TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AU : ዛሬ የታንዛንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኜሬሬ መታሰቢያ ሐውልት ተመርቋል።

ሐውልቱ የተገነባው በአዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የአፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ፊትለፊት ነው።

በምርቃ ስነስርዓቱ ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ተገኝተው ነበር።

@tikvahethiopia
#AU #ETHIOPIA

ትላንትና ምሽት ላይ ለ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመጡ መሪዎች በብሄራዊ ቤተመንግስት የእራት ግብዣ ተደርጎላቸው ነበር።

ዛሬ የጠ/ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ባሰራጫቸው ምስሎች የኬንያው ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ፣ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በእራት ግብዣው ላይ ተገኝተው የነበረ ሲሆን የጎረቤት ሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ አልታዩም።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ትላንት እዚሁ አ/አ ሆነው በሰጡት መግለጫ " የኢትዮጵያ ፀጥታ ኃይሎች ከሆቴል እንዳልወጣ እንዲሁም ከጅቡቲ ፕሬዜዳንት ጋር ሆነን ወደ ጉባኤው እንዳንገባ ክልከላ አድርገውብናል " የሚል ክስ አሰምተው ነበር።

በትላንት ምሽቱ የብሔራዊ ቤተመንግስት የእራት ግብዣ ላይ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህ ከሌሎች ፕሬዜዳንቶች ጋር በመሆን ከፊት መስመር ከፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጎን ተቀምጠው ታይተዋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ግን በስፍራው አልታዩም።

ዛሬ እሁድ " አናዱሉ " የዜና ወኪል ባሰራጨው መረጃ በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቀውን የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ አቋርጠው ወደ ሶማሊያ፣ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል።

@tikvahethiopia
በዲጂታል እና ፋይናንሻል አካታችነት ሴቶችን ማብቃት!

ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ልዩነትን ለማጥበብ እና የሴቶችን የዲጂታል ተካታችነት ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት “Connected Women” ኢኒሼቲቭ- ከ GSMA ጋር በባርሴሎና ስፔን ተፈራርሟል::

ስምምነቱ በሀገራችን የሴቶችን የሞባይል ኢንተርኔት እና የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት /ቴሌብር/ ተጠቃሚ ቁጥር እ.ኤ.አ እስከ 2026 በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ኩባንያው ለተግባራዊነቱ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ እና በመተግበር እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት አካታች የሞባይል ኢንተርኔት እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ማቅረብን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በስምምነቱ ወቅት የኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ “ሴቶች በሀገራችን ልማት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ኩባንያችን አሁን የሚታየውን የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ክፍተት ለማጥበብ የሞባይል ኢንተርኔትና የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎቶችን ለሴቶች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ሴቶች በዲጂታል ኢኮኖሚው ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡” ብለዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #AU #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR #HOF
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AU #Fraud #CBE

ቀሲስ በላይ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሳላዊ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ #ከ6_ሚሊዮን_ዶላር_በላይ (367 ሚሊዮን ብር) ለማዘዋወር ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ፍድር ቤት ቀርበውም ለፖሊስ ተጨማሪ ቀን ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ምን አሉ ?

" በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካለው የአፍሪካ ህብረት ሒሳብ የወጣ ገንዘብ የለም።

አንድ ሰው ሀሰተኛ ሰነዶችን ተጠቅሞ ለማውጣት ቢሞክርም እዛው በቦታው ላይ ተይዟል።

የማጭበርበር ሃሳብና ገንዘብ ለመውሰድ ጥረት ቢደረግም ማክሸፍ ችለናል። ይህንን የሞከሩት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ናቸው። እኔ የማውቀው ይህን ብቻ ነው።

በመሰረቱ ጥሬ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ሊሰጥ አይችልም። አጭበርባሪው መጥቶ  ሲጠይቅ ይህን እንኳን አያውቅም ነበር።

ሰውዬው እዚህ ሀገር የዶላር አካውንት ከሌለው ገንዘቡ ቢተላለፍም የትም ውስጥ ሊገባ አይችልም።

አጭበርባሪዎች በየቀኑ ነው ወደ ባንካችን የሚመጡት ፤ ባንክ ስለምንሰራ ይህ የተለመደ ነው። ነገር ን ሁሌም የማጭበርበር ድርጊቶቹ ከመሳካታቸው በፊት እንደርስባቸዋለን። ለፍርድም እናቀርባቸዋለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፥ የደንበኞቹን ሒሳቦች የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ያንን እያደረግን ነው። የአፍሪካ ህብረት እስካሁን ድረስ በይፋ ቅሬታ አላቀረበብንም። "

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአፍሪካ ኅብረት ምንጭ ምን አሉ ?

"የእኛ ሒሳብ ላይ መሰል ማጭበርበር ሲያጋጥም ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

አሁን ላይ ማጭበርበሩ #በተከበሩ_ሰዎች አማካኝነት እየተሞከረ ነው። ይህ ደግሞ በጣም አስጨንቆናል። አንድ ቀን ባለስልጣናት ተመሳሳይ ነገር ላለማድረጋቸው ምንም አይነት ዋስትና የለንም።

እምነት እያጣን ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ለደሞዝ አነስተኛ መጠን ያለው ፎሬክስ (የውጭ ምንዛሬ) ለመያዝ ወስነናል።

ይህን መሰሉ ሁኔታ የድርጅቱን ገንዘብ በውጭ ማቆየት እንድናስብ እያስገደደን ነው። "

https://telegra.ph/The-Reporter-04-21 #ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ በሚከናወነው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ሌሎች ተያያዥ ስብሰባዎች ምክንያት ከነገ ማለትም ረቡዕ የካቲት 5/ 2017 ዓ.ም ረፋዱ 4፡00 ጀምሮ እስከ መጪው ሰኞ ማለትም የካቲት 10/2017 ዓ.ም ድረስ :-

1. አረቄ ፋብሪካ አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ዲያፍሪክ ሆቴል አካባቢ ፤

2. ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ለገሐር ተርሚናል፤

3. በተለምዶ ጠማማ ፎቅ የሚባለው አካባቢ የነበረው ተርሚናል ወደ ሳር ቤት ድልድይ ስር መዘዋወራቸውን እና ስብሰባዎቹ እንደተጠናቀቁ ወደ ቀድሞ ቦታዎቻቸው እንደሚመለሰ የአዲስ አባባ ከተማ አስታዳደር አሳውቋል።

#AU #ADDISABABA

@tikvahethiopia
#AU #Ethiopia

46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል።

በዚህም ዛሬ በተካሄደው ምርጫ #ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣለች።

@tikvahethiopia