TIKVAH-ETHIOPIA
ወደ ሐዋሳ እያመራ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ። በዎላይታ ዞን በዱጉና ፋንጎ ወረዳ ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ዞንጋ " በተባለው ቦታ ማምሻውን አስከፊ የትራፊክ አደጋ ደርሷል። በዚህም አደጋ የ8 ሰው ሕይወት መቀጠፉ ተሰምቷል። አደጋው የደረሰው በዛሬው ዕለት ምሽት 12:30 ገደማ መነሻውን ከአርባምንጭ ከተማ አደርጎ ወደ ሐዋሳ ከተማ በመጓዝ ላይ…
" የሟቾች ቁጥር ከ8 ወደ 11 ከፍ ብሏል " - ኢስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ
ወደ ሐዋሳ ጉዞውን እያደረገ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 11 መድረሱን የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ትላንት ማምሻውን መነሻውን ከአርባ ምንጭ አድርጎ ወዘ ሐዋሳ እያመራ የነበረ ተሽከርካሪ በዎላይታ ዞን በዱጉና ፋንጎ ወረዳ ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ዞንጋ " በተባለው ቦታ አስከፊ አደጋ እንደደረሰበት ይታወቃል።
በዚህም አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ8 ወደ 11 ከፍ ብሏል።
የሀዋሳ ከተማ የትራፊክ ፖሊስ ኃላፊዉ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ዛሬ ጥዋት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ በመኪናው ውስጥ ከነበሩት ውስጥ አብዛኛው ወጣት የጤና ቡድን አባላት መሆናቸዉን ገልጸው የደረሰዉ አደጋ ከፍተኛ ሀዘን መፈጠሩን ገልጸዋል።
ትናንት ከተገለጸዉ 8 ሰዎች በተጨማሪ ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ 3ቱ ማለፋቸዉን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 11 መድረሱን ገልጸዋል።
ኢስፔክተር ተስፋዬ ፤ " የጤና ቡድኑን ይዞ ይጓዝ የነበረዉ መኪና የፍሬን ችግር እንደነበረበት መረጃ ደርሶኛል " ያሉ ሲሆን አደጋው የደረሰው በዎላይታ ዞን ስር በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
አሁን ላይ በሐዋሳ ያኔት ሆስፒታል ውስጥ 2 ሰዎች በጽኑ ህክምና ክትትል ዉስጥ ሲሆኑ ከ5 በላይ ሰዎች ቀላል ጉዳት በማስተናገዳቸዉ ህክምና ተደርጎላቸዉ መሄዳቸው ተሰምቷል።
አስከፊ በተባለው በዚህ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው የጤና ስፖርት ቡድን አባላት ወጣቶች በሐዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑና ከማህበረሰቡ ጋር ተግባቢ ፣ በፀባያቸው በስራቸው ፣ በማህበራዊ ኑሯቸው በነዋሪዎች ዘንድ እጅግ የሚወደዱ እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።
በተከሰተው አደጋ እና በጠፋው የሰው ህይወት ምክንያት ከተማዋ የሀዘን ማቅ ለብሳለች ሲሉ የከተማው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
መረጃዉን አዘጋጅቶ የላከዉ የሐዋሳው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia

የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች መሰጠት ጀምሯል። ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከዛሬ ካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት እንደተጀመረ ገልጿል። በዛሬው እለት በጤና ፕሮግራሞች በተጀመረው ፈተና ጠዋት 15,440 ተማሪዎች በ23 የጤና ፕሮግራሞች የተፈተኑ ሲሆን ከሰዓት 14,807 ተማሪዎች በ13 ፕሮግራሞች ተፈትነዋል። ፈተናው በሁሉም የፈተና ማዕከላት ከተማ እየተሰጠ…
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ2016 ዓ .ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት ከየካቲት 18/2016 ዓ/ም ጀምሮ መለቀቁን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ፤ ለሁሉም የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ ባስተላለፈው መልዕክት ነው።
ተፈታኞች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ሊንክ ማየት ይችላሉ ተብሏል።

#ወጋገን_ባንክ
በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ወጋገን ሞባይል መተግበሪያን ከፕለይስቶር ወይም ከአፕስቶር በማውረድ ምቾትዎ ተጠብቆ ሂሳብዎን ያንቀሳቅሱ። አገልግሎቱን ለማግኘት የወጋገን ባንክ ሂሳብ በመክፈት የወጋገን የሞባይል ባንክ አገልግሎት *866# ይመዝገቡ፡፡
ከዚያም ቀጣዩን ሂደት ይከተሉ፤
(ሀ) መተግበሪያውን ከአፕስቶር ወይም ጎግል ፕሌይስቶር በማውረድ ስልክዎ ላይ ይጫኑ፤
(ለ) ወደ *866# በመደወል “Activate Your Mobile Application” የሚለውን ይምረጡ፤
(ሐ) በአጭር ፅሁፍ መልዕክት አገልግሎቱን ማስጀመሪያ የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (Activation Code) ሲደርስዎት መተግበሪያው ላይ ይህንኑ ሚስጥራዊ ቁጥር ያስገቡ፤
(መ) የሚስጥር ቁጥር በመቀየር አገልግሎቱን መጠቀም መጀመር ይችላሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በ 866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ፡፡
Download now:
Android:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.act.wegagen&hl
IOS:https://apps.apple.com/in/app/wegagen-mobile/id6472656143

#እንድታውቁት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 ከእድሳትና የማስፋፋት ሥራ በኋላ ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ሁሉም የሀገር ውስጥ በረራዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር አሳውቋል።
ከአዲስ አበባ ወደ ሁሉም የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዲሁም ከሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት በረራዎች በተርሚናል 1 ይደረጋሉ።
በሌላ በኩል ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደንቢዶሎ በሳምንት 3 በረራዎችን ዛሬ መልሶ አስጀምሯል፡፡
ይህ በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ የሚሰጠውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የማስፋፋት አንዱ አካል ነው ተብሏል።

#Mekelle
በመቐለ የታገተ የ9 ዓመት ህፃን ልጅ ለማስለቀቅ 4 ሚሊዮን ብር ቢጠየቅም ልጁ ከ1 ሳምንት እግታ በኃላ በፓሊስና ህብረተሰብ ትብብር ነፃ ሊወጣ ችሏል።
ለመሆኑ እግታው እንዴት ተፈፀመ ?
ልጁ ሳሚኤል መሓሪ ከበደ ይበላል። ገና 9 ዓመቱ ነው። ነዋሪነቱ በዓይደር ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ቀበሌ ነው።
ይኸው ልጅ አገር አማን ብሎ ቅዳሜና እሁድ በመንደሩ ከጓደኞቹ በመጫወትና በመቦረቅ ላይ እያለ በባጃጅ የመጡ ሰዎች አፍነው ወሰዱት።
ወላጆቹ ልጃችን ይመጣል ብለው ቢጠብቁም ብርሃን በጨለማ ተተክቶ የውሃ ሽታ ሆነባቸው።
ወደ ፓሊስ ቢያመለክቱም ፤ ወደ መንግስትና የግል የጤና ተቋማትና አብያተ ክርስትያናትም ጭምር ቢያፈላልጉ የሚወዱት ህፃን ልጃቸውን ማግኘት አልቻሉም።
ከቀናት ፍለጋ በኃላ የህፃኑ ቤተሰቦች ስልክ ተደወለላቸው።
አጋቾቹ ልጃቸው መታገቱንና እንዲለቀቅ ከተፈለገ 4 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ጠየቁ።
በዚህ መሀል ፓሊስ ብርቱ የክትትል እያደረገ ስለነበር ከሳምንት እልህ አስጨራሽ ፍለጋ በኃላ አጋቾቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።
ህፃኑም ለህክምና ምርመራ ወደ ጤና ተቋም እንዲላክ ሆኗል።
በድርጊቱ እጃቸው አለበት የተባሉ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
መረጃው የመቐለ ፓሊስ ዛሬ ለጋዜጠኛች የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ ዋቢ በማድረግ ያደረሰን የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵይም ቤተሰብ አባል ነው።

" በፈንጂ እና በድማሚት ቢሞከረም ሊሳካ አልቻለም " - የከበሩ ማዕድናት አምራች ማህበር ከ12 ቀናት በፊት በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ፤ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት ቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸው ሰዎች የሚወጡበት መፍትሔ አሁንም ድረስ አለመገኘቱን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር እና የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ተናግሯል። ትላንት የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በመገኘት የዋሻውን የላይኛው…
#Update
" አንዳንድ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ የለቅሶ ስነ ስርዓት ፈፅመዋል " - የደላንታ ወረዳ አስተዳደር
በናዳ ከተቀበሩ 18 ቀን የሞላቸው ወጣቶች ዛሬም አልተገኙም፡፡
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ወገል ጤና አካባቢ በማዕድን ቁፋሮ ላይ እንዳሉ ጉድጓድ ከገቡ 18ኛ ቀን የሆናቸውን ወጣቶች እጣፋንታ ለማወቅ የተደረጉ የህዝብና የመንግስት ጥረቶች እስካሁን እንዳልተሳኩ የደላንታ ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል።
አንዳንድ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ የለቅሶ ስነ ስርዓት መፈፀማቸው ተነግሯል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ወጣቶቹን ከተቀበሩበት ጉድጓድ ለማውጣት በሰው ኃይል ሲያደርጉት የነበረው ሙከራ ባለመሳካቱ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመተባበር ለቁፋሮ እንቅፋት የሆነውን የአለት ክፍል በከባድ መሳሪያ ለማስወገድ የተለያዩ ሙከራዎች ሲደረጉ ቢቆይም የተገኘ ምንም ውጤት እንደሌለ ወረዳው ገልጿል።
ወረዳው ፤ በባባህላዊ መንገድ ቁፋሮዎች ለተከታታይ አንድ ሳምንት ያክል ሲካሄድ መቆየቱን ግን ሌላ ናዳ በቆፋሪዎች ላይ ሊያስከትል የሚችል ስጋት በመፈጠሩ በሰው ጉልበት ሲደረግ የነበረው ቁፋሮ መቆሙን አመልክቷል።
ከዚህ ቀጥሎ ዞን፣ ክልልና ፌደራል መንግስት በጋራ ተነጋግረው በባለሙያዎች ተጠንቶ ተራራውን የሚንድ መሳሪያ እንዲመጣ ተደርጎ 35 ቶን የሚመዝን ተተኳሽ ተጠምዶ ተንጠልጣይ ቋጥኙን በፍንዳታ ለማስወገድ ቢሞከርም ሳይቻል ቀርቷል ብሏል።
ዛሬም የአካባቢው የመከላከያ ኃላፊ፣ የዞን የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች በተገኙበት ቋጥኙን በተለያዩ ተተኳሾች ለማስወገድ የተደረገው ሙከራ እንዳልተሳካ ተገልጿል።
ዛሬ ብቻ ቋጥኙን 10 ጊዜ ያክል በታንክ ቢመታም ቋጥኙን ማስወገድ እንዳልተቻለ ወረዳው አሳውቋል።
የደቡብ ወሎ ዞን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በናዳው 20 ያክል ወጣቶች መቀበራቸውን ከዚህ ቀደም ቢያሳውቅም ወረዳው ግን በተጨባጭ አደጋው የደረሰባቸው 9 ወጣቶች ናቸው ብሏል፡፡
ተስፋ የቆረጡ አንዳንድ ቤተሰቦች ለቅሶ መቀመጣቸውን ያሳወቀው ወረዳው ፤ እስካሁን የተደረጉ ሙከራዎች ባይሳኩም የቤተሰብ ፍላጎት እስካለ ድረስ ወጣቶቹን በህይወት የማገኘት እድሉ በእጅጉ የጠበበ ቢሆንም አስከሬንም የሚገኝ ከሆነና በወግና በስርዓት የቀብር ስነስርዓት ለመፈጸም ፍለጋው በሰው ኃይልም ቢሆን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
ፎቶ፦ የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚኒኬሽን

#Infinix_Hot40
በአጭር ደቂቃ ስልኮን ፉል ቻርጅ ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት አዲሱን ኢንፊኒክስ ‘Hot 40 pro’ የግሎ ያድርጉ!
#InfinixEthiopia #InfinixMobile #Infinix_Hot40 #Infinix_HotSeries

ከቴሌብር አካውንት ወደ ሌላ የቴሌብር ደንበኛ አካዉንት ገንዘብ መላኪያ ታሪፍ ላይ እስከ 80% ቅናሽ ማድረጋችንን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
በአዲሱ የታሪፍ ቅናሽ እስከ ብር 5,000 ሲልኩ 0.1% እንዲሁም ከብር 5,001-75,000 ለመላክ 5 ብር ብቻ የአገልግሎት ክፍያ ይፈጽማሉ።
የቴሌብር ሱፐርአፕን ከ https://onelink.to/fpgu4m ያውርዱ ወይም *127# ይደውሉ!
ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

#Amahra #Oromia ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ወገኖችን ወደቄያቸው ለመመለስ ከሰሞኑን በክልሎቹ መካከል የተደረሰበትን የመግባባት ስምምነት በተመለከተ ለሁለቱም ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮዎች ተከታዮችን ጥያቄዎች አቅርቧል። 👉 ከሞት ሸሽተው ወደ አማራ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ለመመልስ ፈቃደኛ ናቸው ? ይህንን ማወቅ ተችሏል ወይ ? 👉 በመንግሥት…
#Update
በጸጥታ ችግር ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ተፈናቅለው በአማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደዬ ቄያቸው ለመመለስ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ እንደነበር የኦሮሚያና አማራ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች በተደጋጋሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው አይዘነጋም።
የክልሎቹ የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ከሁለት ወራት በፊት ሲገልጹ የነበረው፣ የጸጥታ ችግር የነበራቸውን የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በቅድሚያ ሰላምን መስፈኑን በማረጋገጥ ተፈናቃዮቹ እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ እንደሚከናውን ነበር።
ይህን ተከትሎም ከተፈናቃዮቹ መካከል በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች አንዳንዶቹ “ ተገደን ” ነው፣ ሌላኛዎቹ ደግሞ “ በፈቃዳችን ” ነው ባሉት ንግግር ወደ ወለጋ እየተመለሱ መሆኑን ሰሞኑን ሲገልጹ ተስተውለዋል።
ለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበባው መለሰ፣ “ ከኦሮሚያ ክልል ወደ አማራ ክልል የመመለስ ስለሆነ ፕሮግራሙን የያዘው፣ አመራርም መድቦ ሲያወያይ የቆዩት የፌደራልና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት ናቸው ” ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባይሆኑም፣ “ አጠቃላይ መልሶ ማቋቋምን አስመልክቶ ሁለቱ ክልሎች በቅርቡ ይፋዊ መግለጫ ይሰጣሉ ” ሲሉ አጭር የፅሑፍ ምላሽ ሰጥተዋል።
የአማራ ክልል ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) እና ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ለገሰ ተደጋጋሚ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣ ተፈናቃዮች ከፊሎቹ " ተገደን ነው እየተመለስን ያለነው "፣ ከፊሎቹ ደግሞ " በፈቃዳችን ነው እየተመለስን ያለነው " የሚሉ ሀሳቦች ማቅረባቸውን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተላከላቸው የፅሑፍ መልዕክትም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
በተጨማሪ ስለ ተፈናቃዮቹ ቅሬታ ምላሽ መስጠት ይችሉ እንደሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌታ በበኩላቸው፣ “ ተፈናቃዮች ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ ዞኖች፣ ከሱዳንም፣ ከተለያዩ ቦታዎች ሰዎች እየተፈናቀሉ በመጠለያ እንዲሁም Host community ሆነውም የሚኖሩ አሉ ” ብለዋል።
“ ይሄን ደግሞ መንግሥት ትኩረት አድርጎ እየሰራበት ያለ ጉዳይ ነው” ያሉት ኃላፊዋ፣ “እናም ይሄ ከብዙ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራ ጉዳይ፣ በከፌተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተይዞ እየተከናወነ ያለ ጉዳይ ስለሆነ፣ እኛ በቂ ክልትትል ስሌለን፣ አሁንም ደግሞ ይሄ ነው ብለን ለሕዝብ የምንነግረው ያን ያክል ዝርዝር መረጃ ለእናንተ የምናደርሰው በአሁኑ ሰዓት አይኖረንም” ነው ያሉት ኃላፊዋ።
መረጃውን ያዘጋጀው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#ባይቶና በእነ ክብሮም በርሀ እና ኪዳነ ኣመነ የሚመራው "ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የተባለ የፓለቲካ ድርጅት ሙሉ እውቅና ማግኘቱ አስታውቋል። በእነ ዶ/ር ፀጋዛኣብ ካሕሱ ከሚመራው " ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የፓለቲካ ደርጅት ተነጥሎ የወጣው ባይቶና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሙሉ እውቅና ማግኘቱን ገልጿል። በእነ ክብሮም በርሀ እና ኪዳነ ኣመነ የሚመራው …
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የፓለቲካ ፓርቲ ህጋዊ እውቅና አገኘ።
የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አቶ ዓብለሎም መለስ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ "ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የክልላዊ ፓለቲካ ፓርቲ የምዝገባና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አግኝቷል " ብለዋል።
ፓርቲው የምዝገባና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያመሰገኑት ከፍተኛ አመራሩ ፣ ፓርቲው ለሚያካሂደው ፓለቲካዊ ትግል እውቅናው ምቹነት ይፈጥርለታል ብለዋል።
ብሄራዊ ባይቶና ዓባይ ትግራይ ( ባይቶና ) የተባለ የትግራይ ተፎካካሪ ፓርቲ ባለፈው ጥር ወር 2016 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልላዊ ፓለቲካ ፓርቲ የምዝገባና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘቱ መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።