TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🚨BREAKING🚨 ኢራን እስራኤል ላይ የድሮን ጥቃት ከፈተች። ከዛሬ 12 ቀናት በፊት እስራኤል በሶሪያ የኢራን ቆንስላ ጽ/ቤት ላይ እንደፈፀመችው በተነገረ የአየር ጥቃት ከፍተኛ የኢራን ጄኔራልን ጨምሮ 13 ሰዎች ተገድለዋል። እስራኤል ለግድያው ኃላፊነቱን ባትወስድም ኢራን እሷ እንደሆነች ነው የምታምነው። ይህን ተከትሎ ኢራን የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ስትዝት ቆይታለች። መዛት ብቻ ሳይሆን ዝግጅትም…
#UPDATE

ኢራን ለሊቱን እስራኤልን በድሮን ፣ በሚሳኤልና ሮኬቶች ስትደበድብ ከቆየች በኃላ " እስራኤልን የመቅጣቱ ተግባር #ተጠናቋል " ብላለች።

እስራኤል ማንኛውም አፀፋዊ ምላሽ ሰጣለሁ ካለች ግን ከአሁኑ እጅግ በጣም የከፋው ቅጣት ይጠብቃታል ሲትል አስጠንቅቃለች።

ኢራን የትኛውም ህዝባዊ ይሁን ኢኮኖሚያዊ ዒላማዋች እንዳልነበሯት ዒላማዋ የእስራኤል ወታደራዊ ስፍራዎችና አቅም ላይ እንደነበር ገልጻለች።

ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በእስራኤል ላይ እንዲህ ያለውም ቀጥተኛ መጠነ ሰፊ ጥቃት የከፈተችው።

ከ360 በላይ ሚሳኤል እና ድሮኖች ከኢራን፣ ኢራቅ፣ የመን ወደ እስራኤል መወንጨፋቸውን የእስራኤል ሠራዊት አስታውቋል።

አብዛኞቹ ጉዳት ሳያደርሱ (99%) በእስራኤል እና በወዳጆቿ አማካይነት እንዲከሽፉ መደረጋቸው ተገልጿል።

ያም ሆኑ በጥቃቱ መጠነኛ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

እስራኤል የለሊቱን ጥቃት ብቻ ለመመከት 1 ቢሊዮን ዶላር ሳታወጣ አልቀረችም ተብሏል።

የአሜሪካ ጦር በርካታ ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን ከአየር ላይ እንዲከሽፉ አድርጓል። ፕሬዜዳንቷም " እስራኤል የኢራንን ጥቃት የመከተችው በአሜሪካ ድጋፍ ነው " ብለዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይም ከጥቃቱ በፊት የአየር ቅኝት በማድረግ እስራኤልን ሲያግዙ አንግተዋል።

ጆርዳን በአየር ክልሏ ሲያልፉ የነበሩ ድሮኖችን እየመታች የጣለች ሲሆን ይህንን " ለህዝቤ ደህንነት ስል ያደረኩት ነው " ብላለች።

ኢራንም ጆርዳንን " አርፈሽ ካልተቀመጥሽ አንቺም ልክ እንደ እስራኤል ትመቻለሽ " ስትል ዝታባታለች።

እስራኤል በቀጣይ የአፀፋ እርምጃ ትወስድ ይሆን ? የሚለው ብዙዎችን ያሳሰበ ጉዳይ ሲሆን " አሜሪካ ተያት አፀፋ አትውሰጂ " ብላታለች።

ቀድሞኑ በእራኤል እና ፍልስጤም ሀማስ  ጦርነት የተለያየ አቋም ያላቸው የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል። ውጥረቱ ይረግብ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢራን ፥ እስራኤልን የደበደበችው ከዛሬ 13 ቀን በፊት በሶሪያ የኢራን ቆንስላ ጽ/ቤት ላይ እስራኤል እንደፈፀመችው በምታምነው የአየር ጥቃት ከፍተኛ ጄኔራሏን ጨምሮ አጠቃላይ 13 ሰዎች በመገደላቸው ለሱ አፀፋ ነው።

መረጃው ከዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የተሰባሰበ ነው።

More⬇️
https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

@tikvahethiopia