TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠንካራ ሴት ለመሆን የሚከፈለውን ዋጋ በደንብ እንረዳለን፣  ህልምዎና ፍላጎትዎ እንዲሳካ የአደይ ቁጠባችን ያግዝዎታል! ባንካችን ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ያዘጋጀውን አደይ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ አቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ በመክፈት የልዩ አገልግሎቶቹና ጥቅሞቹ ተጋሪ ይሁኑ።

#BankofAbyssina #WomenSavingAccount #bankinginethiopia #banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ፎቶ፦ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለ2 ቀናት መንግሥታዊ ጉብኝት ኬንያ ናይሮቢ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ባለቤታቸው ናይሮቢ በጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ በፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በመቀጠል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የወጣቶችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተሳትፎ የሚያሳይ የአይሲቲ ፓርክ ለጠቅላይ ሚኒስትር አስጎብኝተዋል።

መረጃው የጠ/ሚ ፅ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ ማቅረቡ ይታወቃል። ኮርፖሬሽኑ ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው የተጠናቀቁ ፦ ➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን ➡️ 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ ነው በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ የፈለገው።…
#Update

የጨረታ መክፈቻው ተራዘመ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጋር በመተባበር ያስገነቧቸውን 3,452 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በሽያጭ ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ ይገኛል።

ኮርፖሬሽኑ ፤ ከሕብረተሰቡ መጣልኝ ባለው ጥያቄ መነሻነት የጨረታ መክፈቻ ጊዜው ለ10 ቀናት የተራዘመ መሆኑ አሳውቋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች እስከ መጋቢት 02/2016 ዓ/ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ምሽቱ 1፡30 እንዲሁም እሁድ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 6፡00 በሁሉም ክፍለከተሞች ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
በማንኛውም ቦታ ሆነው በግሎባል ሞባይል ተመዝግበው አካውንትዎን ማንቀሳቀስ፣ ክፍያ መፈፀምና ማስተዳደር ይችላሉ፡፡

ግሎባል ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ለማውረድ ሊንኩን ጠቀሙ  
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ofss.dgbb

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን https://bit.ly/3TkrrXD

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

#GlobalBankEthiopia #GBE #SharedSuccess
#Infinix_Hot40

አዲሱ ኢንፊኒክስ 'Hot 40 pro' ስልክ ያለ ሃሳብ የፈለጉትን መተግበሪያ ለመጠቀም የሚያስችል ‘ Ultra speed helio G99’ የተሰኘ ፕሮሰሰር የተገጠመለት በመሆኑ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ ያደርገዋል!

#InfinixEthiopia #InfinixMobile #Infinix_Hot40 #Infinix_HotSeries
ፍትህ ሚኒስቴር ፤ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

በዚሁ መግለጫ ፤ የሽግግር ፍትህ የባለሞያዎች ቡድን የተሰጠውን ኃላፊነት በወቅቱ ማጠናቀቁን ገልጿል።

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው የመጨረሻ ረቂቅ ስራ እንዳለቀ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተልኮ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በመንግስት እንደሚፀድቅ ተመላክቷል።

(መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚዎች በቀጣይ ሳምንታት ከአደራዳሪዎች ጋር ለመወያየት መርሃ ግብር ተይዟል " - የትግራይ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

የትግራይ ክልል የኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም የካቲት 19/2016 ዓ.ም ምሽት ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ፤ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ውል ሙሉ በሙሉ ባለመተግበሩ ምክንያት የህዝብ ስቃይና ሞት መቆም አልቻለም ፤ ስለሆነም ውሉ በሙሉ እንዲተገበር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተከታታይ ውይይቶች በማካሄድ ላይ ናቸው ብለዋል።  

" ሰላማዊ ፣ ዴሞክራሲያዊና ፓለቲካዊ መንገድ በመጠቀም የትግራይ ህዝብ ጥያቁዎች እንዲመለሱ መስራት ተመራጭ አማራጭ ነው " ያሉት አቶ ረዳኢ ይህንን ታሳቢ በማድግ በሚቀጥሉት ሳምንታት የፕሪቶሪያ የሰላም ውል ፈራሚዎች ከአደራዳሪዎች ለመወያየት መርሃ ግብር ተይዟል ብለዋል። 

በትግራይ የተከሰተው ደርቅ ወለድ ረሃብና ሞት አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት የነበሩ ልዩነቶች ወደ አንድ ማምጣት እንደተቻለ የገለፁት አቶ ረዳኢ ሓለፎም ፤ የጋራ መፍትሄ ለማበጀት በጋራ እየተሰራ መሆኑ አብራርተዋል።

ሃላፊው አያይዘው እንደገለጹት ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 18 ና 19 /2016 ዓ.ም ለ2 ቀናት ባካሄደው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላልፏል።

ካቢኔው የኢንቨስትመንትና የኤክስፓርት መመሪያ እንዲሁም የአርበኞች ኮሚሽን አሁናዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ተሻሽሎ እንዲተገበርና እንዲቋቋም ወስኗል። 

የትግራይ ህዝብ በከባድ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ውስጥ እያለ ፤ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በፀጥታ ሃይል አዛዦች ላይ እየተደረገ ያለው የተቀናጀና የተናበበ የማጥላላት ዘመቻ ያወገዘው ካቢኔው ፤ የትግራይ ህዝብና አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት መንፈስ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት እንዲረባረቡ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

መረጃውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዋቢ በማድረግ አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው። 
                                              
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 ከእድሳትና የማስፋፋት ሥራ በኋላ ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ሁሉም የሀገር ውስጥ በረራዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር አሳውቋል። ከአዲስ አበባ ወደ ሁሉም የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዲሁም ከሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት በረራዎች በተርሚናል 1 ይደረጋሉ። በሌላ በኩል…
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የሀገር ውስጥ በረራ የሚያደርጉ መንገደኞች ወደ ተርሚናል ቁጥር  1 ብቻ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ።

አየር መንገዱ ፤ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 (በተለምዶው የሀገር ውስጥ/Domestic Terminal) የማስፋፊያ እና የማዘመን ስራው ተጠናቅቆለት ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

በዚህም የሀገር ውስጥ በረራ ለማድረግ ወደ ኤርፖርት የሚመጡ መንገደኞች በቀጥታ ወደ ተርሚናል ቁጥር 1 ብቻ እንዲገቡ ብሏል።

@tikvahethiopia
#አሰቦት

" የገዳማውያኑን የእርዳታ ጥሪ በተጠንቀቅ ጠብቁ " - አባ ገ/ሚካኤል

በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ የሰደድ እሳት የተነሳ ሲሆን ከትላንት ምሽት ጀምሮ ግን ወደ ገዳሙ በከፍተኛ ሁኔታ #እየተጠጋ እንደሆነና እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።

አባ ገ/ሚካኤል የተባሉ የገዳሙ አገልጋይ ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል በሰጡት ቃል ፤ የእሳት ቃጠሎ መነሻው በሥርዓት ያልታወቀና የሰደድ እሳት እንደሆነ ገልጸዋል።

ከ3 ዓመታት በፊት ከፍተኛ እሳት ተከስቶ ለዘመናት የኖሩ የገዳሙን ብርቅዬ አራዊትና ደን ማውደሙን አስታውሰዋል።

በአሁኑ ሰዓት እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ፤ የእሳቱ አደጋ የሚከፋ ከሆነና መቆጣጠር ካልተቻለ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን የገዳማውያኑን የእርዳታ ጥሪ በተጠንቀቅ ሊጠብቁ ይገባል ብለዋል።

#Update

እሳቱ ለገዳሙ እንደማያሰጋ ተገልጿል።


#ተሚማ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia #Kenya

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኬንያ እያደረጉት በሚገኘው ይፋዊ ጉብኝት በፕሬዝዳነት ዊልያም ሩቶ በስቴት ሀውስ ኬንያ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፤ " የአቀባበል ስነስርዓቱ ሁለቱ መሪዎች እና ልዑካን ቡድኖቻቸው በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ እያደርጓቸው ያሉ ጉልህ ግንኙነቶች እና ውይይቶች ጅማሮ ነው። " ብሏል።

ሁለቱ መሪዎች በድይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ጥልቅ እና ታሪካዊ ግንኙነት ብሎም ኢኮኖሚያዊ ትስስር አንስተው ይኽንኑ በቁርጠኝነት ማጠናከር እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተነግሯል።

" ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወሳኝ አጋጣሚ ሆኖ የዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የበለጠ ለማዳበር ብሩህ መፃዒ ጊዜን ያመላከተ ሆኗል " ሲል የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ትላንት ለሁለት ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ኬንያ መግባታቸውና ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንደተቀበሏቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia