TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TikTok #USAHouse

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ተሰብስቦ ለዩክሬን ፣ ለእስራኤል እና ለሌሎች የባህር ማዶ የአሜሪካ አጋሮች የ95 ቢሊዮን ዶላር (5,419,427,000,000 ብር) የእርዳታ ጥቅል/ፓኬጅ ረቂቅ ሕግ አጽድቋል።

" ቲክቶክ " በአሜሪካ እንዲታገድም ድምጽ ሰጥቷል።

የተወካዮች ምክር ቤቱ በመጀመሪያ ድምፅ የሰጠው በ " #ቲክቶክ " ጉዳይ ሲሆን ባለቤትነቱ የባይትዳንስ የሆነው መተግበሪያ ለአሜሪካ ኩባንያ ካልተሸጠና ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት ካላቋረጠ በመላው አሜሪካ ውጤታማ በሆነ መንገድ #ለማገድ 360 ለ 58 በሆነ ድምጽ ረቂቅ ሕግ #አጽድቋል

" ቲክቶክ " በአሜሪካ ከ170 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት።

በመቀጠል ምክር ቤቱ ፦

➡️ ለዩክሬን 60.8 ቢሊዮን ዶላር (3,422,796,000,000 ብር)፤

➡️ ለእስራኤል 26.4 ቢሊዮን ዶላር  (1,483,211,600,000 ብር)፤

➡️ ለታይዋን እና ለኢንዶ ፓስፊክ ሀገራት  ' ቻይናን ለሚጋፈጡ ' የ8 ቢሊዮን ዶላር (456,372,800,000 ብር) የእርዳታ ድጋፍ በድምሩ የ95 ቢሊዮን ዶላር ጥቅል እርዳታ ረቂቅ ሕግ አጽድቋል።

የምክር ቤቱ አባላት የዩክሬን ድጋፍ ሲጸድቅ ፤ " ዩክሬን !! " እያሉ በመጮህ የሀገሪቱን ባንዲራ ሲያውለበልቡ ታይተዋል።

@thiqahEth @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ባይደን ፊርማቸውን አኑረዋል ፤ ቲክቶክ " ፍርድ ቤት እንተያይ " ብሏል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በባይት ዳንስ ባለቤትነት ያለው " #ቲክቶክ " ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ #እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል።

" ቲክቶክ " ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ የተሰጠው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው።

በዚህ ጊዜ ይህንን ካላደረገ #እስከወዲያኛው ከአሜሪካ እንደሚታገድ ተገልጿል።

አሁን በአሜሪካ ብቻ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት " ቲክቶክ " ሙሉ በሙሉ የመታገዱ ነገር #እውን ወደ መሆኑ ተቃርቧል።

የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ " የትም አንሄድም። ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን። ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን ፣ እስራኤል እና ታይዋን የቀረበው የ95 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ጥቅል ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
📱 ባይትዳንስ ' #ቲክቶክ ' ን #ለአሜሪካ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ #ቢዘጋው እንደሚመርጥ ሮይተርስ ለኩባንያው ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘገበ።

ኩባንያው በ' ቲክቶክ ' ጉዳይ እስከመጨረሻው ያሉትን የህግ አማራጮችን ተጠቅሞ እንዳይታገድ ማድረግ ካልቻለ ፤ ለአሜሪካ ከመሸጥ ይልቅ እስከመጨረሻው #መዝጋት ይመርጣል ተብሏል።

አሁን ' ቲክቶክ ' የሚሰራበት #አልጎሪዝም ለኩባንያው እንደ ዋናው ነገር እንደሚቆጠርና በዚህ አልጎሪዝም መተገበሪያውን የመሸጥ እድሉ እጅግ ሲበዛ አነስተኛ እንደሆነ የኩባንያው ምንጮች ገልጸዋል።

በዚህም ፤ ለአሜሪካ ገዢ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ እስከወዲያኛው ድረስ መዝጋትን እንደሚመርጥ ተጠቁሟል።

አሜሪካ ' ቲክቶክ ' እንዲሸጥ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ገደብ አስቀምጣለች ካልሆነ ግን እስከ ወዲያኛው እንዲታገድ ሕግ አጽድቃለች።

በርካታ ጉዳዩን የሚከታተሉ የዘርፉ ሰዎች አሁን ባለው የአሜሪካ አቋም 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ' ቲክቶክ ' እስከ ወዲያኛው ድረስ የመወገዱ ነገር እውን መሆኑ አይቀርም ብለዋል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM