TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AfricanDevelopmentBank የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓለም አቀፍ ሰራተኞቹን በአስቸኳይ #ከኢትዮጵያ ሊያስወጣ ነው። ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአንድ ወር በፊት ዋና የኢትዮጵያ ተወካዩ እና ሌላ የባንኩ ሰራተኛ ላይ በፀጥታ አካላት ድብደባ መፈፀሙን ተከትሎ ነው። በወቅቱ ባንኩ ቅሬታውን ለመንግስት አቅርቦ የነበረ ሲሆን መንግስትም አስቸኳይ ማጣራት አድርጎ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ ገልፆ…
#Update

የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓለም አቀፍ ሰራተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሊመለሱ ነው።

የአፍሪቃ ልማት ባንክ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሠራተኞቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ሠራተኞቹን ካስወጣ ከ1 ወር በኋላ ሠራተኞቹ በሙሉ ወደ #ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ዛሬ አስታውቋል።

ባለፈው ወር የልማት ባንኩ ፕሬዝደንት አኪንዋሚ አዴሲና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ዶ/ር ዐቢይ ለአፍሪቃ ልማት ባንክ ይቅርታ በመጠየቅና ለሠራተኞቹም ደህነትና የጸጥታ ዋስትና መስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ባንኩ ዛሬ ባወጣው መግለጫም የተለመደው ሥራውን ለመጀመር ባለሥልጣናት የደህንነት ዋስትና እንደሰጡት ገልጿል።

የአፍሪቃ ልማት ባንክ በዚሁ መግለጫው፤ ዶ/ር ዐቢይ እና አዴሲና ያካሄዱትን ውጤታማ ስብሰባ ተከትሎ፤ መንግሥት ይፋዊ ይቅርታ በመጠየቁና ከክስተቱ ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን በተመለከተ መፍትሄ ለመፈለግ ጠንካራ ቁርጠኝነት መኖሩን በመግለጹ ባንኩ ሥራውን ኢትዮጵያ ውስጥ ይጀምራል ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በዑጋንዳ ካምፓላ የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባኤ ዛሬ የተካሄደ ሲሆን ከጉባኤው ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና ጋር ተወያይተዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ውይይቱን ተከትሎ ፤ " ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያለንን ግንኙነታችንን በይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረናል " ብለዋል፡፡

" ከባንኩ ጋር ያለን አጋርነት ለኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነት ጥረቶች ወሳኝ ነው " ሲሉ አክለዋል።

መረጃው ከአፍሪካ ልማት ባንክ ድረገፅ / ሮይተርስ እና ዶቼ ቨለ የተሰበሰበ ነው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

የአቢሲንያን የሞባይል ባንክ አገልግሎት ወደ *815# በመደወል ብቻ ያለ ኢንተርኔት ወይም በስማርት ፎን መገልገል ይቻላል።


#BoAmobile #mobilebanking #BoA #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#NAM

ትላንት በኢንቴቤ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባን ያስተናገደችው ኡጋንዳ ዛሬ የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ (NAM) ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባኤ አስተናግዳለች።

በትላንቱ የኢጋድ ስብሰባ ላይ ያልተገኘችው ኢትዮጵያ በዛሬው ጉባኤ ላይ ተገኝታ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ወደ ካምፓላ አምርተው ጉባኤውን የተካፈሉ ሲሆን ንግግርም አድርገው ነበር።

በዚሁ ንግግራቸው ፤ " የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የሕዝብን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ፈተናዎችን እየተጋፈጡ ነው " ብለዋል።

የባሕር በር የሌላት ኢትዮጵያም ችግሩን ለመፍታት በሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት መርኅ መሰረት ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉባዔው ጎን ለጎን ፦
- ከኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣
- ከሲሪላንካ ፕሬዚዳንት ራኒል ዊከርሜሲንጌ 
- ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና 
- ከኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቶቹ  በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ነበሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካምፓላ ቆይታቸውን አጠናቀው ማምሻውን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ (NAM) እኤአ በ1961 ላይ የተመሰረተ ሲሆን 120 ሀገራትን በአባልነት ይዟል።

ንቅናቄው ሲመሰረት በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደርሱ ጭቆናዎችን በጋራ መታገል፣ ጸረ ቅኝ ግዛት ትግሎችን መደገፍ ፣ ብሔራዊ ነፃነትን፣ ሉዓላዊነትንና የግዛት አንድነርን መደገፍ የሚሉ ዓላማዎችን ይዞ ነው።

ከተመድ በመቀጠል በርካታ ሀገራትን በአባልነት የያዘ ንቅናቄ ሲሆን ዋና መቀመጫውን ሰርቢያ፣ ቤልግሬድ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ከተራ2016

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በቤተክርስቲያኗ ሥርዓት እና ትውፊት መሰረት የ2016 ዓ/ም የጥምቀት ከተራ በዓልን በመላው ሀገሪቱ አክብረዋል።

በተለይ በአዲስ አበባ ከተራ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሯል።

ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ-ጥምቀት ገብተዋል።

በነገው ዕለት በመላው ሀገሪቱ የጥምቀት በዓል ይከበራል።

@tikvahethiopia
Tecno Spark 20 pro +

የሞባይል ቴክኖሎጂ ብራንዶች አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ ሞባይል አዲሱ ምርት የሆነውን ስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ (Spark 20 Pro+) የተሰኘ  በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተራቀቀ፣ እጅግ ከፍተኛ የካሜራ ጥራትና የፕሮሰሰር አቅም፣ ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚችል ባትሪ፣ ማራኪ ቅርጽ እና ውበት ያለው የመጨረሻው የቴክኖሎጂ ውጤት የያዘውን እንዲሁም ደንበኞች የላቀ የአገልግሎት ተሞክሮ እንዲኖራቸው የሚያስችለውን የስማርት ሞባይል ስልክ ሞዴል  በአዲስ አበባ ፍሬንድሽፕ ፓርክ ልዩ እና ደማቅ በሆነ ዝግጅት  አስተዋወቀ።

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark20pro+ #TecnoMobile #TecnoEthiopia