TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GetachewKassa

በይበልጥ " ሀገሬን አትንኳት " ፣  " ውብ አዲስ አበባ " ፣ " የከረመ ፍቅር " በተሰኙት ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ስራዎች የሚታወቀው አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ድምፃዊ ጌታቸው ባደረበት ህመም የካቲት 12 ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ሀገሬን አትንኳት ...

" የብዙሃን እናት መጠጊያ የምንላት
እማማ ናትና ሀገሬን አትንኳት።

በዓድዋ በማይጨው ጀግኖች የሞቱላት
ህፃን ሽማግሌ የተሰየፈላት
ደመ መራራና ቁጡነት ያለባት
ጎጆዬ ናትና #ኢትዮጵያን አትንኳት !

ዘርዓይ ደረስ ወንዱ በሮሞ የቆመላት
ጀግኖች በጦር ሜዳ ወጥተው የቀሩላት
እኔም በተጠንቀቅ አለሁሽ የምላት
ጥቁሯን አፍሪካዬን ኢትዮጵያን አትንኳት። "

NB. አንፋጋው ድምፃዊ ጌታቸው የተጫወተው ' ሀገሬን አትንኳት ' የተሰኘው ዘመን አይሽሬ ስራ በአንጋፋው ደራሲና ገጣሚ ጋሽ አበራ ለማ የተፃፈ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ለአንድ ሓጅ አጠቃላይ ብር 329,000 እንዲሆን ተወስኗል " - ከኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት የዘንድሮው የሐጅ እና ዑምራ ምዝገባ ነገ ቅዳሜ ጥር 25 በይፋ የሚጀመር መሆኑ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አሳውቋል። የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ በባለፈው ዓመት 2015 ከነበሩት 18 የምዝገባ ጣቢያዎች ላይ 9 አዳዲስ ጣቢያዎችን በመጨመር ወደ 27 ከፍ እንዲሉ መደረጉ ለማወቅ…
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2016 የሐጅ ምዝገባ ቀናት መራዘሙን አሳውቋል።

ምክር ቤቱ ዘንድሮ የምዝገባ ሂደቱን ከተለመደው ጊዜ ቀደም ብሎ ማስጀመሩ ይታወሳል።

የሳዑዲ ሐጅ ሚኒስቴር ከወትሮ በተለየ መልኩ የአመዘጋገቡን ሂደት እና የምዝገባ ጊዜውን ቀደም ብሎ በማስጀመሩ ብቻ ሳይሆን ክፊያዎች የሚጠናቀቁበትን የጊዜ ገደብ ጭምር በመገደቡ የተነሳ #ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኛው የዓለም ሃገራት በተፈለገው ፍጥነት እና በተቀመጠው ቀነ ገደብ የሚፈለግባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት እንዳልቻሉ ተገልጿል።

በዚህም የሐጅ ምዝገባው እንዲራዘም ምክር ቤቱ ጉዳዩ ከሚመለከተው የሳዑዲ ሐጅ ሚኒስቴር ጋር ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጓል።

ይህ ተከትሎ በየካቲት 27 ቀን 2016 ይጠናቀቅ የነበረው የምዝገባ ሂደት የዓመቱ ኮታ እስኪሞላ ድረስ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅ አብይ ኮሚቴ የምዝገባ ሂደቱ እንደሚቀጥል በወሰነው ውሳኔ መሰረት ምዝገባው ይቀጥላል።

እስካሁን ድረስ ቀርበው ያልተመዘገቡ ሑጃጆች በቀረው ጊዜና ኮታ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

በጥር 25 ቀን 2016 በ27 ምዝገባ ጣቢያዎች የዘንድሮውን የሐጅ ምዝገባ የጀመረው ጠቅላይ ምክር ቤቱ  የእቅዱን 80% ሀጃጆችን  መመዝገቡን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Dollar

💵 " ዶላርን በሌላ የመገበያያ ገንዘብ መተካት አይታሰብም፤ ይህን ባደረጉ አካላት ላይ 100% ታሪፍ እጥላለሁ '' -  ትራምፕ

➡️ "አሜሪካ ሌሎች ሀገራት ዶላርን ብቻ እንዲጠቀሙ ለማስገደድ መሞከሯ ያለፈበት እሳቤ ነው '' - ሩሲያ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የBRICS+ አባል ሀገራት የአሜሪካን ዶላር ትተዉ በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ ለአሜሪካ ገበያ በሚያቀርቡት ሸቀጦቻቸዉ ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ዛቱ።

ትራምፕ ባሰራጩት ማስጠንቀቂያ የBRICS+ አባል ሐገራት ከዶላር ለማፈንገጥ ማሰባቸዉ " ማብቃት  አለበት " ብለዋል።

" ዶላርን በሌላ የመገበያያ ገንዘብ መተካት አይታሰብም " ሲሉ ገልጻዋል።

የBRICS+ አባል መንግሥታትን ለአሜሪካ " የጠላትነት አዝማሚያ " የሚታይባቸዉ በማለት ወርፈዋል።

ትራም እነዚህ ሀገራት " ግዙፍ " ያሉትን የአሜሪካን ዶላር ለመተካት አዲስ ገንዘብ ካሳተሙ ወይም በሌላ ገንዘብ ለመጠቀም ከወሰኑ ከአሜሪካ ገበያ መሰናበት አለባቸዉ ብለዋል።

ትራምፕ እንደሚሉት የBRICS+ ሀገራት አዲስ ዶላር ትተው በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ አስተዳደራቸው ወደ አሜሪካ በሚገቡ የየሀገራቱ ሸቀጦች ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ያደርጋል።

ሩሲያ ለዚሁ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዛቻ ምላሽ ሰጥታለች።

" አሜሪካ ሌሎች ሀገራት ዶላርን ብቻ እንዲጠቀሙ ለማስገደድ መሞከሯ ያለፈበት እሳቤ ነው " ብላለች።

የBRICS+ ቡድን ባሁኑ ወቅት
#ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 አባል መንግስታትን ያስተናብራል።

በኢንዲስትሪ የበለፀጉትን 6 ምዕራባዉያን ሀገራትና ጃፓንን የሚያስተናብረዉ ቡድን 7   የሚያደርሰዉን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያለመ ነዉ።

ሩሲያና ቻይናን የመሳሰሉ የBRICS ጠንካራ አባላትና መሥራቾች የአሜሪካ ዶላር በዓለም ገበያ ላይ የሚያደርሰዉን ጫና አጥብቀዉ ይተቻሉ።

ማሕበራቸዉ አማራጭ መገበያያ እንደሚያስፈልገዉም ያሳስባሉ።

የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ግን ዶላርን መተካት " አስደናቂ " ከሚሉት ከአሜሪካ ምጣኔ ሐብት መሰናበት ነዉ።

መረጃው የዶቼቨለና ቴሌግራፍ ነው።

@tikvahethiopia