#Ethiopia
የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎችን በጋራ ገንብተው በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ አክሲዮን ማኅበራት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የዲቪደንድ (የትርፍ ድርሻ) ታክስን ጨምሮ የተለያዩ የግብር ዓይነቶችን እንዲከፍሉ ወስኗል።
በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎችን ገንብተው በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ አክሲዮን ማኅበራት የሕንፃውን ሱቆች በማከራየት ከሚያገኙት ገቢ ላይ ለሚገኙበት ከተማ ወይም የአካባቢ አስተዳደር የኪራይ ገቢ ግብር ብቻ ሲከፍሉ ቆይተዋል።
ሚኒስቴሩ በአክሲዮን ማኅበራት ባለቤትነት ሥር የሚገኙና የሚተዳደሩ የንግድ ማዕከላት ላይ ጥናት ያካሄደ ሲሆን የጥናቱ ግኝትም ፣ አክሲዮን ማኅበራቱ በሕግ የተጣለባቸውን ግብር በተገቢው መንገድ እየተወጡ አለመሆናቸው ያረጋገጠ ነው ተብሏል።
ገቢዎች ሚኒስቴር በጥናት የደረሰባቸውን ግኝቶች መሠረት በማድረግ ሊወሰዱ ይገባል ያላቸውን የማስተካከያ ዕርምጃዎች የተመለከተ ምክረ ሐሳብ ለመንግሥት አቅርቦ በቅርቡ ተቀባይነት ማግኘቱ ተጠቁሟል።
በዚህም መሠረት ፥ በአክሲዮን ተደራጅተው የተገነቡና በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎች ባለቤት አክሲዮን ማኅበሩ በመሆኑ፣ የንግድ ማዕከሉን የሚመለከቱ የግብር ግዴታዎች ላይ ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት ተወስኗል።
በመሆኑም በንግድ ማዕከልነት በሚያገለግለው ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን በማከራየት የሚገኘው ገቢ ላይ በግብር አዋጁ መሠረት የሚጣለውን የኪራይ ገቢ ግብር እንደ ከዚህ ቀደሙ በከተማ አስተዳደሮች እንደሚሰበሰብ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ይሁን እንጂ ሚኒስቴሩ ባካሄደው ጥናት አክሲዮን ማኅበራቱ በሚያስተዳድሯቸው የንግድ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ኪራይ ተመን ፦
- ከወቅታዊ ገበያው በእጅጉ አነስተኛ መሆኑ፣
- በርከት ያሉ ማኅበራትም በንግድ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን በርካሽ ዋጋ ለማኅበሩ አባላት እንዳከራዩ ፣
- ሌሎች በርከት ያሉ አክሲዮን ማኅበራት ደግሞ የባለቤትነት ማስተላለፍ ሥርዓቶችን ሳይከተሉ በንግድ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን እንደ አክሲዮን ድርሻ ለማኅበሩ አባላት አከፋፍለው መገኘታቸው ተመላክቷል።
በመሆኑም ፣ ከ2016 ዓ.ም. የግብር መክፈያ ወቅት ጀምሮ በንግድ ማዕከላቱ ውስጥ የሚገኙ ሱቆች የኪራይ ተመን በገበያ ዋጋ ተሰልቶ የኪራይ ገቢ ግብር እንዲከፍሉ መወሰኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#CBE የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምን አለ ? መጋቢት 7 / 2016 ዓ/ም ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ያለአግባብ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር ፤ በዚህም በርካታ ግለሰቦች በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የወሰዱትን የገንዘብ ልክ እየመለሱ እንደሆነ ገልጿል። ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ወደ #ቤቲንግ (የስፖርት ውርርድ) ተቋማት በማዛወራቸው መመለስ እንደተቸገሩ…
" የመጨረሻ ተጨማሪ 3 ቀን ሰጥተናል " - ንግድ ባንክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 222 ግለሰቦች እስካሁን የወሰዱትን ገንዘብ መመልስ እንዳለጀመሩና እነዚህ ግለሰቦች ጋር ያለው ገንዘብ 4,034,979 ብር ከ75 ሳንቲም መሆኑን ገልጿል።
ባንኩ አሁንም ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ የመጨረሻ የ3 ቀናት ስለመስጡትን አሳውቋል።
ባንኩ ከዚህ ቀደም ሙሉ በሙሉና በከፊል ገንዘብ ያለመለሱ እንዲመልሱ 2 ጊዜ የመጨረሻ ያለውን ቀነ ገደብ አስቀምጦ እንደነበር ይታወሳል። የስም ዝርዝርም ይፋ አድርጎ ነበር።
ባንኩ አስተላልፎ የነበረውን ጥሪ ተከትሎ ፦
➡ ያለ አግባብ ከተወሰደው ገንዘብ ውስጥ ከባለፈው ሳምንት ተጨማሪ ብር 117,612,000 ብር ከ59 ሳንቲም በመሰብሰቡ የተከፈለ አጠቃላይ ገንዘብ 86% መድረሱን እና ያልተመለሰ ገንዘብ ወደ ብር 112,389,455 ብር ከ12 ሳንቲም ዝቅ ማለቱን ገልጿል።
➡ ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው ክፍያ የጨረሱ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 10,857 ከፍ ማለቱን ገልጿል።
➡ የወሰዱትን ገንዘብ መመለስ ያልጀመሩ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 222 ዝቅ እንዳለና ከነዚህ ግለሰቦች የሚጠበቅ ገንዘብም ወደ ብር 4,034,979 ብር ከ75 ሳንቲም ዝቅ ማለቱን ጠቁሟል።
ባንኩ ፥ አንድ አንድ ግለሰቦች ወደ ተለያዩ ተቋማት ያስተላለፉትን ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጣቸው ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ገልጿል።
ይህ ተከትሎ ከነገ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተጨማሪ 3 ተከታታይ ቀናት እንደተሰጠ አሳውቋል።
ባንኩ ፤ የወሰዱትን ገንዘብ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ወደ ከፈቱት የዲጂታል ሒሳቦች አስተላልፈው አሁን ላይ ወደ ባንኩ ለመመለስ የተቸገሩ ግለሰቦችም ካሉ ወደ ማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፎች ቀርበው ዝርዝር ሁኔታውን እንዲያሳውቁ ብሏል።

ታዳጊዋ የት ናት ? በትግራይ ዓድዋ ከተማ የታገተችውና ለማስለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊዋ ማህሌት ተኽላይ እስካሁን እንዳልተገኘች እና ድምጿም እንዳልተሰማ ቤተሰቦቿ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። እገታው ከተፈፀመ 7 ቀናት ሆኖታል። የ16 አመቷ ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ መጋቢት 11 ባጃጅ ይዘው በመጡ ' ማንነታቸው አልታወቀም ' በተባሉ ሰዎች ታፍና ከተወሰደች በኃላ በራሷ ስልክ ለአባቷ…
#ትግራይ
ታጋቹ ከ3 ወር መሰወር በኃላ የማስለቀቂያ ክፍያ ተጠየቀባቸው።
"አጋቾች ነን" ባዮች የጠየቁት ገንዘብ በ1 ሳምንት ጊዜ ካልተከፈላቸው ታጋቹን እንደሚገድሉት እንደዛቱ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
እገታው እንዴት እና መቼ ተፈፀመ ?
የሰዎች እገታ ከህፃናት አልፎ እድሜያቸው በገፉት ላይም በመቀጠል በህብረተሰቡ ውስጥ ቀውስን ማቀጣጠል መቀጠሉ እየተገለፀ ይገኛል።
ታጋቹ ሃለቃ ኣከቦም መሓሪ ኣባይ በትግራይ ፤ ምስራቃዊ ዞን ጉለመኻዳ ወረዳ የፍረዳሽም ቀበሌ ነዋሪ ናቸው።
ከ3 ወራት በፊት ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ / ም ከቤት እንደወጡ አለመመለሳቸው ያሳሰባቸው ቤተሰቦቻቸው ወደ አቅራቢያ ፓሊስ አመልክተው ራሳቸውንና ሌላውን በማሳተፍ በፍለጋ ቢታክቱም ሳይሳካላቸው ቆይተዋል።
የታጋቹ ሃለቃ ኣኮቦም ቤተሰቦች በከፍተኛ የተስፋ መቁረጥና የሀዘን ስሜት ውስጥ ባሉበት ሁኔታ ታድያ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም የሞባይል ስልክ ጥሪ ይደርሳቸዋል።
የታጋቹ ቤተሰቦች የተደወለላቸው የሞባይል ስልክ ቁጥር የወንድማቸው ሃለቃ ኣከቦም ቢሆንም ሞባይሉን ሲያነሱት የሰሙት ድምፅ ግን ከዛ በፊት ሰምተውት አያውቁም።
ይህ ማንነቱ ያልታወቀው ደዋይ በወንድማቸው የሞባይል ቁጥር በመጠቀም ፥ "...ወንድማችሁ ኣከቦም በህይወት ለማትረፍና በአካል ለማግኘት ከፈለጋችሁ 350 ሺህ ብር ክፈሉ። " የሚል ትዕዛዝ ያስተለልፋል።
የታጋቹ ወንድም ግደይ መሓሪ አባይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል በሰጠው ቃል ፥ ስልክ ደዋዩ ከአጋቾቹ አንዱ መሆኑን በማሳወቅ የተጠየቀው ብር እንዲከፍሉ የአንድ (1) ሳምንት ጊዜ ብቻ እንደሰጣቸውና ብሩን ካልከፈሉ ወንድማቸውን እንደሚገድሉባቸው እንደ ዛተ ተናግረዋል።
የታጋቹ ሃለቃ ኣከቦም መሓሪ ኣባይ በማህበራዊ ሚድያ ተሰራጭቶ ያነበቡ አስተያየት ሰጪዎች ፦ " ይህንን ያልተለመደና መጤ የእገታ ተግባር እጅግ አሳስቦናል !፤ ይህ እገታ ማቆምያው የት ይሆን ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
" አስከፊው ተግባር ወደየ ቤታችን ከመድረሱ በፊት መፍትሄ ያሻዋል " ያሉ አስተያየት ሰጪዎች " ከህግ አካላት በቅንጅት መስራት ሲቻል ችግሩ መፍትሄ ሊያገኝ ይችላል " ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓድዋ ከተማ መጋቢት 11/2016 ዓ.ም የታገተችውና እንድትለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ 12 ቀናት ቢያልፋትም ደብዛዋ ሊገኝ አልቻለም።
መረጃው የተዘጋጀው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
ፎቶ 1 ፦ ሃለቃ ኣከቦም መሓሪ ኣባይ
ፎቶ 2 ፦ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ

#Puntland #Somalia
ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ይፋ አድርጋለች።
ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው #ፑንትላንድ በሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ከዚህ ቀደም ሰጥታው የነበረውም ዕውቅና አንስታለች።
የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ፑንትላንድ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና እንዳነሳች አሳውቋል።
ምክንያቱ ምንድነው ?
የሶማሊያ መንግሥት ፓርላማ ብዙ ባወዛገበ ሂደት በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።
የሕገ መንግሥት ማሻሻያው ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የማሰናበትን ሙሉ ሥልጣን የሚሰጥ ሲሆን ‘ አንድ ሰው አንድ ድምጽ ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርግና ሌሎችም ማሻሻያዎች አሉበት።
NB. በሶማሊያ #ውስብስብ የሆነውን እና በጎሳ መሠረት የሚደረገውን ምርጫ ከ50 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡ አሁን ' አንድ ሰው አንድ ድምፅ ' የሚለው ማሻሻያ በፑንትላንድ ባለልስጣናት ተቃውሞ ገጥሞታል።
በአጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት ያካሄደው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ በፑንትላንድ አልተወደደም ውድቅም ተደርጓል።
ፑንትላንድ ፤ " በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ሕገ መንግስታዊ ሂደት እስከሚፈጠር ድረስ የፑንትላንድ አስተዳደር ለፌዴራል ተቋማት እውቅና አይሰጥም፣ ተቋማቱ ላይም እምነት የለውም " ብላለች።
ሕዝበ ውሳኔ (#ሪፈረንደም) የሚደረግበት ሕገ መንግስት እስከሚወጣ ድረስ፣ ፑንትላንድ የራሷ የሆነ መንግስታዊ ስልጣን እንደሚኖራት አስታውቃለች፡፡
ከአሁን በኋላ ፍላጎቷን ለማስጠቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ አማካይነት #የውጭ_ግንኙነቶችን እንደምታደርግ ገልጻለች።
ይህ የፑንትላንድ ውሳኔ ከሶማሊያ ተነጥሎ ነጻ አገርነትን ከማወጅ ጋር ሊስተካከል እንደሚችል በመጥቀስ #ከሶማሊላንድ ቀጥሎ ለፌደራል መንግሥቱ ሌላ ራስ ምታት እንደሚሆን ተንታኞች እየገለጹ ነው።
ፑንትለንድ በተፈጥሮ ሃብቶችና #በቦሳሶ_ወደቧ በመተማመን እ.አ.አ 1998 ነው ከፊል ራስ ገዝ መሆኗን ያወጀችው። እራሷን እንደ ነጻና ሉኣላዊ ሀገር የምትቆጥረው የሶማሊላንድ ጎረቤትም ናት።
መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።

#ሶልኤል
ልክ እንደ ክት ልብስ....
የድርጅቶን ስምና የብራንድ ደረጃ የጠበቁ የሥራ ልብሶችን በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት በሶልኤል ጋርመንት ያገኛሉ።
በመስቀል ፍላወር የሚገኘው ከ200 በላይ ባለሙያዎችን ይዞ የሚገኘው ማምረቻችን የእርሶን ትእዛዝ ይጠብቃል።
▪️ለሆስፒታል እና ለተማሪዎች የሚሆኑ ዩኒፎርሞች፤
▪️የፋብሪካ ቱታዎች እና የጥበቃ የደንብ ልብሶች፤
▪️ለሆቴሎች እና ለመስተንግዶ የሚሆኑ ደረጃውን የጠበቁ የሥራ ልብሶች ከእኛ ዘንድ ያገኛሉ።
በተጨማሪም በዘመናዊ ማሽኖቻችን የተለያዩ የኢምብሮይደሪ ወይም የክር ጥልፍ አግልግሎት እንሰጣለን። 👉 የተለያዩ የ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞችን ለሚያሰሩ ኤጀንሲዎች የዱቤ አገልግሎት ማመቻቸታችንን ስንገልጽ በደስታ ነው።
ይደውሉልን 📞 +251911236545 / 📞 +251992303030
በብዛት፤ በጥራትና በፍጥነት ማቅረብ የታወቅንበት ነው። ይምጡ እና ይጎብኙን።

ሰኞን በስጦታ!
ከባንክ ሂሳባችሁ ወደ M-PESA 1,000 ብር እና ከዚያ በላይ በማስተላለፍ እስከ 50 ብር ስጦታን አግኙ!
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether

“ 1.2 ቢሊዮን የምስኪን ሕዝብን ገንዘብ 4 ዓመታት ሙሉ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ እየተጠቀመበት ነው። በውላችን መሠረት መኪና አላስረከበንም ” - የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት
በስራቸው ከ2,800 በላይ አባላት ያሏቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሕጋዊ የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ከ3 ዓመታት በፊት " ከኦክሎክ ትሬዲንግ/ኃላ/የተ/የግ/ ማኀበር " መኪና እንዲቀርብላቸው ቢዋዋሉም መኪናው ሳይቀርብ የውል ገደቡ እንዳለፈ፣ ከ3 ጊዜ በደብዳቤ ቢጠይቁትም መፍትሄ እንዳልሰጣቸው፣ በመሆኑም መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ኃላፊዎቹ እና እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢዎች ጠይቀዋል።
ኃላፊዎቹና በእንባ የታጀቡት ቆጣቢዎቹ ይህን ያሉት ባለፈው ቅዳሜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ የተፈጠረውን ቅሬታ መነሻና ሂደትና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ለማኀበሩ ጥያቄ አቅርቧል።
የቱሪስት ታክስ ማኀበራት ኃላፊ አቶ ግዑሽ መብራህቶም ምን አሉ ?
➡️ “ ከ2012 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ በሚባል ድርጅት መኪና ያስገባል ወይም ገጣጥሞ ይሰጠናል በሚል ነው የነበረን ሂደት። ነገር ግን በዚህ መሠረት መኪናውን ማስረከብ አልቻለም። ይህም ብቻ አይደለም ‘መኪናውን ካላስረከበ ገንዘባችን ይመለስን’ ብለው የሚሄዱ አባላት ለሦስትና አራት ወራት እየተጉላሉ ነው። ”
➡️ “ በ2012 ዓ/ም መጨረሻ አካበቢ መኪና እናስመጣለን ብለው ማኀበራት ሲመዘግቡ እንሰጣለን ብለው ያሰቡትን ዋጋ በአማካኝ ብጠቀስ፣ 520 ሺሕ ብር ነበር። 520 ሺሕ ብር የነበረው መኪና አሁን ወደ 2 ሚሊዮን ብር አካባቢ ደርሷል። ”
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ለኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ የጻፈው ደብዳቤ ምን ይላል ?
- የቱሪስት ታክስ ማኀበራት በሄሎ ታክስ መዝጋቢነት፣ በኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ መኪና አቅራቢነት የመኪና ሽያጭ ውል እንደተፈራረሙ፣
- የኦክሎክ ጀነራል ትሬዲግ በውሉ አንቀጽ 2 የውል ትርጉም መሠረት የመኪና አቅራቢ በመሆን ውሉ እንደተፈረመ፣
- በውሉ መሠረት እያንዳንዱ አባል ቅድመ ክፍያ እንደዬ መኪናዎቹ ሞደል 60 ሺሕ ብር እንደተከፈለ፣ በተጨማሪ ከውሉ ጋር የመኪናውን የ25% በመክፈል ከኦክሎክ የመኪናውን የቻንሲና የሞተር ቁጥር በውሉ መሠረት እንልተረከቡ ያስረዳል።
ቆጣቢዎች ምን አሉ ?
ኦክሎክ ትሬዲንግ ቢበዛ በአንድ ዓመት ውስጥ መኪናውን እንደሚያስረክባቸው በወቅቱ ገልጾላቸው እንደነበር፣ ይሁን እንጂ “ ከዛሬ፣ ነገ ይመጣል” እየተባለ በወቅቱ ሳይመጣ ዓመታት እንዳስቆጠረ፣ “ይባስ ብሎ” መኪናውን በማስረከብ ፋንታ “አዲስ ውሎ ፈርሙ” እያለ መሆኑን በቁጣ ገልጸዋል።
የቱሪስት ታክስ ማኀበር ኃላፊ በበኩላቸው ኦክሎክ ፈርሙ ያለውን አዲሱን ውል በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያብራሩ ፦ “ የማኀበራት ኃላፊዎች ባሉበትም አይደለም አዲሱን ውል እንዋዋል የተባለው። ዝም ብለው በዬማኀበራት ግለሰቦችን እየጠሩ ነው። በወሬ ወሬ ሰማነው፣ ከዚያ የሆነ አካል ፓስት አድርጎ በቴሌግራም አደረሰን። ከዚያ ሕዝቡ/ቆጣቢው ተንጫጫ። ስናየው አዲሱ ውል ከ85 በመቶ በላይ ለድርጅቱ የሚያደላ ነው ” ብለዋል።
አክለውም ፣ “ እውነትም አቅም ካለው ውሉ መሠረት መኪናውን ያስረክብ። አቅም ከሌለው በሚመጥን ዋጋ ገንዘቡን ኳልኩሌት አድርጎ ይመልስ ” ሲሉ በአባላቱ ሥም ጥሪ አቅርበዋል።
“ እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባ ፈልጎ ነው?” ሲሉ እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢ እናትን ጨምሮ የሌሎቹን ቆጣቢዎች የቅሬታ ቃል በቀጣይ እናቀርባለን። #TikvahFamilyAA

#አዲስአበባ #ነዳጅ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱንና ምክንያቱ ደግሞ ጅቡቲ ላይ የዘነበ ከባድ ዝናብን ተከትሎ የመንገድ መቆራረጥ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጿል።
በተጨማሪም አስቀድሞም ከቦታዉ በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እየተጫነ ባለመሆኑ መሆኑን አመልክቷል።
የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ደሳለኝ አበባየሁ ፥ እነዚህ ምክንያቶች ከነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች የተነገራቸዉ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ችግሩ ለመስተካከል ጊዜ ይወስድ እንደሆን የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ " ጉዳዩ ትልቅ ነዉ፤ እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም ያሉን ሲሆን፤ በእርግጠኝነት መንግስትም ሌት ተቀን ርብርብ አድርጎ ነገሮችን ያስተካክላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን " ብለዋል።
ከጅቡቲ ከሚመጣዉ በተጨማሪ ክምችት ውስጥ ነዳጅ አልነበረም ወይ ? የተባሉት አቶ ደሳለኝ፤ " ቤንዚን ከአዋሽ ፣ ከሱሉልታ ዲፖዎች ነው እየተጫነ ያለዉ ፤ አሁን ላይ ግን ከክምችት ለመጫን ያልፈለጉበት የራሳቸዉ ምክንያት ይኖራቸዋል ፤ መንግስትም ይህንን አይቶ መፍትሄ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን " ብለዋል።
" አንድ ያለን መንገድ የጅቡቲ ብቻ ነዉ " ብለው " መንገዱ የተበላሸ በመሆኑ ደግሞ የመቆራረጥ ችግር ያጋጥማል ከባድ ዝናብ ሲዘንብ ደግሞ ችግሩን ከፍ ያደርገዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" እንደዚህ ዓይነት ችግሮች የሚያግጥሙ በመሆኑ ለተወሰነ ጊዜ በትዕግስት ማለፍ አስፈላጊ ነው " ብለዋል።
ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች እየተስተዋሉ ይገኛል።
ይህ መረጃ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#Axum
በጭንቅላት የተጣበቁ መንትዮች ተወለዱ።
ሴት መንትዮቹ (Conjoined twins) እንዲሁም እናቲቱ በመልካም የጤና ሁኔታ ይገኛሉ ተብሏል።
መጋቢት 22 /2016 ሌሊት በሪፈር የተላከች እናት በቆዶ ጥገና 5 ኪሎ የሚመዘኑ በጭንቅላት የተጣበቁ ሴት መንትዮች እንደተገላገለች የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ገልጿል።
ወላጅ እናት ለአዋላጅ ሃኪም የሰጠችው መረጃ በመጥቀስ ባለሙያዎች እንዳሉት ፥ እናቲቱ የፅንስ ክትትል በአቅራቢያዋ በሚገኝ የጤና ማእከል ውስጥ ስታደርግ የቆየች ብትሆንም የአልትራሳውንድ ምርመራ ባለማድረግዋ በማህፀንዋ የነበሩት መንትዮች ሁኔታ ቀድማ ማወቅ አልቻለችም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው ያገኘው።

" የመጨረሻ ተጨማሪ 3 ቀን ሰጥተናል " - ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 222 ግለሰቦች እስካሁን የወሰዱትን ገንዘብ መመልስ እንዳለጀመሩና እነዚህ ግለሰቦች ጋር ያለው ገንዘብ 4,034,979 ብር ከ75 ሳንቲም መሆኑን ገልጿል። ባንኩ አሁንም ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ የመጨረሻ የ3 ቀናት ስለመስጡትን አሳውቋል። ባንኩ ከዚህ ቀደም ሙሉ በሙሉና በከፊል ገንዘብ ያለመለሱ እንዲመልሱ 2 ጊዜ የመጨረሻ…
#ፎቶ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ108 ሺህ እስከ 305 ሺህ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ " እስካሁን አልመለሱልኝም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶግራፍ ይፋ አደረገ።
ወደዚህ እርምጃ ከመግባቱ በፊት በተደጋጋሚ ማስጠንቀቁን አስታውሷል።
በዚሁ መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ ይፋ ማድረጉን ገልጿል።
አሁንም ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም የተራዘመውን የገንዘብ መመላሽ ዕድል ተጠቅመው ገንዘብ ያልመለሱ እንዲመልሱ አስጠንቅቋል።
በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ እንደሚያቀርብም ገልጿል።