአማራ ክልል ከማንም ጋር የሚወዳደር አይደለም ፤ መምህራን ጥይት በላያቸው ላይ እያፏጨ ነው ያስተማሩት " - ማኀበሩ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር / ኢመማ / በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ከባድ የሚባል ፈተና ለመጋፈጥ እየተገደዱ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ። ቃሉን ለቲክቫህ የሰጠው ማኀበሩ፣ መምህራኑ በከፋ የጸጥታ ችግር ውስጥ ሆነው እየሰሩ ባለበት እንኳ ደመወዛቸው እየተቆረጠባቸው…
🔈#መምህራን

" ብሔሩ ተቆጥሮ ያልተፈናቀለ መምህር የለም !! " - የኢትዮጵያ
መምህራን ማኅበር

በተለያየ ጊዜ በብሔራቸው አማካኝነትያ ከተለያዩ ክልሎች የተፈናቀሉ
መምህራን በሥራ አጥነት ሳቢያ የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር (ኢመማ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለልጿል።

የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አበበ በሰጡት ቃል፣ " ትግራይ ክልል ዝግ ሆኖ የቆዬ አካባቢ ነው፡፡ ከዚያ አንጻር የተፈናቀሉ
መምህራን አሉ " ብለዋል፡፡

" የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሥራ ፈትተው የተቀመጡ
መምህራን አሉ። የትግራይ ክልል መምህራን ሆነው ከአማራ ክልል የተፈናቀሉ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ያሉም አሉ " ሲሉ ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡

" ኮይሃ የሚባል አካባቢም የትግራይ ክልል ተወላጆች ሆነው ግን አፋር ክልል ይሰሩ የነበሩ ተፈናቅለው ሥራ ፈትተው የተቀመጡ
መምህራን አሉ " ሲሉ አክለዋል።

" በትግራይ ክልል ይሰሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጅ መምህራንም ቢሆኑ ተፈናቅለው ጎንደር የተቀመጡ አሉ " ያሉት አቶ ሽመልስ፣
መምህራን የትም አካባቢ ሂደው መስራት እንዳለባቸው ቢታመንም ችግሮች ግን ጎልተው እየተስተዋሉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም እንዲሁ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው ለመውጣት የተገደዱ
መምህራን እንደነበሩ አስታውሰው፣ " ብሔሩ ተቆጥሮ ያልተፈናቀለ መምህር የለም " ብለዋል፡፡

" በተለያዩ ጊዜያት ችግራቸው እንዲፈታ፣ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሳውቀናል" ሲሉ ማኅበሩ ያደረገውን ጥረት አስረድተዋል፡፡

" ለትግራይ ትምህርት ቢሮ አሳውቀናል፡፡ ትግራይ ክልልም የሰው ኃይል እጥረት አለና ቀጥራችሁ አሰሯቸው የሚል ሃሳብ ነው እያነሳን ያለነው " ብለዋል፡፡

መምህራን ያለምንም ፈቃዳቸው በተለያየ መንገድ ደመወዝ እንደሚቆረጥባቸው ፣ የደረጃ እድገት እየተሰራላቸው እንዳልሆነ ማኅበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#ወላይታዞን “ ከ1,000 በላይ መምህራንና የቢሮ ሠራተኞች የሐምሌ ደመዎዝ አልተከፈለንም ” - የወላይታ ዞን መምህራን  “ በአራት ወረዳዎች ሙሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው ” - የዞኑ ትምህርት መምሪያ በወላይታ ዞን የሚገኙ መምህራን የሐምሌ 2016 ዓ/ም ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው፣ በዚህም የትምህርት ሥራ ሙሉ ለሙሉ እንዳልተጀመረ መምህራኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ክፍያ አለመፈጸሙን…
🔈#መምህራን

በወላይታ ዞን መምህራን በፖሊስ እየታሠሩ መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል።

እስሩ የተፈፀመ ያለድ መምህራኑ ከደሞዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታቸውን ለማስገባት መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።

ፖሊስ መምህራኑን የሚያስረው " አመፅ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል፤ የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል " በሚል መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል።

መምህር ዳንኤል ፋልታሞ በዳሞት ወይዴ ወረዳ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በእንግሊኛ ቋንቋ መምህርነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

መምህሩ በዞኑ ፖሊስ አባላት እስከታሠሩበት እስካለፈው ሰኞ ድረስ የመምህራን ደሞዝ እንዲከፈል ለመጠየቅ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንደነበሩ የሚያውቋቸው የስራ ባልደረቦቻቸው ገልጸዋል።

መምህሩን ሌሊት ፖሊሶች ከቤት ይዘዋቸው እንደሄዱ ነው የ3 ልጆች እናት የሆኑት ባለቤታቸው ለሬድዮ ጣቢያው የጠቆሙት።

ፖሊሶች ሌሊት 9 ሰዓት ላይ ወደ ቤት እንደመጡ የጠቀሱት የመምህሩ ባለቤት " በወቅቱ ምንም የተፈጠረ ነገር አልነበረም። ቤተሰቡ በሙሉ በእንቅልፍ ላይ ነበር። ቤቱን አስከፍተው ከገቡ በኋላ አልጋ እና ፍራሽ ሳይቀር ፈትሸው ምንም ሊያገኙ አልቻሉም። በመጨረሻም ግን ባለቤቴን ይዘውት ሄዱ " ብለዋል።

ለደህንነታችን ሲባል ስማችን አይጠቀስ ያሉ ሌላ ሁለት የዚሁ ወረዳ ነዋሪዎች ባሎቻቸው ደሞዝ ይሰጠን ብለው የዳቦ ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ታሰረውብናል ብለዋል።

" ፖሊሶች ወደ ቤት ሲመጡ ምንም አይነት የፍርድ ቤት መያዣ ወረቀት አላሳዩም " ያሉት የመምህራኑ ቤተሰቦች " የተሳሳተ መረጃ አሰራጭታችኋል " በሚል መያዛቸውን ከአንድ ፖሊስ አባል መስማታቸውን ተናግረዋል።

" የመምህራን ደሞዝ ይከፈል " በሚል የፊርማ ማሰባሰብ ስራ ሲያከናውኑ ከነበሩት መካከል 3 በቅርብ የሚያውቋቸው መምህራን መታሰራቸው የተናገሩ አንድ የዳሞት ወይዴ ወረዳ መምህር አስተባባሪዎቹ ከመታሠራቸው በፊት " እረፉ " የሚል መልዕክት ከወረዳው አመራሮች ተልኮባቸው እንደነበር ጠቁመዋል።

የወረዳው እና የዞን ኃላፊዎች ለቀረበው ክስ ምላሽ አልሰጡም።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ሰብሳቢ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ ለሬድዮ ጣቢያው ፤ " መምህራን ደሞዝ የመጠየቅ መብት መንግሥትም የመክፈል ግዴታ አለበት። የደሞዝ ጥያቄ በማቅረባቸው እሥርና ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል የሚል መረጃ እስከአሁን እኛ አልደረሰንም። ነገር ግን ድርጊቱ ተፈጽሞ ከሆነ ትክክል አይደለም። እኛም የምንታገለው ይሆናል " ብለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM