TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ' አክሲዮን እናሻሽጣለን ' የሚሉ ማስታወቂያዎችና ግለሰቦች ህገወጥ ናቸው " - የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፤ " የአክሲዮን ድርሻ እናሻሽጣለን " የሚሉ ማስታወቂያዎችም ሆኑ ግለሰቦች ህገወጥ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ይወቅልኝ አለ።

በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፍተኛ የካፒታል ገበያ አማካሪ አቶ አሰፋ ስሞሮ ፤ " በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ ከአክሲዮን ገበያ ጋር በተገናኘ #የድለላ ስራ እየሰሩ ያሉ #ህገወጥ ግለሰቦች መኖራቸውን መረጃውን አለን ነገር ግን አንዳቸውም ከባለስልጣኑ ፈቃድ አላገኙም " ብለዋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ለጊዜው ፈቃድ መስጠት አለመጀመሩን የገለጹት ባለሙያው የፈቃድ መመሪያው ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩን በማንሳት በሚደረጉ ቀጣይ ውይይቶች ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በአሁኑ ወቅት ከባለስልጣኑ ፈቃድ ውጪ " አክሲዮን እናሻሽጣለን " የሚሉ ማስታወቂያዎችም ሆነ ግለሰቦች ህገወጥ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ሊያውቅ ይገባል ሲል አስገንዝበዋል።

በተቀመጠው አዋጅ መሰረት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች በሚል መጠሪያ ተቋሙ ፈቃድ እንደሚሰጥ በመግለጽ አስፈላጊው ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግባቸው እንደሚሆኑም ከአሁኑ ጠቁመዋል፡፡

ባለስልጣኑ በይፋ ፈቃድ መስጠት ሲጀምርም በመሰል ህገወጥ ተግባራት የሚሳተፉ ግለሰቦችን በህግ #ተጠያቂ እንደሚያደርግም አሳውቋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ #የአሃዱሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለጉምሩክ ሰራተኞች ' ጉቦ ሰጥቼ መኪኖችህን አስለቅቃለሁ ' በሚል 1 ሚሊዮን ብር ቼክ ሲቀበል የነበረ ትራንዚተር እጅ ከፍንጅ ተይዟል " - ፌዴራል ፖሊስ " ጉቦ ሰጥቼ መኪኖችህን አስለቅቅልሃለሁ " ብሎ ከባለ ጉዳይ የ1 ሚሊየን ብር ቼክ ሲቀበል የነበረ አንድ ትራንዚተር እጅ ከፍንጅ ተይዞ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። " ጉቦ ሰጥቼ መኪኖችህን አስለቅቅልሃለሁ " ብሎ…
የጉምሩኩ ታንዚተር #ክስ ተመሰረተበት።

1 ሚሊየን ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል በተባለው የጉምሩክ ትራንዚተር (አስተላላፊ) ግዑሽ አዳነ ላይ የሙስና ወንጀል ክሥ ተመሰረተ።

ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

የሙስና ወንጀል ክሱ ዝርዝር ላይ ምን ይላል ?

- ተከሳሹ በሚሰራው የጉምሩክ አስተላላፊነት ስራ መሰረት ከቀረጥ ነጻ ለኢንቨስትመንት የገባን " ቶዮታ ሀይሉክስ " ተሽከርካሪ ነብዩ ቡሽራ ከተባለ የግል ተበዳይና 1ኛ የዓቃቢ ሕግ ምስክር ከሆነው ግለሰብ ጋር በመሆን የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ለመፈፀም በመስማማት የግል ተበዳይን የ7 ዓመት የመኪናውን ቀረጥ እና ታክስ 1 ሚሊየን 511 ሺህ 356 ከ66 ሣንቲም እንዲከፍሉና ተሸከርካሪውን በአካል እንዲያቀርቡ ይናገራል።

- የግል ተበዳይ በኅዳር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ልዩ ቦታው " ሳሪስ አቦ "ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን መሥሪያ ቤት ሲቀርቡ ተከሳሹ ተሽከርካሪው ለጥያቄ እንደሚፈለግ እና መሿለኪያ ኃይሌ ይርጋ ሕንጻ ላይ በሚገኘው የጉምሩክ ዋና መሥሪያ ቤት መጠየቅ እንዳለባቸው ይገልጸል።

- በዚህም ተሽከርካሪው እንዲለቀቅ #ከጉምሩክ_ኮሚሽን_ኃላፊዎች ጋር #እንደሚያደራድራቸው ለግል ተበዳይ በመንገር እና መኪናውን ለመልቀቅ የግል ተበዳይ 1 ሚሊየን ብር እንዲከፍሉ #ኃላፊዎች_መግለፃቸውን በማሳወቅ በኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 7 ሠዓት ከ30 አካባቢ ቦሌ መድሃኒያለም አከባቢ ልዩ ቦታው " ኦኬዥን ካፌ " ውስጥ ከግል ተበዳይ ጋር በመገናኘት 1 ሚሊየን ብር በአቢሲኒያ ባንክ የተጻፈ ቼክ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

ዐቃቢ ህግ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦበታል።

ዐቃቤ ሕግ ከክስ ዝርዝሩ ጋር የሰውና የሠነድ ማስረጃ አያይዞ አቅርቧል። ተከሳሹ ችሎት ቀርቦ ክሱ እንዲደርሰው ከተደረገ በኋላ የክስ ዝርዝሩ በችሎት በንባብ ተሰምቷል።

መረጃው የኤፍቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" መፍትሄ ሳይሰጠን የዓመቱ አራተኛ ወር ሊገባ ነው " - ተማሪዎች በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እስካሁን ለተማሪዎቻቸው ጥሪ አላደረጉም። ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ያልጠሩት በክልሉ ባለው ተለዋዋጭ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት እንደሆነ ይታመናል። በክልሉ በሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ጊዜው ሳይሄድ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርቡም እስካሁን መፍትሄ…
የመፍትሄ ያለህ . . .

" መፍትሄ የሚባል ነገር ሳይሰጠን የትምህርት ዓመቱ 5ኛው ወር ሊገባ ነው " - ተማሪዎች

በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች እስካሁን ድረስ ወደ ሚማሩበት ዩኒቨርሲቲዎች አልተጠሩም።

ተማሪዎቹ መቼ እንደሚጠሩ አያውቁም ፤ መፍትሄም አልተሰጣቸውም።

ስለተማሪዎቹ ጉዳይ መፍትሄው ይሄ ነው ሳይባል የትምህርት ዘመኑ 5ኛ ወር ሊገባ ተቃርቧል።

ተማሪዎቹ ቤት ከዋሉ ወራት አልፈዋል። ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ላይ የሚገኙ ሲሆን የነሱ እኩዮች የትምህርት ዓመቱን አጋማሽ ለማጠናቀቅ ቀርበዋል።

ተማሪዎቹ እስካሁን ወደ ሚዲያ ወጥቶ መፍትሄ የሚናገር አካል ባለማግኘታቸው " በዚህ ዓመት ላንማር እንችላለን " የሚል ስጋት አድሮባቸዋል።

እነዚህ ተማሪዎች  ፤ በቅድሚያ በኮሮና ቫይረስ ተፅዕኖ፣ በኃላም በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ይፈጠሩ በነበሩ የፀጥታ ችግሮችና አሁን ደግሞ በአማራ ክልል ባለው ወቅታዊ የሰላም መደፍረስ ምክንያት ትምህርታቸውን ባግባቡ መማር አልቻሉም።

ተማሪዎቹ በእነሱ ጉዳይ ተገቢ መረጃ የሚሰጥ አካል እንደሌለ ይናገራሉ።

በራሳቸው መንገድ እየደወሉ ይመለከታቸዋል የሚባሉ አካላት ሲጠይቁ " ምንም አናውቅም " ይሏቸዋል። አንዳንዶች ስልክ አያነሱም፣ አጭር የፅሁፍ መልዕክትም አይመልሱም ፤ ተስፋ የሚሰጥ ነገርም አይናገሩም ሲሉ ይወቅሳሉ።

ተማሪዎቹ የዚህ ጊዜ " ባች " ከአንደኛ ዓመት ጀምሮ ብዙ ተግዳሮቶችን እየተጋፈጠ የመጣ " ባች " ነው ብለዋል።

* በኮሮና ምክንያት ብዙ ጊዜ ግቢ ውስጥ ለመቆየት ተገደዋል።
* በተለያዩ አለመረጋጋቶች የትምህርት ክፍለጊዜዎች እየተጓተቱ፣ እየተቆራረጡ፣ አንድ ወሰነ ትምህርት በ45 ቀናት እየተማሩ ነው የመጡት።
* ብዙ የትምህርት ክፍሎች አልተሸፈኑም፣ እነዚህ ደግሞ የመውጫ ፈተና አካል ናቸው ተማሯቸውም አልተማሯቸውም " ተምረዋቸዋል "ተብሎ ነው የሚታሰበው።
* የተማሯቸው የትምህርት ክፍሎች እንኳ በበቂ አልተማሯቸውም።
* የመውጫ ፈተና ላይ እንዴት ልንሆን ነው የሚልም ሃሳብ አለባቸው።

አሁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ቢገቡ ያልተሸፈነው ትምህርት እንዴት መሸፈን እንዳለባቸው ሲያስቡ ተማሪዎቹ ካሁኑ ጭንቅ ውስጥ እንደገቡ አስረድተዋል።

ተማሪዎቹ ያለትምህርት ረጅም ጊዜ ቤት መቀመጣቸው ለከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና እንደዳረጋቸውም ገልጸዋል።

ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ድረስ ተማሪዎች ተወክለው ቢጠይቁም ፤ ብዙ አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ አመልክተዋል።

በተለይም የጤና ተማሪዎች ፤ ትምህርታቸው ተጨማሪ ኮርሶች ያሉት የትምህርት መስክ በመሆኑ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ትምህርቱ ካልተሰጠ አስቸጋሪ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ምናልባት ጊዜ ካለፈ በኋላ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ በይድረስ ይድረስ ትምህርቱ የሚሰጥ ከሆነ ተማሪው በቂ እውቀት ይዞ አይወጣም ብለዋል።

በመጨረሻም ትምህርት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቷቸው መፍትሄ የሚለውን ነገር በይፋ እንዲያሳውቃቸው ጥሪ አቅርበዋል። ሁኔታው ተስፋ እንዳስቆረጣቸውም አስገንዝበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎችን ቃል የወሰደው ከዶቼ ቨለ ሬድዮ እንዲሁም በውስጥ ከመጡ መልዕክቶች ሲሆን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በእነዚህ ተማሪዎች ጉዳይ መሰል መልዕክት ማጋራታችን ይታወሳል።

የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ብዙ ጥረት ብናደርግም ይህ ነው ተብሎ ለተማሪና ወላጅ የሚነገር ምላሽ አላገኘንም።

@tikvahethiopia
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የፌስቡክ ገፅን https://bit.ly/47R6ZSI ይወዳጁ ባሉበት ሆነው ጥያቄዎችን ይመልሱ ሽልማቶችን ያግኙ፡፡

ነገ ማለትም ሐሙስ ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የመጀመሪያውን ዙር የጥያቄና መልስ ፕሮግራም ከእናንተ ተከታዮቻችን ጋር እንጀምራለን፡፡

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን
#ገና #ላልይበላ

ቀደም ባሉት ዓመታት (ዘመናት) ሁለት ሚሊዮን ምዕመናን ይታደሙበት የነበረው በላልይበላ የሚከበረው የገና በዓል ዘንድሮ ግን ታዳሚው እስከ 300 ሺህ ሊወርድ እንደሚችል የቅዱስ ላልይበላ ገዳም ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

የደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም ዋና አስተዳዳሪ አባ ህርያቆስ ፀጋዬ ለጋዜጣው ምን አሉ ?

" ዘንድሮ ክልሉ ባጋጠመው የፀጥታ ችግር ምክንያት በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ቁጥራቸው ከ300 ሺሕ ላይበልጥ ይችላል  " ሲሉ ተናግረዋል።

" ይህ በዓል የእምነቱ ተከታዮችና ከእምነቱ ውጪ ያሉ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ የሚገኙ እንግዶች የሚታደሙበት ታላቅ በዓል ነው። " ያሉ ሲሆን ፦
* ከጎጃም፣
* ከጎንደር፣
* ከሰሜን ሸዋና ከወሎ አካባቢዎች የተወሰኑ ምዕመናን በእግርና በተሽከርካሪ ሊመጡ ይችላሉ የሚል ግምት መኖሩን ገልጸዋል።

በበዓሉ ከሚታደሙ ምዕመናን አብዛኛዎቹ በአውሮፕላን ከሩቅ እንደሚመጡ የገለፁ ሲሆን ፤ " በዚህ ሁለትና ሦስት ሳምንት ምን ሊፈጠር እንደሚችል አናውቅም፡፡ ምናልባት የፀጥታ ችግሩ ከተረጋጋና እንደ ቀድሞው ከሆነ የምዕመናን ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር ይችላል " ብለዋል።

ወጣቶች በተለያዩ ችግሮች ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የፈለሱ ቢሆንም፣ ያሉትን በማስተባበር የእንግዶችን እግር ለማጠብና ሌሎች የተለመዱ መስተንግዶዎችን ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አባ ህርያቆስ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በዓሉ ሲከበር " የሚያሠጋ ነገር አልነበረም " ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፣ " ከትግራይ በኩል ያሉ ወገኖቻችን መሳተፍ አልቻሉም ነበር፡፡ ከዚህ ውጪ ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ ምዕመናን በርካታ ነበሩ " ብለዋል፡፡

" በአሁኑ ወቅት ያለየለት የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ ብንሆንም፣ ወደ በዓሉ በሚመጡ ወገኖች ላይ አስቦ ጉዳት የሚያደርስ ኃይል አለ ብለን አናስብም " ያሉት አባ ህርያቆስ፣ ነገር ግን በድንገት የተኩስ ልውውጥ ካለ የሚሞቱት ንፁኃን ዜጎች በመሆናቸው ሥጋት ሊኖር ይችላል ስሉ አስረድተዋል፡፡

ከአዲስ አበባና ከተለያዩ አካባቢዎች በተሽከርካሪ የሚመጡ ምዕመናን ቁጥር ሊቀንስ ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል፡፡

" በዓሉ የበረከት ነው " ያሉት አባ ህርያቆስ፣ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን ለማድነቅ ብቻ ሳይሆን የእምነትን ፍሬ ለማግኘት የሚመጡ ምዕመናን በእግዚአብሔር ተማምነው በመምጣት የበዓሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የአካባቢው ማኅበረሰብም በዓሉን በታላቅ ተስፋ ስለሚጠብቅ እንግዶችን ለመቀበል መዘጋጀቱን ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል።

ይህ መረጃው ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#TPLF

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)  ለሳምንታት በዝግ በማካሄድ ላይ የሚገኘው ስብሰባና ግምገማ እያጋባደደ መሆኑ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ አካላት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንደ መረጃ ምንጮቻችን ህወሓት ለ40 ቀናት ያህል በማካሄድ ላይ የሚገኘው ዝግ ስብሰባና ግምገማ ወደ መገባደጃው እየደረሰ ነው። 

እያንዳንዱ የደርጅቱ ስራ አስፈፃሚና ማእከላዊ ኮሚቴ የሂስና ግለ ሂስ ግምገማ ያካሄደ ሲሆን ፤ የግምገማ ውጤቱ በድርጅቱ ካድሬዎች ወደ ሚካሄደው ስብሰባ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበት ተጨማሪና ማስተካከያ ከታከልበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የድርጅቱ የስራ አስፈፃሚና የማእከላይ ኮሚቴ እንዲሁም የካድሬዎች ስብሰባና ግምገማ ከተካሄደ በኃላ ህወሓት ጉባኤ እንደሚጠራ የገለጹት የመረጃ ምንጮቻችን ፤ ጉባኤው ለማሳለጥ ከድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ 3 ፣ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን 3 ፣ እንዲሁም ካድሬዎች 3 በድምር  ዘጠኝ አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ተመርጧል።

ዘጠኝ አባላት ያሉት የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ የህወሓት ጉባኤ ለማካሄድ መቼ እንደሚጠራ ቁርጥ ያለው ቀን ያልታወቀ ሲሆን ድርጅቱ ለ40 ቀናት ያህል በዝግ ስለ አካሄደው ስብሰባ  መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

የትግራይ ህዝብ ከጦርነት ማግስት ድርቅና ረሃብ ጨምሮ በበርካታ ፓለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ተዘፍቆ እያለ ህወሓት ለ40 ቀናት በዝግ ስብሰባ መቀመጡ ከውስጥም ከውጭም የሚነቅፉት ብዙዎች ሲሆኑ ፤ ጥቂቶች ደግሞ ድርጅቱ ጉዞው ለማጥራት የሚያስችለው ጥልቅ ሰብሰባና ግምገማ ማካሄዱ ይደግፉታል።  

ባለፉት ወራት በጊዚያዊ መንግስቱ (ክልሉን በበላይነት በሚመራው) እና በህወሓት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር 6 የዞን የህዝብ አደረጃጀት ሃላፊዎች ፣ አንድ የስራ አስፈፃሚ የሚገኝባቸው 4 የህወሓት የማእከላይ ኮሚቴ አባላት ከመንግሰት የስራ ሃላፊነት ማንሳቱና ማገዱ ይታወሳል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ የቲክሻህ አትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                                       
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቤቲንግ

የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ሲስተም የሚሰጡ ድርጅቶች ፍቃድ ለሌላቸው የውርርድ ቤቶች ሲስተም እየሰጡ መሆኑን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ሲስተም የሚሰጡ ድርጅቶች ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህጋዊ ፍቃድ ላላገኙ አካላት የመወራረጃ ሲስተም በመስጠት ህገወጥ ስራ እየሰሩ ነው ብለዋል።

አቶ ቴዎድሮስ ፤ ህገወጥ የውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች እየተበራከቱ የመጡት ውርርዱን እንዲሰራ የሚያደርገውን ስርዓት (system) የስፖርት ውርርድ ሲስተም ሰጪ ድርጅቶች ፍቃድ ለሌላቸው የቤቲንግ ቤቶች እየሰጡ በመሆኑ እንደሆነ ገልፀዋል።

" በዚህ ምክንያት የስፖርት ውርርድ መመሪያው እየተሻሻለ ነው " ያሉ ሲሆን " ሲስተሙን የሚሰጡ ድርጅቶች ለአንድ ሲስተም ለሚፈልግ ግለሰብ ሲስተሙን ከመስጠታቸው በፊት የብሄራዊ ሎተሪ ፈቃድ አለህ ወይ ? ብለው ማረጋገጥ አለባቸው " ብለዋል።

" ፍቃድ የሌላቸው በቀላሉ ሲስተሙን የሚያገኙ ሰዎች ከቅርንጫፍ ስታንዳርድ እና ከኛ ቁጥጥር ውጪ የቤቲንግ ቤቶችን እየከፈቱ ነው " ያሉት አቶ ቴዎድሮስ ይህ በህግ ስርዓት ላይ እንዲገባ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

" ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሲስተም ፕሮቫይድ የሚያደርጉ ድርጅቶች በስፖርት ውርርድ መመሪያ ውስጥ እንዲካተቱ ይደረጋል" ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የውርርድ ቤቶች ቅርንጫፍ ከመከፈታቸው በፊት በመመሪያው መሰረት ስለመከፈቱ እንዴት ታጣራላችሁ ? የሚል ጥያቄ አንስቷል።

አቶ ቴዎድሮስ ፤ በቁጥጥር ሰራተኞቻቸው በኩል ቅርንጫፍ ከመከፈቱ በፊት መመሪያውን ተከትሎ ስለመከፈቱ ቀድመው ሄደው እንደሚያዩ አስረድተዋል።

ፍቃድ የሌላቸው እና ሲስተሙን በቀላሉ የሚያገኙ ሰዎች በየቦታው ህገወጥ የውርርድ ቤቶችን እየከፈቱ መሆኑን በመጠቆም በተለይ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከተሞች ይሄ ችግር በስፋት መኖሩን ጠቁመዋል።

በቅርቡ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር መመሪያውን ባልተከተሉና ህገወጥ የውርርድ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ያስታወሱት አቶ ቴዎድሮስ ፤ በክልል ከተሞች የተሰራው የቁጥጥር ስራ አመርቂ ውጤት እንዳልታየበት በመጥቀስ " አዲስ አበባ ላይ እየታየ ያለውን መልካም ውጤት በክልሎች ለመድገም እንሰራለን " ብለዋል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
#Update

የሰላም ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ 2 አዲስ አመራሮች እንደተሾሙለት ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ተሿሚዎቹን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ  ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ እና አቶ ቸሩጌታ ገነነ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አድርገው ሾመዋቸዋል።

ይህም ሹመት ከተሿሚዎቹ ማረጋገጥ ተችሏል።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ ከሳምንታት በፊት ከሥልጣናቸው ተነስተው መታሰራቸው አይዘነጋም።

ሌላኛው ዴኤታ ዶ/ር ስዩም መስፍን  ፤ አቶ ታዬ ከስልጣን በተነሱበት ሳምንት ለስብሰባ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ባቀኑበት ወደ ሀገር ሳይመለሱ በዛው ኮብልለው ቀርተዋል።

ዶ/ር ስዩም፤ የመጨረሻ ስብሰባቸው በኬንያ እንደነበር የሚኒስቴር መ/ቤቱ ምንጮች የገለፁ ሲሆን ፤ " ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር " ግን እስካሁን ወደ ስራ ገበታቸው እንዳልተመለሱ ተመላክቷል።

ዶ/ር ስዩም በትላንትናው ዕለት በይዊ ፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ከኃላፊነት መልቀቃቸውን የሚያመለክት መልዕክት አጋርተዋል።

በዚህ ጽሁፋቸው ብልጽግና ፓርቲ እና መንግስትን " ቁመናው የወረደ፣ የመንግስታዊ ባህሪ ያልተላበሰ፣ ከህዝብ የተነጠለና የተጠላ " ሲሉ ተችተዋል።

ዶ/ር ስዩም ፤ " እንደ አንድ የመንግስት አካል ሆኘ በቆየሁባቸው ጊዜያት በህዝብ ላይ ለደረሰው ጉዳትና በደል ይቅርታ እጠይቃለሁ " ሲሉ በአሁኑ ሰዓት በመንግሥት ኃላፊነት ላይ አለመሆናቸውን አመልክተዋል።

አዳዲሶቹ ተሿሚዎች እነማን ናቸው ?

👉 አቶ ቸሩጌታ ገነነ (ሚኒስትር ዴኤታ) ፦

- የኃላፊነት ሹመት የተሰጣቸው  አቶ ታዬ ከስልጣን በተነሱበት ታህሳስ 1/ 2016 ዓ.ም ነው።

- የትምህርት ዝግጅታቸው በፖለቲካ ሳይንስ ላይ ያተኮረ ነው። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ2007 ዓ.ም አግኝተዋል።

- ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ ትምህርት ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው።

- በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በባለሙያነት አገልግለዋል።

- የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን መስሪያ ቤት የኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማረጋገጫ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል።

- በአሁኑ ጊዜ በሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታናት ስራ መጀምረዋል።

👉 ዶክተር ከይረዲን ተዘራ (ሚኒስትር ዴኤታ) ፦

* የሹመት ደብዳቤ የደረሳቸው ሰኞ ታህሳስ 15 ነው።

* የአንትሮፖሎጂ ምሁር ናቸው።

* በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን ወክለው በአዲስ አበባ ከተማ የተመረጡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ናቸው።

* በህ/ተ/ምክር ቤቱ የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የነበሩ ሲሆን ዛሬ ይህንን ኃላፊነታቸውን አስረክበዋል።

* በታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከዲላ ዩኒቨርስቲ በ1997 ዓ.ም. አግኝተዋል። በ2004 ዓ.ም. በሶሻል አንትሮፖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።

* በሶሻል አንትሮፖሎጂ ሶስተኛ ዲግሪያቸውን በጀርመን ባይሮይት ዩኒቨርስቲ አጠናቀዋል። የሶስተኛ ዲግሪ ጥናት #በግጭት_አፈታት ላይ ያተኮረ ነው።

በሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱአለም በሚመራው ሰላም ሚኒስቴር ፤ ሁለት የሚኒስትር ዲኤታ ዘርፎች ናቸው ያሉት።

የዚህ መረጃው ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛ ነው።

@tikvahethiopia
#Hawassa

" . . . ማንም አካል በመንግስት ንብረት የግል ፍላጎቱን ማራመድ አይችልም ፤ እንዲህ አይነት ፍላጎት ያለዉ አካል ስልጣኑን ለቆ ፍላጎቱን ማሳካት ይችላል " - የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ

" ጉዳዩ በውስጣዊ አሰራር ህግና ደንብ መሰረት ተይዞ በሂደት ላይ ነው። " - የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ

" ... ለጊዜዉ በሌለሁበት ከስራ እንድታገድ ወስነዉብኛል። ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ብዬ እየጠበኩ ነው። " - ኢኒስፔክተር ተስፋዬ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መነጋገሪያ ሆነው የሰነበቱት የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ማስተባበሪያ ኃላፊዉ ኢንስፔክተር ተሰፋዬ ደምሴ ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ ታግደዋል።

ይህ በተመለከት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኢንስፔክተር ተስፋዬን እና ጉዳዩ ይመለከታቸው ያላቸውን አካላት ለማነጋገር ጥረት አድግጓል።

ከሰሞኑ የሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ በተለቀቀዉ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ፤ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ነጻና ገለልተኛ ሁኖ ማህበረሰቡን የሚያገለግለዉን የፖሊስ ንብረት በግላቸዉ ለሚከተሉት ሀይማኖታዊ አገልግሎት በማዋላቸዉ ምክኒያት ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ መታገዳቸዉ ይገልጻል።

በወቅቱ ስብሰባዉን የመሩት የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ኃላፊዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ባስተላለፉት መልእክት ፤ ማንም አካል በመንግስት ንብረት የግል ፍላጎቱን ማራመድ እንደማይችልና እንዲህ አይነት ፍላጎት ያለዉ አካል ስልጣኑን ለቆ ፍላጎቱን ማሳካት እንደሚችል ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጰያ ተጨማሪ ማብራሪያ የተጠየቀዉ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በበኩሉ ጉዳዩ በዉስጣዊ አሰራር ህግና ደንባቸዉ መሰረት ተይዞ በሂደት ላይ ያለ መሆኑን አሳውቋል።

ይሁንና ከሰሞኑ በነበረዉ ስብሰባ ወቅት የተነሳዉን የኢንስፔክተር ተስፋዬን ከስራ መታገድ በተመለከተ ለጊዜዉ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ስለሁኔታው ምን ምላሽ እንዳላቸው በስልክ ጠይቋቸው " ኢየሱስ ይመጣል የሚለዉን መልእክት ባስተላለፍኩበት ወቅት እንዳያችሁት በተፈጠረዉ ሁኔታ ከስራ ታግጃለሁ ፤ ለጊዜዉ በሌለሁበት ከስራ እንድታገድ ወስነዉብኛል። " ብለዋል።

" ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ ብዬ እየጠበኩ ነው እግዚያብሄር መልካም ነዉ " ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቤቲንግ

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ነገ ከጥዋቱ 2:30 ላይ የስፖርት ውርርድ ፈቃድ ከተሰጣቸው ድርጅቶች ጋር ሊመክሩ ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል።

ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር አዘጋጀሁት ባለው የምክክር መድረክ ላይ ፤ የስፖርት ውርርድ ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ጥዋት 2:30 ላይ ቀበና አካባቢ በሚገኘው ራስ አምባ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ እንዲገኙ ጥሪ አቅርቧል።

አስተዳደሩ ነገ የድርጅት ሥራ አስኪያጅ ወይም አንድ ተወካይ እንዲገኝ ጥብቅ ማሳሰቢያ የሰጠ ሲሆን በውይይቱ ላይ የሚቀርቡ መረጃዎች፦

1. የድርጅቱ ቅርንጫፍ መ/ቤቱች ዝርዝርና ሙሉ አድራሻ / አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ክልል ከተሞች የሚገኙ ቅርንጫፎች በተናጠል / ከተቻለም በቅርቡ በተደረገው ዘመቻ የተዘጉ ቅርንጫፎች እንዲለዩ ወይም የተለየ ምልክት እንዲደረግባቸው፤
2.  የድርጅቱ ሠራተኞች ብዛት
3. የድርጅቱ የቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅት ሥምና አገር ናቸው ብሏል።

በውይይቱ ላይ፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ እና የአዲስ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ተወካዮች ይገኛሉ ተብሏል።

በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ 3,241 የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ " ቤቲንግ " ቤቶቹን ለማሸግ ምክንያት ናቸው ያላቸው ፦

- ከስፖርት መጫወቻነቱ ባለፈ ሀገር  ተረካቢ ትውልድን እያጠፋ በመሆኑ፤
- ከፍተኛ የወንጀል ማስፍፊያ እየሆነ በመምጣቱ፤
-  የከተማውን ወጣት ግዜውን አላግባብ በስፍራው እያሳለፈ በመምጣቱ፤
- ከተፈቀደላቸው ፈቃድ ዉጪ እየሰሩ በመምጣታቸው፤
- የሰዉ ልጅ ህይወት አላግባብ እየጠፋ በመምጣቱ፤
- ተማሪዎችም ትምህርታቸውን ትተዉ በቦታው እየተገኙ በተገቢው መንገድም እንዳይማሩ በማድረጉ ፤
- የመማር ማስተማሩን ሂደት እያወከ በመምጣቱ የሚሉት እንደሚገኙበት አይዘነጋም።

@tikvahethiopia