TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቅሬታ “ እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው #የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባ ፈልጎ ነው ? ”- እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢ እናት 2012 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር አማካኝነት መኪና ለማስመጣት ገንዘብ ሲቆጥቡ የነበሩ ከ40 በላይ በሆኑ ማኀበራት ሥር የሚገኙ ከ2 ሺህ 800 በላይ ቆጣቢዎች፣ ውል የገባላቸውን መኪና አስመጪ…
#Update

ኦክሎክ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማሕበር “ ገንዘብ ተጨምሮብናል ” በማለት እያለቀሱ ቅሬታ ላቀረቡ የታክሲ ቆጣቢዎች ምን ምላሽ ሰጠ ?

የመኪና ቆጣቢዎች በ " ኦኮሎክ ሞተርስ " ላይ ያላቸውን ቅሬታ በገለጹበት ወቅት እያለቀሱ መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

አንዲት እናት፣ “ እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው #የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባ ፈልጎ ነው? ” ሲሉ እያለቀሱ መናገራቸው መረጃ አድረሰናችሁ ነበር።

ሌሎች እናቶች፣ አባቶች እያለቀሱ ያላቸውን ቅሬታ አሰምተዋል።

ቆጣቢዎች ፦

➡️ " ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር (ኦክሎክ ሞተርስ) መኪናውን በወቅቱ አላስረከበንም "

➡️ " የገንዘብ ጭማሪ አደረገብን " ላሉት ቅሬታ ምላሻችሁ ምንድነው ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኦክሎክ ሞተርስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሳሁንን ጠይቋል።

የኦክሎክ ሞተርስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሳሁን ፦

“ እኔ እዚህ ላይ ትኩረት አድርጌ መልስ መስጠት እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም ' በእናንተ ድርጅት እዳለቀሱ ነው ' የሚለው የተሳሳተ ግንዛቤ ነው የሚል ሙሉ አቋም አለን። 

በውላችን መሠረት 35 ፐርሰንት ለእኛ ይከፍላሉ ውሉን ሲዋዋሉ። ከዚያ መኪናው ከመምጣቱ ከአንድ ወር በፊት 65 ፐርሰንት ከፍሎ 100 ፐርሰንት ሲሞላ መኪናውን ይወስዳል።

ስለዚህ አልቅሰዋል የተባሉት እናትም ይሁኑ አባት 35 ፐርሰንት ለድርጅታችን ከፍለው፣ 65 ፐርሰንትም ወይ ከአበዳሪ ድርጅት ወይ ከራሳቸው ካሽ ከፍለው መኪና ሳንሰጥ ቀርተን ነው ወይ ያለቀሱት ? ወይስ 35 ፐርሰንት ወይም 20 ፐርሰንት ከፍያቸሁና ስጡኝ ነው ጥያቄው ? ”

ይሄ ነው ትክክለኛ ያልሆነው። ያለቀሰ ሰው ሁሉ ትክክለኛ ነው ማለት አይደለም። ያላለቀሰ ሰው አይ ተስማምቷል ማለት እንዳልሆነው ሁሉ” ብለዋል።

1.5 ሚሊዮን ተጨሞሮብኛል ያሉትን ቅሬታ አቅራቢ ቆጣቢ እናትን በተመለከተም ፦ “ እኝህ እናት 1.5 ሚሊዮን ብር ተጨመረብኝ ካሉ እንግዲህ እኔ ደጋግሜ ነው የምናገረው ወይ መኪና ቀይረዋል ” ሲሉ መልሰዋል።

ያሉት 1,500 ተመዝጋቢዎች እንደሆኑ ፣ ከዚህ ውስጥ 400 የሚሆኑት 35 ፐርሰንት እንደከፈሉ፣ አሁንም 200 መኪናዎች እንዳሉት ማኀበራቱ ቀሪውን ከፍለው መውሰድ እንደሚችሉ ኦክሎክ ሞተርስ አስታውቋል።

#TikvahaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia