TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ "...መግለጫው የኤርትራ ጦር የተለያዩ አካባቢዎችን በኃይል ይዞ እንደሚገኝ ያመላከተ ነው " - አቶ ረዳኢ ኃለፎም የትግራይ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን መሬት በኃይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላም ቢሆን መሬቱን ለቆ እንዳልወጣ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደርን ጨምሮ ሀገራትና ተቋም በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል። በቅርቡ እንግሊዝ የሚገኘው…
#Tigray
" የኤርትራ ሰራዊት በራሱ ግዛት ነው ያለው የሚለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ ራስን ከማሞኘት ያለፈ ትርጉም የለውም " - አኒና የኢሮብ ማህበረሰብ መብት ጠባቂ ማህበር
አኒና የተባለው የኢሮብ ሲቪክ ማህበረሰብ ማህበር መጋቢት 1/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ኢትዮጵያ በሚገኙ 3 ዞኖች የሚገኙ በርካታ አከባቢዎች ተቆጣጥሮ ነዋሪዎች እያንገላታና ግፍ እየፈፀመ ይገኛል ብሏል።
ስቪክ ተቋሙ የኤርትራ መንግስት የካቲት 28/2024 ያወጣው መግለጫን በተመለከተ " የኤርትራ መንግስት የትግራይ ኢትዮጵያ መሬቶች መያዙ በዚህ በሰለጠነ የመረጃ ዘመን ፈፅሞ መካድ አይቻልም " ብሎታል።
የኤርትራ መንግስት የሰጠው መግለጫ ከእውነት የራቀና በፍፁም መወገዝ ያለበትን ነውም ብሏል።
የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ፦
- የዛላኣንበሳ ከተማ
- በጉሎመኸዳ ወረዳ ማርታ ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ዓለም ፣ ሸዊት ለምለምና ሰበያ
- በኢሮብ ወረዳ እንዳልጌዳ ፣ ወርዓትለ ዓገረ ሎኽማና ዓሊቴና የተባሉ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ተቆጣጥሮ ይገኛል ሲል ገልጿል።
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በታሕታይ ኣድያቦ የኩናማ ማህበረሰብና ሌሎች የሚኖሩባቸው ገማህሎ ፣ አደመይቲ ፣ የባድመ ከተማና አከባቢው ፣ ዓዲ ፀፀር ፣ ለምለም ሸዊት ፣ ሸምበሊና ፣ መንጠብጠብ ፣ ዓዲ ኣሰር ፣ ሰየምቲ አድያቦ በኤርትራ ስራዊት ስር እንደሚገኙ ፀሃይ የሞቀው ሃቅ ነው ሲልም አክሏል።
የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ማእከላዊ ዞን የእገላና ራማ አከባቢዎች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቆጣጥሮ የአከባቢው ህዝብ የመንግስት አገልግሎት እንዳያገኝ በማድረግ ለበርካታ ችግሮች እንዳጋለጠው ያመለከተው አኒና የኢሮብ ስቪክ ማህበረሰብ መግለጫ ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ህዝቡ ከእንግልትና መከራ እንዲታደገው ጥሪ አቅርቧል።
አኒና የኢሮብ ሲቪክ ማሕበረሰብ ያወጣውን መግለጫ የተከታተሉ የመቐለ ነዋሪዎች ለመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሰጡት አስተያየት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚዎች የፌደራል መንግስትና ህወሓት ፣ የአሜሪካ ፣ የአውሮፓ ፣ ኢጋድና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተዛቢዎች በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ዛሬ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውል አተገባበርና አፈፃፀም አስመልክቶ በሚካሄደው ግምገማ በኤርትራ ሰራዊት ስር ስላሉ የትግራይ ኢትዮጵያ ግዛቶች ጉዳይ የውይይቱ አካል ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia

#Update የጥንታዊውና ታሪካዊው ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት መነኮሳት በ " ኦነግ ሸኔ " ታጣቂዎች መገደላቸው አንድ አባት ደግሞ አምልጠው ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ መነገሩ ይወሳል። ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ መላከሰላም ቀሲስ ዳዊት ያሬድ በሰጡት ቃል ፤ " ከተገደሉት አባቶች መካከል ያልተገኙ አንደኛው…
" ገዳሙ የ2016 ዓ/ም የማህበር ቀለብ መሸመት እስከማይችል ድረስ ኢኮኖሚያዊው ተጎድቷል " - ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም
በመላው ዓለም የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሙሉ ለዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ ቀረበ።
ጥሪውን ያቀረበው ገዳሙ ነው።
ይህ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ገዳም ከቅብር አመታት ወዲህ የመነኮሳትን ህይወት መስእዋትነት እስከማስከፈል የደረሰ ለዘርፈ ብዙ ጥቃት መጋለጡን ገልጿል።
ገዳሙ ከዚህ ቀደም በገንዘብ ከተፈፀመበት ዝርፊያ ባለፈ በቅርቡ ለገዳሙ አይን የሆኑ 4 መነኮሳት አባቶች አሰቃቂ በሆነ መንገድ መገደላቸውን ይህም የመነኮሳትን ልብ የሰበረ እንደሆነ አመላክቷል።
በ2012 የተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ በሀገሪቱ በየትኛው ተቋም ላይ ያደረሰው አሉታዊ ተፅእኖ በገዳሙም ላይ እንዲሁ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን አሁን ላለበት እጅግ ዘርፈ ብዙ ችግር መጋለጥ የጀመረው ግን ህገወጥ ታጣቂዎች አካባቢው ላይ መንቀሳቀስ ከጀመሩ ጊዜ አንስቶ ነው ብሏል።
ገዳሙ ፤ ህገወጥ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ወደ ገዳሙ በመግባት የጥበቃ ትጥቅ በመንጠቅ ገዳሙን በመዝረፍ አራቁተውታል ሲል ገልጿል።
ይህ ሁኔታ የ2016 ዓ/ም የማህበር ቀለብ መሸመት እስከማይችል ድረስ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን እንደጎዳው አስረድቷል።
በተለያዩ መስኮች እና አገልግሎቶች መንፈሳዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለጸው ገዳሙ አሁን እየደረሰበት ያለው ጥቃት ሁለንተናዊ ችግር ላይ ስለጣለው የህዝበ ክርስቲያኑን ትብብር ግድ የሚልበት ደረጃ ላይ መደረሱን በይፋ አሳውቋል።
በመሆኑን በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች አቅማቸው በፈቀደ በገንዘብም ፣ በቁሳቁስ፣ በሞያ፣ በሃሳብ የእርዳታ እጃቸውን ለገዳሙ እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርቧል።
የገዳሙ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000011282222 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ወይም 31905877 (አቢሲንያ ባንክ) መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ውጭ ገዳሙ የመደበውም ሰው ይሁን ማህበር ስለሌለ ከተጠቀሰው አካውንት ውጭ #እንዳታስገቡ ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከገዳሙ አስተዳደር ነው ያገኘው።

ወጋገን ባንክ ኢ- ስኩል
ከመዋዕለ ህፃናት እስከ 2ኛ ደረጃ ላሉ የትምህርት ተቋማት የአገልግሎት ክፍያን በዲጂታል የባንካችን አገልግሎቶች ካሉበት ቦታ ሆነው ይፈፅሙ፡፡
በወጋገን ባንክ ኢ-ስኩል የሚሰጡ አገልግሎቶች:-
•የተሟላ የትምህርት ክፍያ አስተዳደር ዝርጋታ
•የተለያዩ የትምህርት ቤት ክፍያዎች ዝርዝር መግለጫ
• የመማር ማስተማር ሂደትን የሚያግዝ የአስተዳደር ስርዓት መዘርጋት
•ደህንነት እና ምስጢራዊነት የጠበቀ የተማሪ መረጃ አያያዝ
• ሪፖርት ማዘጋጀት፣ ለተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ማድረግ
ለተጨማሪ መረጃ በ866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ::
#WegagenBank #WegagenEschool #MobileBanking
Follow us and get more information...
https://linktr.ee/WegagenBank

ተረክ በM-PESA ሊጠናቀቅ የመጨረሻው ቀን ዛሬ ነዉ፤ መኪናዋን ዛሬም የእናንተ መሆን ትችላለች!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether

#MoE ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ2016 ዓ .ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት ከየካቲት 18/2016 ዓ/ም ጀምሮ መለቀቁን አሳውቋል። ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ፤ ለሁሉም የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ ባስተላለፈው መልዕክት ነው። ተፈታኞች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ሊንክ ማየት ይችላሉ ተብሏል። @tikvahethiopia
" የ114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር በመውጫ ፈተና ላይ ኩረጃና ሌሎች የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞችን ውጤት ሙሉ በሙሉ እንደሰረዘ አሳወቀ።
በመውጫ ፈተና ፦
- ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት፣
- መኮረጅና የተለያዩ የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል።
የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙት 114 ተፈታኞች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ መሠረዙንና የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ ይገለጻል ብሏል።
ከየካቲት 6-11/2016 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት በተሰጠው ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና 119, 145 ተፈታኞች መፈተናቸው ይታወሳል።

#AddisAbaba የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ ማቅረቡ ይታወቃል። ኮርፖሬሽኑ ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው የተጠናቀቁ ፦ ➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን ➡️ 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ ነው በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ የፈለገው።…
#Update
የቤቶች ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ተጠናቀቀ።
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነቧቸውና ለጨረታ ያቀረቧቸው 3,146 የመኖሪያና 306 የንግድ ባጠቃላይ 3,452 ቤቶች የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ በዛሬው ዕለት መጋቢት 02/2016 ዓም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት መጠናቀቁ ተገልጿል።
ከጥር 27/2016 ዓ/ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የሰነድ ሽያጭ በዛሬው ዕለት መጠናቀቁን ተከትሎ በነገው ዕለት መጋቢት 03/2016 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ይከፈታል ተብሏል።
በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ለጨረታ የቀረቡት 935 የመኖሪያና 15 የንግድ ቤቶች ላይ ተጫራቾች ያስገቧቸው ሰነዶች በታዛቢዎች ፊት የሚከፈት ይሆናል ተብሏል።
መረጃው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ነው።

#Update የቤቶች ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ተጠናቀቀ። የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነቧቸውና ለጨረታ ያቀረቧቸው 3,146 የመኖሪያና 306 የንግድ ባጠቃላይ 3,452 ቤቶች የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ በዛሬው ዕለት መጋቢት 02/2016 ዓም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት መጠናቀቁ ተገልጿል። ከጥር 27/2016 ዓ/ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የሰነድ ሽያጭ…
የቤቶቹ ጨረታ ላይ የተነሳው ጥያቄ ምንድነው ?
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የ1997 ዓ.ም. የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ዕጣ ያልወጣላቸው ቆጣቢዎች ያቀረቡለትን አቤቱታ መሠረት በማድረግ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከ3 ሺህ ቤቶች በላይ በሽያጭ ለማስተላለፍ ያወጣው ጨረታ ላይ የሕጋዊነትና የፍትሐዊነት ጥያቄ አንስቷል።
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አጋጠመኝ ያለውን የፋይናንስ አቅም ችግር ለመፍታትና ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ለመገንባት፣ ከከተማው የዲዛይንና ግንባታ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን 3,146 የመኖሪያ ቤቶችንና 306 የንግድ ሱቆችን በጨረታ ለመሸጥ ማቀዱን መግለጹ ይታወሳል።
በ1997 ዓ.ም. ተመዝግበው ከስቱዲዮ እስከ ባለ3 መኝታ ቤት ድረስ ቤቶች ለማግኘት እየቆጠቡ ያሉ 959 ነዋሪዎች፣ እያንዳንዳቸው ምን ያህል እንደቆጠቡ የሚገልጽ ሙሉ ስማቸው ከፊርማቸው ጋር ያረፈበትና በድምሩ 144,820,085.43 ብር መቆጠባቸውን ከሚያሳይ ሰነድ በማያያዝ፣ ኮርፖሬሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን ለመሸጥ የጀመረውን ሒደት #እንዲያሳግድላቸው የሚጠይቅ ደብዳቤ ለዕንባ ጠባቂ ተቋም ጨረታው ይፋ በተደረገበት ዕለት አስገብተው ነበር።
አቤቱታቸውን የተቀበለው ዕንባ ጠባቂ ተቋም የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም በዋና ዕንባ ጠባቂ እንዳለ ኃይሌ (ዶ/ር) ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ፣ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ ምላሹን እንዲያሳውቀኝ ሲል 4 ጥያቄዎችን አቅርቧል።
1ኛ. ኮርፖሬሽኑ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በሽያጭ የማስተላለፍ ሕጋዊ መሠረት ያለው ስለመሆኑ በማስረጃ ተደግፎ እንዲቀርብ ብሏል።
2ኛ. መኖሪያ ቤቶቹ በጨረታ ለሽያጭ ሲቀርቡ የ1997 ዓ.ም. እና የ2005 ዓ.ም. የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎችን ቅድሚያ በመስጠት፣ በልዩ ሁኔታ ተሳታፊ ያልተደረገበት ምክንያት እንዲገለጽ ጠይቋል።
3ኛ. ኮርፖሬሽኑ የመኖሪያ ቤቶችን ከዕጣና ከምደባ ውጪ በጨረታ ሽያጭ ለማስተላለፍ ሲወስን፣ በ1997 ዓ.ም. እና 2005 ዓ.ም. ተመዝግበው ቤት እየተጠባበቁ ያሉ ነዋሪዎች ጉዳይ ላይ ግልጽና የመጨረሻ ውሳኔ ያልተሰጠበትን ምክንያት እንዲገለጽ የሚል ጥያቄ አቅርቧል።
4ኛ. ኮርፖሬሽኑ ቤቶችን በጨረታ ለመሸጥ ሲወስን ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የከተማው ነዋሪዎችን አቅም ባገናዘበ መንገድ የጨረታ መነሻ ዋጋና የአከፋፈል ሥርዓት ሊታይ ያልቻለበትን ምክንያት በመግለጽ፣ ኮርፖሬሽኑ ምላሹን በሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ እንዲሰጥ ሲል በደብዳቤ ጠይቋል።
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Reporter-03-11-2
Credit ➡ Ethiopian Reporter

#አቢሲንያ_ባንክ
3ኛ ዙር እችላለሁ ! የሴቶች የሥራ ፈጠራ፣ የሙዚቃ፤የቲክቶክ ቪዲዮና እያሳተፉ ይሸለሙ ውድድር !
ባንካችን በየአመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ በያዝነው የአውሮፓውያን ወር ከማርች 8-31, 2024 ድረስ በሁለት የተከፈሉ ውድድሮችን አዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ክፍት አድርጓል፡፡
1) የሙዚቃ እና የቲክቶክ ቪዲዮ ተሰጥዖ ውድድር
ይህ ውድድር የሚከናወነው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓም. ሲሆን ባንካችን የሙዚቃ ተሰጥኦ ያላቸውን ሴት ተሳታፊዎችን በማወዳደር በባለሙያና በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የህዝብ ድምጽ የተለዩ አሸናፊዎችን በየደረጃው ይሸልማል፡፡ በዚህም መሰረት
👉🏾 1ኛ 100,000 ብር
👉🏾 2ኛ 75,000 ብር
👉🏾 3ኛ 50,000 ብር ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡
በዚህም መሠረት በመርሃ-ግብሩ መሳተፍ የምትፈልጉ ሴት ተወዳዳሪዎች አስቀድማችሁ የአቢሲንያ ባንክ የፌስቡክ ገፅን https://www.facebook.com/BoAeth/ መወዳጀት ይኖርባችኋል፡፡ በመቀጠልም በሙዚቃው ዘርፍ ተሰጥኦዬን ያሳያል የምትሉትን ከሶስት (3) ደቂቃ ያልበለጠ የሙዚቃ ሥራ ያለ ሙዚቃ መሣሪያ በቪዲዮ ሰርታችሁ ከዚህ በታች በተቀመጠው ቴሌግራም መላክ ይኖርባችኋል፡፡
በተመረጡ ቲክቶከሮች መካከል ባንካችን ለሴት ደንበኞቻችን ያዘጋጃቸውን አደይና ዘሃራ የቁጠባ ሂሳቦችን በተለየ መንገድ የማስተዋወቅ ውድድር ይካሄዳል፡፡
የቴሌግራም አድራሻ------------0942-728501
2) የሥራ ፈጠራ ውድድር
የሥራ ፈጠራ ውድድር የሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታት ባንኩ ካሉት 10 ዲስትሪክቶች ከእያንዳንዱ አምስት(5) የስራ ፈጣሪዎችን በአጠቃላይ 50 የሥራ ፈጣሪ ሴቶችን በመምረጥ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔና ካለመያዣ እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቶችን የምታሟሉ የሥራ ፈጣሪዎች አቅራቢያችሁ ባሉ ቅርንጫፎችና የዲስትሪክት ፅ/ቤቶች በመቅረብ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓም. ባሉት ቀናት ብቻ በፁሑፍ ጥያቄያችሁን እንድታቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
2) እያሳተፉ ይሸለሙ
በዚህ ውድድር ደግሞ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሴቶች የሚሳተፉበት ለባንካችን አዳዲስ ደንበኞችን በመመልመል በመለመልዋቸው የደንበኞች ብዛት መጠን ተሳታፊዎች የገንዘብ ሽልማት የሚሸለሙበት ውድድር ይከናወናል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለሴቶች ደንበኞቻችን የተዘጋጁትን የመደበኛ አደይና የወለድ አልባ ዘሃራ አገልግሎቶችን በመጠቀም የተሻሉ ጥቅሞችን እንድታገኙ እንጋብዛለን፡፡
ዝርዝር የብድር እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ከዚህ በታች የሚገኘውን የቴልግራም ሊንክ ያግኙ፡፡
https://t.iss.one/BoAEth
መልካም የሴቶችቀን !