TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ ታጋቹ ከ3 ወር መሰወር በኃላ የማስለቀቂያ ክፍያ ተጠየቀባቸው። "አጋቾች ነን" ባዮች የጠየቁት ገንዘብ በ1 ሳምንት ጊዜ ካልተከፈላቸው ታጋቹን እንደሚገድሉት እንደዛቱ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። እገታው እንዴት እና መቼ ተፈፀመ ? የሰዎች እገታ ከህፃናት አልፎ እድሜያቸው በገፉት ላይም በመቀጠል በህብረተሰቡ ውስጥ ቀውስን ማቀጣጠል መቀጠሉ እየተገለፀ ይገኛል። ታጋቹ…
#Update
ታግታ ከተወሰደች በኃላ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታጋዲዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ታግታ ከተወሰደች 20 ቀናት ሆኗታል።
ቤተሰቦቿ " ልጃችንን አፋልጉን " ሲሉ በፈጣሪ ስም ተማጽነዋል። መላው ኢትዮጵያ ህዝብ እና የፀጥታ ኃይል ልጃቸውን እንዲፈልግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ቤተሰቦች ከትግራይ ዓድዋ ከተማ ያስተላለፉት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ ምን ይላል ?
የማህሌት ተኽላይ ቤተሰቦች ፦
" ታዳጊ ልጃችን ተማሪ ማህሌት ተኽላይ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ከ 11:00 ሰዓት በኃላ ወደ ቋንቋ ትምህርት ቤት በመሄድ ሳለች በትግራይ ዓድዋ ከተማ ዓዲ ማሕለኻ ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍና ተወስዳለች።
አጋቾቹ በወሰዱዋት ቀን በራስዋ ሞባይል ስልክ ወደኛ በመወደወል ለማስለቀቅያ 3 ሚሊዮን ብር እንድንከፍላቸው ጠይቀውናል። ከዛ በኃላ ግን በደውሉበት የልጃችን የሞባይል ቁጥር ብንደውልም አናገኛቸውም፤ በሌላ የሞባይል ቁጥር ደውለውም ያሉን ነገር የለም።
ስለሆነም እኛ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ወላጆች በከፍተኛ ጭንቅና ሃዘን ውስጥ እንገኛለን። ስለዚህ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና የፀጥታ አካላት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ እናቀርባለን። "
ማህሌት ተኽላይ የሚመለከት ማንኛውም አይነት መረጃ ለመስጠት ፦
+251938819844 ሙሴ ተኽላይ
+251992733943 ደጀን ተኽላይ
+251935036100/
+251962529287 ሚልዮን ተኽላይ
በሚሉ የሞባይል ቁጥሮች እንድትጠቀሙ በትህትና እንጠይቃለን። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁኔታውን እንዲያብራሩ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ቤተሰቦችን ጠይቆ ፥ " የዓድዋ ፓሊስ እኛን መልሶ ምን አዲስ ነገር አለ ብሎ ይጠይቀናል ? " ሲሉ መልሰዋል።
የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ #ዓድዋ እና #አክሱም ያደረገው ጉዞ በፓሊስ አመራሮች ስብሰባ ምክንያት አልተሳካም።
#TikvahFamilyMekelle
@tikvahethiopia

#Mekelle
በመቐለ የሚገኘው " ፍሬምናጦስ የአረጋውያን የአእምሮ ህሙማን የህፃናት እንክብካቤ ማእከል " በእሳት ቃጠሎ አደጋ ምክንያት ከፍተኛ ወድመት አጋጥሞታል።
አደጋው ያጋጠመው ሚያዝያ 7/ 2016 ዓ.ም ሲሆን ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ የእርዳታ ጥሪ ተማጽኖ አቅርቧል።
የምግባረ ሰናይ ድርጅቱን የተለያዩ በጎ አድራጊዎች ሲረዱት ቆይተዋል።
የሚያዘያ 7ቱ የእሳት አደጋ ከአጋዦቹ አንዱ የሆነው መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ ሚሊዮን ብሮች በመስጠት ባሰራው አዳራሽ ነው የደረሰው።
በተነሳው ቃጠሎም አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ሲወድም በተረጂዎች ማደሪያ ፣ መመገብያና ፣ መስሪያ ክፍሎች ወድመት ደርሷል።
በከፍተኛ ውጪ የተሰራው አዳራሽ ሚያዝያ 6/2016 ዓ.ም. የተመረቀ ሲሆን በነጋታው ሚያዝያ 7/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ነው በእሳት ሙሉ በሙሉ የወደመው።
የአደጋው መንስኤ በኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ በተነሳ ቃጠሎ ነው ተብሏል።
ያጋጠመው ቃጠሎ ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም በህዝብና በመቐለ የእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ የተቀናጀ ርብርብ በማእከሉ በሚገኙ አቅመ ደካሞች የህይወት ማጣት አደጋ አልደረሰም።
ምግባረ ሰናይ ድርጅቱ በእሳት አደጋ ቃጠሎ ምክንያት የመኝታ፣ መመግብያ ክፍሎቻቸው የተቃጠለባቸው የሚንከባከባችው አቅሞ ደካሞች ሜዳ ላይ ተጥለው እንደሚገኙ በመጠቆም በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ሰብአውያን ሁሉ እንዲረዱት ጥሪ አቅርበዋል።
መርዳት የሚፈልጉ ወገኖች ፍሬምናጦስ የአረጋውያን የእአምሮ ህሙማንና የህፃናት እንክብካቤ ማእከል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000622132404 ሂሳብ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ።