#Axum
በጭንቅላት የተጣበቁ መንትዮች ተወለዱ።
ሴት መንትዮቹ (Conjoined twins) እንዲሁም እናቲቱ በመልካም የጤና ሁኔታ ይገኛሉ ተብሏል።
መጋቢት 22 /2016 ሌሊት በሪፈር የተላከች እናት በቆዶ ጥገና 5 ኪሎ የሚመዘኑ በጭንቅላት የተጣበቁ ሴት መንትዮች እንደተገላገለች የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ገልጿል።
ወላጅ እናት ለአዋላጅ ሃኪም የሰጠችው መረጃ በመጥቀስ ባለሙያዎች እንዳሉት ፥ እናቲቱ የፅንስ ክትትል በአቅራቢያዋ በሚገኝ የጤና ማእከል ውስጥ ስታደርግ የቆየች ብትሆንም የአልትራሳውንድ ምርመራ ባለማድረግዋ በማህፀንዋ የነበሩት መንትዮች ሁኔታ ቀድማ ማወቅ አልቻለችም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው ያገኘው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#አክሱምኤርፖርት የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አውሮፕላን ማረፍያ ለማደስ በጨረታ ላሸነፈው የኮንስትራክሽን ድርጅት ይፋዊ የርክክብ ስነ-ሰርዓት አላካሄደም ተብሏል። ይህ ሁኔታ ደግሞ የእድሳት ሰራው በፍጥነት በሙሉ አቅም እንዳይሰራና እንዲዘገይ ምክንያት እየሆነ ነው በሚል ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገልጸዋል። መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር…
#Axum
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰኔ 2016 ዓ/ም ወደ ትግራይ አክሱም ከተማ በረራ እንደሚጀመር መግለጹን ትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በትግራይ በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት በደረሰበት ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።
በቅርቡ ግን አውሮፕላን ማረፊያው መልሶ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።
የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለማየ ያደቻ ለትግራይ ቴሌቪዥን በስልክ በሰጡት መረጃ ፤ " በአውሮፕላን ማረፍያው ሲካሄድ የቆየው የጥገና ምዕራፍ ወደ መጨረሻ መደረሱን ተከትሎ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት መልሶ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል " ብለዋል።
ወደ ታሪካዊቷ አክሱም ሲከናወን የነበረው የአውሮፕላን በረራ በመቋረጡ ምክንያት ነዋሪዎች መቸገራቸው እንዲሁም በአከባቢው የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ከፍታኛ መቀዛቀዝ እንዲታይ ማድረጉ በተደጋጋሚ መዘጋቡ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

" የሃውልቱ ዲዛይንና መሬት ላይ የተገነባው ለየቅል ነው ፤ አይገናኝም ! "
ዛሬ በአክሱም ከተማ የማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሃውልት ተመርቋል።
ነገር ግን ከሃውልቱ ግንባታ ጋር በተያያዘ በርካቶች " አይመጥንም " በሚል ተቃውመዋል።
በአክሱም በይፋ የተመረቀው የማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሃወልት ለግንባታው አራት (4) አመት መፍጀቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል።
በምረቃ ስነ-ሰርዓቱ የተገኘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሃውልቱ ግንባታ ዙሪያ የተነሳው ተቃውሞ ተከታትሏል።
በምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙ ምእመናን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የኢትዮጵያና የዓለም የዜማ አባት የሆነው ማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ የሚያስታውስ ሃወልት መቆሙ ቢያስደስታቸውም " ሃውልቱ የዜማ አባቱን ክብርና ዝና የሚመጥን አይደለም " ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
በስነ-ሰርዓቱ ላይ የተገኙት የአክሱም ገዳማት ወ አድባራት አስተዳዳሪ ንቡረ እድ ጎደፋ መርሃ ምእመናኑና እና ታዳምያን " ሃወልቱ አይመጥንም " ሲሉ ያነሱትን ቅሬታ ተጋርተውታል።
የምረቃ ስነ-ሰርዓቱ በሚድያ ለህዝብ ይፋ ከሆነ በኃላ ' ሃወልቱ ቅዱስ ያሬድን አይወክልም ፤ አይመጥም ' የሚል በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያለው ወገን ተቃውሞውን በማህበራዊ ሚድያ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት እያጋራ ነው።
ከዚህ አለፍ ሲል ፈርሶ ድጋሜ እንዲገነባና ሃወልቱ ማህሌታይ ያሬድን በሚመጥን መልኩ በሀገር ያሉና በውጭ ያሉ ባለሞያዎችን አሳትፎ እንዲገነባ " ገንዘብ እናዋጣለን " እንዲሁም እውቀታችንን እናካፍላለን ያሉ አሉ።
" የሃውልቱ ዲዛይን እና መሬት ላይ የተገነባው ለየቅል ነው አይገናኝም " ያሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ባለመከታተሉ ወቅሰዋል።
ሃወልቱ #በመቐለ_ዩኒቨርስቲ እና በአክሱም ገዳማት ወ አድባራት አስተዳደር ትብብር የተገነባ ሲሆን ለግንባታው ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።

#Axum የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰኔ 2016 ዓ/ም ወደ ትግራይ አክሱም ከተማ በረራ እንደሚጀመር መግለጹን ትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል። የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በትግራይ በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት በደረሰበት ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል። በቅርቡ ግን አውሮፕላን ማረፊያው መልሶ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ…
#Ethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው #ሰኔ_ወር 2016 ዓ/ም ወደ ሁለት የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎች በረራ ይጀምራል።
አየር መንገዱ #ከሰኔ_10_ጀምሮ ወደ ወለጋ ፣ ነቀምቴ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል።
በረራው በሳምንት 4 ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ከዚህም ባለፈ ፥ በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ወደ አክሱም የሚደረገው በረራ ከሰኔ 1 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ታውቋል።
የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በጦርነቱ በደረሰበት የከፋ ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።
ከሰኔ 1 ጀምሮ ግን የመንገደኞች በረራ ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።
#Ethiopia #OromiaRegion #TigrayRegion #Wollega #Axum

#Axum #Tigray
" በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው ከባድ ነበር !! "
ወ/ሮ በላይነሽ መኣሾ (የአክሱም ነዋሪ ለድምጺ ወያነ) ፦
" ሰላም በመሆኑ ጥሩ ነው ያለው። ብርሃን አየን።
በሰላም እየተንቀሳቀስን ነው። #ሕጻናት እየተጫወቱ ነው።
ብዙ ለውጥ ነው ያለው።
በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው እጅግ ከባድ ነበር። አሁን በጣም በጣም ይሻላል ፤ ቢያንስ #እፎይ ብለን መተኛት እንችላለን።
ቢሆንም ግን #የከፋው_ሰው_አለ ፤ ሰው የሚበላው የሚጠጣውን አጥቶ በጣም ከፍቶታል ፣ የመንግስት ሰራተኛውም ያለፉት ዓመታት ደመወዝ ባለመከፈሉ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ነው ያለው ፣ የተፈናቃዮች ነገርማ #አይወራም ፣ ሕጻናት ልጆች የሚበሉትን አጥተው በየከተማው #በልመና ነው ተሰማርተው ያሉት። "
#Ethiopia #TigrayRegion #Peace

#Ethiopia የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው #ሰኔ_ወር 2016 ዓ/ም ወደ ሁለት የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎች በረራ ይጀምራል። አየር መንገዱ #ከሰኔ_10_ጀምሮ ወደ ወለጋ ፣ ነቀምቴ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል። በረራው በሳምንት 4 ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጿል። ከዚህም ባለፈ ፥ በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ወደ አክሱም የሚደረገው በረራ ከሰኔ 1 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ታውቋል።…
ፎቶ ፦ የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ ኤርፖርት #በተያዘለት_የጊዜ_ሰሌዳ አገልግሎት መስጠት እንዲጀመር የሚያስችሉት የጥገና ስራዎች አሁን ላይ ወደመጠናቀቁ መሆናቸው ተነግሯል።
በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰበት ኤርፖርቱ የጥገና ስራው ቀን እና ሌሊት እየተሰራ ነበር።
የጥገና ተቆጣጣሪ አካል የአውሮፕላን ማረፍያው የሚገባውን ጥራት በያዘ ደረጃ ስራው እየተሰራ መሆኑን ጠቁሟል።
በረራው እንዲጀመር በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ በረራው እንዲጀመር የማጠናቀቅ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ አክሱም መደበኛ በረራ እንደሚጀመር ማሳወቁ ይታወሳል።
#Ethiopia #Tigray #Axum
Photo Credit - Tigray TV

ፎቶ ፦ የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ ኤርፖርት #በተያዘለት_የጊዜ_ሰሌዳ አገልግሎት መስጠት እንዲጀመር የሚያስችሉት የጥገና ስራዎች አሁን ላይ ወደመጠናቀቁ መሆናቸው ተነግሯል። በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰበት ኤርፖርቱ የጥገና ስራው ቀን እና ሌሊት እየተሰራ ነበር። የጥገና ተቆጣጣሪ አካል የአውሮፕላን ማረፍያው የሚገባውን ጥራት በያዘ ደረጃ ስራው እየተሰራ መሆኑን ጠቁሟል። በረራው…
#Update #Axum
የአክሱም ኤርፓርት ሰኔ 2/2016 ዓ/ም ዳግም የበረራ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።
በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ ኤርፖርት ሰኔ 2 የመጀመሪያ ዳግም በረራውን ያደርጋል።
እሁድ ሰኔ 2 በኤርፓርቱ ዳግም መደበኛ የበረራ አገልግሎት ስነ-ሰርዓት ማስጀመሪያ ጥሪ የተደረገላቸው የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአክሱም ከተማ ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
የአክሱም ኤርፓርት ሰኔ 2/2016 ዓ/ም ዳግም የበረራ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።
በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ ኤርፖርት ሰኔ 2 የመጀመሪያ ዳግም በረራውን ያደርጋል።
እሁድ ሰኔ 2 በኤርፓርቱ ዳግም መደበኛ የበረራ አገልግሎት ስነ-ሰርዓት ማስጀመሪያ ጥሪ የተደረገላቸው የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአክሱም ከተማ ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Axum የአክሱም ኤርፓርት ሰኔ 2/2016 ዓ/ም ዳግም የበረራ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ ኤርፖርት ሰኔ 2 የመጀመሪያ ዳግም በረራውን ያደርጋል። እሁድ ሰኔ 2 በኤርፓርቱ ዳግም መደበኛ የበረራ አገልግሎት ስነ-ሰርዓት ማስጀመሪያ ጥሪ የተደረገላቸው የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት እንደሚገኙ ቲክቫህ…
#Axum #Update
የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ ከሶስት ዓመት በኃላ ዛሬ እሁድ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት የመጀመሪያውን ይፋዊ የአውሮፕላን በረራ አስተናግዷል።
የዳግም በራራ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት የክልል እና የፌደራል ባለስልጣናት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
በቦታው የሚገኘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በላከው መረጃ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን አዲስ አበባ ተነስቶ ከቀኑ 6:00 ላይ አክሱም የደረሰው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-700 አውሮፕላን 140 ተጓዦች ይዟል።
ከተጓዦቹ ውስጥም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ፣ የፌደራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች ይገኙበታል።
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዜዴንት አቶ ጌታቸው ረዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
#Axum #Ethiopia #Tigray